ድብቅነት
"በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም" ይባላል። ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ደብቀው መጨረሻ ላይ ሊረዱ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሆነው ይገኛሉ። ራሳቸውን እንደ ገደሉ ያህል ይቆጠራል፣ አብሯቸው ያለውም ሰው መርዳት ባለ መቻሉ ያዝናል። የማኅበራዊነትና የቤተሰብ ጥቅሙ መመካከር መቻሉ ነው። መመካከር ከሌለው ከተማው በረሃ ነው። የሰው ቅርጽ ማየት ሳይሆን የሰውነትን በጎነት መለዋወጥ የመኖር ትርጉም ነው።
ለመንፈሳዊ አገልጋይ ያለበትን ውድቀት የደበቀ ምእመን ለሰይጣን ምርኮኛ መሆኑ የታወቀ ነው። ከሰይጣን ታላላቅ ፈተናዎች አንዱ ድብቅነት ነው። ልጆች ድብቅ በሆኑ ቁጥር ውሎአቸውንና ስሜታቸውን በሰወሩ መጠን እየተጎዱ ይመጣሉ። ብዙ ልጆች በቤት ውስጥ ቢኖሩም ወላጆቻቸውም አያውቋቸውም። የዚህ ችግር ልጆችን በሁሉ ነገር መቆጣት ፣ ማቅረብ አለመቻል ነው። ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ እንደምንቀበላቸው ካወቁ፣ የልባችንን ስፋት ካስተዋሉ ሊነግሩን ይችላሉ። ለልጆች ወላጅ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም መሆን መልካም ነው። ሁሉን ለማወቅ ጥረት ካደረግን ልጆች ድብቅ ይሆናሉ። ማንም ለመርማሪ ፖሊስ ግልጽ መሆን አይፈልግምና ።
መፍትሔ የሚገኝበት ቦታ ላይ ድብቅ መሆን አደጋው ከፍ ያለ ነው። ለወላጆች፣ ለጓደኛ፣ ለሐኪም ፣ ለሥነ ልቡና አማካሪ ፣ በአበ ነፍስ፣ ለአገልጋይ ግልጽ መሆን በጣም ጠቃሚ ነው።
ድብቅነት ብለን ያነሣነው ካለማወቅና በእውቀት ድብቅ የሆኑ ሰዎችን ለማረም ነው። ድብቅነት ሽሽግነት ፣ ሽማቂነት፣ ስውርነት ፣ ለሰዎች ቅኔ መሆን፣ በልብና በአካል ከወዳጆች መሸሸ፣ ምንነቱ የማይታወቅ ሰው መሆን ፣ ግራ በማጋባት መደሰት ነው። ድብቅነት በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል። አሳብን መግለጽ በማይቻልበት ቤተሰብ በማደግ ሊመጣ ይችላል። የጨዋነት መለኪያ ዝምታ አይደለም። በአንዳንድ ቤተሰብ ልጆች እንዳይናገሩ በገደብ ያድጋሉ። ግልጽ በመሆናቸው ምክንያት ቁጣና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ድብቅ ይሆናሉ። ሌሎች ደግሞ በጉራ ኑሮ ተሸፋፍነው ስለሚኖሩ ሰዎች ከቀረቡአቸው ባዶነቱ ገሀድ እንዳይወጣ ድብቅ ይሆናሉ።
ያልሆነውን እንደሆንን አድርጎ ማቅረብ የሆነውን እንድንደብቅ ያደርጋል። በዚህ ዓለም ላይ ጥቅሙም ጉዳቱም የባለቤቱ የሆነበት ምርጫ ብዙ ነው። ባለጠጋ፣ አዋቂ፣ ጌጠኛ ብንሆን ለራሳች ን ነው። ይህ ሁሉ ባይኖረንም የመኖር መብት አለን። የድብብቆሽ ኑሮ እንዳንኖር የሆነውን መቀበል ያስፈልጋል። ራሳችንን ስንቀበል ሰዎች ይቀበሉናል። በሽታችንን፣ መልካችንን፣ ኑሮአችንን መቀበል ስልጣኔ ነው። መቀበል ለዓለም ችግር ትልቅ መፍትሔ ነው:: ችግሮች ሰባ ፐርሰንት የሚቀንሱት በመቀበል ነው። ትክክለኛ ማንነታችን ሁልጊዜ ሊገኝ ይችላልና አናፍርም፣ ስለዚህ የሆነውን ይዞ መቅረብ ይገባናል። ያን ጊዜ ከሰዎች ፍቅርና ክብር እናገኛለን። ድብቅነት ሰዎች ራሳቸውን አስረው የሚያሰቃዩበት የዓለማችን ትልቁ እስር ቤት ነው። ድብቅ በሆንሁ መጠን ክብር አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ሥቃይ ውስጥ ይከታል።
ድብቅነት የአእምሮ ፈተና፣ የሰይጣን ውጊያ ሊሆን ይችላል። ሁሉ ሰው ስለ እነርሱ ጥናት እያደረገ የሚመስላቸው፣ ሰዎች ይከታተሉኛል ብለው በማሰብ በብዙ አጥር ውስጥ ራሳቸውን የሚከቱ ሰዎች አሉ። የዚህ ችግር ለከፍተኛ ጭንቀት እየዳረጋቸው ይመጣል። ነገሮችን በቀላሉ ከማየት እያከበዱት ይመጣሉ። እያንዳንዱን የሰላምታ ልውውጥ እየፈሩት ይመጣሉ። እፈልጋለሁ አልፈልግም ብለው ቁርጡን ከመናገር ዙሪያ ገባውን የሚዞሩ ይሆናሉ። ማንኛውም ሰው ሊያጠቃኝ ይቻላል ብለው ስለሚያስቡ የቅርብ ሰዎቻቸውንም አያምኑም። በሚፈለጉበት ሰዓት ከመገኘት በአሳቻ ሰዓት ራሳቸው ሌሎችን መፈለግ ይመርጣሉ። የማላውቀውን ስልክ አላነሣም ፣ ብዙ ሰዓት ሰዎችን ማግኘት አልፈልግም ፣ ጨዋታ ይረብሸኛል ወደ ማለት ይሄዳሉ:: ስላሉበት ሁኔታ ማንም ሰው አለማወቁ የድል ስሜት እየመሰላቸው ይመጣል።
የድብቅነት ችግሩ ጉልበት ይጨርሳል። ጦርነት በሌለበት እየፈጠረ ይዋጋል። ነገሮችን አጋኖ ይመለከታል፣ ስልክ ለመደወል ላስብበት ይላል። ችግር ላለመስማት ሽሽት ውስጥ ይገባል። የማይታወቅ ፍርሃት ይንጠዋል። የቀን ሰላም፣ የሌሊት እንቅልፍ ይከዳዋል።
ለሁሉ ሰው መገለጽ ተገቢ አይደለም። በቦታው ግልጽ አለመሆን በሽታ ነው። ድብቅነት ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ያፈርሳል። አንዳንድ ሰዎች ከስለላ ስልጠና የተነሣ ድብቅ ይሆናሉ፣ ሌሎች ደግሞ ተንኮለኛ በመሆን ድብቅ ይሆናሉ። ስለ እኔ ማንም አያውቅም የሚል ጨዋታ መጫወት ድል ይመስላቸዋል። የእነዚህ ድብቆች የኋላ ዕድሜ በጣም ከባድ ይሆናል። ትዳራቸውም ፣ ወዳጅነታቸውም ላይጸና ይችላል። ድብቅነት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ይዘወተራል። ግልጽ መሆን ሕይወትን ቀላል ያደርጋል። ሰዎች ከእኛ ጋር መሆን የሚፈልጉት ቀለል ያለ ሕይወት መምራት ስንችል ነው።
ድብቅነት እንደ ክፉ ሰው እንድንታይ ያደርጋል። ሰዎች እየፈሩን ይሸሹናል። የሰዎችን እርዳታ በፈለግን ሰዓት እንኳ እንዳናገኝ ያደርገናል። ድብቅነት ለሞት ይደርጋል፣ አሰቃይቶ በመግደልም የታወቀ ነው። ሐኪም ቤት ስንሄድ የመጀመሪያው ምርመራ "ተንፍስ" የሚል ነው። መተንፈስ የተቃጠለውን አየር ያወጣል፣ ያለንበትን ሁኔታ ይገልጣል፣ መፍትሔ ያመጣል።
ትልቅ መንፈሳዊ ውድቀት የሚመጣው በድብቅነት ነው:: ካህኑ ሲናዝዝ፦ "መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን፣ ሰይጣን የሸመቀውን ኃጢአታቸን ይቅር ይበለን" ይላል። ሽምቅነት የሰይጣን ጠባይ ነው:: ሽምቅነት ችግሩ አለ፣ መፍትሔ እንዳያገኝ መደበቅ ነው ።
ከድብቅነት እንውጣ! በየጊዜው መተንፈስን እንለማመድ ፣ ከቅርብ ሰዎቻችን ጋር እንመካከር፣ አብሮ የመኖር ዋጋው ደስታና ችግርን በጋራ መካፈል ነው::
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤76👏3
ዝምተኛነት
ዝምተኛነት ተፈጥሮ ሊሆን አይችልም። ጨለማ የተፈጠረ ሳይሆን የብርሃን አለመኖር ነው ይባላል። መብራት ማብሪያና ማጥፊያ አለው። ውኃም መክፈቻና መዝጊያ አለው። ሰው የመናገሪያና የዝምታ ጊዜ አለው፡፡ ዝም ብሎ መቅረት ዱዳነት ፣ ሲናገሩ መኖር ለፋፍነት ነው። ዝም ፣ ድርግም ማለት ዱዳነት ፣ ሁልጊዜ ተናጋሪ መሆን እብደት ነው። ሙቅና ቀዝቃዛ ውኃ ተመጣጥኖ ሲወርድ ምቾት ይሰጣል። ዝምታና ንግግርም መመጣጠን አለባቸው። የምናመጣጥነውም ለራሳችንና ለሰዎች ጤንነት በማሰብ ነው።
የተመጠነ የሚባለው ከበርበሬውም ሳያቃጥል፣ ከሽሮውም አልጫ ሳይሆን ነው:: ሁልጊዜ መናገርም ያቃጥላል፣ አንደበት እሳት ነው፣ የፈተና መግቢያም ነው። ሰው ለፈተና የሚዳረገው በመናገርም ነው። በዚህ በኩል ጎበዝ ነኝ ሲል፣ ሲፈርድ፣ ራሱን ከመጠን በላይ ሲገልጥ ለፈተና ሊዳረግ ይችላል። ሁልጊዜ ዝም ማለትም ተገቢ አይደለም። ግዑዝ የትራፊክ ምልክት እንኳ ይናገራል። ሐውልትም ዘመንና ታሪክን ያወሳል። ሰው ከእነዚህ አንሶ ዝም ቢል ይወቀሳል። ዋናው የምንናገርበትና ዝም የምንልበት ሁኔታ በዓላማ ሊሆን ይገባዋል።
ዝም የሚሉ ሰዎች ሲበዛ ሰዎችን ያስጨንቃሉ፣ እንደ ድብቅ ይታያሉ። ንግግር ገና በጠዋቱ የጀመርነው በልምምድ ነው:: ዝምታ በልምምድ የተገኘውን ቋንቋ ማጥፋት ነው። ዝም የሚሉ ሰዎች ከምናውቃቸው የተለየ ጠባይ አላቸው። ጥያቄ መፍጠርና ጥያቄ መሆን ደስ ይላቸዋል። በዝምታቸው ሰዎች ሲተራመሱ ማየት በጣም ይወዳሉ። ዝምታ በቀልም ሊሆን ይችላል። ደስታቸውን መግለጥ ስለማይፈልጉ ስሜታቸውን ሰው እንዳያውቅባቸው ይፈልጋሉ። አጠገባቸው ያሉትን ተናጋሪ ሰዎች በዝምታ መቅጣት ይፈልጋሉ። ተናጋሪ ራሱ ነዶ እስኪጠፋ ድረስ ያዩታል። ውስጣቸው ጠንካራ ሲሆን ሁሉም ነገር ከልክ አያልፍም የሚል አሰተሳሰብ አላቸው።
ዝም የሚሉ ሰዎች ከሌሎች በተሻለ ስለ ዓለም ግንዛቤ አላቸው። ማወቃቸውን ግን ሰዎች እንዲያውቁባቸው አይፈልጉም። ከራሳቸው ጋር በጣም ልዩ ፍቅር አላቸው። ወደ ውስጣቸው በጣም ስለሚያወሩ ከሰዎች ጋር ማውራትን አይፈልጉም። ራሳቸውን አውርተው አይጠግቡትም። አጠገባቸው ስላሉት ሰዎች ቸልተኝነት ሊሰማቸው ይችላል። በጣም የሚወዱት ነገር ጫጫታ ነው። ብዙ ዝምተኞች ኳስ ፣ ዘፈን፣ መዝሙር፣ በዓላት፣ ሰርግ ፣ ድምፁ ከፍ ያለ ነገር ይወዳሉ። ቀኑን በሙሉ የሚለፈልፉ የሬዲዮ አፍቃሪዎች ናቸው። መናገርን ባይፈልጉም የሚዝናኑት ግን ጩኸት በመስማት ነው።
ዝምተኞች ራሳቸውን ገለል ማድረግ ሲወዱ ሁልጊዜ መፈለግ እንዳለባቸው ያስባሉ። በውስጣቸው የማይገለጽ ደስታ ሲኖራቸው ያንን ለሌሎች ማጋራት አይችሉም። ሥራ መሥራት ያስደስታቸዋል :: ሥራቸውን ግን መግለጽ ስለማይችሉ አይታወቅላቸውም። ወንዶች ከሆኑ ብዙ ሴቶችን የማስከተል አቅም አላቸው። ዝምተኛ ሴቶችም በዙሪያቸው ለፍላፊ ወንዶች አሉ። ዝም የሚለው ግን ዝም ያለ አይደለም። ተናጋሪዎችን ቀጥሯል፣ አሊያም በጽሑፍ ተደብቆ ይናገራል። ሥዕል ይሥላል::
የዝምታው ምንጭ ለመናገር የሚያበረታታ ቤተሰብ አለማግኘት ሊሆን ይችላል። በቂ እውቀት አለማዳበር ዝም ያሰኛል። ፍርሃትም የዝምታ ምንጭ ነው። ዝምታን እንደ ቅድስናና ጨዋነት ማሰብም ዝም ያሰኛል። በመከራና በአደጋ መደንገጥ ወደ ዝምታ ዓለም ይወስዳል። ብናገር ሰው ላስቀይም እችላለሁ በማለት ዝም ሊባል ይችላል። ከመጠን በላይ ሰዎችን ማክበርና መፍራትም ዝምታን ይወልዳል።
ዝም የሚሉ ሰዎች ብዙ ዕድሎች ያመልጧቸዋል። ክብርን ያገኙ ቢመስላቸውም በተቃራኒው ግን ምንም እንደማያውቁና ስሜት አልባ እንደሆኑ ይገመታሉ። ተገቢ ንግግር አለማድረጋቸው ከቅን ፍርድ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል። የአንደበትን አገልግሎት አልተረዱምና ሌሎችን መስበክ ያቅታቸዋል። ችግርን መናገር እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥሩት በቀላሉ ጉዳይ ትልቅ ዋጋ ይከፍላሉ። ራሴ እወጣዋለሁ የሚል ኩራት ቢኖራቸውም መረዳዳት ግን አስፈላጊ መሆኑን ይረሳሉ።
ለመናገር ጊዜውን፣ ቦታውን ፣ ሁኔታውን መርምሩ ! እንዲሁም ለዝምታ ጊዜውን፣ ቦታውንና ሁኔታውን ተመልከቱ !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤73👍5👏2
ዛሬ ዓርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
Telegram
Nolawi ኖላዊ
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
❤9
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ዛሬ
እሑድ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 7 ይቀጥላል
ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ከ40 በላይ ምክንያቶች ይተነትናል።

❤19👏3
ተወዳጅነት
ተወዳጅነት በብዙ መንገዶች ሊመጣ ይችላል። እውነተኛ ተወዳጅነት ግን ዋጋ የሚያስከፍል፣ ግላዊ መለወጥን የሚጠይቅ ነው:: ሁላችንም ተወዳጅ መሆን እንፈልጋለን፤ ተወዳጅነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ግን ፈቃደኛ አይደለንም። መቼም በሕይወት ውስጥ ሁሉም ሰው ይወደኛልና ሁሉም ሰው ይጠላኛል ብሎ ማሰብ ሁለቱም ጤናማ አይደለም:: ይህ ዓለም በግና ተኩላ እኩል ተሰማርተው ያሉበት ዓለም ነው:: ስለዚህ ሁሉም ሰው ሊወደን አይችልም። የጉዞ መመሪያዎችም ከሰዎች ተጠበቁ፣ ተጠንቀቁ የሚሉ ናቸው ። እግዚአብሔር ወዳጅ ነውና ወዳጅ ይሰጣል። የሚወዱን ሰዎች ስጦታዎቻችን ናቸው:: አጥብቀን፣ አክብረን ልንይዛቸው ይገባል። ሁሉ ይወደኛል ብሎ መዘናጋት፣ ሁሉ ይጠላኛል ብሎ መስጋት ተገቢ አይደለም። ሁሉ ቢወደን ሞትን አያስቀርልንም፣ ሁሉ ቢጠላንም መኖር የአንድ አምላክ ፈቃድ ነው:: ሁሉ የሚጠላቸው የምድር ገዢዎች አምሮባቸው ይታያሉ። እግዚአብሔር ለጥላቻ ድል ስለማይሰጥ አይጎዱም። የተረገሙ ሰዎች ሲለመልሙ የሚታዩት እኛው ፍርድ ሰጪ ፣ ቅጣት ሰንዛሪ ስለሆንን ነው።
ተወዳጅ ሰዎች እነማን ናቸው?
1- ሰዎችን የሚወዱ ናቸው:- ፍቅር እግዚአብሔር ነውና ክንፎቹ በጣም ሰፊ ናቸው። ስለዚህ ሁሉን መውደድ እንችላለን። ሁሉን በመውደድ ክርስቶስን እንመስለው ዘንድ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" አለን። ጾታ፣ ዕድሜ፣ ወገን፣ ቋንቋ፣ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ወረቀት ሳያዩ ሁሉን የሚወዱ ሰዎች ተወዳጅ ናቸው። መሬት ካልዘሩባት አታበቅልም፣ ሰው መሬት ነውና ፍቅርን ካልዘራንበት አይሰጠንም። ካልወደድን የሚወደን የለም። ተወዳጅ ለመሆን ቀድመን መውደድ አለብን።
2. ትሑታን ናቸው፦ ትዕቢተኛ ሰዎችን በሩቅ አይተን እንጠላቸዋለን። በአረማመዳቸው መሬት አይንካን የሚሉትን ለመተናኰል እንፈልጋለን። ትሑታን ካልሆንን እኛም የሚያየን ሁሉ ይጠላናል፣ ይተናኰለናል። ትሕትና የራሱን ክብር የሚፈልግ ሰው ለሌላም ክብር የሚሰጥበት ነው። ትሕትና በእውቀት ሙሉ የመሆን ውጤት ነው። አላዋቂ የበታችነት ስለሚሰማው ትዕቢተኛ፣ ዋስትና ስለማይሰማው ተንኰለኛ፣ ሁሉን ስለሚጠላ ቀማኛ ይሆናል። አላዋቂ ከገዛ አባት እናቱ ጉቦ ይቀበላል:: ትሑት ሠርቶ የሚያሠራ፣ ሁሉን በቋንቋው የሚያናግር፣ ያለውን ገንዘብ፣ ሙያና እውቀት ለመስጠት የማይሰስት ነው ። ትሑታን ስንሆን ሰዎች ይወዱናል፤ ጉረኛ፣ ራሳችንን የምንቆልል ፣ መስፈርት የምናበዛ ሰዎች ስንሆን መጠላትን እናተርፋለን።
3. የማይታዘቡ ናቸው፦ ሰዎች ተናደው ስለ ልጃቸው፣ ስለ ትዳራቸው መጥፎ ንግግር ቢናገሩን እንዴት ልጁን እንዲህ ይላል? ብለን መታዘብ አይገባንም። ሰው አለ ብለው ወደ እኛ ሲመጡ ሰው ሆነን መገኘት አለብን። በዚህ ዓለም ላይ እጅግ ክፉ ሰዎች የሚታዘቡ ናቸው። ሰዎች የልባቸውን፣ ለማን ልንገር ? የሚሉትን የቤታቸውን ጉድ፣ ውስጣቸው የበገነበትን ኑሮአቸውን ሲነግሩን አብረን እያለቀስን ልንካፈላቸው ይገባል። ዛሬ ለእኛ እሑድ ፋሲካ ቢሆን ፣ ለእነርሱ ዓርብ ነውና ልናግዛቸው ይገባል። የእኛም ዓርብ እየመጣ ነውና። ተወዳጅ ሰዎች ሳይታዘቡ፣ ያዩትን ለማሳየት ሳይጥሩ የተቆጣውን ያበርዳሉ፣ እንባን ያብሳሉ። ተወዳጅ ለመሆን አለመታዘብ ይገባል ::
4. የሚረዱ ሰዎች ናቸው፦ ፊትን አንብበው ያንን ሰው ያረጋጉታል። ያልመጣው ስላልተመቸው፣ ያልሰጠኝ ስለሌለው ነው ብለው ያምናሉ። በጎ፣ በጎውን ስለሚያስቡ ጤነኛ አእምሮ አላቸው:: የራሳቸውን ድርሻ ይወጣሉ እንጂ በኑሮአቸው ፉክክር ውስጥ አይገቡም። አንዳንድ ሰዎች ስልክ ለመደወል ሰነፍ ናቸው፣ ያንን ድካማቸውን ተረድተው ራሳቸው ይደውላሉ። በመጠባበቅ ፍቅርን አያከስሙም። ተወዳጅ ሰዎች ለመሆን ሰዎችን መረዳት አለብን። ሰዎች የሚረዳቸውን ሰው በጣም ይወዳሉ። የትም ሄደው ቢመጡ እንደ ክርስቶስ እንደሚቀበላቸው ያምናሉ።
5. አይፈርዱም፦ እንደ ማኅበረስብ ፈራጅ ተብለን ብንፈረጅ ተገቢ ይመስላል:: በአገራችን ትልቁ ኃጢአት ፈራጅነት ነው። ሳያጣሩ በለው ማለት፣ በማይመለከተን የሰው ጉዳይ ላይ ጊዜ ማባከን፣ የራሳችን አሮብን የሰውን ማማሰል ፣ እንዴት ይህን ያደርጋል ? ማለት የቀን ውሎአችን ነው:: እንሰርቃለን፣ ሌባ ይገደል እንላለን። እናመነዝራለን፣ አመንዝራ ይጥፋ እንላለን። ኃጢአትን አንጠላም፣ ኃጢአተኛን እንጠላለን። ተወዳጅ ሰዎች የወደቀውን ለማንሣት የሚጥሩ፣ ፍቅርን የሚሰጡ፣ እጃቸውን የሚዘረጉ ናቸው:: እግዚአብሔር ለፍርድ ቢነሣ የማይታሰር የለም። ፍርድን ለእርሱ መተው፣ ባወቅህ ማረን ማለት ተገቢ ነው::
6. በመንገዳቸው ላይ ናቸው:- ዓላማቸውን፣ ሃይማኖታቸውን ፣ ራእያቸውን አይቀያይሩም። "እኛስ የሃይማኖት ለዋጮችን ሥራቸውን እንጸየፋለን" እንደ ተባለ ተለዋዋጭ ሰው የተጠላ ነው። በአቋው የጸና የተወደደ ነው። በሌላው መስመር ላይ የማይገቡ፣ የሚመለከታቸውን ለይተው ያወቁ ፣ ዋዛ ፈዛዛን ሳይሆን ቁምነገርን የሚፈልጉ ተወዳጅ ናቸው። የሌላውን ዓላማ አይቃወሙም፣ በኃይል ወደ እኔ ላምጣው አይሉም። በዚህ ምክንያት ተወዳጅ ፣ መስሕብ ያለው ሰው ይሆናሉ። ተወዳጅ ለመሆን በዓላማችሁ፣ በሃይማኖታችሁ ጽኑ !
ይቀጥላል
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤62🥰6👏2
ተወዳጅነት (2)
ተወዳጅ ሰዎች እነማን ናቸው?
7. ምሥጢር ጠባቂ ናቸው፦ ሰውን ሰው ከሚያሰኙ ነገሮች አንዱ ምሥጢር ጠባቂነት ነው። ምሥጢር ሊጠብቅ የማይችል ሰው ለክህነት፣ ለመንግሥታዊ ሹመት ሊበቃ አይገባውም። ይህች ዓለም ቆማ የምትሄደው በምሥጢር ነው። ምሥጢር ጠባቂ ሰዎች ለትልልቅ አደራዎች ይታጫሉ። ባለጠጎችና ባለ ሥልጣናት የቅርብ ሰው በጣም ይፈልጋሉ። መስፈርታቸውም፦ ምሥጢር ጠባቂነት፣ ታማኝነትና ንቁነት ነው። ምሥጢር ጠባቂዎች ሰፊ እውቀት ላይኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን በመብራት ይፈለጋሉ። በዚህ ዓለም ላይ ጓዳን የሚያሳዩት፣ የሚገለጡለት ፣ ይታዘበኛል ብለው የማይፈሩት ሰው አስፈላጊና ውድ ነው።
የጨዋ አስተዳደግ አየሁ አላየሁም፣ ሰማሁ አልሰማሁም ነው። አዋቂ የሆኑ አሳዳጊዎች ለልጆቻቸው የሚነገርና የማይነገር ነገርን ገና በጠዋቱ እየነገሩ ማሳደግ አለባቸው። በለጋነት ያልተቃናን በጉልምስና ማቃናት ከባድ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ከአስተዳደግ ያለፈውን መንፈሳዊነት ይቀርጸዋል። ለትምህርትና ለለውጥ ረፈደ አይባልም። ፈያታዊ ዘየማን ጣር ላይ ሆኖ ተለወጠ። ከመጀመሪያው የመጨረሻው የተሻለ ነው። ብዙዎች የአስተዳደግ ውጤት ናቸው፣ ምሥጢር ጠባቂነት እጅግ አስፈላጊ ነው። ምሥጢር የሚባል የለም፣ ሁሉም ነገር ገሀድ መውጣት አለበት የሚሉ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የስልካቸውን፣ የባንካቸውን ፣ የኢሜላቸውን የምሥጢር ቍጥር ግን ለማንም አይሰጡም። መስጠትም የለባቸውም። በዚህ ዓለም ላይ የንግድ፣ የአስተዳደር፣ የፖለቲካና፣ የፓርቲ፣ የክህነት፣ የሙያ፣ የቅመማ፣ የወታደራዊ ዕዝ፣ የኒውክለር ምሥጢሮች አሉ። አንድ ሰው ፍጹም ራሱን ስቷል የሚባለው ሁሉንም ነገሩን አደባባይ ሲያወጣ ነው። ልብስ መልበስ ምሥጢራዊነት ነው። ቤት ማደር ፣ በር ዘግቶ በሽተኛን ማከም፣ የታካሚዎችን ምሥጢር መጠበቅ እነዚህ ሁሉ ምሥጢር ናቸው ። ምሥጢርን መጠበቅ ሕጋዊ ግዳጅም አለው። የሰሙትን ምሥጢር እንዲናገሩ ዳኛም የ ማያስገድዳቸው ባለ አደራዎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ የምሥጢር አገልጋይ የሆኑት አበ ነፍሶች ናቸው።
ምሥጢር የሚጠብቅ ሰው ተወዳጅ ነው። ተወዳጅ ሰው ለመሆን ምሥጢርን መጠበቅ መለማመድ አለብን። ሁሉም ሰው እንዲጠበቅለት የሚፈልገው ምሥጢር አለና የነገሩንን ያሳዩንን መግለጥ አይገባም። ይልቁንም ሁለት ሁነው ያወሩትና የሠሩት ለሦስተኛ አካል አይነገርም። ይህን ዱርዬም የሚጠብቀው ጨዋነት ነው። ምሥጢር ጠባቂነትን ጠባይ ስናደርግ የምንውለው በቤተ መንግሥት ከነገሥታት ጋር፣ በቤተ ክህነት ከጳጳሳት ጋር ነው።
8- አቅልለው የሚያዩ ናቸው፦ ሰዎች በግድ የለሽነት፣ ተስፋ በመቁረጥ፣ በፍልስፍና ነገሮችን አቅልለው ሊያዩ ይችላሉ። ከሁሉ በላይ ይህችን ዓለም የሚያዝባት የእግዚአብሔር ሥልጣን እንዳለ በማመን ፣ ያልኩት ሳይሆን ያለው ይሆናል በሚል እምነት ነገሮችን አቅልለው የሚያዩ አሉ። በርግጥም ይህችን ዓለም ለመቀላቀል ብርና ወርቅ ወሳኝ ቢሆን ኖሮ ዕራቁታችንን አንወለድም ነበር። የመንገድ ስንቅ መሆን ቢችል ኖሮ ዕራቁታችንን አንቀብርም ነበር። የሰው ልጅ በልደትና በሞቱ በመጀመሪያውና በመጨረሻው ምዕራፍ ፍጹም ድህነቱን ይገልጣል። ትቶት የሚሄደውም ሀብት ሰላምን አሳጥቶ ቤተሰብን ያባላል፤ ፍቅርን ነሥቶ እናትና ልጅን ያካስሳል። ስንፍናን ዘርቶ ሥራ አስቁሞ ወራሹን ሱሰኛ ያደርጋል። የውርስ ገንዘብ የሞት አዚም ስላለው ብዙም አይበላምና የእጃችንን ሥራ መመኘት ይገባል። እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ እንጂ ውርስህን እባርካለሁ አላለም። ያልለፉበት ገንዘብ ሕይወትን ያለፋል። እነዚያን የገፋ እኛን ያቆስላል። ታዲያ ዕራቁቱን ለተወለደ ቁምጣ መች አነሰው ይባላልና ነገሮችን አቅልሎ ማየት ይገባል። በዚህ ዓለም ላይ ሐሰት የተባለው የመጀመሪያው ዲያብሎስ ሲሆን ሁለተኛው ውበት ነው ። ውበት ሐሰት ነው። ቅቡ አንጥረኛ ጋ ሲሄድ ወርቅ እንዳልሆነ ይታወቃል። እንዲሁም በኑሮ ውስጥ ቀዩ ይጠቁራል፣ ጥቁሩ ይገረጣል። ደጋ ቢሄድ ይመጠጣል፣ ቆላ ቢወርድ ይጠቁራል። ውበት ሐሰት ነው ። ከንቱና ባዶ ነው።
አቅልለው የሚያዩ ሰዎች ከችግሩ ይልቅ ለመፍትሔ ይተጋሉ። በሰማሁት ነገር ላይ የእኔ አስተዋጽኦ ምንድነው? ይላሉ። በዓለም ላይ አዲስ ነገር እንደሌለ የታሪክ እውቀት አላቸው፣ እግዚአብሔር ነገን እንደሚያስተካክል ጽኑ እምነትን ገንዘብ አድርገዋል። ተራራውን በእምነት ቃል ደልድለው ሲያሳዩ የተጨነቀው እፎይ ይላል። መፍትሔ አያጡምና እነርሱ በመጡልኝ ይባላሉ። አቅልለው የሚያዩ ሰዎች ቁጭ ብሎ ከማሰብ መንቀሳቀስ ለውጥ እንደሚያመጣ ያውቃሉ። ሁሉም ነገር ትልቅ የሚሆነው ተቀምጠው ሲያዩት ነው። አቅልለው የሚያዩ ሰዎች ለክብራቸው ለስማቸው ሲጋጩ የሚኖሩ አይደሉም። ሁሉንም ነገር በልኩ ያዩታል፣ ላለው አያረግዱም፣ የሌለውን አያግዱም። ሁሉንም ነገር በመጠኑ ማየትና ከልኩ አያልፍም በሚል እምነት በመጠን ይኖራሉ። ሰላማቸውን ይጠብቃሉ። የነገር እሳትን እያቀጣጠሉ ጠብን ብሔራዊ አያደርጉም። የሚጠቅምን እንጂ የሚጎዳን ነገር ለማንም አያስተላልፉም ። ተወዳጅ ለመሆን ነገሮችን አቅልለን የምናይ መሆን አለብን።
9. ንጹሕ ናቸው:- የልብ ንጽሕና ዋና ነገር እንደሆነ ሁሉ አካላዊ ንጽሕናም ወሳኝ ነው። አብዛኛው የብሉይ ኪዳን የሥርዓት ሕግጋት ከንጽሕናና የራስንም የሌሎችንም ጤና ከመጠበቅ ጋር የተያያዘ ነው። አካላዊ ንጽሕና ለጤና፣ ለነጻነት ስሜት፣ ለክብር፣ ራሳችንን ለመቀበል፣ በሌሎችም ለመወደድ አስፈላጊ ነው። ንጽሕናውን የማይጠብቅ የእአምሮ ችግር ውስጥ እያለፈ ነው። ንጽሕናን አለመጠበቅ የጭንቀት ስሜትን እያባባሰ ይመጣል። በአእምሮ ጭንቀት ውስጥ የሚያልፉ ሰዎችን ለመርዳት ልብሳቸውን ፣ መኝታቸውን ንጹሕ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው። የንጽሕና ችግር ራሳችንን እንድንጠላው ያደርገናል። ሰዎችንም ከእኛ እያሸሸ ይመጣል። አንዳንድ ጊዜም ለትዳር መፈታት እንደ ምክንያት ይሆናል። የመጨረሻው የስንፍና ጥግ የራስን ንጽሕና መጠበቅ አለመቻል ነው።
ብዙ ጊዜ የማንገነዘበው ነገር ጤናችንን የሚጎዳው የንጽሕና ችግርና የአመጋገባችን ሁኔታ ነው። ከራስ ፀጉራችን እስከ እግር ጥፍራችን ድረስ ንጽሕናን መጠበቅ ይገባናል። ንጽሕናን ለመጠበቅ ቀጠሮ ሊኖረን አይገባም። ከመኝታ ስንነሣ ተግባራችን ሊሆን ይገባዋል። ይልቁንም ሰዎች እስኪናገሩን መጠበቅ የመጨረሻው ሞት ነው። እግዚአብሔር ዓይንና አፍንጫን የራሳችንን የቤታችንን ንጽሕና እንድንቆጣጠርበት የሰጠን ጸጋ ነው። ውኃ የተዘጋጀው ለንጽሕና ነው። መቆሸሽና ራስን መጣል መንፈሳዊነት አይደለም፣ ስንፍና ነው። ሰዎች እኛን እንዲወዱን ብቻ ሳይሆን ራሳችን እንድንወደውም ንጹሕ መሆን አለብን። አካላችንን፣ ልብሳችንን፣ ቤታችንን ማጽዳት ማስተካከል ግድ ነው። ይህን መሥራት ካልቻልን ምን እንሠራለን? የገጠሩ ሰው ባይታጠብ እንኳ የተሻለ ነው፣ የከተማው ሰው ግን አኗኗሩና አመጋገቡ ስለ ተበከለ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ሰዎች አንድ ቀን በገፋቸው ቆሻሻና ጠረን ሁልጊዜ ይገምቱናልና ጎበዝ መሆን አለብን። ዋና ዋና የሚባሉ የአካል ክፍሎቻችንን በየዕለቱ ማጽዳት ተገቢ ነው። አሊያ በቁማችን መሞትና መበከልን እንለማመደዋለን። ተወዳጅ ለመሆን ንጹሕ፣ ቀልጣፋ፣ ሥነ ሥርዓት ያለው፣ የማይዝረከረክ ፣ ሞኝነትን ያራቀ ሰው መሆን ይገባል።

❤32
10- ስጦታ የሚሰጡ ናቸው:- እግዚአብሔር ፍቅሩን የገለጠው አንድ ልጁን በመስጠት ነው። የክርስትና ሃይማኖት የቆመው በጸጋ ወይም በስጦታ ላይ ነው። ለወዳጆቻችን ስጦታ መስጠትን መለማመድ አለብን። ስጦታ የፍቅር መግለጫ ነው። ያንን ስጦታ ባዩ ቁጥር እኛን ያስታውሳሉ። ስጦታ አነሰ በዛ ሳይባል የሚሰጥ ነው። ዓላማው ፍቅርን መግለጫ ነው። ለስጦታ የሚረዱ አነስተኛ ፖስት ካርዶች ዛሬ ላይ እየጠፉ ነው። በሌላው ዓለም ግን አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው። የመስቀል፣ የሥዕል፣ የመጻሕፍት ስጦታዎች አሁን አሁን እየቀሩ ነው። ራሳቸው በእጃቸው ሥዕል ሥለው፣ ጥልፍ ተጠልፈው፣ ሹራብ ሠርተው ስጦታ የሚሰጡ ወገኖች ነበሩ። በዚህ ዘመን እነዚህን ስጦታዎች አክብሮ የሚቀበልም እየጠፋ ነው። ብቻ ስጦታ የሚሰጡ ተወዳጅ ናቸው። በዚያ ሰው ልብ ላይ በልዩ ይቀመጣሉ።
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
❤48🥰4👍3
Forwarded from Nolawi ኖላዊ
በዲያቆን አሸናፊ መኰንን የተጻፉትን ና በገበያ ላይ ያሉትን እነዚህን መጻሕፍት በሙሉ ለሚገዙ አዲስ አበባ ላይ ላሉ ወዳጆች ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!
1- የእግዚአብሔር ትዕግሥት 400
2- የኑሮ መድኅን 200
3- ተንሥኡ ለጸሎት 60
4- ረጅሙ ፈትል 170
5- የጊዜው ቃል 200
6- ቅዱስ ጋብቻ 200
7- እንደ እኔ ከተሰማችሁ 150
8- የሕይወት መክብብ 150
9- አካላዊ ቃል 250
10- ቃና ዘገሊላ 250
11- ኒቆዲሞስ 170
12- ሳምራዊቷ ሴት 250
13-መጻጉዕ 250
14- የወዳጅ ድምፅ 180
15- ኅብስተ ሕይወት 250
16- የሕይወት ውኃ 250
17- ኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ 300
18- ምዕራፈ ቅዱሳን 200
19- የደስታ ቋጠሮ 130
20- የዕለቱ መና 200
21- የበረሃ ጥላ 200
22- ወዳጄ ሆይ 200
23- የአገልግሎት ቱንቢ 250
24- ጴጥሮስ ወጳውሎስ 250
25- ሰንፔር 170
26- መንፈሳዊ በረከት 500
27- ጥበበኛው ድሀ 2ዐዐ
አጠቃላይ ድምር 5,980 ብር
በሚከተሉት የባንክ ሂሳብ በመላክ በ0911 699907 ላይ በቴሌግራም ደረሰኙን ይላኩ ፈጥኖ ይደርሰዎታል
የሕይወት ዘመን ስንቅ ያለባቸው ድንቅ መጻሕፍት!!!
አሸናፊ መኰንን ወርቁ
Ashenafi Mekonnen worku
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000165078482
አቢሲንያ ባንክ
23202573
ወጋገን ባንክ
0870286030101
አዋሽ ባንክ
Awash Bank
01320034656200

👍8❤5
ተወዳጅነት (3)
ተወዳጅ ሰዎች እነማን ናቸው?
11- አመስጋኝ ናቸው:- ኑሮአቸው አነስተኛ ቢሆንም ያመሰግናሉ ። ለማመስገን ማመስገን ብቻ ምክንያት ይሆንላቸዋል። አመስጋኝ ሰዎች ተወዳጅ ናቸው። በምስጋና ውስጥ ኃይል አለ፣ ጳውሎስና ሲላስ ሲያመሰግኑ የወኅኒው ደጃፍ የተከፈተው ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለመላው እስረኛ ነው። ስናመሰግን አጠገባችን ያሉት ሰዎች በኃይል መሞላት ይጀምራሉ። የኃይል ምክንያት የሚሆነውን ሰው የማይወድ የለም፣ ዓለሙ የሚያደክም ነውና። አመስጋኝ ሰዎች እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ውለታ የዋሉላቸውን ሰዎችም ያመሰግናሉ። ብዙ ጊዜ ከምንረሳቸው ነገሮች አንዱ አለማመስገን ነው። ወላጆቹን የሚያመሰግን ጥቂት ነው። ብዙ ዓመታት ተሸክመውት ሳለ አንድ ሳምንት በቤቱ ለማስተናገድ የሚታክት ብዙ ውለታ ቢስ አለ። ሌላው ወገን ከትዳሩ ጀምሮ ሲያድግና ሲያደርግ እንደ ወደዱት ይረሳል። የማይወደደውንና ምንም ማድረግ የማይችለውን ትንሹን ማሙሽ የወደዱትን መርሳት እንዴት ይቻላል? እኩዮቻችንን አናመሰግንም፣ ለእኛ ጊዜና ፍቅር የሰጡ ናቸው። በዘወትር ትግላችን የሚያደምጡን ናቸው። ወዳጆችን ፣ ያገዙንን፣ መምህራንን ማመስገን እየረሳን ነው። ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን ለማመስገን ረስተናል።
ምስጋና ቢስ ሰው ከእባብ ስለታም ጥርስ በላይ የሚጎዳ ነው። ምስጋና ቢስ ልጅ ፣ ምስጋና ቢስ ወዳጅ ይጎዳሉ። ሰው የምስጋና ዕዳውን ካልመለሰ በነፍሱ የታሰረ ነው። ብዙ አስከፊ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ከምስጋና ቢሶች በላይ ግን አስከፊ የለም። ምስጋና የዘወትር ሕይወት የሆነላቸው ሰዎች ተወዳጅ ናቸው። በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ እንድንሆን ማመስገንን፣ ባለን ነገር መደሰትን ዘይቤ ማድረግ አለብን። አማራሪ ስንሆን ሰዎች ይርቁናል። አንድ ቀን ምርር ስንል የሰሙን ሰዎች በሚገርም ሁኔታ እስከ ዛሬ ድረስ አላገኘናቸውም።
12- ታማኝ ናቸው፦ ታማኝነት ለራስ ነው፣ ታማኞች በየትኛውም ዘመን ዋጋቸው አይወርድም። ታማኞችን የሚፈልጉ ብዙ ባለጠጎችና ባለሥልጣናት አሉ። በአብዛኛው ሰው ደጅ የሚያድረው ቤት ጠፍቶ አይደለም፣ መተማመን ስለ ጠፋ ሁሉም ቤቱን ዘግቶ ነው። ብዙ ቤቶች አይጥ እየጨፈረባቸው ነው። ሰው ለማስጠጋት ግን ፍርሃት አለ። የሥራ ዕድሎችም ሙሉ በሙሉ የተዘጉ አይደሉም፣ ታማኝ ሰዎች ግን እየጠፉ ነው። ታማኝነት ቢኖር ኖሮ የኑሮ ዋጋ ይቀንስ ነበር ። ለጥበቃ፣ ለካሜራ፣ ለ ፖሊስ የሚወጣው ወጪ ስለሚቀር ሸቀጡ በርካሽ ዋጋ ይገዛ ነበር ። በአከራይና በተከራይ መካከል መተማመን እየጠፋ ነው፣ ወደፊት ቤት በጣም ሊወደድ፣ ካለው በላይ ሊጨምር ይችላል። ሰዎች ከማከራይ በሰላም ብኖር ይሻለኛል ወደሚል ስሌት ይገባሉ። ታማኝነት በጎደለ ቍጥር ኑሮ ከባድ ይሆናል። ታማኝ ሰው በጊዜው ግዳጁን የሚወጣ፣ አክባሪዎቹን የሚያከብር፣ ወዳጅነት ለነገም ስንቅ መሆኑን የሚያስብ ነው።
ውሻ ከሰው ይልቅ ታማኝ እየሆነ ነው። በከፍታም በዝቅታም ከባለቤቱ አይለይም። በዚህ ዘመን ሰዎች የረሀባቸውን መድኃኒት፣ ወድቀው ያነሣቸውን ፣ እንጀራ የዘረጋላቸውን ደግ እየከዱ ነው። ከውሻ ባነሰ የሞራል ዝቅታ እየወረዱ ነው። ታማኝነቱን ያጎደለ ሰው ቢሄድም የሚጓዘው ወደ ተሰበረ ድልድይ ነው። የተከዳው ሰው ግን ነገን በማትረፉ ደስ ሊለው ይገባል። ዘላለም አብሮት የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው። ከዳተኛ ሰዎች አታላይ ጠባይ አላቸው፣ መጀመሪያ ላይ ለስላሳ፣ አፍቃሪ መሳይ፣ ፍጹም የሚጠጉ መስለው ስለሚቀርቡ ከዛሬው ክዳት በላይ እንዴት ትላንት ተታለልሁ ? ብለው የተከዱ ሰዎች ይበሳጫሉ። ኤልያብ መልኩ አታላይ ስለ ነበር ነቢይን አሳስቷል። እንደ ላዩ ውስጡ ያማረ አልነበረም። ከዳተኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ ቆንጆና መለሎ ናቸው፣ የክዳታቸው ምክንያቱም ሁሉም ሰው ለጊዜያዊ ነገር ስለሚወዳቸው ነው። ሁሉም ሰው የሚወደው መጨረሻ ላይ ወዳጅ አልባ ይሆናል። ብዙ ሙያ ያለው ስለማይረጋጋ በረሀብ ይሞታል። ሁሉ የሚፈልገው በቅምሻ ያልቃል። ብቻ ተወዳጅ ለመሆን ታማኝነት ወሳኝ ነው።
13. ተጫዋች ናቸው፦ አለቃ ገብረ ሃና ተጫዋችና ደስተኛ ሰው ስለ ነበሩ በዚያም ላይ ሊቅ ስለሆኑ በሦስት ነገሥታት ቤተ መንግሥት ኖረዋል። ጨዋታ አስፈላጊ ነው፣ ሳቅም የጤና ምንጭ ነው። ሁልጊዜ መጫወት ግን ቁም ነገሩን ሊጋርድ ይችላል። በጊዜው መጫወት ግን ሳቢ ሰው ያደርጋል። ዓለም ያላስለቀሰው ሰው የለም ፣ የሚያስቀውን በርግጥ ይፈልጋል። ጨዋታ የሚለው ቃል ጨው፣ ጨዋማ፣ በጨው የተቀመመ፣ ጣዕም ያለው ንግግር ማለት ነው። እኛ የምንወዳቸው ሰዎች እነማን ናቸው? ለምን ወደድናቸው? ያንን ካወቅን ተወዳጅ ሰው እንሆናለን።
14 - በንግግር አያስቀይሙም፦ በንግግር የሰውን ክብር የማይነኩ፣ በሃይማኖት በጎሣ ልዩነት መናገርን የማይወዱ ሰዎች ተወዳጅ ናቸው። ሁለም ሰው ሃይማኖቱንና የወጣበትን ነገድ ሲነኩበት ደስ አይለውም። ለውበት የተፈጠረው ልዩነት ለመናናቅ ሲውል እግዚአብሔርም ያዝናል። ታዲያ ሳት ብለን የሰውን ሃይማኖትና ጎሣ ስንነቅፍ ጥላቻን እናተርፋለን። ከሁሉም ቦታ ደግና ክፉ ሰው አለና እገሌ ጎሣ ደግ ነው፣ እገሌ ክፉ ነው ማለት ልፋት ነው። ዛሬ እንዲህ ምስኪን ሆነው የምናያቸው ነገ ላይ ትልቅ ቦታ ይደርሳሉና ተስፋ የሚያስቆርጥ ንግግር እንዳንናገር መጠንቀቅ ይገባል። ዞር ብለው "ጌታዬ አንተ ነህ የምታሰድበኝ፣ ብትሰጠኝ ኖሮ የንግግር መለማመጃ አልሆንም ነበር" ብለው ያለቅሳሉ። በእኛ ንግግር ፈጣሪ እንዲወቀስ እናደርጋለንና በደሉ ከፍ ያለ ነው፣ ፍጡርን በፈጣሪ ላይ በጠላትነት ማነሣሣት ከባድ ወንጀል ነው። ደግሞም ሐሜት ወዳጅን ያሳጣል፣ በሚቻለን አቅም ልናስወግደው ይገባል።
15 - ግልጾች ናቸው፦ ተወዳጅ ሰዎች ተገቢ የሆነ ግልጽነት አላቸው። ሲደስቱም ሆነ ሲቀየሙ በግልጽ ይናገራሉ። ከተናገሩ በኋላም ቂም አይዙም ። ግልጽ ሰዎችን እንወዳለን፣ እኛ ግን ድብቆች መሆናችን ይገርማል ። ተወዳጅ ለመሆን እነዚህን 15 ነጥቦች ማየት ተገቢ ነው። ለመውደድና ለመወደድ ካልሆነ የምንኖርበት ሌላ ምክንያት የለም።
ተመስገን ጌታዬ ሁሉ ካንተ ነው!
ተፈጸመ
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤54👍3🥰2👏1
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ነገ
እሑድ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 8 ይቀጥላል

❤29👏3