Telegram Web Link
፳፪ ፡ ፫ ፡ ፳፻፲፬ዓ.ም

ከስርዓተ ነጥቦቹ በስተቀር በድምፅ መቅጃ የተወሰደ።

እንደ 'ኔ ጥያቄ አጠያየቅ ነው የ'ሱም ምላሽ።

•ከ'ሱ•
ምቱኩ አሻግሬ እባላለሁ። እዚሁ አዲስ አበባ ነው የምኖረው። እማራለሁ ፬ተኛ ክፍል ነኝ። ጠዋት ከጓደኞቼ ጋር ወደ ት/ቤት እሄዳለኹ። ከት/ቤት ስመለስ በዛው ወደዚህ እመጣና እስከ ማታ ድረስ ሚዛን ሰርቼ ወደ ቤት እገባለኹ። እንደውም የተወሰነውን ፎቶው ላይ አንስተሃው የለ ፥ ዩኒፎርሜን 'ምቀይረው ፣ መክሰስ የምበላው ፣ የቤት ስራ የምሰራው እዚኹ ቦታ ላይ ነው። ሚዛን ሰርቼ የማገኘውን ገንዘብ አክስቴ ባንክ ከፍታልኝ እዛ
እያጠራቀምኩ ነው።

•ከ'ኔ•
መንገዱ ነው ያስተዋወቀኝ። ፒያሳ አካባቢ ነው ያገኘኹት። በቻልነው ሁሉ ተዋውቀናል። ፎቶዎቹን በወፍ በረር ካያቸው በኋላ ደስ ያለኝን አሳጥቤ(Print) አድርጌ ብሰጠው ደስ እንደሚለው ነግሮኝ እኔም በየመንገዱ በተመዘንኩ ቁጥር ኪሎዬ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ የማለቱ ነገር እያስገረመኝ እና እያናደደኝ ብቸገርም ፥ ''የምትኩ ሚዛንስ ልክ ናት'' በማለት ተመዝኜ እና ሌላ ጊዜ ከፈለኩት አልፎ አልፎ ካልሆነ ከ9:00 በኋላ እዚሁ እንደማገኘው ነግሮኝ ተለያየን።

ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
፳፪ ፡ ፫ ፡ ፳፻፲፬ዓ.ም


#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject
በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት ምስል አለ።

ትክ እና ልብ ብዬ የተመለከትኩትን ማሳየት ብቻ ነው የያዝኩት። ከተማው አንድ ነው ፥ መንገዱም የመጣሁበት ራሱ ነው። ለምን የምስሉ መለያየት እዚኽ ድረስ ሊኾን ቻለ? የምጠይቀው ራሴን ነው። በመንገዳቹ ኹሉ የማትረሱት አልጠፋ ያላቹ ምስል ይኖር ይኾን? ለኔ እነዚኽ ሁለት ምስሎች እንደዛ ናቸው።

There are two pictures in one city.

I just wanted to show what I truly saw. The city is one, and its the same road i have passed. Why did the image differ this much? I asked myself. Is there an image that you will never forget along the way? To me, these two images are like that.

ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
፲፩ ፡ ፬ ፡ ፳፻፲፬ዓ.ም

#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject
@Mykeyonthestreet
2025/10/21 23:49:04
Back to Top
HTML Embed Code: