Telegram Web Link
ትናንት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ የሙሉ ወንጌል ማምለኪያ ቦታ ሙሉ በሙሉ በነዋሪዎች ተቃጥሏል።
ምክንያቱ ለህክምና ወደ አከባቢው አቅንተው የነበሩ እስራኤላዊያን ወንጌልን ሊሰብኩ ነው የመጡት በሚል ሰበብ ነው።

የሚገርመው ቃጠሎው ሲከሰት በአከባቢው የነበሩ የፀጥታ ሃይሎችና የከተማ አስተዳደሩ ጥፋተኞቹን ለማስቆም ምንም ጥረት አላደረጉም።

ይህ ስለሆነ ማዘን የለብንም ማዘንስ ያለብን በሃይማኖትና በባህል ተተብትበው ወንጌል ሳይገባቸው በጭፍን ጥላቻ ተዘፍቀው ለሚኖሩ ሰዎች ነው።
በማወቅም ባለማወቅም ይህን ያደጋቹ እግዚአብሔር ይባርካቹ፣ ፊቱንም ያብራላቹ፣ አይኖቻችሁ ይብሩ፣ ልጆቻቹ በሰላም እና በጤና ይደጉ፣ የወንጌል ብርሃን ይብራላቹ።

ወንጌል ተከሶ እንጂ ከሶ ሸንጎ ቆሞ አያውቅም!
በዚያ የምትገኙ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያበርታቹ በፀሎት አብረናቹ ነን!

በእነዋሪ ከተማ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ተጨማሪ መረጃ በ @SakieAdmin_bot አድርሱን
@christian_mezmur @puritytube @youth4christ
👉“ ከራሴ ጋር የማደርገውን እጠላዋለው”👈

👤A4P እንግዳ:- “አስራ ስድስት አመቴ ነው ። የሴት ጓደኛ የለኝም ትክክለኛ ጊዜው ነው ብዬም አላስብም።ነገር ግን ብጥብጥ የሚያደርገኝ የሆነ ጠንካራ ወሲባዊ ስሜት አለኝ።
#ማድረግ #የማልፈልገውን #ነገር #እንዳደርግ #ያደርገኛል። በእግዚኣብሄር አምናለው በቤተክርስቲያንም እሳተፋለው። ላወራቸው የምችላቸው ጥሩ ጓደኞችም አሉኝ ሁሉም ግን እንደኔ አይነት ትግል ውስጥ ናቸው።
ቤተሰቦቼ አማኞች እንደመሆናቸውና በቤተክርስቲያን ስላደግኩ ስለውጪው አለም ምንም ኣላውቅም። እግዚኣብሄርንም የእርሱንም ህዝብ እወዳለው ፣ እግዚኣብሄር በሂወቴ አላማ እና እቅድ እንዳለው አውቃለው።

አሁን አሁን ግን በሂወቴ የእግዚኣብሄርን መልካምነት መጠራጠር ጀምሬኣለው።
እግዚኣብሄር በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ወሲባዊ ስሜቴን ለምን እስከማገባ ድረስ ገታ አላረገውም😟? ሚሲ , በእውነት ሃጢያትን ማድረግ ኣልፈልግም።
#ከራሴ_ጋር_የማደርገውን_እጠላዋለው ፣ ራሴን እጠላለው ፣አንዳንዴ ሁሉም አንዲያበቃ እፈልጋለው። ባለፈው አመት ራሱን ያጠፋውን የክፍሌ ተማሪ ሁሌ ትዝ ይለኛል።
እሱም በኔ ሁኔታ ውስጥ ኣልፎ ይሆን እያልኩ ኣስባለው……..
በዚህም ውስጥ እግዚኣብሄር ለኔ መልካም ነው ትያለሽ?
በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ለምንድን ነው በዚህ ውስጥ የማልፈው? …….. አስጠልቶኛል፣ ራሴንም ጠልቻለው ! እርዳታ እሻለሁ

💁A4P፦ ዋው! ይሄ አስራዎቹ ውስጥ እያለው ከምታገልባቸው ሚሊዮን ጥያቄዎች ኣንዱ ነው። ስለዚህ እንዴት እንደሚሰማህ አውቃለው።
በጣም አስፈሪ ነው ኣይደል? 👌እግዚኣብሄር ላንተ መልካም ነው ወይ? መልሴ “ኣዎ ነው።” የሚል ነው ። ምክንያቱም የእግዚኣብሄር ቃል እንደዛ ስለሚል።( መዝ 100፥5, መዝ 136፥1) …….. መልካም መሆን የእርሱ ማንነት ነው።
አዎ እግዚኣብሄር ለኛ መልካም ነው። እናም በሂዎታችን የሚያደርገው ሁሉ ነገር አንድ አጀንዳ ብቻ ነው ያለው እሱም ፍቅር ነው።(መሃልዬ 2፡4)
👉ስለዚህ ለእንደዚህ አይነት ጥያቄ መልስ ስትፈልግ እውነታው ላይ ለመድረስ ከዚህ መነሳት አለብህ ።
አየህ ብዙ ጊዜ ጾታዊ ማንነታችንን ከእኛነታችን ለይተን ለማየት እንሞክራለን እውነታው ግን አብይ የእኛነታችን ተፈጥሮ ነው። ጾታዊ ማንነታችንን ራሱን የቻለ ነገር ሳይሆን የእኛነታችን ግንባታ አካል ነው። እንደውም ጾታዊ ማንነታችንን የስብእናችን ማዕከል ነው ብዬ ነው ማስበው። የእኛነታችን ምሰሶ ነው። 💯

እግዚኣብሄር በርግጥ ለኛ መልካም ከሆነ ለምን ወሲባዊ ስሜታችንን ለምን እስከምናገባ ድረስ ገታ አላረገውም? አግባብ ጥያቄ ነው። 󾠬እንደዛ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ምንም ያልበሰልን እና ሃላፊነት የጎደለን ባሎችና ሚስቶች ፣ኣባቶችና እናቶች እንዲሁም ዜጎች በሆንን ነበር።

አስተውል የአስራዎቹ ዕድሜያችን አግባብ ባልሆኑ ጾታዊ እሴቶች(sexual immoralities ) የምንባክንበት ዕድሜ ሳይሆን በንጽህና መልካም ዘርን የምንዘራበት ጊዜ ሲሆን ከትዳር በኋላ ያለው ጊዜ ደግሞ በአስራዎቹ ዕድሜያችን የዘራነውን የምናጭድበት ነው።
የአስራዎቹ ዕድሜያችንና የ“single” (በእኔ አመልካከት “single” የሚባለው ከ18 ዓመት በላይ ላሉት ነው) ዓመታት እግዚኣብሄር “ምሰሶውን” በ “ፈተና እሳት”🔥🔥 የሚያጠነክርበት ወቅት ነው፣ ስለዚህም ሌሎች ክርስቲያናዊ ባህሪያት ኣብረው ይገነባሉ።

በጾታዊ ጉዳይ የተዘበራረቀ ሂዎት ኖሮት ቃሉን የሚጠብቅ ፣ መልካምና የታመነ ወንድም ወይም የተሰጠ ባልና አባት እስካሁን ኣላገኘሁም። የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖር አይችልም🔑። የውሸት እየኖረ ሰውን ሊያታልል ይችላል። እግዚኣብሄርንና ራሱን ግን ሊያታልል አይችልም። ለሴትም ቢሆን ተመሳሳይ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖራት አይችልም።💯

ለምን? ምክንያቱም ጾታዊ ማንነታችን በትዳር ውስጥ ለአንድ ሰው እንድንሰጥ የተሰጠን በዚያም ውስጥ እንድንረካ ነው።(1ኛ ቆሮ 7፥1-3) ከዚህ ከጾታዊ ማንነታችን ጀርባ ያለውን መሰረታዊ ዓላማ ስናውቅ ሃጥያታዊና ራስወዳድ ነገሮች ይገደላሉ።
👉ነገርግን ለዚህ ዓላማ ጀርባችንን ሰጥተን ጾታዊ ማንነታችንን ለራሳችን ደስታ ፍለጋ ካዋልነው ስብዕናችንን እንረብሻለን። ምክንያቱም ከተፈጠርንበት ዓላማ ዉጪ እየሄድን ሰለሆነ።
󾠬 ለዛም ነው አንዳንድ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ራሳችንን ለማጥፋት የምናስበው ።
👉የተወደድክ ሆይ ፣ እነዚህ በፈተና የተሞሉ ዓመታት መልካም ናቸው ። ምክንያቱም
በእግዚኣብሄር መደገፍንና የእርሱን ጥበቃ የምትማርባቸው አመታት ናቸውና። ለጾታዊ ስሜትህ መልስ ሊሆኑ የሚችሉት ሴቶች ወይም ወሲብ እንዳልሆኑ ትረዳለህ። የሚያስፈልግህ አንድና ብቸኛ ነገር ክርስቶስን ማወቅ እንደሆነ ትማራለህ። ፍላጎቶችህን በራስህ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ለእግዚኣብሄር አንዴት ማቅረብ እንዳለብህ ትማራለህ። 󾠬በዚህም ሂደት ውስጥ ለአንዲት ሴት ብቻ በፍቅር የሚማርክ ልብ ይኖርሃል። ከዚያም ማንንም ሴት በክርስቶሰ እህትህ እንድትሆን በእግዚኣብሄር እንደተፈጠረች ውድ ስጦታ እንጂ እንደ ወሲብ ዕቃ አታይም።
አስተውል፥ ደግነት፣ ሃቀኝነት ፣ ፍትሃዊነት ፣ሁለገባዊነት ፣ጽኑነትና ሌሎችም መልካምና የተመሰገኑ እሴቶች የሆነ ሰው እጁን ጭኖ ሲጸልይልህ አይደለም የሚመጡት። ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እሳት🔥🔥 በሚነደው ጾታዊ ፈተና ውስጥ በድል ማለፍ ስትችል ያኔ ቀስበቀስ በእርግጠኝነት እነዚህን እሴቶች መያዝ ትችላለህ። ግን አስታውስ በቀላሉ አይመጡም ። ሁሉንም ለማግኘት መታገል አለብህ።

እስራኤላውያን ወተትና ማር ወደ ምታፈሰው ምድር እንዴት በትግል እንደገቡ አስታውስ ። ኣዎ እግዚኣብሄር ከእነርሱ ጋር ነበር ቢሆንም ግን መታገል ነበረባቸው።
👉ጾታዊ ፍላጎቶቻችን ለሌሎች የሂወታችን ዘርፎች መሰረት ናቸው። ነገርግን መሰረቱ የሚንቀጥቀጥ ከሆነ ምንም ነገር በላዩ ላይ ሊገነባ አይችልም። እናም መልካም ትዳር እንዲገነባ መሰረቱ እነዚህ እሰቶች መሆን መቻል አለባቸው።
👉ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለብህ ፈተና አንተን ለማጥፋት ሳይሆን እምነትህ ከወርቅ ይልቅ የተፈተነ ይሆን ዘንድ ነው።(1ኛ ጴጥ 1፥7)
🔑🔑ልታደርገው የምትችለው አንድ በጣም ጥሩ ነገር ይህ ነው፦
👉ለዚህ “ጭራቃዊ ” ስሜትህ በሃጥያት የተሞላ መረጃ ይመግበው ዘንድ ለራስህ አትፍቀድለት ። 👉የምታየውንና የምትሰማውን ለይ፣ ከማን ጋር እንደምትውልም ምረጥ። 👉ይህን ፍላጎትህን ከሚመግቡ ነገሮች መሸሽ ብችኛው መጽሃፍቅዱሳዊ መፍትሄ ነው።(1ኛ ቆሮ 6፥18)

አስታውስ ከእግዚኣብሄር ስሞች ኣንዱ “ተዋጊ” የሚል ነው። ተዋጊም ስለሆነ ተስፋቸውን ለመውርስ ከሚታገሉት ጋር ዓላማውን ለመፈጸም ይወዳል።(2ኛ ዜና 16፥9) ስለዚህ መዋጋትህን እስከመጨረሻው እንዳታቆም 👌። ምክንያቱም በመጨረሻ ሚጠብቅህ ድል በመዋጋትህ እንዳትቆጭ የሚያደርግህ ነውና።💯💯


#single #General

ይህን መልዕክት ለሌሎች ያካፍሉ

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል!

"ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፤ በተደረገው ምርመራ አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" - ኢ/ር ታከለ ኡማ

Koronaavaayirasiin Itoophiyaati seene!

"Qorannaa taassifameen Lammiin jaappaan tokko vaayirasiin "Corona " irratti argameera.
Hundumti kenya tuttuqqaa harkaafi walitti qabama hin barbaachifne irraa akka of qusannu hubachiisuun feedha."

ሁላችንም በያለንበት እንፀልይ🙏🏾
Hundummti keenyaa bakka jirutti haa kadhannu🙏🏾
@PurityTube @christian_mezmur @youth4christ
አንብባችሁ ለሌሎችም አስተላልፉ
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!< ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡
< ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡
< በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! < የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡
1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡
< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡
2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡
3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?
1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡
ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?
1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡
< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡
2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡
3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

#christiantube
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @Christian_mezmur 💢💢
ሰበር ዜና - እንቅስቃሴዎች ታግደዋል!!

ኢትዮጵያ ትምህርት እና ስፓርታዊ እንቅስቃሴ አግዳለች!!

Ethiopia suspend schools, Sporting Events.
@Yenetube @Fikerassefa
💢💢 @puritytube 💢💢
ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

#ካነበቡ_በኋላ_እባክዎ_ሼር_ያድርጉ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደሚታወቀው በዓለምም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወቅቱ ስጋት እንደሆነ ቀጥሏል ፡፡

የሰው ልጅ በቴክኖሎጂ ምጥቀቱ ተማምኖ ከፈጣሪ ጋር ፉክክር ውስጥ ለመግባት በከጀለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ የሆነ በሽታ መከሰቱ እስካሁንም የኖርነው በምህረቱና ጥበቃው እንጂ በጥበባችንና በጥንቃቄያችን ያለመሆኑ ማሳያ ነው ፡፡

በመሆኑም ከዚህ በሽታ ራሳችንንና ሌሎችን ለመታደግ ማድረግ ያለብንን መሰረታዊ ጥንቃቄዎች ማድረጋችንን ሳንተው መደገፊያችን ግን እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ተረድተን አብዝተን ወደ እሱ እንጩህ ፡፡

" ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፤ "
(መጽሐፈ ኢዮብ 22:27)

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን🔴
በዓይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት፦
😱ፖርኖግራፊምንድነው?
😳ራስን በራስ መድፈር?
🙊ከሰውነት ወደ እንስሳነት🚷
🤕ፖርን ያቆሰለው አእምሮ ምን ይመስላል?
🙊ያልተነገሩ የመውጫ መንገድ ተግዳሮቶች ዊዝድሮዋል ሲምፕተምስ እና ሌሎችም በ @puritytube ያካፍሉ
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን🔴
#ክፍል

ውድ የፒውሪቲ ቲዩብ ቤትሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም እና ፀጋ ለእናንተ ይሁን!

ከዚህ ቀጥሎ በሚኖሩን ጥቂት ጊዜያት👉#ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን ” በሚል ረዕስ የሚቀርቡ አጫጭር እና ተከታታይ መንፈሳዊ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ ትምህርቶች አቀርባለሁ። ለዛሬ እንደ መግቢያ የመረጥኩት #የፖርኖግራፊ ትርጓሜው ምንድነው? #ፖርኖግራፊ ናቸው ብለንስ የምንፈርጃቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው? ድንበራቸውስ የት ድረስ ነው? የሚለዉን እንድናይ ነው።

አብዛኛው ክርስቲያን የፖርኖግራፊን ትርጓሜ በተለምዶ፦
👉“የብልግና ተንቀሳቃሽ ምስሎች🎥 እና እርቃን ምስሎች📷” በሚል አጭርና ⚠️የተዛባ ትርጓሜ ስለገደበው ሌሎች ተያያዥ እና አደገኛ ወሲባዊ ልምምዶች እንደ ጤናማ የሕይወት እንቅስቃሴ ተቆጥረው በብዙ ክርስቲያን ወጣቶች ዘንድ ያለከልካይ ሲተገበሩ ይስተዋላል።

🔴ፖርኖግራፊ 📌“ፖርኔ” እና📌“ግራፋይን” ከሚሉ የግሪክ ቃላት የመጣ ነው።
📌“ፖርኔ” ጋለሞታ ሴት ማለት ሲሆን 📌“ግራፋይን” ደግሞ መመዝገብ ወይንም መፃፍ ነው። በጊዜውም ባለው ጥንታዊ ትርጉም፦
👉የአንዲትን ጋለሞታ ሴት ወሲባዊ ሕይወት መዝግቦ በፅሁፍ እና በስዕል በማቅረብ ሰዎችን ባልተገባ እና ኃጢያት በሆነ መልኩ ለዝሙት እና ወሲባዊ ምኞት የሚያነሳሳ ድርሰት ነው። ይሄው ወሲባዊ ኃጢያትን የመጻፍ፣የመሳል እንዲሁም የመድረስ ሴጣናዊ አባዜ በየዘመኑ እየሰፋ እና እያደገ መጥቶ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል።
ይሄም🔑 መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ1፥24-28 (ይነበብ‼️) ላይ እደሚያስረዳን ሰዎች እግዚአብሄርን ለማወቅ እና ለመታዘዝ ባልወደዱ መጠን የተተዉበትን ከባድ የኃጢአትና የሥነ-ምግባር ዝቅጠት የሚያሳይ ነው ።
🚫በሰዎች መሀል ከሚደረግ ዝሙት አንስቶ እስከ 🚫ሰው ከእንስሳ ግንኙነት 🚫ከግብረሰዶማዊነት አንስቶ እስከ 🚫በስጋ ዘመዶች መሃል የሚደርግ እርኩሰት ያሉ ድርጊቶችን በቪድዮ ቀርፆ🎥 በምስል አንስቶ📸 በመጽሐፍ ደርሶ📕 ኢንተርኔት በሚባል መረብ ሊያጠምድ የእህቶቻችንና እና የወንድሞቻችንን እንዲሁም የታዳጊ ህጻናትን ደጅ በስልኮቻቸው📱፣በታብሌቶቻቸው እንዲሁም በኮፒዉተራቸው💻 በኩል ደጆቻቸዉን ያንኳኳል።
💢💢@puritytube 💢💢
💢💢 @puritytube 💢💢
አሁን ባለውና ተቀባይነት ባገኘው ትርጉሙ፦
🔴 ፖርኖግራፊ ማለት ማንኛዉም የታተመ እና የተጻፈ ምስል፣ድምጽ እና ቪዲዮ በውስጡም ማንኛዉንም ዓይነት ጾታዊ ግንኙነት የሚመስል(መሳሳም እና ያልተገባ አካላዊ ንኪኪን ይጨምራል) የያዘ ወይንም ወሲባዊ ድርጊቶችን፣እርቃንነትን እና ወሲባዊ ንግግሮችን ያካተተ ነገር ነው። ስለዚህ ክርስቲያን ሆይ❗️የቆምክበትን ቦታ ታውቃለህ🚦 የምታያቸውን፣የምትሰማቸው እና የምታነባቸዉን ነገሮች ታስተውላለህ

የሀገራችን ወጣቶች አዘውትረው የሚያዳምጡት የምዕራባዊያኑ 🎙ሙዚቃ ፖርን ሰለመሆኑ ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም። እያንዳንዱ የሴትና የወንድ ፆታዊ የአካል ክፍል እየተነሳ የሚሞገስበት፣እርቃንነት የሚወደስበት እናም በትዳር ላይ መባለግ እንደ ጀብዱ የሚጨፈርበት ሙዚቃ ከዚህ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።ዝሙት ነውና❗️
ሌላው ደግሞ ፊልም🎬 በሚባል መዝናኛ በሚመስል ማር በመርዝ🐍 ተቀምመው የሚቀርቡ የፍቅር ታሪኮች ውስጥ ያሉ ከጋብቻ በፊት የሚደረጉ መሳሳም፣ አካላዊ ንኪኪ አልፎም ወሲባዊ ድርጊቶች እና ሌሎችም በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ የፍቅር ፈንጠዝያዎች የወጣቱን ቀልብ ገዝተው ባሳደሩት ተጸዕኖ እንደ ጤናማ ድርጊት ያለ ዕፍረት በየአደባባዩ ይተገበራሉ። ስለዚህ አንባቢ ሆይ አሁን ትርጉሙንም ድንበር የለሽነቱንም አይተናል። እናስተውል🤔 እራሳችንንም ክርስቶስን እድንመስል በተጠራንበት እውነት እና ፍቅር እንፈትሽ።የስልክ ንግግሮቻችን ከእንዲህ ዓይነቱ ማማለል የፀዱ ናቸውበማህበራዊ ድህረገፆቻችን የምንላላካቸው መልክቶችስከተቃራኒ ፆታስ ጋር ያለን ግንኙነት

በበራልንም እውነት ፀንተን ለመኖር የሚያስችለንን ጸጋ እግዚአብሄር ይስጠን! በቀጣይ ክፍል እንገናኝ
ጸጋው ይብዛላችሁ!
✍🏿በካም
✍🏿የማይታይ ፊርማ
💢💢@puritytube💢💢
💢💢@puritytube💢💢
🛑 በጣም ጠቃሚ መረጃ

በቻይና ሰዎች የሰጧቸው ዋና ዋና ጠቃሚ ምክሮች:-📌
.
#1. ሁለት አይነት ጫማ ይኑርዎት። አንዱ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሌላኛው ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ቤት ውስጥ አያስገቡ። ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ውጪ አያውጡ።

#2. አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች ለማኖር የሚያገለግል አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች በሙሉ ለምሳሌ እንደ መድሐኒት: መጠጦች: አትክልቶች እና ሌሎችንም ሳይነኩ ለ24 ሰዓት በጠረጴዛው እንዲቆዩ ያድርጉ።

#3. በተቻለ መጠን የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን አይስጡ: አይቀበሉ። የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን ወደ ወደ ቤት የሚያመጡ ከሆነ ለዚህ ጉዳይ ለይተው ባስቀመጡት ጠረጴዛ ላይ ለ24 ሰዓት አቆይተው ይጠቀሙ።

#4. ሁሉንም አይነት አትክልቶች ማለትም ቀይ ሽንኩርት: ነጭ ሽንኩርት: ድንች እና ሌሎችንም በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርገው ይጠቡ። በፈላ ውሃ ሊታጠቡ የማይችሉ አትክልቶችን አይግዙ።

#5. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የእጅ ስልክዎን ይዘው አይሂዱ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።

#6. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የቤት ቁልፎችን ይዘው አይውጡ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።

#7. ከቤት ወጥተው ሲመልሱ እጅዎንና ፊትዎን በሳሙና ይታጠቡ። ቤት እንደተመለሱ የለበሱትን ልብስ አውልቀው እንዲታጠብ ያድርጉ።

#8. ሴት እህቶቻችን ከቤት ስትወጡ ጸጉራችሁ በአግባቡ መጠቅለሉን አረጋግጡ:: ጸጉራችሁን በእጃችሁ አትነካኩ:: ፊታችሁን ጸጉር በነካ እጃችሁ አትንኩ።

#9. አትክልት ለመግዛት ሲሄዱ የእጅ ጓንት ያድርጉ። ወይም አትክልቶችን ሲያነሱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በሁለቱም እጅዎት ማጥለቅዎትን እርግጠኛ ይሁኑ። ወደ ቤት ሲመልሱ የእጅ ጓንትዎን ማጠብዎን አይዘንጉ። በፕላስቲክ ከረጢቶች ተጠቅመው ከሆነ ወደ ቤት ሲመልሱ ወይም ወዲያውን ከተጠቀሙ በኋላ ያስወግዱ።

#10. ሁልጊዜ ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ራስዎን እና የሚያመጧቸውን ነገሮች ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ያቅዱና በቂ ዝግጅት ያድርጉ።

#11. በጣም የግድ ካልሆነ በስተቀር ምግብ ወይም መድሐኒት ለመግዛት ባይሰለፉ ይመረጣል። መሰለፉ ደግሞ የግድ ከሆነ እስከ ሁለት ሜትር ርቀትዎን ይጠብቁ።

#12. ከውሾች እና ድመቶች ጋር ያለዎትን ንክኪ ያስወግዱ።

#13. በተቻለ መጠን አረጋውያን ወደ ውጪ ባይወጡ ይመክራል። ቤት ውስጥ ያሉ ወይም በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለአረጋውያን የሚፈልጉትን ነገር ገዝተው ቢያመጡላቸው ይመክራል።

#14. ሁልጊዜ ከቤትዎ ከመውጣትዎ በፊት ከላይ የተጠቀሱትን መልዕክቶች በመመልከት አቅደው ተግባራዊ ያድርጉ።

ኮሮና ለመከላከል
ከላይ የተባሉትን መተግበር!

#TimeToPray4World
#TimeToPray4Ethiopia
@christian_mezmur

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢


ምንጭ ፡ ድረ ገጽ
#🔑some thing big is coming

Who expecting this
On evanglical tv📺📡
And we start soon
Our offical
YouTube channel
Share and join
@thestic @thestic @thestic
@thestic @thestic @thestic
@thestic @thestic @thestic
@thestic @thestic @thestic
@thestic @thestic @thestic
😱😱“ከወንድ ጋር እስካልተኛው በራሴ የማደርገው ኃጢያት አይደለም🤷‍♀” አንዲት ወጣት

ሰላም ውድ ቤትሰቦቻችን!
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና🔴 በሚል ረዕስ በጀመርነው ትምህርት ከቀረበው
🔴"ፖርን ምንድነው?" ከሚለው ክፍል ምን አዲስ ዕይታን እንዳገኛችሁ በ @appeal4purity_bot ብታጋሩን ይደርሰናል
ሌላው 📌ማስተርቤሽን ምንድነው? በሚለው ጥያቄ ላይ እና ከላይ ባለው የወጣቷ ሴት ድምዳሜ ላይ ያላችሁን ሃሳብ ልንሰማ ወደናል።
💢💢@appeal4purity_bot💢💢
💢💢@puritytube💢💢
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና ክፍል፪🔴 💀ማስተርቤሽን እንደ አስገድዶ መድፈር😱😱

📖ማስተርቤሽን፦ ፃታዊ የአካል ክፍልን በመነካካት ወሲባዊ እርካታን ማግኘት

ሰላም የፒውሪቲ ቲዩብ ቤትሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን! በክፍል ሁለት ደግሞ ማስተርቤሽን ምንድነው የሚለውን እናያለን፦
የፖርንና የፍትወት መገባደጃው 📌ማስተርቤሽን ነው። #⃣በተለምዶም "ራስን በራስ ማርካት" ወይም ግለ ወሲብ የሚል ትርጓሜ አለው።
ነገር ግን ይሄ ትርጉም ትክክል አይደለም በ3 መሰረታዊ ምክንያቶች:
1ኛ እግዚአብሄር የወሲብን ስጦታ የሰጠው በትዳር ዉስጥ ላሉ ባልና ሚስት ብቻ ነው❗️ ስለዚህ ወሲብ በባህሪው የሁለትዮሽ ትስስር እንጂ የአንድዮሽ ተግባር አይደለም። ሊሆንም አይችልም❗️
2ኛ በትዳርም እንኳን ቢሆን ወሲብ ፍቅርን❤️ ጥልቅ በሆነ መንገድ የመግለጫ ስጦታ ነው።ይሄም🔑በ1ኛ ቆሮ 7÷3-5 እንደተጻፈ አንዳቸው አንዳቸውን ከራሳቸው አብልጠው ለማስደስት በሚያደርጉት ጥረት የጋራ እርካታን የሚያገኙበት እንጂ የራስን ፍላጎት እና ስሜት ብቻ ለማርካት የሚኬድበት ጉዞ አይደለም❗️
3ኛ ወሲብ አካላዊ ስሜትን ከማርካት በላይ መንፈሳዊ ትርጉም አለው ይሄውም በትዳር መሃል የሚፈጠርን አድነት የሚያመጣ ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሄር ስጦታ የሆኑት ልጆች👨‍👩‍👧‍👦 የሚገኙበት መንገድ ነው። ስለዚህ ወሲብ ከዚህ ሁሉ ኃላፊነት ጋር የተሰጠ ጋብቻዊ ጸጋ ነው❗️
ይሄም ጉዳይ ራስን በራስ የማርካት ጉዳይ ሳይሆን ሌላ ሁለተኛ አካል የሚፈልግ የሁለትዮሽ ትስስር ነው።👆🏾 ከነዚህ ዋና ዋና የወሲብ መገለጫዎች ተነስተን 📌ማስተርቤት የሚያደርግ ሰው በተለያየ መንገድ ለምሳሌ በምስል፣በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሌላ ወንድን ወይንም ሴትን አምጥቶ/ታ ነው። ወይም በምናቡ ስሎ/ላ ነው ከሚል ግልጽ ከሆነ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን። ይሄ ደግም መሰረታዊ እና የማይነጣጠሉ 💀የኃጢያት ልምምዶችን ይዞ ይመጣል እነዚህም 🚫ምኞትን የራስ ባል ወይም ሚስት ያልሆነን ሰው ለዝሙት መመኘትን፣ምኞትም ደግሞ 🔑በማቴ5፥28 እንደተፃፈ🚫ማመንዘርን ይወልዳል። ይሄም ወሲብን ከተፈቀደበት መንገድ ውጪ ለገዛ ስጋዊ ምቾት ማዋልን ያመጣል በዚህም🔑በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፥18 እንደተጻፈ በገዛ ስጋ ላይ 💀ኃጢያትን መስራትን ያስከትላል።
♦️ስለዚህ የማስተርቤሽን ገላጭ ትርጉም ምን ይሁን? በፒውሪቲ ዙርያ የሚሰሩ አንድ ዶ/ር ስዩም አንቶንዮ የተባሉ ሰው በአንድ ወቅት ሲናገሩ፦
📌ማስተርቤሽን ማለት ራስን በራስ መድፈር ነው!” የሚል ትርጉም ሰተውታል። በእርግጥም ይሄ ትርጉም አቻ ቃሉ ባይሆንም 💀ከኃጢያትነቱ እና ከሚያስከትለው የአእምሮ ቀውስ አንፃር የሚመጥነው ትርጓሜ ነው።
🔑1ኛ ቆሮ 6 ላይ እንደተፃፈ 👉ስጋ ለጌታ እንጂ ለዝሙት አይደለም። እዛውም ክፍል ላይ ቀጥሎ 👉በዋጋ ስለተገዛን የራሳችን አለመሆናችንን ያመለክተናል ታዲያ ለዚህ ለጌታ በሆነው ማንነታችን ላይ ይህን 💀ኃጢያት መፈጸም እና ማዋረድ አልፎም ጌታን ብቻ እንድናከብርበት የተጠራንበትን መጠራት በፍትወት ማቆሸሽ 📌የራስን ንፅህና በራስ መድፈር ነው እንጂ ሌላ ምንም ሊባል ይችላል?
👆🏾የቀጠለ
🎤በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች 🔴ፖርኖግራፊ እና 🔴ማስተርቤሽን በቀጥታ 🔑መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተጠቀሰ ኃጢያት አይደለም ሲሉ ይደመጣል። የእነዚህን ሰዎች ስንኩል አመክንዮ ለመረዳት አንድ ምሳሌ ማየት ጠቃሚ ይመስለኛል፦
💬በአንድ ወቅት አንድ በባልንጀራው ላይ የሚቀና ሰው ነበር ይሄም ሰው የባልንጀራውን ንብረት ሁሉ የራሱ ለማድረግ ምኞት ነበርው። ይሄንንም ድብቅ ፍላጎቱን የምታውቀው ሚስቱ ስትመክረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
🔑ዘጸ 20 ላይ “....የባልንጀራህን ሚስት ሎሌዉንም ገረዱንም በሬዉንም አህያዉንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ” የሚለውን ታነብለታለች። ይሄም ሰው ልቡ በስጋዊ ፍላጎት ታውሮ እውነትን ለማየት አልፈቀደምና እንዲህ ሲል መለሰላት “ ውዴ እኔ መች ሚስቱን ተመኘሁ? ደግሞስ ምን በሬና አህያ አለውና ተመኘሁ? እኔኮ የተመኘሁት ድርጅቱን እና መኪናዎቹን ብሏት አረፈ!🤷‍♂😳
እነዚህም ሰዎች ልክ እንደምሳሌው ናቸው እንጂ 🔑መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቅቄ እና በቅን ልቦና አይፈትሹም ይልቅስ ስጋዊ ስሜቶቻቸውን የሚያረኩበት ቀዳዳ ለማግኘት ሲሉ ቃሉን እስከማጣመም ይደርሳሉ።
አንባቢ ሆይ አስተውል🤔.. እንደዚህ ዓይነት ልምምዶች በሕይወትህ/ሽ አሉ? 🔈እንግዲህ ወደ እግዚአብሄር ጩህ/ሂ!
🔈በንስሃ ወደ እርሱ ቅረብ/ቢ!
🔈 ለዚህ ኃጢያት የሚጋብዝህን/ሽን ነገር ሁሉ ከሕይወትህ/ሽ አስወግድ/ጂ።
"🔑በኃጢያታችን ብንናዘዝ ኃጢያታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" 1ኛ ዮሐ 1፥9

በበራልን እውነት ፀንተን ለመኖር የሚያስችለንን ጸጋ እግዚአብሄር ይስጠን! በቀጣይ ክፍል እንገናኝ
ጸጋው ይብዛላችሁ
✍🏿በካም
✍🏿የማይታይ ፊርማ
💢💢@puritytube💢💢
💢💢@puritytube💢💢
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና ክፍል3🔴
በቀጣይ✍🏾
📌የኢንተርኔት ላይ ወንደኛ እና ሴተኛ አዳሪ ክርስቲያኖች
📌የሳይበር ወሲብ ጣዖት በጋብቻ ውስጥ
@puritytube ያጋሩ
💢💢@puritytube💢💢
💢💢@puritytube💢💢
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና ክፍል3🔴
😱😱ክርስቲያን ፖርን ስታሮች😱😱
📡በሳይበር መስኮት📶

📖የሳይበር ወሲብ ማለት፦ ማንኛውንም ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን ለምሳሌ ስልክ፣ታብሌት፣ላፕቶፕ እና የመሳሰሉትን በመጠቀም 📡በኢንተርኔት ወይም በሌሎችም አገልግሎት አቅራቢ 📶ኔትዎርኮች አማካኝነት የሚደረግ ቅጥ አምባሩ የጠፋ ወሲብ ነው።

ሰላም የፒውሪቲ ቲዩብ ቤትሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን! ለዛሬ
ከዚህ ትልቅ የሳይበር 🚫የወሲብ ባህር ዉስጥ የምናተኩረው በሁለት 📌ዓሣዎች ላይ ነው። እነዚህም ዓሣዎች በተለምዶ ፦
📌live cam(ቪዲዮ ሴክስ) እና 📌ቻት ሴክስ በመባል ይታወቃሉ። ይሄንን የ#ክፍል3 ጽሁፍ ከስር መሰረቱ ለመረዳት አንባቢ 👉🏿#ክፍል1 እና #ክፍል2 ን በሚገባ መረዳት አለበት።ከክፍሎቹም ተያያዥነት አንፃር አንዱ ክፍል ብቻውን ሙሉ ሃሳብ የሚያስተላልፍ ሳይሆን በቀደሙት ክፍሎች ላይ ተንሰላስሎ የሚገባ ሰንሰለት ነው።

👉ወጣት ክርስቲያኖች አንዴ በ ቪዲዮ እና ቻት ሴክስ ኃጢያት ተፅዕኖ ውስጥ ከወድቁ በኋላ የሚያደርጉትን ባለማስተዋል እንደ እንስሳ በስሜታቸው እየተመሩ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ እንዲሁ እራሳቸውን 🔴ለፖርኖጋራፊ ጣዖት መስዋዕት ያደርጋሉ። 🔑መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ6፥13 ...ብልቶቻችሁን የዓመፃ የጦር እቃ አድርጋችሁ ለኃጢያት አታቅርቡ... ይላል። በተቃራኒው እነዚህ ወጣቶች በቪደዮ እና በምስል የራሳቸውን እርቃን በአማላይ ድምጽ እና ጹሁፍ ቀምመው ከሚያውቁት ወይም ደግሞ ምንም ትውውቅ ከሌላቸው ሰው ጋር በመመለዋወጥ📮 ስሜታችውን ለማርካት ይጓዛሉ። 📡ኢንተርኔቱም ሲፈልጉ ከሚያውቋቸው ጓደኞቻቸው ጋር ሳይፈልጉ ምንም ከማያቁት ሰው ጋር የሚገናኙበትን ምስጢራዊ የዝሙት ድግስ ደግሶ ኑ ይላቸዋል። እነሱም ከቤታቸው ሳይወጡ ከፈለጉበት ሆነው ጥቂት የስልክ ወይም የ ኮምፒውተር ቁልፎችን በመጫን ይሄን ልቅ ድግስ ይታደማሉ። 🚫ድግሱን ለመታደም የሚያስፈልገው መስፈርት ቅለት እና 🚫ምስጢራዊነቱ ለወጣቶቹ ጊዜያዊ መደበቂያን እና ምቾትን በመፍጠር የበለጠ ከሱሱ ጋር እንዲላተሙ ያደርጋቸዋል። ያልተረዱት አንድ እውነት ግን ምናልባት ከሰው ምስጢር ማድረግ ይቻል ይሆናል ሁሉን ከሚያይ አምላክ አይኖች ስር ግን የት መደበቅ ይቻላል?😳 ሰማይ ዙፋኑ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት!... “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።” ዕብ 10፥31 😔😭
ሳይበር ሴክስ አስከትሎቱ ምንድነው
1ኛ ሳይበር ሴክስን የሚያደርጉ ሁሉ የፖርኖግራፊ(ክፍል 1 ይመልከቱ) መሪ ተዋናዮች በተለምዶም ፖርን ስታርስ ናቸው። ነገር ግን ይሄን እውነታ እንዳያዩ ዓይናቸው ይታወራል። ወሲባዊ ስሜቱን በጽሁፍ እርቃኑን ደግሞ በምስል📸 አድርጎ ለአድንም ይሁን ለብዙ ሰው የሚያጋራ ግለሰብ 🔴ፖርን የሚተውን 👉ተዋናይ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?
2ኛ, በዚህ ልቅ ድግስ ላይ የሚሳተፍ ወንድም ይሁን ሴት ጋለሞታነትን ይለማመዳል።በግልፅ አነጋገር ወንደኛ ወይም ሴተኛ አዳሪ ይሆናል። ለጊዜያዊ ደስታ እርቃናቸውን የሚቸረችሩ፣ንፁህ ጓደኞቻቸውን የሚያስነውሩ፣የማያውቃቸው ሰው ለጥቂት ደቂቃ ቻት ሴክስ የሚገዛቸው 💀ጋለሞታዎች ይሆናሉ።
🔔ስለዚህ አንባቢያን ሆይ🔑 “ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን አይገባም።ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን1ኛ ቆሮ6÷15-16
ይቀጥላል...
✍🏿በካም
✍🏿የማይታይ ፊርማ
💢💢@puritytube💢💢
💢💢@puritytube💢💢
📌📌 ከፀጋ በታች 📌📌

(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 6)
----------
13፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

14፤ #ኃጢአት_አይገዛችሁምና_ከጸጋ_በታች_እንጂ_ከሕግ_በታች_አይደላችሁምና



👉 በኃጢአት አለመገዛት ወይም ነፃነት የሚገኘው የሆኑ ህጎችን በማድረግና ባለማድረግ ውስጥ ሳይሆን ከፀጋ በታች በመሆን ነው ፡፡

⭕️ ከፖርኖግራፊ ከማስተርቤሽን ሱስ በማመለጥ ነፃ መውጣት የሚቻለው ፤ እነዚህን የኃጢአት ድርጊቶች ከዛሬ ጀምሮ አላደርግም ብሎ በመወሰን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ፀጋ በታች በመጠለል ነው ፡፡

ታዲያ ይህ ፀጋ ምን ያደርግልናል

📌 " ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"
(ወደ ቲቶ 2:12-13)


#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
Purity Tube pinned «🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና ክፍል3🔴 😱😱ክርስቲያን ፖርን ስታሮች😱😱 📡በሳይበር መስኮት📶 📖የሳይበር ወሲብ ማለት፦ ማንኛውንም ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን ለምሳሌ ስልክ፣ታብሌት፣ላፕቶፕ እና የመሳሰሉትን በመጠቀም 📡በኢንተርኔት ወይም በሌሎችም አገልግሎት አቅራቢ 📶ኔትዎርኮች አማካኝነት የሚደረግ ቅጥ አምባሩ የጠፋ ወሲብ ነው። ሰላም የፒውሪቲ ቲዩብ ቤትሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም…»
ተጀመረ!
የ100 ብር የሞባይል ካርድ አሻናፊ የሚያደርገው #Challenge ተጀመረ!
ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተያያዘ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያምር ዲዛይን ሰርታቹ በ @ChristianMezmur_bot ላይ በመግባት #StayAtHomeChallange በሚለው ሳጥን ላኩ!

ትናንት በርከት ያላቹ ቤተሰቦቻችን ፎቶ የላካቹ ሲሆን፤ አንዳንድ የቤተሰባችን አባሎች የሌላ ሰው ፎቶዎችን ስትልኩ መታዘብ ችለናል። የቤት ቆይታችንን ለማሳመር ስለሆነ የራሳችንን ብንልክ ይመረጣል።

ማሳሰብያ
ፎቶ ስትልኩ ወደ ቡቱ ቀጥታ ስትልኩ እኛ ጋር አይደርስም። ቡቱን start ከደረጋቹ በኋላ ከሚመጡላቹ በተኖች መካከል
🔸#StayAtHomeChallange🏠 በኩል ብቻ መላክ የምትችሉ መሆንኑ እንገልፃለን።

ብዙ ላይክ ያገኘ ሰው የ100 ብር ካርድ ተሸላሚ ነው። ይህን ውድድር ለማሸነፍ ወዳጆቻቹን ወደ @christian_mezmur በመጋበዝ ላይክ እንዲያደርጉላቹ ማድረግ ትችላላቹ!


መልካም እድል!
@christian_mezmur
2025/07/04 04:54:36
Back to Top
HTML Embed Code: