Telegram Web Link
ከቅዥት ነፃ የሆነ ሕይወት @Appeal4purity.MP4
86.9 MB
#ሊታይ_የሚገባ_ድንቅ_መልዕክት
👩‍🏫በዶ/ር መስከረም ክፈተው

ብዙዎች ሃሰተኞች ነቢያት ባሉበት በዚህ በመጨረሻው ዘመን

የአንዳንዶች ትዳር የብዙዎችም ወደ ትዳር ጉዞ ተጨናግፏል፡፡

ብልህ ግን ሁሉን በቃሉ መነፅር ያያል

#Share

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Purity Tube pinned a photo
🛑 #ድንግልና_የደም_ኪዳን 🛑

እግዚአብሄር ለምን የሴት ልጅ የፆታዊ ግንኙነት ክፍልን በስስ ሽፋን እንደሸፈነ አስባችሁ ታውቃላችሁ

በእንግሊዘኛ "Hymen" ይባላል የሴት ልጅን ብልት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚሸፍን ስስ ስጋ ነው፡፡

🤔 ለምን ሰሪያችን እግዚአብሄር ሊበጠስ የሚችል በደም የተሞላ ህዋስ በብልት መግቢያ ላይ ማስቀመጥ አስፈለገው

ለምንስ ነው በሚበጠስበት ጊዜ በሚጥለቀለቅ ደም የተሞላው ?ለምን?

ያለጥርጥር ይህ Hymen የሚባለው ነገር መግቢያ በር ነው!!

👉 እግዚአብሄር ይህን በደም የተሞላ ነገር እንደ ቃልኪዳን መከልከያ ወይም ድንግልናን በሚወስደው እና በሴቷ መሃል እንደ የቃልኪዳን መሃላ ይሆን ዘንድ በዚያ ቦታ አስቀምጦታል፡፡

በእግዚአብሔር ፊት የሴት ልጅ ድንግልና መገርሰስ እንደ አንድ ተራ ነገር አይቆጠርም፡፡

👉ይልቁንም በደም መፍሰስ የሚረጋገጥ ትልቅ ቃልኪዳን ነው፡፡

⚠️ ድንግልና " ማንም ወደዚህች ሴት የሚገባ ሁሉ ከእሷ ጋር ቀሪ ዘመኑን ሁሉ ለማሳለፍ የግድ የደም ቃልኪዳን ማሰር አለበት፡፡ " የሚል የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፡፡

👉 ሰውነታችንን ፣ የወሲብ ስሜታችንን የሚያነሳሱ ሆርሞኖቻችንንና ነርቮቻችንንም ጭምር የሰራው ራሱ እግዚአብሄር እንዲህ በግልፅ ይናገራል፡፡

⛔️ " #ሰውነት_ለዝሙት_አይደለም !! "

ማንም ሰውነቱን ለዝሙት ለመጠቀም የመረጠ ሁሉ አንድ ነገር ማወቅ አለበት፡፡
⛔️እሱም በቀጥታ ከእግዚአብሔር እቅድ ውጪ እየሰራ/እየሰራች መሆኑን ነው!!

ይህም ስራ ደግሞ በእርግጠኝነት አሁን ወይም በኋላ የራሱን መዘዝ ያመጣል፡፡

#General
እባክዎ #ሼር
Please #share

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
#እግዚአብሄር_ሚስትህ_እንድሆን_ልኮኝ_ነው_አግባኝ


👤A4P እንግዳ ፡- የ34 አመት ወንድ ነኝ ፡፡ Sexually ንፁህ ለመሆን እታገላለሁ፡፡ አብረን የምንፀልይና ስለግል ጉዳዮቻችን ፆታዊ ትግሎቻችንንም ጭምር የምንወያይ የወንድ ጓደኞች አሉኝ፡፡

እገግዚአብሄር ሚስት እንዲሰጠኝ ብዙ ጊዜ እፀልያለሁ ግን እስካሁን ፀሎቴ መልስ አላገኘም ፡፡

ምንም አይነት ሱስም ሆነ የሃጢያት ልምምድ የለብኝም፡፡ እግዚአብሄር ለምንድን ነው ፀሎቴን የማይመልሰው?

💁A4P:- ያልተገባ ፆታዊ ልምምዶች IQ አለመግባትህ ያስመሰግንሃል፡፡

የግል ጉዳይህን የምታወያያቸው የወንድ ጓደኞች በማበጀትህ ጥሩ አድርገሃል፡፡

♦️ነገርግን እግዚአብሄር ሚስት እስኪያመጣልህ መጠበቁ ግን እሱ አይመስለኝም ትክክለኛው አካሄድ፡፡

🔖በአለም ላይ ቢያንስ ከሶስት እስከ አራት ቢሊየን ሴቶች ይኖራሉ፡፡ ከዛ ውስጥ ሶስት ቢሊየኑ ከገበያ ውጪ (ያገቡ ፣ የሸመገሉ ወይም ህፃናት) ናቸው እንበል አስበው እንግዲህ ፤ ከዛ ደግሞ ወረድ በልና በቸርችህ ውስጥ ስንት ያላገቡ ሴቶች ይኖራሉ፡፡ እግዚአብሄር ታዲያ ከዚህ በላይ እንዴት ይርዳህ🤔

💢አስበኸዋል እግዚአብሄር አሸዋንና ዛፎችን ሰጥቶ ሲያበቃ ቤት እንዲሰራልን መጠበቅ እንደማለት ነው፡

👉የእግዚአብሔር ድርሻ እና የሰው ድርሻ የሚባል ነገር አለ፡፡

♦️እንደ ወንድ ያንተ ድርሻ ሚስት የምትሆንህን ሴት በእግዚአብሔር ቃል እየፈተሽክ መፈለግ ነው፡፡

🔑ስለዚህ መሄድ መፈለግና ማግኘት ያንተ ድርሻ ነው እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡

🔴ፍፁም የሆነችን ሴት እየጠቅክ እንደሆነ አላውቅም እንደዛ ከሆነ ነገሩ ልንገርህ ወንድሜ እድሜ ዘመንህን ሳታገባ መኖርህ ነው፡፡

☑️የምንኖርባት ፕላኔት ፍፁማን ሰዎች የሚኖሩባት አይደለችም፡፡ ሁላችንም ብዙ ግድፈቶች ያሉብን ሰባራዎች ነን፡፡

👉እና ደግሞ እድሜህ በጨመረ ቁጥር መስፈርቶችህም በዛው ልክ እንደሚጨምሩ እወቅ፡፡ ከሚስትህ የምትፈልጋቸው ነገሮች ዝርዝር እየተወሳሰበ ነው ሚሄደው፡፡

♦️ችግሩ የምትፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ የምታሟላልህ ሴት ማግኘት አለመቻልህ ነው፡፡

💢መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር
" ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 18:22) ይላል፡፡
( “He who finds a wife finds what is
good and receives favor from the LORD.” Proverbs
18:22. )

💢ይህ ጥቅስ ቃልኪዳን ሳይሆን የጠቢብ ምክር ነው፡፡ ምንም ያልፈለገ ምንም አያገኝም፡፡

👉አንተ መርጠህ ያመጣሃትን ሴት ወደ እግዚአብሄር አቅርባት እሱም አንድነታችሁን ይባርካል፡፡

ስለዚህ ወንድሜ ራስህን ቢዚ አድርግ አይኖችህን ገልጠህ ዙሪያህን ቃኝ፡፡

📌እንጂ እግዚአብሄር በርህን አንኳክታ " ሰላም ፤ ሚስትህ እንድሆን እግዚአብሄር ልኮኝ ነው፡፡ በል አግባኝ" የምትልህን ሴት እንዲያመጣልህ ምትጠብቅ ከሆነ ሳታገባ መቅረትህ ነው፡፡

👉እሱ ብቻ ሳይሆን በተዘዋዋሪ አንድን ሴት ሳታገባ እንድትቀር ማድረግህ ነው፡፡ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ አየህ? በል ወንድሜ ድርሻህ መወጣት ጀምር፡፡

#single


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛📛 ዛሬ የማይታይ ዝገት ⛔️⛔️

👱‍♀"አንድ ልጅ አለ በጣም አስተዋይ ሰው ነው ግን በጌታ አይደለም እና እንዳገባው ጠየቀኝ ከዛ...."

👱" የምወዳት ልጅ አማኝ አይደለችም ግን ከብዙ ክርስቲያን ነን ባይ ሴቶች የተሻለ ምግባር አላት....."

👩" ይኸው ላለፉት ስምንት አመታት ከብዙ ክርስቲያን ወንዶች ጋር ግንኙነት ፈጥሬ አውቃለሁ ግን ከሶስት ወር በፊት ያወኩት አህዛብ ልጅ ግን ሁሉንም ያስንቃል...."

ከላይ ያሉትና የመሳሰሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይጠየቃሉ፡፡

👉 በወርቃማ ቅብ ያማረ ብረትን ጌጥ ብለህ በእጅህ ላይ ብታስረው ምናልባት እንደጌጥ ሊያገለግልህና ኮራ ብለህ በሰዎች ፊት ልታሳየው የምትችለው በጣም ውስን ለሆነ ጊዜ ነው፡፡

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የምትኮራበት ያ ጌጥ እራሱ የምታፍርበት መሆኑ አያጠራጥርም ፡፡ ምክንያቱም በእጅህ ላይ ያሰርከው በወርቃማ ቀለም የተሸፈነ ብረት እንጂ ወርቅ አይደለምና በላዩ የተቀባውን ቀለም አሸንፎ ዝገቱን ያጋልጣል ፡፡ የዛገን ነገር እንደጌጥ መጠቀም ማን ይመርጣል

ከላይ ተቀንጭበው የተጠቀሱት ታሪኮችም በወርቃማ ቀለም ከተሸፈነው ብረት የተለየ ሁኔታ የላቸውም ፡፡

▶️ "በጣም ጥሩ ሰው ነው" ፣ " ፀባዩ አንደኛ ነው" ፣ " እጅግ አስተዋይ ናት " እና የመሳሰሉት ወርቃማ ቀለሞች ምናልባት ለጊዜው በእውቀትና በእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን በስሜት እንድንገዛ ሊጎትቱን ይችሉ ይሆናል፡፡

ጊዜያዊ ስሜታችንም እሰኪበርድ ድረስ ጥልቅ ፍስሃ ይሰጡ ይሆናል፡፡

💠ነገርግን ያ የሚያምረው ወርቃማ ቀለም ሲደበዝዝ ከታች ያለው ማለትም እንደ "ግን በጌታ አይደለም" ፣ "ግን አማኝ አይደለም " እና የመሳሰሉ ዝገቶች "ሙታን" በሚለው መፅሀፍቅዱሳዊ ቃል ማህተም ታትመው ራሳቸውን መግለጥ ሲጀምሩ ትላንት የፈጠሩትን ደስታ የሚያስረሳ ሃዘን ይዘው ይከሰታሉ፡፡

🗣 ለዚህ ምስክር ይሆን ዘንድ በስህተት ካላመኑ ሰዎች ጋር በትዳር ከተጠመዱ ሰዎች አንደበት የሚወጡ የፀፀት እና የምሬት ቃሎችን መስማት በቂ ነው፡፡

👉ለስሜት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ የአስተዋይ ሰው ምርጫ ነው፡፡

#single

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💍 ፍፁም የሆነ ትዳር እንዲኖርህ መጣርህን አቁም!!⛔️

💢በእውነቱ ከሆነ 'የተሻለ ትዳር' እንዲኖርህ ባትጥርም መልካም ነው!!

🔑 ይልቁንም ለራስህ የተሻለ ማንነት ለመፍጠር ትጋ!!

ትኩረትህ እግዚአብሄር አንተ እንድትሆን
የሚፈለግውን አይነት ሰው መሆን ከሆነ የዚህ ነገር ውጤቱ ይህ ነው
👉 ሚስትህ የተሻለ ባል ይኖራታል የተሻለ ትዳርም ይኖራችኋል

እርግጥ ነው ከሚስትህ ጋር የተሻለ ተግባቦት መፍጠር መቻል አለብህ፡፡

🔵 ግጭቶች በሚኖሯችሁ ጊዜ ለራስህ ተሟጋች ልትሆንና ጭራሽ እሷን ላታዳምጣት ትችል ይሆናል፡፡

መፅሀፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ያስተምርሃል፡፡

📜" ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤" ያዕ 1: 19

መልስ ለመስጠት ሳይሆን ሚስትህን ለመረዳት የምታዳምጣት ከሆነ የተሻልክ ሚዛናዊ ሰው ሆነሃል ማለት ነው፡፡ የዚህ ነገርም ውጤት ከሚስትህ ጋር የሚኖርህ መልካም ተግባቦት ነው ማለት ነው፡፡

#Married


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ሻሎም የጌታ ቤተሰቦች

አንድ ወዳጃችን በመቀሌ ቆይታው ያጋጠመውን ነገር እንዲህ ሲል አጫወተን፡፡

" በዘጸዓት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን የመቀሌ አጥቢያ ያሉ አገልጋዮች በጣም ለወንጌል ስራ የተሰጡና ዘወትር የሚተጉ መሆናቸውን ለማስተዋል ችያለሁ፡፡

ሆኖም ግን የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ቁጥር አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር ካሉትም ውስጥ አብዛኛዎቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመሆናቸው በገንዘብ እየተቸገሩ እንደሆነ አየሁ፡፡

ለምሳሌ በአንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ የተፈለገው ገንዘብና የተሰበሰበው ሰማይና ምድረ ሆነው አይቻለሁ፡፡ ስለዚህ ለምን በዚህ ቻናል እና በሌሎችም ቻናሎች ቴሌግራምን በመጠቀም ለወንጌል አገልግሎት ድጋፍ ለቤተክርስቲኒቷ አናደርግም !? "

እኛም ይህን መልካም ስራ ለመስራት ብዙ መልካም እጆች እንደሚዘረጉ በማመን ይኸው ቤተክርስቲያኗን በገንዘብ ለማገዝ እንድትዘረጉ በጌታ ፍቅር ጠየቅናችሁ፡፡

እንደተነገረን ከሆነ 100 ሰዎች 20 ብር ቢያዋጡና 2000 ብር ገቢ ቢደረግላቸው ለእነሱ ትልቅ ነገር ነው ለእኛ ግን በጣም ጥቂት ነው፡፡

ስለዚህ ከታች ባለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የአቅማችሁን እንድትደግፉ አሁንም በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን

Birhan Bank
Zetseat A.R. church
Mekelle
Acc. # 2500150057990

ጌታ ይባርካችሁ!!

#share #share #ሼር #ሼር

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ማርች 8 የሴቶች ቀን!!

እግዚአብሄር "...የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።" ብሎ ሴትን ሲፈጥር ወንድ ብቻውን መሆኑ መልካም እንዳይደለ ስለሚያውቅ ነው፡፡

ሴቶች 👉እናት ሆነው ወልደው አሳድገውናል!
👉እህት ሆነው አግዘውናል!
👉ሚስት ሆነው ቤተሰብ ሰጥተውናል !

እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሳችሁ🙏

ይህን ፅሁፍ ለሚያውቋቸው ሴቶች ሁሉ በመላክ መልካም የሴቶች ቀን ይበሉ!

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ተከታታይ ትምህርት
@Appeal4purity

ርዕስ ፦ ♥️የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት♥️
👉 መቼ
👉 እንዴት
👉 ማንን

🕒 ዛሬ ማታ 3:00 ይጀምራል፡፡

#ሼር በማድረግ ወዳጆን ይጋብዙ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
👫የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት

▪️▪️▪️▪️ክፍል አንድ▪️▪️▪️▪️

💠 👫የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት ፅንሰ ሐሳብ መነሻ

የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት አሁን የመጣ ሀሳብ ወይም ሰይጣን እኛን ለማጥመድ ብሎ የፈጠረው ሳይሆን በእግዚአብሔር የዘላለም ፕሮግራም ውስጥ የነበረ ደግሞም ኃጢያት ወደ ምድር ከገባ በኋላ ምንም እንኳን የዘላለም ዕቅድነቱ ቢቀርም የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ ሆኖ የቀጠለ ነው፡፡

👉 ለአዳም እግዚአብሔር እጅግ በጣም ብዙ ነገሮችን ሰጥቶታል ለምሳሌ ምንም የማይጎድልበትን መኖሪያ (ኤድን ገነት)፣ በጣም ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸውን እንስሳት፣ ለመብላት ደስ የሚያሰኙ ፍራፍሬዎችን፣ ወዘተ... ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር (ዘፍ2፤20)፡፡

💢 ለመጀመሪያ ጊዜ አዳም የተሟላ የደስታ ኑሮ መኖር የጀመረው እንደ እርሱ ያለች ረዳት ሔዋን ስትፈጠርለት ነበር፡፡

👉እንደውም እግዚአብሔር ከአዳም የጎን አጥንቱ ላይ ወስዶ ሔዋንን በመፍጠር ወደ አዳም ሲያመጣት በሚገርም ሁኔታ ከየት እንደመጣች እንኳን ማንም ሳይነግረው በቀጥታ እንዲህ ነበር ያለው አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። (ዘፍ 2፤23-24)

🔴ይሄ የሚያሳየን የሴትና ወንድ ጓደኝነት የሰይጣን ፈጠራ ወይም ደግሞ የሰዎች ስሜት ብቻ የፈጠረው ሳይሆን ከጅምሩ የእግዚአብሔር መልካም ሐሳብ እንደነበረ ነው፡፡

🔴እንደዚህ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ለጥቅማችንም የተፈጠረ ሆኖ እያለ ግን አዳም በሰራው ኃጢያት ምክንያት ሰው ስለወደቀ ሰይጣንም ለክፉ ስራው ማስፈፀሚያነት ይጠቀምበት ጀመር፡፡

👉እኛ ክርስቶስ ኢየሱስን አምነን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም የተወለድን ቅዱሳን በሙሉ ለየት የሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ አንዱ በሰይጣን ተበላሽቶ ከወደቀው ዓለም የተዋጀንና በአዲሱ አዳም (ኢየሱስ) የዘር ግንድ የገባን መሆናችን ነው፡፡

💢የወደቀውና የተበላሸው ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ የአኗኗር ስርአትና የሚመሩበት ሕግ (መልካምም ሆነ ክፉ) እንዳላቸው ሁሉ እኛም ደግሞ የሚገዛንና ስርአት የሚያስይዘን የህይወት መንፈስ ሕግ አለን፡፡

👉አንድ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ ዕቃ የራሱ ማኑዋል እንዳለው ሁሉ እኛም የራሳችን የሆነ ማኑዋል አለን፡፡ ለምሳሌ የቶሺባ ላፕቶፕ💻 ኦፕሬቲንግ ማኑዋል📄 ለአንድ የተበላሸ አፕል ላፕቶፕ መስሪያነት እንጠቀም ብንል ወይ በጭራሽ አይሰራልንም አሊያም ደግሞ የባሰ አበላሽተነው እናርፋለን ስለዚህ የግድ አፕል ላፕቶፑን ከሰራው አካል የመጣ የራሱ የሆነ ማኑዋል መጠቀም ይኖርብናል፡፡

📄ማኑዋል የሚያስፈልገን ዕቃውን በሚገባ እንድንጠቀምበት እና ሲበላሽ ደግሞ ለመስሪያነት ነው፡፡

👉በአጭሩ ማኑዋል ማለት ስለዕቃው ያለንን ማንኛውም ጥያቄ የምንመልስበት እንዲሁም ዕቃውን መጠቀም እስካለብን ጥግ ድረስ እንድንጠቀም የሚያግዘን መመሪያ ነው፡፡ የቶሺባ ላፕቶፕን ማኑዋል የሚያሳትመው ራሱ የላፕቶፑ ፈጣሪ ድርጅት እንጂ ፈፅሞ ሌላ አካል አይደለም፡፡

🔵በተመሳሳይ መልኩ እኛንም የሚመራን የፈጠረን አካል የሰጠን ማኑዋል አለን እርሱም መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

🔴ስለ ሰው ለሚፈጠርብን ማንኛውም ጥያቄ መልስ የምናገኘው ማንዋላችን ከሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡

🔑እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ሴት እና ወንድ እርስ በርስ እንዲፈላለጉ እና እንዲፋቀሩ የሚያደርግ ስሜት በውስጣቸው አስቀምጧል፡፡

💯እንግዲህ የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነትና የትዳር ዲዛይነር እግዚአብሔር ከሆነ፤ እንዴት በቅድስና እንደምንይዘው የሚያሳይ ደግሞ መንገድ አለው ማለት ነው፡፡

💢ታዲያ ፈጣሪችን የሆነው እግዚአብሔር እንተዳደርበት ዘንድ የሰጠን ማኑዋል መፅሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ ስለኛ አፈጣጠር የማይመለከተው አካል አቅጣጫ ሊያሳየን አይችልም፡፡

ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ለሚገጥሟቸው ችግሮችና ጥያቄዎች መፍትሄ ለማግኘት የሚጥሩት ከ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ከተለያዩ የፍልስፍና እና የስነልቦና መፃሕፍት፣ በዘርፉ ሊቅ ከተሰኙ ሰዎች… ወዘተ ነው፡፡

እንደዛ ከሞከርን ደግሞ ላፕቶፑን ለመስራት የተሳሳተ ማኗል ስንጠቀም የባሰ እንደሚበላሽ ሁሉ እኛም ከእግዚአብሔር ሐሳብ እና መልካም ፈቃድ በእጅጉ በመራቅ ክፉኛ እንበላሻለን፡፡

በዚህች ፅሑፍ ላይም ለምናነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ የምንሰጠው መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል በሚል ነው፡፡

.......ይቀጥላል

#General #couple #Married

ለወዳጅዎ #ሼር ማድረግዎን አይርሱ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ ስለሞቱት ሰዎች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን በA4P ስም እንገልፃለን ፡፡


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🕑🕑 መቼ

ክፍል ሁለት

የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር ትክክለኛ ጊዜውን ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

የብዙ ሰዎች ጓደኝነት ትዳር ላይ ሳይደርስ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ያለጊዜው መጀመሩ ነው፡፡

👉 ጓደኝነትን ያለጊዜ በመጀመር ከሚደርሱት ጉዳቶች ውስጥ ደግሞ ዋነኛው የቅድስና ችግር ነው፡፡

💯 ከእነዚህ ሁሉ ችግሮች ለመዳን የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት እውን ትክክለኛ ጊዜው ነውን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፤ ምን መጠየቅ ብቻ እርግጠኛ የሆነ መልሱንም ማወቅ አለብን‼️

ጊዜ አለመጠበቅ የሚያመጣውን ጉዳት በሚገባ ያስተዋልን እንደሆነ “ታዲያ እንዴት ነው ጊዜውን ማወቅ የምንችለው? 🤷‍♂የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮአችን ይመጣል፡፡

👉የዘጠኝ ዓመት ሕፃን ልጅ ፍቅረኛ ልያዝ ወይ ብላ ብትጠይቃችሁ በእርግጠኝነት የምትመልሱላት መልስ አንቺ እኮ ገና ሕፃን ልጅ ነሽ ፍቅረኛ ለመያዝ ትንሽ ማደግ አለብሽ የሚል ነው፡፡

👉ነገር ግን አንድ የሀያ አምስት አመት ኮረዳ ተመሳሳይ ጥያቄ ብትጠይቃችሁ ህፃን ነሽ እደጊ አትሏትም ወይም ደግሞ እንዴት በሀያ አምስት ዓመትሽ አትሏትም ይልቁንም ልጁ ማነው? ክርስትያን ነው ወይ? ባሕርይው ምን ዓይነት ነው? እና ሌሎችንም ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለማጣራት ነው የምንሞክረው፡፡

💢 ከዚህ የምንረዳው የፍቅር ጓደኝነትን መያዝ ወይም አለመያዝ የሚወሰነው በእድገታችን ነው ማለት ነው፡፡

እድገት ምንድን ነው በእድሜና በአካለመጠን የመግዘፍ ብቻ ወይስ አርቆ የማሰብና የማስተዋል መጠን ክፍል እየቆጠሩ መመረቅ ብቻ ወይስ በማህበራዊና ስነልቦዊ ዕውቀት መራቀቅ፣ እድገት ምንድን ነውስንት ዓይነት እድገት አለ


🗝እድገት የሚለካው ሁሉን አቀፍ በሆነ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ አንድ ሰው ሀያ እና ሀያ አንድ አመት ስለሞላው ብቻ አድጓል ማለት አንችልም❗️💯

🛑በትምህርት ልቆ ዶክተር ኢንጂነር ቢባል ይህ ብቻውን የእድገቱ ማሳያ ሊሆን አይችልም፡፡

👉 እድገት ዘርፈ ብዙ፣ መጠነ-ሰፊና፣ እና ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡

👉የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት በቅድሚያ ሁለንተናዊ የሆነ እድገታችንን መመርመር መቻል አለብን፡፡

💢 ይህን ስናደርግ ትክክለኛ ጊዜው ይሁን አይሁን መወሰን ቀላል ይሆንልናል፡፡


.....ይቀጥላል

#Married #couple #General #single

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ🙏


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ደረሰ 💫💫

👉በየዓመቱ በጉጉት የሚናፈቀው
#SUPREMACY_OF_CHRIST

አዘጋጅ 👉EvaSUE ኢቫሱ

🗓ቀኑ 👉 መጋቢት 6-8

👉ቦታው 💒 በቤዛ አለምአቀፍ ቤተክርስቲያን

♦️መካፈል የምትችሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ተጋብዛችኋል

#አይቀርም

#ሼር በማድረግ ሌሎችን ይጋብዙ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Purity Tube pinned a photo
#ለተቃራኒ_ፆታ_ጓደኝነት_ብቁ_መሆናችንን_የምንለካባቸው_የእድገት_አይነቶች

ክፍል ሶስት

💢ሁለንተናዊ እድገትን ሊለኩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ የእድገት ዓይነቶች (ዘርፎች) የሚከተሉት ናቸው፡-

1⃣የአካለ-መጠን እድገት (Physical Maturity)፡-

የአካለ መጠን እድገት ማለት ለአቅመ-አዳም/ሔዋን የመድረስ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሴቶች እዚህ ደረጃ ላይ ቀድመው ደርሰው ቢገኙም ነገር ግን በአማካኝ ለወንድም ለሴትም ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ ሲሆኑ አዋቂ ሰው (adult) መባል ይጀምራሉ፡፡

✔️በአደጉት አገሮች የሚኖሩ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብ ስለሚመገቡ እንዲሁም ምቹ እና ጤናማ የሆነ ኑሮን ስለሚኖሩ ልክ አስራ ስምንት አመት ሲሞላቸው የገዘፈ ሰውነት ይኖራቸዋል፡፡

🔹ለዚህም ነው አስራ ስምንት ዓመት የሞላውን ሰው አዋቂ (Adult) ብለው የሚጠሩት፡፡

🔴በእኛ ሐገር ግን አስራ ስምንት ዓመት የሞላው ሰው ገና ኮሌጅ እንኳን ያልተቀላቀለ በሰውነቱም ቢሆን እምብዛም ያልገረደፈ እምቦቀቅላ ታዳጊ ሊሆን ይችላል፡፡

👉ይህን ስናይ የፈረንጆቹን የአዋቂነት የዕድሜ ገደብ እንደወረደ መጠቀም ብዙም እንደማያዋጣን እንረዳለን፡፡

🔵እንደው በድምሳሳው ግን ከሀያ እስከ ሀያ ሶስት ዓመት ያለ አንድ ኢትዮጲያዊ ሴት ሆነ ወንድ አዋቂ ሰው ነው ብንል የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር እጅግ በጣም ትንሹ የዕድሜ ክልል ይሄ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡

🗝ይሄ ማለት ግን ሃያ ዓመት ያለፈው ሰው ሁሉ ለጓደኝነት ብቁ ነው ማለት አይደለም ምክንያቱም ሌሎች ሊያሟላቸው የሚገባቸው የእድገት አይነቶች አሉ፡፡


2⃣የስነልቦና (የአእምሮ) ዕድገት (Mental Maturity)፡-

👉ጓደኝነትን ለመጀመር በስነልቦናና በአእምሮ ብስለት የተዘጋጀ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

💢አንድ ሰው ጓደኝነቱን እንዴት በቅድስና መጠበቅ እንዳለበት፣ ያለ ምንም እንቅፋት እንዴት ወደ ትዳር ማድረስ እንዳለበት፣ ሰዎችን ላለማሰናከል ምን ማድረግ እንዳለበትና… ወዘተ ለማወቅ የአእምሮ ብስለቱና ዝግጁነቱ አናሳ ከሆነ ስኬታማ የጓደኝነት ሕይወት አይኖረውም፡፡

👉ከዚህም ባሻገር በትዳር ወቅት ስለ ቤት አስተዳደር፣ ስለገንዘብ አያያዝ፣ ስለ ልጆች አስተዳደግ፣ ስለ ስራ ፈጠራ፣ እና ወዘተ ለማወቅ የስነልቦና እና የአእምሮ እድገት ወሳኝ ነገር ነው፡፡

3⃣መንፈሳዊ እድገት (Spiritual Maturity)፡-

🔴 መንፈሳዊ እድገት ለማንኛውም ዳግም የተወለደ ክርስትያን ሁሉ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነገር ነው፡፡

🔴የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር ደግሞ በይበልጥ መንፈሳዊ ሕይወታችን ያደገ እና የበሰለ ክርስትያን ልንሆን ያስፈልገናል፡፡

🔵ይሄንን እንደ መሰረታዊ ግብዓት መጥቀስ ያስፈለገበት ምክንያት ከብዙ የቅድስና እና የሞራል ውድቀቶች ስለሚጠብቀን ነው፡፡

👉በግንኙነታችን ወቅት እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በፅድቅና በቅድስና እንድንኖር የሚረዳን ያለን መንፈሳዊ ብስለትና አስተዋይነት ነው፡፡

💢በተቻለ መጠን ዕለት ዕለት መፅሐፍ ቅዱሳችንን በማንበብ (በማጥናት)፣ የግል የፀሎት ጊዜ በማካሄድ፣ ከቅዱሳን ጋር ሕብረት በማድረግ፣ ተለያዩ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ እንዲሁም ምንም አይነት አስተምሕሮአዊ ዝንፈት የሌለባቸውን መፅሀፍት (በተለይ በትዳር እና እጮኝነት ዙሪያ) በማንበብ… ወዘተ በመንፈሳዊነት ማደግ ይቻላል፡፡

ለምሳሌ አሁን ይሄንን ፅሁፍ እያነበባችሁ ያላችሁት በእጮኝነትና ትዳር ዙሪያ የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል የሚለውን ለማወቅ ነው… እንደዚህና መሰል ፅሁፎችን ማንበብ መንፈሳዊ እድገታችንን ያፋጥንልናል፡፡

በሚቀጥለው ክፍል እድገትን ከኢኮኖሚ አንፃር እናያለን

........ ይቀጥላል


#single #General



💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
👱‍♀ቆንጆ ሴት👱‍♀

የዚህ አለም አምሮት ልቧን ያልሰረቀ

በእርባናቢስ ሩጫ ወዟ ያለቀቀ

ሃሜትና ወሬ ከውስጧ ያልፈለቀ

ለዝሙት ለኃጥያት ገላዋን ያልሰዋች

ለቅዱሱ መንፈስ ማደሪያ የሆነች

እሷ ናት ቆንጆ እጅግ የተዋበች፡፡

ገጣሚ መቅዲ ላቀው

👉 📜" ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 31:30)

ከወደዳችሁት #ሼር

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🤔🤔ማንን?

▪️▪️▪️▪️ ክፍል አራት ▪️▪️▪️▪️

🔵በአካለ መጠን (physically)፣ በስነልቦና (በስነአዕምሮ) (mentally)፣ በመንፈሳዊ (spiritually) እና በገንዘብ አቅም (economically) አድጊያለሁ ብሎ የሚያስብ ወይም የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነትን ለመጀመር ብቁ ነኝ የሚል ሰው በቀጣይ መመለስ ያለበት ጥያቄ ቢኖር “ማንን” የሚል ነው፡፡

🔵ሁለንተናዊ የሆነ ዕድገትን ያደገ ሰው በእርግጥ የሚመከረው በቶሎ ወደ ትዳር መስመር እንዲገባ ነው፡፡

🤔እውነት ግን የወደፊት ትዳር አጋራችን ማን ነው/ናትደግሞስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅ ይቻላል

🔹በተለምዶም ይሁን በማወቅ በአብዛኞቻችን ዘንድ የፍቅር ጓደኝነትን ስለመጀመር ሲታሰብ ወደ አእምሮአችን ቀድሞ የሚመጣው ጉዳይ “የእግዚአብሔር ፈቃድ ናት/ነው ወይ?” የሚለው ጥያቄ ነው፡፡

👉እንደ ክርስቲያን ይሄንን ወሳኝ ጥያቄ መጠየቅ ብልሕነት ነው ምክንያቱም በክርስቲያን የፍቅር ጓደኝነት የመጨረሻ ግብ የሆነው ትዳር ላይ እንዲደርሱ በትዳርም ደግሞ እስከ መጨረሻው እንዲዘልቁ የሚያደርጋቸው በመሆኑ ነው፡፡

👉እግዚአብሔር በአምሳሉ ለፈጠራቸው የሰው ልጆች ትዳርና ጓደኝነትን በተመለከተ መልካም ፈቃዱን የሚገልጥባቸው እጅግ ብዙ መንገዶች አሉ፡፡

💢ጥቂቶቹ እና መሰረታዊ የሆኑት ፈቃዱን ማወቂያ መንገዶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-

1⃣ፆታ
2⃣እምነት
3⃣ፍቅር

እይያንዳንዳቸውን በዝርዝር እንይ👇

1⃣ፆታ 👉 የፆታ ጉዳይ ቀለል ያለ ነገር ይመስላል ግን ከዘመኑ እየከፋ መሄድ የተነሳ በጣም አሳሳቢ እና አፅኖት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

💢ትዳርንና የፍቅር ጓደኝነትን (እጮኝነትን) በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሴት ከወንድ ጋር፣ ወንድ ደግሞ ከሴት ጋር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ለጓደኝነት ያሰባችሁት ሰው ከእናንተ ጋር ተቃራኒ ፆታ ከሆነ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱን አሟልታችኋል ማለት ነው፡፡

2⃣እምነት ፡- ትዳር ማለት አንድ አካል መሆን ማለት ነው፡፡

👉የፍቅር ጓደኝነት ደግሞ አንድ አካል ወደ መሆን መሄጃ መንገድ ነው፡፡

🔑ስለዚህ ከሞት ወደ ሕይወት የመጣ አንድ ሰው ገና ሞት ውስጥ ካለ ሰው ጋር አንድ አካል ፈፅሞ ሊሆን አይችልም፡፡

💢አንድ ሰው ክርስትያን ሲሆን እርሱ ሞቶ በውስጡ የሚኖረው ደግሞ ህያው የሆነው ክርስቶስ ነው፡፡

👉ታዲያ እንዴት ክርስቶስ ከጣኦት ጋር ይጋባል፣ እንዴት የክርስቶስ ቤተ-መቅደስ ከጣኦት ማደርያ ጋር ይጋጠማል፣🤷‍♂ በምንም ተአምር የሚያምን ከማያምን እንደዚህ አይነት ሕብረት ሊኖራቸው አይገባም፡፡

🗝ምናልባት እንደዚህ አድርገን ብንገኝ በቶሎ ንስሐ ገብተን ግንኙነታችንን በማቋረጥ ወደ ትክክለኛው መንገድ መምጣት አለብን⛔️፡፡

⛔️አለበለዚያ ግን ኢየሱስን ከዲያቢሎስ ጋር ሕብረት እንዲያደርግ ከመጋበዝ ጋር እኩል የሚስተያይ አደገኛ ሙከራ ነው፡፡

👉ነገር ግን ሁለት ሰዎች ጌታን ከመቀበላቸው በፊት ቢጋቡ እና አንድ አካል ከሆኑ በኋላ ከሁለት አንዳቸው ጌታን ቢያገኙ እነዛ ሰዎች መፋታት አለባቸው ማለት አይደለም፡፡

ምክንያቱም ምናልባት ሚስትየዋ ቀድማ ድና ከሆነ በሷ የተነሳ ባሏ ይድን ይሆናል ወይ ደግሞ ምናልባት ባልዬው ቀድሞ ድኖ ከሆነ በሱ የተነሳ ሚስቱም ትድን ይሆናል፡፡

👉እነዚህ ሰዎች ሳይፋቱ በፍቅር እንዲኖሩ የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ላይም በግልፅ ተፅፏል፡፡
1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7 ሙሉውን ብታነቡየተሻለ ትረዱታላችሁ፡፡

ነገ በክፍል አምስት ስለ ሶስተኛው ነጥብ ስለ ፍቅር አንስተንና ለፅሁፉ ማጠቃለያ ሰጥተን ይሄን ተከታታይ ትምህርት እንቋጫለን፡፡


...... ይቀጥላል

#General #single


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ክፍል አምስት

3⃣💑ፍቅር (መዋደድ)፡-

🔹 ሁላችንም እደምናውቀው የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር በሁለት ተቃራኒ ፆታ ያላቸው ሰዎች መካከል ፍቅር (መዋደድ) ሊኖር ይገባል፡፡

🔹ይሄ ፍቅር ግን ዝም ብሎ የእወድሀለሁ እወድሻለሁ ቃላት መነጋገርያ ዓይነት ነገር ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የሆነ የክርስቶስን ዱካ የተከተለ መሆን አለበት፡፡

👉መፅሐፍ ቅዱስ በሴትና በወንድ መካከል ያለውን ፍቅር የሚገልፀው በቤተክርስትያንና በክርስቶስ መካከል ባለው የማይነጥፍና ሕያው የሆነ ፍቅር ነው፡፡

🙏እባካችሁ አሁን ይሄንን ፅሑፍ የምታነቡ ወንድሞቼ እና እሁቶቼ ሆይ በጌታ ፍቅር ልለምናችሁ አሁኑኑ ኤፌሶን ምዕራፍ አምስትን አውጥታችሁ ሙሉውን (በተለይ ከቁጥር 22 ጀምሮ) አንብቡ፤ ለሌላ ቀን ቀጠሮ አትስጡት አሁኑኑ ይሄንን አቁማችሁ ምዕራፉን ማንበብ ጀምሩ ከዛ ወደዚህ ፅሑፍ ትመለሳላችሁ፡፡

🤷‍♂ምዕራፍ አምስትን እንዴት አገኛችሁት?

👉በእርግጠኝነት የባልና ሚስት ፍቅር የቤተክርስቲያንና የክርስቶስ ዓይነት እንደሆነ ተረድታችኋል፡፡

💢ቁጥር 25 እንዲህ ይላል “ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ”

💢እጮኝት ወይም የፍቅር ግንኙነት ማለት ወደ ትዳር የመሄጃ ጥርጊያ መንገድ ነው፡፡

👉ከትዳር እኩል ክብር እና ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ የፍቅር ሞዴላችን ክርስቶስ ነው፡፡

🔵ስለዚህ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን በከፈለው መስዋዕትነት ልክ፤ ባሳየው ቅንነትና ፍቅር ልክ፤ እንዲሁም የእኛም ፍቅር ይሄንን መምሰል አለበት፡፡


📌📌📌📌ማጠቃለያ📌📌📌📌

👉በዕድሜ እና በአካለመጠን (physically)
👉በአእምሮ እና በማስተዋል (mentally)
👉በመንፈሳዊነት (spiritually)

👉በገንዘብ አቅም (financially) …. እና በሌሎችም ዋና ዋና የዕድገት ዓይነቶች ቢያንስ እጮኝነትን ለመጀመር የሚያስችል ዕድገት አድጊያለሁ ብሎ የሚያስብ ሰው የሚመከረው በቶሎ ወደ እጮኝነትና ትዳር መስመር እንዲገባ ነው፡፡

💢 ያለጊዜው በመጀመር በተለያዩ የቅድስና ውድቀቶች ውስጥ ገብተን እግዚአብሔርን፣ ቤተክርስቲያንን ፣ እና ወላጆቻችንን ላለማሳዘን ሲከፋም ደግሞ ከዘላለም ሕይወት መስመር ላለመውጣት ከፈለግን ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቀን ልናደርገው ይገባል፡፡

በዚህ ተከታታይ ትምህርት የተጠቀማችሁ ለወዳጆቻችሁ #ሼር እንድታደርጓቸው አደራ እንላለን ፡፡

👉የዚህን ፅሁፍ አዘጋጅ ቅዱስ ስሜነህን ልናመሰግን እንወዳለን

ተባረኩ

#single #General


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
2025/07/09 21:59:35
Back to Top
HTML Embed Code: