Telegram Web Link
ሁሉም ሰው ለሚወደው ሰው ሲል የሚሽረው ሕግ ይኖራል
♡ ሙስሊም ነኝ እኔ ♡ | I am Muslim
🌸🌸ድንቅ ታሪክ 🌸🌸 አንድ ባለሃብት ነበር ። አላህ ብዙ ኒዕማዎችን የዋለለት በሰዎች ዘንድ የሚከበርም ነበር ስሙ ኑህ ይባላል። ይህ ሰው ከሃብት ንብረቱ እና ክብሩ በተጨማሪ ያማረ ስነምግባር ያለው ፣በዲኑ ጠንካራ እና አላህን የሚፈራ ነበር ። አንዲት ሴት ልጅም ነበረችው ቁንጅናዋ ጥግ የደረሰ "ጨረቃን የሚያስንቅ ውበት" የሚባልላት ነበረች። እሷም እንደ አባቷ የመልካም ስነምግባር ባለቤት እና አላህን…
አለቃውም ይሄን ሲሰማ ቆም ብሎ አሰበ ከሁሉም አቅጣጫዎች አሰበ መረመረ ።እንደ አይን ብሌኑ ለሚሳሳላት ሴት ልጁ አጣገቡ ከቆመው ባሪያው ሙባረክ የበለጠ መልካም አጋር እንደማያገኝላት አወቀ ።

ወደ ሙባረክም ዞሮ እንዲህ አለው፦ ለአላህ ብዬ ከባርነት ነጻ ብዬሃለው ልጄን ለመስጠት ካንተ የተሻለ ሰው እነማላገኝም አረጋግጫለው ልጄን ላንተ ልድራት ነው የምፈልገው ።

ሙረክም ፦ሃሳቡን አቅርብላት ለእኔ ልትድራት እንደምትፈልግም ንገራት አለው ።

አባትም ወደ ልጁ አመራ እና ሃሳቡን አሳወቃት ያጋጠመውንም አጫወታት እና እንዲህ አላት፦ "ልጄ ሆይ ነገራቶችን አጤንኩኝ ሁኔታዎችን መረመርኩኝ ግና ላንቺ ከሙባረክ የተሻለ ማንንም እንደማላገኝልሽ አረጋግጫለው "

አላህን ፈሪ የነበረችው ሴት የሷሊኋ ሴት መልስ ግን ይደንቅ ነበር ።
ልብ በሉ ይቺ ሴት የሃብት፣ የቁንጅና እና የክብር ባለቤት ይሆነች ሴት ናት እንድታገባው የተጠየቀችው ደግሞ ባሪያ የነበርን ሙባረክ………

እንዲህ አለች "አባቴ ሆይ እሱን ለእኔ ወደህ ፈቅደህልኛል ?"
አባትም "አዎን ልጄ "
እሷም እንዲህ አለች " አባቴ ሆይ እኔም ምንም ለማይደበቅበት ጌታዬ አላህ ብዪው ፈቅጃለው ተቀብያለው "
ታዲያ ይህ ከሙባረክ ጋር ለአላህ ተብሎ የተደረገ ጋብቻ የተባረከ ነበር ።

የዚህ ጋብቻ ፍሬ ምን እንደነበር ማን ይገምታል ?

ይህቺ ሴት ወለደች የልጃቸውንም ስም አብደላህ ብለው ሰየሙት
አብደላህ ማን ነው ?

አብደላህ………

ሁላችንም የምናውቀው አብደላህ…… ታላቁ ሙሃዲስ አብደላህ ……ታላቁ ዛሂድ አብደላህ…… ታላቁ አቢድ አብደላህ ኢብኑ ሙባረክ

ማንም የታሪክ መዛግብትን ቢያገላብጥ ታሪኩ በወርቃማ ብዕር ተከትቦ የሚያገኘው ታላቁ

ሰው አብደላህ ኢብኑ ሙባረክ رحمه الله
አሏህ ሆይ

«በሀላል መሰተር የፈለገን ሁሉ ጋብቻውን አፋጥንለት አሚን»

nuredinal_arebi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቁርአን ግብዣ

በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን
በሸይኽ ኢብኑ ባዝ
በሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አሊ ሸይኽ
በሸይኽ ፈዉዛን

የሞቱትን አላህ ይዘንላቸዉ ያሉትን አላህ ይጠብቃቸዉ።
"አንቺ ከዲጃ ሆይ እኔ ድሀ ነበርኩኝ
አላህ ባንቺ ሀብታም አደረገኝ"



ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ  ወሰለም
🌹ሁሉም ሰው ሲሰልም የነበረበትን ሂወት እያሰበ ይቆጫል በፊት አግኝቸው በነበር እያለ ሁሉም ሰው እንድሰልም ይፈልጋል
🌹ሁሉም ሴት አዲስ ኒቃብ ስትለብስ ያለበሰችበትን ጊዜ እያሰበች ትቆጫለች በፊት ለብሸው በነበረ እያለች ሁሉም ሴት ኒቃብ እንድትልብስ ትፈልጋለች
የኛ ውድ ነብይ ﷺ ለዓኢሻ ረዲየሏሁ ዓንሀ  እንዲህ አሏት
ስትናደጂብኝ እና ሳትናደነጂ መለየት እችላለው
ዓኢሻም እንዴት? አለች
ስትናደጂ በ ኢሳ ጌታ ሳትናደጂብኝ ደግሞ በሙሀመድ ጌታ እያልሽ ትምያለሽ
اللهم حب كحب الرسول لعائشة🫀
በሙዳችሁ አትመሩ!

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ስራ በመስራት በሕይወታችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ከሰዎች ጋር ሰላም እየሆናችሁ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ጤናማ አድርጋችሁ ማቆየት አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ስፖርት እየሰራችሁ ጤናማ አካል ልትገነቡ አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ እያነበባችሁ ራሳችሁን ማሻሻል አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ዓላማችሁን በመከተል ራእይና ሕልማችሁን ማሳካት አትችሉም፡፡

ጥሩ ቢሰማችሁም ባይሰማችሁም መሰራት ያለባቸው ስራዎች አሉ!

ብትነቃቁም ባትነቃቁም መከናወን ያለባቸው ተግባሮች አሉ!

ብትጓጉም ባትጓጉም መጓዝ ያለባችሁ ጎዳናዎች አሉ!

ጥሩ ሙድ ላይ ብትሆኑም ባትሆኑም መጠበቅ ያለባቸው የሰው-ለሰው ግንኙቶች አሉ!

ቀጣይነት ይኑራችሁ!

መልካም ምሽት የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

Dr eyob
አላህ የሰውን ልጅ ከሚጠገንባቸው መንገዶች መካከል አንዱ መርሳት ነው።
ሐቢቢ حبيبتي ! አቤት ያ የማይረሳ የሚመስለው ነገር ሁሉ ተረሳ ከማለትህ ቀጥሎ ጌታዬ ሆይ ምስጋና ይገባህ በል በይ።
የዐሹራእ ፆም ሳምንት ቅዳሜ ይሆናል ማለት ነው
ሙሐረም ~ 10
የዐሹራእን  ፆም መፆም የ1 ዓመት ወንጀል ያስምራል
አላህ ያድርሰን
ሰላም ላንተ «ያልፋል!»ማለት በቁስልህ መቀለድ ለሚመስለኝ። ላፅናናህ አቅም ለሚያንሰኝ፣ ለብርታትህ ሰበብ ለመሆን ብሞክር የምሰብርህ ለሚመስለኝ አንተ ሰላም ለልብህ! ልብህ እንደ የቲም ልጅ እንክብካቤ ለሚፈልገው ሰላም ለልብህ!
ጠንክሮ መሥራት ለሁለቱም ዓለም ስኬት!

~እስልምና ሰነፍ ሰው አይወድም፡፡ ለስንፍናም ቦታ የለውም፡፡ ሁለቱም መልካም ቢሆኑም ጠንካራው አማኝ ከደካማው እንደሚበልጥ ያሰተምራል፡፡ ሰጭ እጅ ከተቀባዩ እንደሚሻልም ይናገራል፡፡ እስልምና ተግተው የማይሰሩ ኮሳሳ አማኞችን ያወግዛል፡፡ የአጓጉል ምኞት ተከታዮችን ያጥላላል፡፡

• ነቢያችን «አላህ ሆይ! ከስንፍና ባንተ እጠበቃለሁ፡፡» ይላሉ፡፡
• ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ «ደከመኝ» ማለትን ይጠሉ ነበር፡፡
• ታላቁ ኸሊፋ ዑመር ኮሳሳና ልፍስፍስ መስለው የሚታዩ ሰዎችን አይወዱም ነበር፡፡ ቀና፣ ቀልጠፍ እና ቆፍጠን ያለ ሙስሊም ያረካቸዋል፡፡ ሥራ ትተው መስጊድ ውስጥ የሚውሉትንም ይቆጡ ነበር፡፡

እስልምና አባላቶቹ ዓላማ ያላቸው፤ ብቁና ንቁ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ በሁሉም ዘርፍ በላጭ የሆኑትን ያበረታታል፡፡ ታላቁ ነቢይ ሙስሊሙ አማኝ ምርጥ የተባሉ ሥነምግባራት ባለቤት እንዲሆን ያበረታተቱ ነበር፡፡

ነገም ሆነ ዛሬ ሁሉም የሰው ልጅ የሥራ ውጤቱን ነው የሚያገኘው፡፡
• ሐምዛ «አሰዱሏህ» የአላህ አንበሳ  የተባለው ያለ ውሎው አይደለም፡፡
• ዐብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ  ሀብታም የሆነው ነግዶ ነው፡፡
•  ሙዓዝ የሐላል እና ሐራም ኤክስፐርት ለመሆን የበቃው ተምሮ ነው፡፡
• ኻሊድ ‹ሰይፉላህ አልመስሉል› ከአፎቱ የተመዘዘ የአላህ ሰይፍ› የሚል ስያሜ የተሰጠው ጀግኖ ነው፡፡
• አቡበከር በስምንቱ የጀነት በሮች ሊጠራ የቻለው ሰርቶ ያገኜውን ንብረቱን በሙሉ በአላህ  መንገድ ሰጥቶ ነው፡፡
•  በጀነት የተበሰሩት አስሩ ሰሃቦች ደክመው ለፍተው ነው፡፡
 እኔና አንተ አንቺ ምን ሰራን?፡፡

ስለሆነም…በምድር ላይ እስካለን ድረስ እንስራ፡፡ የሥራን ዋጋም እንወቅ፡፡ ሰራተኛና ሰነፍ ሰው ደረጃቸው የተለያያ መሆኑን እንገንዘብ፡፡ ለመኖር ብቻ ሣይሆን ለመጥቀም እንኑር፡፡ ለህይወት ጨማሪዎች እንጂ ጭማሪ አንሁንባት፡፡

- ባርነት ስንፍና ሲሆን ሥራ ነፃነት ነው፡፡
- መለመን ውርደት ሲሆን መለገስ ክብር ነው፡፡ 
☞ ድሃ፣ ሰነፍ፣ ደካማ …የሚለው መጠሪያ የሚውለው ወደኋላ ለቀሩት ነው፡፡
☞ ሀብታም፣ ጎበዝ፣ ጠንካራ ..የሚለው ደግሞ ለቀደሙት ነው፡፡ ታዲያ ለምን ከፊት አንሆንም?

የሙስሊም ባህሪ ወደላይ ነው፡፡ የሚመኘውም ሆነ የሚያልመው ምርጥ ነገር ነው፡፡ ሁሌም ተሸሎ ለመገኘት ይጥራል፡፡ ምኞቶቹ ትላልቅ፤ ህልሞቹም ውድ ናቸው፡፡ መዋያዎቹ ፅዱ፤ እኩዮቹም ምርጥ ነገሮች ናቸው፡፡ ለተራ ነገር እጅ አይሠጥም፡፡ ለርካሽና ውዳቂ ነገሮች አይሸነፍም፡፡ አትተኙ!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጓጓ ጠንክር ...…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿احْرِصْ على ما يَنْفَعُكَ، واسْتَعِنْ باللَّهِ وَلا تَعْجِزْ، وإنْ أَصابَكَ شَيءٌ، فلا تَقُلْ: لو أَنِّي فَعَلْتُ كانَ كَذا وَكَذا، وَلَكِنْ قُلْ: قَدَرُ اللهِ وَما شاءَ فَعَلَ؛ فإنَّ (لو) تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطانِ.﴾


“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ። አንዳች ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ይህን ይህን ነገር ባደርግ ኖሮ ይሄ ነገር አይከሰትም አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ። እሱም የፈለገውን ነገር ያደርጋል’ በል። ለው ‘እንዲህ ባደርግ ኖሮ’ የሸይጧንን ስራ ትከፍታለች።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 2664
ስለ ሰላም ከጠየኩሽ ስለ ኒቃብ ንገሪያቸዉ
➧. #_ለፓስፖርት_ፈላጊወች_ታማኚና_ፈጣን አገልግሎት ጀምረናል!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
       በሁሉም ክልሎች ላይ✔️
❶.  አስቸኳይ ፓስፖርት
❷. አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
❸. ለማሳደስ
❹. የጠፋ / የተሰረቀ ለማውጣት
❺. እድሜ ለማስተካከል

      ➧. በተጨማሪ  ወደ ውጭ ሀገር!
➧. ወደ ሳኡዲ አረቢያ   ዱባይ ኳታር  ለስራ ወይም ለጉብኝት መሄድ ከፈለጉ ሀሎ ይበሉን 👍
➧ . ለበለጠ መረጃ:-  #ቀጠሮ_ለማስያዝ_ይደውሉ!!👍

➧.    0914367877
➧.    0914367877      ይደዉሉልን  !!

➧. በቴሌግራም በዉስጥ መስመር ያገኙናል.👇
➧.    @Mah_Ye      @Mah_Ye    !!
ኢየሱስ የሚባል ፍጡር እንጂ ኢየሱስ የሚባል ፈጣሪ የለም።➢አገኛቹኝ👍
የት ለመድረስ ነው?
በተኙ ሰዎች መሀል ስትነቃ፣ በደከሙ ሰዎች መሀል ጠንካራ ስትሆን፣ ባረፉ ሰዎች መሀል ስትታገል "የት ለመድረስ ነው?" በሚል ጥያቄ  ሊያደክሙህ ይፈልጋሉ። አንተም "እናንተ አይደርስም ብላችሁ የምታስቡት ቦታ ላይ ለመድረስ ነው።" ብለህ መልስላቸው።

"ولسوف يعطيك ربك فترضى"
ዓሹራእ
አጫጭር ምክሮች
የሙሐረም ወር አስረኛውን ቀን መፆም ያለው ደረጃ

🔊ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
አላህ ሙሉ አፍያህን ይስጥህ ውድ ኡስታዛችን
2025/07/04 04:46:52
Back to Top
HTML Embed Code: