Telegram Web Link
ደስ የሚል በቀል!

እልህ ይዞሽ ያውቃል? የሚንቁሽና የበታችነት እንዲሰማሽ የሚያደርጉሽ ሰዎች ህይወትሽን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልጊ ንብረት ለማውደም ትጠቀሚበታለሽ ስትፈልጊ ደግሞ ምግብ ታበስይበታለሽ፤ ታዳ ለናቁሽ ሰዎች ማንነትሽን ለማሳየት ጠንክረሽ ሰርተሽ ራስሽን ለውጠሽ በስኬትሽ የያዘሽን እልህ ለምን አትወጭውም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁሽ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው።

hiba_islamic_post
ሰዎችን ስትጠላቸው ብቻ ሳይሆን በጣምም ስትወዳቸውም ከነሱ መሸሽ መራቅ ትፈልጋለህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንድ ላጤዎች አግቡ ሲባሉ......
ለድሀ ያልሠጠ
ለሐኪም መስጠቱ ግድ ነው ይላሉ ።

ምን ማለት ነው?
"ህመምተኞቻችሁን በሰደቃ አክሙ።" የሚል ሐዲሥ አለ።

ካልሆነ ለመታከሚያ ታወጣላችሁ።
ጥቆማ

🔻ኒቃብ አንድ ሸሪዓዊ ትዕዛዝ ነው።

🔻 ከዚህ በኋላ ነው ሚለበሰው ተብሎ ተርቲብ የለውም።

🔻ለሴት ልጅ ኒቃብ ለመልበስ ፆታዋ ሴት መሆኑ ብቻ በቂ ነው ።

🔻ኒቃብ ለመልበስ እውቀት ይቀደማል ለሚባለው
ሴት ልጅ መሰተር አለባት ሚለውን ማወቅ እውቀት መሆኑን አንዘንጋ?!

🔻ኒቃብ የለበሰችው የእውቀት ጫፍ ደርሳ ለማቆም ሳይሆን ባወቀችው ሰርታ ለመጨመር ነው።

🔻ኡምደቱል አሕካም ኪታብ ላይ በየእለቱ የሚማሩትን ነገሮች ለመተግበር እኮ ኪታቡን እስኪጨርሱ አይጠበቅም።

🔻ኒቃብ ለብሰው እስልምናን ያሰድባሉ ለሚባው  ሰዎች በእስላም ይለካሉ እንጂ እስልምና በሰዎች አይለካም።

🔻 ኒቃብ ለብሳም ተሳሳተች ሳትለብስም ተሳሳተች መሳሳቷ ምንም ከልብሷ ጋር ሊዛመድ አይገባም።

🔻ማህበረሰቡ ኒቃብ ያደረገችን ማትሳሳት እና ጥግ የደረሰች አድርጎ ስለሳላትና ስላሰባት ስህተቷ ይገናል እንጂ ያለበሱ ሴቶች ከሷ በላይ ቀይ መስመር እንደሚረግጡ አንዘንጋ?!

🔻ኒቃብን ለመልበስ እንሞክር ዱዓ እናድርግ እንጂ ኒቃብና ኒቃቢስቶችን ከመኮነን እንጠንቀቅ።

🤲አላህ ለእናንተ እህቶቻችን ሂጃብ የምትለብሱበትን ለኛ ለወንድሞቻቹ ደግሞ ዓይናችንን የምንሰብርበትን ኢማንን ይስጠን !!!
ሙስሊም ወንዶች ኒቃብ ለሚለብሱ ሴቶች ያለንን ክብርና ቦታ ብታውቁ ሁሉም ሴት ኒቃብ በለበሰ ነበር
እናንተ የምድር ላይ ኑርአልዓይኖች አላህ ከከፏ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ>>
ከወንዶች የተሰጠ ሃሳብ
ለምን እንደዚህ አደረግኩ ? ለምንስ እንደዚህ አላደረግኩም ? የምላቸው ብዙ ታሪኮች አሉኝ ። ለመሆን የምጣጣራቸው ብዙ ማንነቶችም ከፊቴ አሉ ። መሆን የምፈልገውንም በጊዜ ባለመሆኔም እራሴን የምወቅስበትና ተስፋዬን በማመናመን ስሜት የምተክዝበት ወቅትም ቀላል አይደለም ።

ነገር ግን ምን አልባት ይህ ሁሉ የሚሆነው ተሰርቼ ስላላለቅኩ ቢሆንስ ? የስኬቴ መንገድ በብዙ ውጣውረዶች የሚሸጋገርና አሁን ያለሁበት ተጨባጭም የዚያ መንገድ አንዱ አካል ቢሆንስ ?

እውነት ነው ዛሬ ከባድ ነው ። ቢሆንም ግን ታሪኬ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ፣ እኔም ተሰርቼ አላለቅምኩም ። ለጥፋቶቼ እና ስህተቶቼ እራሴን ይቅር ማለትና መማር ይኖርብኛል ። የምፈልገው ስኬት ላይ ለመድረስ ደግሞ ጊዜ መስጠት እና ጥረት ማድረግ ይኖርብኛል ። ታሪኬ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ፣ እኔም ተሰርቼ አላለቅኩም…

ኢን ሻ አላህ ነገ ቆንጆ ይሆናል ፣ . ወደፊት ኸይር አለ …..🌸

Inshallh
ሁሉም ነገር የሚሆነው
እኛ ስለፈለግነው ሳይሆን
አላህ ስላለው ብቻ ነው!!
...ሰው አይደለች ይደክማታል እኮ

ከዉጭም ከውስጥም ሰላሟን የሚነሳት ችግር ብዙ ነው...ሰዎች ችግሯን ሊረዷት ቀርቶ ሊሰሟትም ፍቃደኛ አይደሉም...ሁሉም የራሱን ፍላጎት እና ስሜት እየተከተለ የሷን ጭንቀትና ህመም ምንም አይመስለውም።ሰው አይደለችም እንዴ ይደክማታል እኮ!!

ህይወቷን በደስታና በተረጋጋ መንፈስ እንዳትመራ መኖር እንዳትመኝ ህልሟን ነጥቃችኋት   መልካምን ሳትሰንቅ ዱንያዋንም አኼራዋንም ብልሽትሽት አድርጋችሁ ውዷን ርካሽ ለማረግ አሰባችሁ
ግን
ግን
እሷ የኔ ሴት ተንኮታኩታ፣ፈርሳ፣ተሰብራ የምትቀር አይደለችም ይልቅ እምባዋን ጠርጋ ዳግም መንገድ የምትጀምር እንጂ...

hiba_islamic_post
«...ለሱሪ ለባሽ ጓደኛሽ ላኪላት...»

«.......አንቺ ማለት እኮ….…..»
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በጣት ጥፍሮችሽ ላይ ላስቲክ አስገጥመሽ፣
አርቲፊሻል የሆንሽ ዘመንሽን ቀድመሽ፡
በራስሽ ላይ ደግሞ የዊግ ቆብ አጥልቀሽ፡
ሰውነት የቸከሽ ሴት መሆንን ፍቀሽ፡
ከንፁህ እሳቤ በጣሙን እርቀሽ፡
ፆታሽን ቀይረሽ ወንድ መሆን ናፍቀሽ፡

በሰው ሰራሽ ነገር የምትመሰጪ፡
ለትዳር ለሀላል የማትቀመጪ፡
አሻንጉሊት የሆንሽ ከሰው ተራ ወጥተሽ፡
የተፈጥሮን ፀጋ አራክሰሽው ትተሽ፡
የሚገርመው ነገር እንደዚህ ነሽ አሉ፡
አብረውሽ ያደጉት ነገሩኝ በሙሉ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ዱርዬ ልበ-ቢስ ይሉሻል አንዳንዴ፡
ሴትነትን ጥለሽ የምትሆኝ ወንበዴ፡
ኸረ ብዙ ሰማሁ እውነት ይሆን እንዴ!!
የፈጣሪን ጥበብ አንች ቀይረሽው፡
የአለሙን ዳኛ አሏህን ደፍረሽው፡
ዛሬ ከእቃ በታች ረክሰሽ አረፍሽው⁉️
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ፋሽን ተከታይዋ ቆማ ተገትራ፡
ሙስሊሟ ቆንጆ ግን አምራ ተሰትራ፡
በኒቃብ አጊጣ ስራዋን ስትሰራ፡
ያች ሱሪ ለባሽ ገባች👉አሰንሰራ፡
ኒቃቢስት እህቴን ለማራከስ ደፈርሽ፡
ድንኳን ለባሽ ብለሽ ለመሳለቅ ሞከርሽ፡
በሸይጧን እሳቤሽ ቅናት ይዞሽ ሰከርሽ፡
ስሜቷን ትከተል በማለትም መከርሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▸ውድ ነሽ አይዞሽ...!!
ኒቃቢስቷ አንች ግን ቀጥ በይ በአቋምሽ፡
የማንም ዘለፋ ፈፅሞ እንዳያምሽ፡
ሁሌም ከአሏህ ዘንድ ከፍ ያለ ነው ስምሽ፡
አለልሽ ቃል ኪዳን ውብ ጀነት ነው ህልምሽ፡

እንደ ዘመኑ ሴት ቻፕስቲክ ያላየሽ፡
ከመጥፎ ጓደኛ ቀድመሽ የተለየሽ፡
ዘር ጎሳና ብሔር መልክ ሳትቆጥሪ፡
የሰጠሽ ተፈጥሮን ለማርከስ ሳ'ጥሪ፡
ዘመናይ ነኝ ምትል ኋላ ቀሯን ቀድመሽ፡
በኒቃብ ተውበሽ ሁሉን አስደምመሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

ከልብ የምትገቢ ነሽ የአይን አበባ፡
ወንድን የሚረብሽ የለሽም ወለባ፡
ምርት በአንች ታይቷል ሌላው ነው ገለባ፡
ከአሏህ ቃል ውጭ ያላቆመሽ ታኮ፡
ከነቢ ትዕዛዝ ውጭ ንግግርሽ ሾልኮ፡
ከውጭ ያልተሰማ ድምፅሽ አፈትልኮ፡
የሴቶች ልዩ ነሽ አንች ማለትኮ....!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በኑረዲን አል አረቢ➊❹❹❹
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አል-በይሀቂ አቡ በክር አል-አሽዕሪ እንዲህ ብለዋል፡-

**ኢማም ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል፡-

የሚከተለው የቁርኣን አንቀፅ
«{مَنْ فِي السَّمَاءِ}» («በሰማይ ያለው») የሚለውን ትርጉሙ፡- 
«ከሰማይ በላይ፣ ከዐርሽ ላይ ያለ ነው»
እሱም ፦ «{الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى}» («አል-ራህማን በዐርሽ ላይ ሆነ።») የሚለው አንቀፅ ያስረዳል። 

ማንኛውም ከፍ ያለ ነገር «ሰማይ» ይባላል። ዐርሸም ከሁሉም ሰማያት በላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ከዐርሽ ላይ ከፍ ያለ ሲሆኑ «እንዴት» ወይም «አኳሃኑ» ሳይጠየቅ (بلا كيف) እንደሆነ ተገልጿል። 

(መናቂብ አሽ–ሻፊዒ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 398)
ቀን አለ ......

ለልባችሁ ቀን እንዳለ ንገሩት። አዎ የሆነ ቀን አለ። ደስተኛ የምትሆኑበት። ስትመኙት የነበረውን ነገር የምታገኙበትና ከደስታችሁ የተነሳ «ጌታዬ ሆይ በከንቱ እንደማታስቀረኝ አውቅ ነበር» የምትሉበት ቀን አለ።

ትናንት ያልነበር ሊሆን ይችላል። ዛሬም ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አንድ ቀን አለ። ተስፋችሁን መቼም ቢሆን እንዳትጥሉት። አብሽሩልኝ። «ደስተኝነት ምንድነው?!» ስትባሉ «እኔ ያለሁበት ሁኔታ ነው» ብላችሁ የምትመልሱበትን ቀን አሏህ ቅርብ ያድርግላችሁ።
{وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ}
إنا لله وإنا إليه راجعون ......
"በወንዶች በሆነ ነገራቸዉ የምቀና ብሆን ኖሮ ወደ መስጅድ በሚያደርጉት ጉዞ እቀናባቸዉ ነበር።

=
ዱአ አድርጉልኝ ማለት ከባድ አማና መጣል ነው
🔖ሴቶች ለመጽናናት እና ከፈተና ለመዉጣት ማድረግ ያለባቸዉ ሶስት ቁልፍ ነገሮች..!

የሚያስጨንቃችሁን ነገር መቀነስ
ጤናን መጠበቅ
⓷አንች ከሌለሸ ሁሉ ነገርእንደሚቆም (እንደሚቀጥል)መረዳት
🖋ወንድ ሆይ!!!
ሴት ልጅ የማይቻለውን ነገር አድርግልኝ ብላ አትጠይቅህም ነገር ግን አንተ ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ወንድ ሁንላት!
ሴቶች የሌሉበት ቤት ከእስር ቤት የተለየ መሆኑን እጠራጠራለሁ….🌸
🎁 10ሩ የዙል ሂጃ ቀናቶች❗️

ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ የተባሉ የ ዙል-ሂጃ አስርቱ ቀናቶች ሊገቡ ትንሽ ቀናት ብቻ ይቀሩናል።

የአላህ መልዕክተኛ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ

أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّة

ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስርቱ የዙል ሂጃ ቀናቶች ናቸው።

በሌላም ሀዲስ እንዲህ በማለት በነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለው ደረጃ ያስቀምጣሉ

ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،*
  قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟
     قال ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء

ከነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላህ ሚወደድበት ቀን የለም አሉ

ሶሀቦችም በአላህ መንገድ ላይ መታገል{መጋደል}ቢሆንም? ብለው ሲጠይቋቸው
"አዎ በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም ግን አንድ ሰው ሲቀር'' አሉ
እሱም "በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረው" አሉ

አላሁ አክበር! በመሆኑም እነዚህን አስርት ውድ ቀናቶች ተጠባብቀን በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል። አላህ በሰላም አድርሶን ተጠቅመንባቸው የምናልፍ ያርገን

የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)“ወደ መልካም ያመላከተ እራሱ እንደሰራው ነው” ብለዋል፡፡ ስለዚህ ሼር በማድረግ ላልሰሙ ሙስሊሞች እናሰማ።
:
2025/06/29 21:01:48
Back to Top
HTML Embed Code: