Telegram Web Link
ለጥናትና ምርምርዎ እገዛ ይፈልጋሉ?
    አዎ ከሆነ መልስዎ!
በመንግስትም ሆነ በግል ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በዲፕሎማ፣ዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም ለምትማሩ እና ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ የምርቃት ጊዜያችሁን በጉጉት ለምትጠብቁ ሁሉ ስለ ጥናትና ምርምር በቂ እዉቀትን በመያዝ የመመረቂያ ፅሁፋችሁን ተመራጭ እና ተወዳጅ አድርጋችሁ በመስራት በጥሩ ዉጤት ትመረቁ  ዘንድ እናግዝዎታለን፡

If you need support related to:    
1 Assignment / አሳይመንት
2 Research / ሪሰርች
3 Proposal / ፕሮፖዛል
4 Term Paper /  ተረም ፔፐር
5 Case study/ ኬዝ ስተዲ
6 Article Review
7  Mini research
8  Business plan
9  Environmental impact assessment [EIA]

Any other Questions
Contact us via
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
👍469
በግዜ እጥረት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ትምህርታችሁ ላይ አፋጣኝ እገዛ የምትፈልጉ ተማሪዎች እና ተመራቂዎች
Research ከtitle መረጣ እስከ ማጠቃለያ (Discussion, conclusion and recommendations) ድረስ እናግዛለን።
ማንኛውንም አይነት አሳይመንት እናግዛለን።
ለDefense - powerpoint ለሚፈልጉም ማዘጋጀት እና possible defense questions እናቀርባለን
ማንኛውንም እገዛ በጥራት እና በፍጥነት
ለእገዛ👉🏾@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
👍3
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች ይወስዳሉ - የትምህርት ሚኒስቴር

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በሚሰጠው ድብልቅ የ12ኛ ክፍል መልቂያያ ፈተና ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን እንደሀገር የአቅም ችግር በመኖሩ ምክንያት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት አለመቻሉን ተገልጿል።

በመሆኑም የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ በትምህርት ቤቶች አቅም የሚወሰን ይሆናል ነው የተባለው።

የኦንላይን ፈተና ውጤትን በቶሎ በማሳወቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈተናን ለመስጠት፣ ስህተትን በመቀነስ እና በሌሎችም ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

ከኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር በመስራትና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር ጀነሬተሮችን በፈተና መስጫ ተቋማት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል።

ተማሪዎች ለኦንላይን ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንዲያመጡ ተገደዋል የሚባለው ወሬ እውነትነት የሌለውና ከትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ውጪ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል።


© ትምህርት ሚኒስቴር

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
👍29
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
👍32
ለተማሪዎች በሙሉ!!!
ለ MSc,MBA , Bsc, BA students from all discipline, !!!!
👍👍👍👍👍👍
ለማንኛውም
✍️Thesis MA/MSc
✍️Reaserch BA/BSc
✍️Proposal
✍️Title selection
✍️Research editing
✍️Power point preparation
spss software training
✍️Term Paper
✍️Case Study
✍️Assignment any
✍️Article Review
✍️Data Analysis
✍️Seminar Paper
✍️Feasibility Study
✍️Business Plan
✍️Project
👇  በሚፈልጉት research area በፍጥነትና በጥራትበማስተማር/ ስልጠና መስጠትና በሚፈለገዉ ጊዜ አጠናቆ በመስራት ከማንም ልዪ ያደርገናል::
ፍጥነታችን መለያችን ነው
ለእገዛ👉🏾@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
👍33
⭐️የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ

⭐️የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ(

ከሐምሌ 3-5 /11/2016 ዓ.ም ለማህበራዊ ሳይንስ

ከሐምሌ 9 -11/11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ


በቅደም ተከተል ይሰጣል
!!

⛔️ተፈታኞች በቀሪ ቀናት አስፈላጊውን የስነ ልቦና ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቹሀል‼️

© የካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
👍14🔥3
#Result #Remedial #Exit_Exam

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

(ከቲክቫህ ዩንቨርሲቲ የተገኘ)

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ #ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው #በፊት ይፋ ይደረጋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
👍26👌16
#2024_Commencement

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ደብረ ብርሃን - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
👍5113
ይፋ የሆነው የሬድሚዲያል ውጤት እንዴት ነው? እንዴት አገኛችሁት?

@NATIONALEXAMSRESULT
🎉23👍20
ለተማሪዎች በሙሉ!!!
ለ MSc,MBA , Bsc, BA students from all discipline, !!!!
👍👍👍👍👍👍
ለማንኛውም
✍️Thesis MA/MSc
✍️Reaserch BA/BSc
✍️Proposal
✍️Title selection
✍️Research editing
✍️Power point preparation
spss software training
✍️Term Paper
✍️Case Study
✍️Assignment any
✍️Article Review
✍️Data Analysis
✍️Seminar Paper
✍️Feasibility Study
✍️Business Plan
✍️Project
👇  በሚፈልጉት research area በፍጥነትና በጥራትበማስተማር/ ስልጠና መስጠትና በሚፈለገዉ ጊዜ አጠናቆ በመስራት ከማንም ልዪ ያደርገናል::
ፍጥነታችን መለያችን ነው
ለእገዛ👉🏾@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
👍202
የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ኦንላይን ስለሚካሄድ ትምህርት ቤቶች ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የተማሪዎችን ምዝገባ ኦን ላይን ለማካሄድ በለማው የኢ ስኩል ቴክኖሎጂ ዙሪያ ለርዕሳነ መምህራን  ጨምሮ ለአይ ሲቲ እና መረጃ ባለሙያዎች በዙር ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው ላለፉት ሁለት አመታት  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን  የ ኢ ስኩል ፕሮጀክትን በመቅረጽ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው በቴክኖሎጂው አማካይነት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የተማሪዎች ምዝገባን በሲስተሙ አማካይነት ኦን ላይን ማካሄድ እንደመሆኑ ሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ኦንላይን በመመዝገብ  ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም ትምህርት ቤቶች ለምዝገባው የሚያስፈልጉ ኮምፒውተሮችን ጨምሮ የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶችን ከወዲሁ ዝግጁ በማድረግ የምዝገባው  ሂደት ሴኬታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

የ ኢ ስኩል ፐሮጀክት የመማር ማስተማር ሂደቱን በቴክኖሎጂ ተደገፈ ከማድረጉ ባሻገር  ፖሊሲ አውጪዎችም  ሆኑ በጀት መዳቢ አካላት ከትምህርት ጋር የተገናኙ መረጃዎችን በቀላሉ  ማግኘት እንዲችሉ የሚያስችል ሲስተም መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዮናስ ጠቁመው  ምዝገባው በትምህርት ቤት መረጃ አስተዳደር ሲስተም (school information management system) አማካይነት የሚካሄድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ቂርቆስ ልደታ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን  እንዲሁም የአይ ሲቲ እና መረጃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ለቀሪ ክፍለ ከተሞችም ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
👍384
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ኦን ላይን ተፈታኞች በዛሬው እለት የሙከራ ፈተና ተሰጠ፡፡

የሙከራ ፈተናው አብርሖት ቤተ መጽሀፍትን ጨምሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የኦን ላይን መፈተኛ ጣቢያዎች የተሰጠ ሲሆን የሙከራ ፈተናው በዋናነት የፈተና ጣቢያዎቹን ዝግጁነት በማረጋገጥ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም እንከን መውሰድ እንዲችሉ የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ለመገምገም ታስቦ መሰጠቱን ከመርሀ ግብሩ አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ኦን ላይን  ፈተናን በስኬት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኢትዮ ቴልኮም እና ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  ጋር በጋራ በመሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  አመራሮች ጋር በመሆን  የሙከራ ፈተና ሂደቱን ለመከታተል በአብርሖት ቤተ መጽሀፍ በሚገኘው የፈተና ጣቢያ በተገኙበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በሙከራው የፈተና ሂደት የኮመፒወተሮች ዝግጁ መሆን የኢንተርኔት አገልግሎቱ አስተማማኝነት እንዲሁም እንዲሁም በየፈተና ጣቢያዎቹ ጄኔሬተሮችና ሌሎች ለኦን ላይን ፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች  መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ከመገለጹ ባሻገር ልምምዱ ተፈታኝ ተማሪዎቹን ለፈተናው በአግባቡ እንዲዘጋጁ ያስቻለ ተግባር መሆኑ ተገልጹዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍342
የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ፡፡

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ።

ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለፈተና ቁሳቁሶች እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ኅብረተሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባዘጋጀው የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መረጃ በመላክ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን ያቀርባል።

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍12🔥1
🔥 በርካታ ተማሪዎች ታግተዋል


ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል።

ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል።

አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች።

ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች።

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል።

የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን  አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
😢31👍30
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን እየገለጽን ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ በድጋሜ እንገልጻለን።

በመሆኑም ተማሪዎች ይሄንኑ ተገንዝባችሁ ዝግጅታችሁን እንድትቀጥሉ ሆኖ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ እንደተለመደው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንና ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉን እናስገነዝባለን።


ትምህርት ሚኒስቴር

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍181
ቴሌግራም እንደ ቲክቶክ ገንዘብ የምንሰራበትን Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ቴሌግራም ይህን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መጥቷል። አሁን ላይ ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት ትችላላቹህ።

አሁኑኑ ጀምሩት


https://www.tg-me.com/major/start?startapp=835671370
👍7🔥3
#AddisAbaba #NationalExam

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍253
2025/07/10 15:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: