በመጨረሻም
በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ለታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኅሊና ወልቡና ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሚያዝያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

http://t.meortodoxtewahedo
Audio
ሁሉም ተፈጸመ//ተፈጸመ ኩሉ
                                              
Size:- 31.5MB
Length:-1:30:32
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://t.meortodoxtewahedo
Audio
ትንሳኤ
                         
Size 6.7MB
Length 19:00

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://t.meortodoxtewahedo
#ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ-
ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ-
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ-
አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ-
አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ-
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ-
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ-
ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" #ልደታ ለማርያም ድንግል "*+

#ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::

" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) "

=>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

+ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

+እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

"ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8)

=>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::

+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::
እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

+እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9)

+እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
-ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
*በአባቷ በኩል:-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

=>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ)
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቴክታና በጥሪቃ
4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
(፩)ልደታ ለማርያም እናቴ
#ድንግል ሆይ
የነብያት-ትንቢታቸው
የሐዋርያት-ሞገሳቸው
የሰማዕታት-አክሊላቸው
የመላእክት-እህታቸው
የምንዱባን-እናታቸው
የነዳያን - ምግባቸው
የደካሞች-ምርኩዛቸው
የደናግል-መመኪያቸው
አንቺ ነሽ🌹
እመቤቴ ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው እንኳን አደረሳችሁ🌹🌹
ልደታ ለማርያም
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡

💠መልክአ ኤዶም

የቃል ኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን ።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#የሊባኖሷ_ሙሽራ

በመጀመርያ በክንፍ ላይ ስሎ ለመላእክት ሲገልጣት የጠባቂነት መዓረግን መስጠቱ ነበርና ከማኅፀን ጀምሮ እንዲጠብቃት አደራ በተሰጠው መልአክ በኩል እንደተናገረው በዘመድ በኩል ቢሆንም ቅሉ ለምትወለደዋ ሕፃን ዘመዶቿ የሰማይ መላእክት  ነበሩና በእነርሱ ተከባ ወደ ምትወልድበት ስፍራ እንዲሄዱ ተነገራቸው ።

እራሷ ከዓለም አይደለችምና በመወለዷ በቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ዓለማዊ ተድላ ደስታን እንዳያደርጉ በመንፈሳዊያን ዘመዶቾ በመላእክት ታጅባ ከቤት ወጣች ። ከቤቱ ወጥቶ ሕገ እግዚአብሔርን ስቶ የነበረ አዳምን የሚፈልግ ጌታ እናቱ ናትና ከቤት ወጥታ ቀድሞ አባቶቿ ነብያት እርሷን በራዕይ ወደ ተመለከቱበት ታላቅ  ስፍ ወደ ሊባኖስ ተራራ ተጓዘች ። በሊባኖስ ተራራ ጉያ ስር በእንበሶች ጉድጓድ እንደምትወለድ ትንቢት የተነገረላት የሊባኖስ ሙሽራ እርሷ ናትና ።

ከጉሩማኑ አናብስት ከነዳዊት ከነሰሎሞን ፤ ከተላላቁ ተራሮች ከነ አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ አብራክ የተገኘችው እመቤታችን ሰው በማይኖርበት ስፍራ ልትወለድ ተወሰነ። በዚያም ሳሉ ክብሯ ከአድባራት ሁሉ በላይ የሆነ ከቀደሙትም ከኋለኞቹም በላይ ስሟ የገነነ ፣ ከፀሐይ ይልቅ የምትደምቅ እመቤታችን በግንቦት አንድ ቀን ተወለደች ።

እሷ የሁሉ ፍጥረት ናት እንጅ የሐናና የኢያቄብ ብቻ ባለመሆኗ በአንድ ሰው ቤት ውስጥ እንዳትወለድ መንፈስ ቅዱስ ከለከለ ።

     ( ሕይወተ ማርያም ገጽ 85-87 ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ )

አማላጅነቷ የእናትነት ፍቅሯ ይጠብቀን ።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚

📖ዳግም ትንሣኤ

📖ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር ቀደም ሲል በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟል፡፡

“እስመ ሰሙነ ዐብይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ
ናሁ ትንሣአ” ሲል ይገኛል፡፡
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ፤

የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡ ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?

📖ዳግም ትንሣኤ የተባለበት

ምክንያት፡- በአከባበር፥በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት
መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “ፈጸምን አግብዓተ ግብር” ይባላሉ፡፡ “ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ “አግብዓተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡
ዮሐንስ 7፥4

በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡ ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡ ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡ በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡ ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡ ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች)
በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡
በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡

ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና
ብቃት ነው፡፡ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ 21፥24–29

ለብርሀነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን
ያድርገን! አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo

💚💛❤️💚💛💚💛❤️💚💛
Audio
መልካሙ ዘመን ደረሰ
ቅዱስ ያሬድ

Size:-12.4MB
Length:-54:32

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Audio
በታላቅ ኃይል ተነሣ

Size:-12.4MB
Length:-1:16:39

    በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
የቅድስት ሥላሴ ስዕል እንዴት ይሳላል  በአምሳለ አረጋዊ  ስለምን  ይሳላሉ?

በውስጥ  ብዙዎቻችሁ  በጠየቃችሁት  መሰርት  የቀረበ 

ቅድስት  ሥላሴ ሲሳሉ  በስም በአካል በግብር ሦስት መሆናቸውን  በአገዛዝ  በስልጣን አንድ መሆናቸው መገለጥ አለበት ፡፡ አንድነታቸውን  ለማመልከት በኪሩቤል  መንበር  ላይ እንደተቀመጡ ያለ ቅደም ተከተል (ፊትና ዋላ ከላይ  ወደታች  ሳይሆን )አንድ አይነት  አስተያየትና አቀማመጥ ተቀምጠው  ልብሳቸው  ወይም  ቀሚሳቸው አንድ ላይ  ሳይነጣጠል (ለየብቻው  ሳይሆን )በአንድ አይነት  ቀለም  ይሳላል። መንበር  የስልጣን  የአገዛዝ የመንግስት  ምሳሌ ሲሆን  በአንድ  መንበር  መቀመጣቸውም  በስልጣን  በአገዛዝ   አንድ መሆናቸውን  ያምለክታል። ተቀምጠው መሳላቸው በሁሉቦታ ያለ በሁሉ የነገሰ (ንጉሰ ነገስት እግዚአ አጋእዝት) መሆኑን ለመግለጽ ነው ።
ያለቅደም  ተከተል  መቀመጣቸውም  በቅድምና  አንድ  መሆናቸውን  ያሳያል።

 ሦስትነታችውን  ለመግለጥ አለምን  በግራ እጃቸው እንደያዙ በቀኝ እጃቸው ሲባርኩ(ጠቋሚ ጣት  ወደላይ  ቀጥ  ብሎ  ከመሃል ጣት  እስከ ትንሽ ጣት ያሉት ሦስት  ጣቶች  ታጥፈው )ያሦስቱም  ፊት ወደ አንድ አቅጣጫ  ሆኖ  ወደ አንድ አቅጣጫ  የሚያይ ሆኖ  አካላዊ  ገጽታቸውም  እኩል በተመጣጠነ  የልብሳቸውም  ከውስጥና እና ከውጭ መጎናጸፊያቸው  ቀይ ተደርጎ ይሳላል  ::
ሲሣሉም  በአምሳለ አረጋዊ መሆን አለበት።ይህም ዘላለማዊነታቸውን  በሁሉቦታ  መኖራቸውን  ታጋሽነታቸውን  ፈራጅነታቸውን  አስተዋይነታቸውን  ለመግለጥ ነው።የምድር ነግስታት ያልፋሉ  እሱግን  የተለየ የማያልፍ  መነሻውም  መድረሻውም የማይታወቅ  መሆኑን  ለመግለጥ በአምሳለ አርጋዊ ይሳላሉ

ዳን 7፥9  ዙፋኖችህም  እስኪዘረጉ ድረስ አየው  በዘመናትም የሸመገለው ተቀመጠ እንዲል

 ከዚህ  በተጫማሪ በዙፋናቸው  ዙሪያ በአራቱ  መዕዘናት  አራቱ እንስሳት ባለስድስት ክንፍ ሆነው በገጸ አንበሳና  በገጸ ላህም  በገጸ ሰብ እና በገጸ ንስር  በሁለት  ክንፎቻቸው  እጃቸውን ሸፍነው  በሁለት ክንፋቸው እግሮችቸውን ሸፍነው  በሁለት  ክንፋቸው  ደሞ ቀኝ እና ግራ ዘርግተው ይሳላሉ ። ሃያራቱ ካህናትም  ልብሰተክኖ ለብሰው  በእጃቸውም እጣን  የሞላበት የወርቅ መዕጠንት ይዘው  አንድም  አክሊላችውን   ከራሳቸው  አውርደው  በዙፋኑ ፊት ሲሰግዱ  መሳል አለበት።
ለወዳጆ ያካፍሉ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ወርሃዊ መታሰቢያ  እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል  በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን  በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
2024/05/15 22:40:34
Back to Top
HTML Embed Code: