Telegram Web Link
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ቴክኖሎጂያዊ አቅሙን ያለማቋረጥ እያሳደገ መሆኑ የሚያኮራ ነው ዐቢይ አህመድ (ዶክተር)

“እኛ ጦርነት አንፈልግም። የግድ ከመጣብን ግን የጦርነት ወሳኝ አቅም የሆነው አየር ሃይላችን ራሱን በቴክኖሎጂ ያለማቋረጥ እያሳደገ መምጣቱ በእጅጉ የሚያኮራ ነው” ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ጋር የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከጎበኙ በኋላ ነው።

‎ሰው ላይ ከተመሰረተ ይልቅ ቴክኖሎጂያዊ የውጊያ አቅም መፍጠር ላይ ማተኮሩ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እንደሀገር የመከላከያ ሃይላችንን በማጠናከር ረገድ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በጉብኝቱ በአየር ፣ ከአየር ወደ ምድር እና ከምድር ወደ አየር ውጊያዎች አስተማማኝ አቅም ስለመገንባቱ የገለጹት የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው ከተቋማዊ ሪፎርም ወዲህ አየር ሃይልን በኢትዮጵያ ልክ እያገዘፍን እንገኛለን ብለዋል
በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ቲክ ቶክን በመጠቀም ሰዎችን ሲያስፈራራና ሲዝት የነበረው በቲክቶክ ስሙ ቡራ ቡል (Burabull) ወይም ብሩክ ተስፋዬን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፤ ግለሰቡ ከዛቻ አልፎ በሁለት ሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት ማድረሱም በምርመራ ታውቋል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ቡራ ቡል (Burabull) ወይም ብሩክ ተስፋዬ ሰዎችን ስጋት ውስጥ የሚከቱ እና አስደንጋጭ የዛቻ ይዘት ያላቸውን እንዲሁም የፀጥታ አካላትን ስም የሚያጠለሹ መልእክቶችን በቲክቶክ ላይ ሲያሰራጭ ነበር፡፡

ግለሰቡ በሚለቃቸው ህገ-ወጥና ያልታረሙ መልዕክቶች ስጋት ውስጥ የገቡና አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ወደ ትግራይ ክልል የሄደ ቢሆንም ከክልሉ ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥ ስር ማዋል እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎና ነገር መጠቀም እየተቻለ በተቃራኒው ህዝብን ስጋት ውስጥ የሚከቱ መልዕክቶችን ማሰራጨት ተገቢነት የሌለው ተግባር እንደሆነ ፖሊስ አስታውቆ መሰል ድርጊት የሚፈፅሙ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹ 🌼

🌼 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ 1,000,000 የሚደርስ የበአል ቅናሽ በቤቶቻችን ና ሱቆችቻችን ላይ ከጃንቦሮ ሪልእስቴት

🔺 ሱቅ ኪራይ አማሮታል ???

🌼 ግንባታን በፍጥነት ጨርሶ በማስረከብ የሚታወቀው

🌼 ጀንቦሮ ሪል እስቴት በሳር ቤት(ቫቲካን ኤምባሲ )ጎን ግዙፍ የንግድ ሞል ላይ ሱቆትን ያድርጉ


   🔺የንግድ ሱቆቻችን
👉🏿ከ 18 ካሬ ጀምሮ - 57 ካሬ
👉🏿 ከ 18 ካሬ ጀምሮ = 4,248,000 ብር
👉🏿 15% ቅድመ ክፍያ = 637,200 ብር


🔺. የመኖሪያ አፓርትመንት
👉🏿በ10% = ቅድመ ክፍያ ብቻ*
👉🏿 ከ106m2 = 182 m2
👉🏿2 መኝታ ቤት = 3 መኝታ

🔺📞 0977191398
🔺Telegram =@selamssa
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓመታዊ የገቢ ግምት (Annual estimated revenue) $1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ ተተንብዩዋል። የዘንድሮውን የኢትዮጵያ በጀት 10% ማለት ነው። ይህ ጮቤ ባያስረግጥ ነበር የሚገርመን። የግድቡ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳም ከሚታሰበውም በላይ ነው።

ግብጽ የሚያንገበግባት የአባይን ጥቅም ስለምታውቅ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ላይ ትላንት በድህነቷም ሉዓላዊነቷን ያላስደፈረች ሀገር ፥ አሁን ኢኮኖሚያዊ ጡንቻዋን ለማፈርጠም ስትተጋ ማየት ያስደነግጣል። እውነቱን ከመቀበል ውጪ ሌላ ምርጫ የላቸውም።

ሀገራችን ለአባይ ታወጣ የነበረው ወጪ በገቢ ይተካል። እንደህዳሴ ያሉ ፖሮጀክቶችን የመስራት አቅሟ በሁለት እጥፍ ያድጋል። የማዳበሪያ ፋብሪካን በ3 ዓመት ገደማ ለማጠናቀቅ ውጥን ይዛለች። ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር እያደራጀች ነው። የባህር ኃይሏ ከ33 ዓመታት ቧሃላ ዳግም ተደራጅቷል። ግብፅ እንዴትስ አትደንግጥ !?

ኢትዮጵያ ተስፋ አላት። ያን መቀበል ያስፈልጋል። እየተለወጠች እንዳለ አንዱ ማሳያውኮ የጠላት ሀገራት ድንጋጤን ማየት በቂ ነው። በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለን ተሳትፎ ከዚህ እንቅፋትነት የተነጠለ መሆን አለበት። ኢትዮጵያን ያለ አብሯት ይቁም !
Drop of Tears !

#GERD #ItsMyDam
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፥ እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን ደስ አላችሁ። እንኳን በደስታ ሲቃ ለምንቀበለው አዲስ ዓመት አደረሳችሁ።

እንኳን ደስ አለን!
እንኳን አደረሰን!
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳቹ 🌼

🌼 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ 1,000,000 የሚደርስ የበአል ቅናሽ በቤቶቻችን ና ሱቆችቻችን ላይ ከጃንቦሮ ሪልእስቴት

🔺 ሱቅ ኪራይ አማሮታል ???

🌼 ግንባታን በፍጥነት ጨርሶ በማስረከብ የሚታወቀው

🌼 ጀንቦሮ ሪል እስቴት በሳር ቤት(ቫቲካን ኤምባሲ )ጎን ግዙፍ የንግድ ሞል ላይ ሱቆትን ያድርጉ


   🔺የንግድ ሱቆቻችን
👉🏿ከ 18 ካሬ ጀምሮ - 57 ካሬ
👉🏿 ከ 18 ካሬ ጀምሮ = 4,248,000 ብር
👉🏿 15% ቅድመ ክፍያ = 637,200 ብር


🔺. የመኖሪያ አፓርትመንት
👉🏿በ10% = ቅድመ ክፍያ ብቻ*
👉🏿 ከ106m2 = 182 m2
👉🏿2 መኝታ ቤት = 3 መኝታ

🔺📞 0977191398
🔺Telegram =@selamssa
ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለመከላከያ ሠራዊት የክብር አባላት የተላለፈ መልዕክት፤

ለሁሉም የመከላከያ ሠራዊት የክብር አባላት ።

እንኳን ወደ አዲሱ ዓመት 2018 ዓ/ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። ያለፈው 2017 ዓ/ም ከባድ የትግል ዓመት ነው መስዋዕትነት እየከፈልንና እየከፈላችሁ ከውስጥና ከውጪ ሊያጠፋን ያሰፈሰፉትን ሃይሎች በፅናት ታግለን ያሸነፍንበት የድል ዓመት ነው። አሁን ወደ አዲሱ ዓመት በድል የተሻገርንበት የ2017 መጨረሻ ዓመት ላይ ነን።

ዛሬ ማታ ሕዳሴ ግድብ ላይ ሆኜ የፅናት ተምሳሌት ዜጎችን ሳስብ ለሕዳሴ ግድብ ስኬት ሲሉ ሕይወት የከፈሉትን አካላቸውን ያጎደሉትን ወታደሮችና የሕዳሴ ግንባታ ሲያከናውኑ የተሰውትን፤ ገንብተው ያሸነፉትን የሕዳሴ ግድብ ጀግና ሠራተኞችን ሁሉ በሕልና ፀሎት አስታወስኳቸው። ጨክኖ ከኢትዮጵያ አገሩ ጋር የቆመውን፤ መቀታቸውን ፈተው የሰጡ እናቶችን፤ በጠቃላይ ግድቡን ጨርሱ ላለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ።

አንዳንድ ዜጎች ተሽጠው ከጠላት ወግነው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ሲያጠለሹ ሲያጣጥሉ ማህበራዊ ተፅኖ ሲፈጥሩ በነፍጥ አገር ሲያዳክሙ አገር ትወረር ሲሉ እናንተ የመከላከያ የክብር አባላት ግን በወገንተኝነት በደፋርነት በአገር ወዳድነት የጠላትን ማህበራዊ ተፅኖ ተቋቁማችሁ ያደረጋችሁት የትግል ታሪክ ተመዝግቦ ይኖራል። ለዓመታት ለኢትዮጵያ ብላቸሁ የጮሃችሁትን ጩኸት የያዘ ቪዲዮ ለልጆቻችሁ አስቀምጡና ታሪክ ስለሰራችሁ ልጆቻችሁ አያፍሩበትም። ፀረ ኢትዮጵያ የሰሩ ዜጎቻችንም የሰሩትን ፀረ ኢትዮጵያ ተልዕኮ ለልጆቻቸው ያሳልፉና ሁለቱም ልጆች ጎን ለጎን ቆመው የሁለታችሁንም ታሪክ ይተርኩ። ሁለት ትረካ ለቀጣይ ትውልድ ይቀርባል። የአርበኛና የባንዳ ማንነትን ነገ በታሪክ መነፀር ልጆች እንደሚያዩት አልጠራጠርም።
እንኳንም የክብር አባሎቻችን አደረግናችሁ መልካም አዲስ አመት፤ እንኳን አደረሳችሁ።
እንኳን ደስ አለን!

የኢትዮጵዊያን የደምና የላብ ጠብታ ለሆነው ብሔራዊ ፕሮጀክታችን ተጠናቆ ለምርቃት በመብቃቱ መላው ኢትዮጵዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን!

መላ ሕዝባችን ያሳየውን ትብብር፣ አንድነትና ተሳትፎ እንዲሁም ተስፋ ወደ ተጨበጠ ውጤት በመቀየር የአገራችን የኩስመና ታሪክና ቁማና እንዲያበቃ በሁሉም ዘርፍ እየሰጡት ላለው አመራር እና የሕዳሴ ግድባችን እንዲጠናቀቅ ባለራዕዩ መሪያችን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለሰጡት ቀጥተኛ አመራርና ክትትል ላቅ ያለ ምስግናየን አቀርባለሁ፡፡

ለባለራዕዩ መሪያችን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ግዙፉን ፕሮጀክት በማጠናቀቅና የዘመናት የሕዝባችን ህልም እውን በማድረግ፣ ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል ፣ የዚህ ደማቅ ታሪክ ባለቤት በመሆንዎ እንኳን ደስአለዎት ለማለት እወዳለሁ፡፡

የሕዝብን አደራ ተቀብላችሁ ሌትና ቀን በመስራት በላብ ጠብታችሁን ታሪክ የሰራችሁ የታላቁ ፕሮጀክት ሠራተኞች፣ በደም ጠብታችሁ አሻራቹህን ላኖራችሁ ሕያው የጸትታ ሀይላችንም ምስጋናየ አቀርባለሁ፡፡

የህዳሴ ግድባችን መጠናቀቅ የሀገራችን ታላቅ የታሪክ እጥፋት ፣ መጪው ጊዜ የብልጽግና፣ የእድገት ስለመሆኑ የብርሐን ዘመን ምልክት ማሳያ ነው፡፡ የጨለማው ዘመን አብቅቷል ፣ ወንዞቻችንን እና የተፈጥሮ ሀብታችን ተጠቅመን ከድህነት እና ከኋላቀርነት ለመውጣት የምናደርገው ጥረት አሁንም አጠናክረን መቀጠል አለብን፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ትርጉሙ ለኢትዮጵዊያን ከኤልክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ መጠናቀቅ በላይ ነው፡፡ የዘመናት ስብራት እና ቁጭት ነው መልስ ያገኘው፡፡ ከዚህ ግድብ ያወጣነው ብርሀን ነው፡፡ ከላፋን በአንድነት ከተባበርን ሀገራችን ንጋት ላይ ነች እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የምናገረግጥበት ጊዜ ሩቅ አይድለም፡፡

የህዳሴ ግድባችን መቶ በመቶ በኢትዮጵዊያን የፋይናንስ ዓቅም የተሰራ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ለልጆቻን የብልጽግና ቁልፍ የሆነ ትልቅ ቅርስ እንድናወርስ እድል ፈጥሯል፡፡ በተመሳሳይ የኢትጵያን አቅምን ለዓለም ማሳየት ችለናል ፡፡ የሀገራችን ገጽታ ከመሰረቱ እንዲቀየር እድልም የሚፈጥር ነው፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ቦንድ በመግዛት ፣ በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑም በተከታታይ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሚናውን ተወጧል፡፡ የዚህ ታሪክ አካል በመሆናችንም ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል፡፡

እንደ ተቋም መንግስትና ሕዝብ የሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት አገራዊ ለውጡን መነሻ አድረገን የጀመረውን ስኬታማ ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክረን የምንስቀጥል ይሆናል፡፡ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ በቀጣይ ሁሉንም የማህበረሰብ ታሳቢ ያደረጉ ግዙፍ የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የቅደመ ዝግጅት ሥራ እያጠናቀቅን በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንሰራት ጊዜ ላይ ናት፡፡ ተባብረን ከሰራን በከፍተኛ ሁኔታ የማደግ ተስፋና አለንና በአጭር ጊዜ የምናልመውን በልጽግና እውን ይሆናል፡፡ እንደ ተቋም አይቀሬውን ብልጽግና እውን ለማድረግ የኮርፖሬሽናችን አመራሮችና ሠራተኞች በላቀ ሀገረዊ ፍቅር እንሰራለን ፡፡

በድጋሜ እንኳን ደስ አለን !

ረሻድ ከማል ሰዒድ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ታላቁ_የኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች በምረቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ሲሆን 5,150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው።
2025/10/31 09:56:27
Back to Top
HTML Embed Code: