Telegram Web Link
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ትጋ
በአሏህም ታገዝ
አትድከምም!!
ትክክለኛ ጓደኛ የኛ ደስታ
ያስደስታቸዋል
እህቱን ለሚወድና ሴትን ለሚያከብር....


እህቴ ተሰብራ አታውቅም!!
------------------------
በርግጥ ብዙ መከራ አልፋለች፡
ብዙ ስቃይም ተጋፍጣለች፡
ግን በፅናት አልፋዋለች...
የኔ እህት ጀግና አይደለች...!?

ምንም እንኳን፤
ግፉ በዝቶ ብትጓዝም በቀላጥም፡
ሁሌም ቢሆን የኔ ጀግና፤
ለሰከንዶች ተስፋ አትቆርጥም፡
ሰው አድርጎ ፈጥሯት ጌታ፤
መውደቅማ የት ይቀራል፡
ግን ስትወድቅ አንደበቷ፤
እንደ ትንቢት የተስፋ ቃል ይናገራል፡
አይቻለሁ በህይወቴ፤
ብዙ ቦታ ስትተክዝ ስትመረር፡
አትቀርም እንጂ ተሰብራ፤
ክንፏን አራግፋ ከመብረር፡

.....እህቴማ ልዩኮ ነች....

ተከፍታ እንኳን፤
እያየኋት ስጠይቃት ትስቃለች፡
አጃዒብ ነው ተፈጥሮዋ፤
ኸረ የኔስ ትደንቃለች፡
ከገደል ላይ ወድቃ አለመሰበሯ፡
ከወደቀችበት ተነስታ መብረሯ፡
በየ ጎዳናው ተጠልፋ በየመንገዱ ተገፍታ፡
በወደቀች ቁጥር፤
አንሱኝ አላለችም ጭራሽ አቅም አጥታ፡

.....ታዲያ አትደንቅም በአሏህ..!?

በማይቻል ግፍ ተንጣ፡
በነበልባል እሳት ቀልጣ፡
ሁሉን አልፋ ከኔ ስትመጣ፡
ፈገግ ነው ሳትቆጣ....

.....ሁሌም ቢሆን...

ወድቃ እንጂ ተሰብራ አታውቅም፡
ታዲያ ይህች ሴት አትደንቅም.!?


አለመውደቅ አትችልም የብልጠት አቅም የላትም፡
በየዋህነቷ ደገፍኩሽ ያላትን ማመን አይከብዳትም፡
ግና የተደገፈችው አታሎ ሲጥላት፡
ወድቆ የመነሳት እምቅ አቅም አላት፡
ሞራል አላት ወድቃ አትቀርም፡
በፍፁም ከሰው ፊት አታቀረቅርም፡
--------------------
ይገርመኛል ላለመውደቅ አትሞክርም፡
ላመናት ታማኝ ነች አታንገራግርም፡
ስጭኝ ለሚላት ሰው ልቧን አታስቀርም፡
...........................
ሁሉንም ስታደርግ ተሳስታ አታውቅም፡
ብትሳሳትማ ትማርበት ነበር ብትማር አትወድቅም፡
ታዲያ በዚህ ዘመን የኔ እህት አትደንቅም...!?
------------------------
መቼም አይፈታም የእምነት ቁጥራቷ፡
እውነተኝነት ነው የውስጥ ብስራቷ፡
የበቀለችበት ኢስላም ነው እምነቷ፡
......ትገርማለች ኒቃቢስቷ..፡
------------------------
እርሷ ጭንቅ የላትም ከችሎታ በቀር፡
ቀና ማለት እንጂ አታውቅም ማቀርቀር፡
እምነት ነው መስፈርቷ ወዳጇን ለማፍቀር፡
ሰወችን በውሸት አታውቅም አግባብታ፡
በወደቀችበት አታውቅም አንብታ፡
ትሰጣለች እንጂ ጭራሹን ፈገግታ፡
----------------------------
ቆራጥ ልበ ሙሉ ሰንደቅ ነች የፅናት፡
እሱን ተምራለች ከሙስሊሞች እናት፡
ምንም ቢሏት የገፏትን አትጠይቅም፡
ትንቃለች የጣሏትን ከሳ አታውቅም፡
በአሏህ ታዲያ ይህች ሴት አትደንቅም።..!?
የኔ ልዩ በሰው ልጆች ተሰብራ አታውቅም...
ከአሏህ የተሰጠ አላት ግሩም አቅም፡
....እህት አለሜ እወድሻለሁ።

✍️በኑረዲን አል አረቢ
«እህቴ ተሰብራ አታውቅም»
🎙በኑረዲን(አቡ-ፉሩቅ)
.

እህቴ ተሰብራ አታውቅም‼️




.....🎙ኑር
አላህ ትንሽ አፍያን ያዝ ሲያደርግብህ
ድንህን የተውክላት ዱንያ ተራ መሆኗን ትረዳለህ


ድጋሚ ትረሳዋለህ ኖርማል ትሆናለህ ወይ የሰው ልጅ ገራሚ ፍጡር
‣ የኔ ዱዓማ ይህን ሁሉ እንድታረግልኝ አልነበረም። አላህ ሆይ ችሮታህ በዛብኝ የሚል ሰው አጋጥሟችሁ ያውቃል?!

አልሐምዱ ሊላህ!
በእርግጥ እንደ ዩኑስ አ. ሰ በግልጽ ከአሳ ነባሪ ሆድ አልገባንም
እንደ ኢብራህም አ. ሰ ከእሳት አልተወረወርንም
እንደ ዩሱፍም ከጥልቅ ጉድጉአድ አልተጣልንም


ያንን ያክልም አልተፈተንም ሆኖም ግን በወንጀል እቅፍ ዉስጥ ሆነን, ነፍስን በመበደል አዝማሚያ ተከበን ምሕረትህን ከጅለናል 🤲...

صلو على محمد❤️
በነፃ ገብተህ ሰላምን መረጋጋትን አርፍት አትርፈህ ምተወጣው መስጅድ ብቻ ነው
#_ከነፍስ ጋር መታገል ከትግሎች ሁሉ ትልቁ ትግል ነው
አንዳንድ ሰዓቶች ቀናቶች አሉ ምንም ማይቀየሩ ሚመስሉ አላህ በቁዋው ባላሰባቹበት ሁኔታ ገር የሚያደርጋቸው አልሃምዱሊላህ አላኩል ሃል
አብሺሩ አሁንም ሁሉም ይግራል
በሰዎች ቤት ደጋግማችሁ ከታያቹ ትረክሳላችሁ
በአሏህዬ ቤት ግን ደጋግማችሁ ከታያችሁ ትወደዳላችሁ🌸
👀እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል?

ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።

በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣

እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡

ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅኑ፣ እምነታችሁም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጡ ምክንያቱም የእናንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል። የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የራሳችሁን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅሩ
🔍
⎷ የማያልፉ የሚመስሉ ነገሮች ሁሉ እያለፉ ነው። አብሽሩ !

መልካም ምሽት!
እነዚያ ሚያማምሩት ቀናት ደማማቆቹ ምሽቶች እነዚያ ከአላህ ጋር እጅጉን ምንቀርብባቸው ለሊቶች እየደረሱልን ነው🥹
ውዷ እህቴ የተሻልሽ ሁነሽ መገኘት ከፈለግሽ ከሌሎች ሰዎች ሳይሆን ከትናት ማንነትሽ ነው

ሁሌም የተሻልሽ ሁነሽ ለመገኘት ተስፋ ሳትቆርጭ ሁሌም ጠንክሪ
ጥሩ ሰው ለመሆን እንደታገልኩ ረመዷን አልፎ ረመዷን መጣ። አሁንም እታገላለሁ ። ትልቁ ትግሌ ከራሴ ጋር ነው።
አላህ ሆይ ሁኔታችንን ካለንበት ወደተሻለ ሁኔታ ለዉጥልን።
القارئ هزاع البلوشي | ولا تقولن لشيء إني فاعل ذلك غدا
💭🌸خدمة تلاوات🎧
ቁርአን መስማት ልብን ያረጥባል !

ከቁርአን ጋር እንኑር

=
2025/07/06 12:45:03
Back to Top
HTML Embed Code: