Telegram Web Link
7⃣ ፍቅር የራሱን ጥቅም ብቻ አይፈልግም

📛 በጋብቻ ህይወት ችግርን ከሚፈጥሩ ሁኔታዎች መካከል ትልቁ ሁሉም የራሱን ፍላጎትና ምቾት ለማሟላት ስለ ሚፈልግ ነው፡፡

💯 ሰው በራሱ ላይ ብቻ ካተኮረ አጠገቡ ያለውን ሰው ሲረጋግጥና ሲጫን አይታወቀውም ፡፡

💢 ሁለቱም ወገን የየራሱን ጥቅምና ፍላጎት ለማሟላት ሲታገል ብዙ መጋጨትና መተሻሸት ይፈጠራል ፡፡

💯 ፍቅር በመካከላቸው የፈሰሰ እንደሆነ ግን የሌላው ጥቅም እንጂ የራሳቸው ጥቅም እንዳይታያቸው ይሆናል ፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
8⃣ ፍቅር አይበሳጭም

🛑 ጋብቻንና እጮኝነትን ከሚያደፈርሱ ፀባዮች መካከል አንደኛው ቁጣና ንዴት ነው፡፡

💢 ትዕግስት በማጣት ብቻ ትንሹ ነገር እንደ ትልቅ ነገር ተጋኖ የብዙዎች ቤት ፈርሷል፡፡

አብረው ሲኖሩ የሚያበሳጭ ነገር አይኖርም አይባልም ፡፡

👉 ግን በፍቅር ውስጥ ከኖሩ በንግግር ባይጣጣሙ እንኳን መራራና ጠብ አጫሪዎች አይሆኑም ፡፡ ቁጣን ያበርዳሉ እንጂ አይበሳጩም፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🕗🕘🕚 በቅርብ ቀን 🕜🕝🕞

🛑 በ APPEAL4PURITY
ይጠብቁን

#ሼር ያድርጉ ወዳጆዎን ይጋብዙ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
9⃣ ፍቅር በደልን አይቆጥርም

🤵👰 ባልና ሚስት ወይም ሁለት እጮኛሞች አልፎ አልፎ በመካከላቸው አለመግባባት ሊያጋጥማቸው ይችላል ፡፡

🗝 ያጋጠማቸውን አለመስማማትና በወቅቱ ተነጋግረው ያለፉትን ነገር ሁሉ ተመልሶ መቁጠር ወይንም ቆፍሮ ማውጣት ችግራቸውን ይበልጥ ስለ ሚያባብሰው ሁሉንም በፍቅር ሊያልፉት ይገባል፡፡

👉 በልቡ ውስጥ ቂም አጠራቅሞ በደልን መቁጠርና ለመበቀል መሞከር ከቶ የፍቅር ምልክት አይደለም ፡፡


ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🔟 ፍቅር ክፋት በሆነ ነገር አይደሰትም

⭕️ በፍቅር የተሞላ ሰው በሌላው ላይ ክፉ ነገር ሲደርስበት ያዝናልእንጂ ደስ አይለውም፡፡

👉 ሚስት የማትደግፈውን እርምጃ እንዳይወስድ ባሏን ትመክረዋለች ፡፡

የሰጠችውን ምክር ባለመቀበል አደጋ ቢደርስበት ፤ በፍቅር የተሞላች ሴት ከሆነች "ምክሬን አልሰማ ብለህ ይኸው ይሄ ደረሰብህ ጎሽ ! " አትልም😊 ፡፡

ምክንያቱም ክፋት በሆነ ነገር ደስ ስለማይላት ነው፡፡


ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
#11 ፍቅር እውነት በሆነ ነገር ደስ ይለዋል

👉 ባልና ሚስት ብዙ ጊዜ ጮክ ባለ ድምፅ ሲከራከሩ ይሰማሉ፡፡

ብዙ ጊዜም የጩኸታቸው ምክንያቱ አንደኛው አሸናፊ ሆኖ ሌላኛው ተሸናፊ ለማድረግ ነው፡፡

👉 አንዳንዴም አንደኛው ወገን ትክክል እንዳልሆነ እያወቀም እውነትን ለመግለጥ ሳይሆን ራሱን አሸናፊ ለማድረግ ይከራከራል፡፡

🔑 የፍቅር ሰው የሆነ ሰው እውነት ተሸፋፍኖ ከሚደበቅ ይልቅ በግልጥ ቢወጣ ደስ ይለዋል ፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
#12 ፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል

💯 ፍቅር ከኑሮ ጓደኛው በሚደርስበት መጎዳት ለመታገስ ኃይልን ይሰጣል ፡፡

ምሬትንም ለውጭ ሰው አውጥቶ ላለመናገር አፍን ይዘጋል ፡፡

👉 በዚህም የሚስትንና የባልን ድክመት የውጭ ሰው እንዳያውቅ ፍቅር ይከላከላል፡፡

🔑 ይህ ደግሞ ብዙ ጊዜ ለብዙ ትዳሮች መፍረስ ምክንያት የሆነውን የቤተሰብ ወይም የሌላ የውጭ ሰው ጣልቃ ገብነትን ያስቀራል ፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
13) ፍቅር ሁሉን ያምናል

👉 መጠራጠር በሁለቱ በሚዋደዱ ባልና ሚስት መካከል ችግርን ይፈጥራል፡፡

👉 ፍቅር ስለ ሌላው ሰው በጎነት ያምናል እንጂ ክፉውን በማሰብ አይጠራጠርም፡፡

የኑሮ ጓደኛን ውስጣዊ ምኞትንና ድርጊትን እንዲሁም በጎነትን አምኖ መቀበል በሁለቱ መካከል ያለውን ሕብረት በጣም ያጠናክረዋል፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
14) ፍቅር ሁሉን ተስፋ ያደርጋል

ፍቅር የሌለውን አቋም ተስፋ ያደርጋል እንጂ አይጠራጠርም፡፡

ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች አካባቢውን በሚሞላበት ጊዜ እንኳን አንዱ በአንደኛው ላይ ተስፋ ያደርጋል እንጂ አይጠራጠርም ፡፡


ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
#15 ) ፍቅር በሁሉ ነገር ይጸናል !

👉 መታገስና መፅናት ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ያሳያል፡፡

🔰 ፍቅር ምንም አይነት ፈተናና ችግር ሲያጋጥም በደስታና በሙሉ ትምክህት ተሞልቶ ማለፍ ያስችላል፡፡

💯 ጋብቻን ማፍረስ ወይንም መፋታት በሁሉ ነገር መጽናት የሚለውን የፍቅርን ባህሪና አቋም አይገለፅም ፡፡


አለቀ

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Purity Tube pinned a photo
📛 ቅድመ ጋብቻ ወሲብ 📛

ክፍል አንድ

💢 ይህ ጉዳይ በዘመናችን ካሉ ነቀርሳዎች አንዱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

🔹 ስለ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ በሁለት ተቃራኒ ጎራዎች የተከፈሉ አመለካከቶች አሉ ፡፡

👉 አንደኛው አለም የፈጠረችውና ' ዘመናዊ' ተብሎ የተፈረጀው አመለካከት ሲሆን
👉 ሁለተኛው ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገውና አለም ደግሞ 'ባህላዊ ' የምትለው ነው ፡፡

ዛሬ የመጀመሪያውን አመለካከት እናያለን

1⃣ አለም ምን ትላለች⁉️

🔰 ብዙ አዋቂ የተባሉና የተማሩ የተባሉ ሰዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የቅድመ ጋብቻ ወሲብ አስፈላጊትን ሲያቀነቅኑ ማየት አሁን አሁን እጅግ የተለመደ ነው፡፡

👉 በብዛትም የሚሰጡት ምክንያት ላይ ላዩ ሲታይ እውነት ቢሚመስልም ነገርግን አሰተዋይ ለሆነ ለባለእምሮ ሰው ሞኝነት ነው፡፡

🔸 ምክንያታቸውን እንዲህ ሲሉ ያቀርባሉ

🔴" 21ኛው ክፍለዘመን የስልጣኔ ዘመን ነው ማንም ሰው ደስታውን መቀማት የለበትም፡፡ "

😒 አያችሁ አለም ወሲብን በዋናነት የምታያይዘው ከደስታ ምንጭነት ጋር ነው፡፡

🔸ሌሎች ደግሞ ጥበብ በሚመስል ንግግር እንዲህ ሲሉ ለማሳመን ይጥራሉ

🔴 " ወሲብ የትዳር መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡ ወሲብ በትዳር ውስጥ ጣፋጭ ካልሆነ ያ ትዳር የመቀጠሉ ነገር በጣም አጠራጣሪ ነው ፡፡ ስለዚህ ሁለት ጥንዶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ግዴታ በወሲብ መጣጣማቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ። "

ኦውው አሳማኝ ይመስላል አይደል⁉️
ግን እውነት ነው እንዴ ⁉️

👉 ቅድመ ጋብቻ ወሲብስ የስልጣኔ ምልክት ነው?

👉 በእርግጥስ የወሲብ ዋናው ኢላማ ደስታን መፍጠር ነው?

❗️በፍፁም አይደለም❗️

ታዲያ እውነቱ ምንድነው
መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?

........... ይቀጥላል

#couples
#Singles
#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
record20190808075903.3gpp
8.7 MB
🤷‍♀🤷‍♂How would I know the will of God?
By Doctor Meskerem T. Kifetew
#single

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛ቅድመ ጋብቻ ወሲብ📛

ክፍል ሁለት

ከዚህ ቀደም በቀረበው ክፍል ላይ አለም ስለዚህ ጉዳይ ምን ትላለች የሚለውን አይተናል፡፡

ዛሬ ደግሞ ስለ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ከመፅሀፍቅዱስ አንፃር እናያለን ፡፡

2⃣ መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል

አንዳንዶች እንደሚፈልጉት መፅሀፍ ቅዱሳችን በቀጥታ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ሃጢያት ነው ብሎ ባያስቀምጥም በተለያዩ መንገዶች ስለዚህ ነገር አስነዋሪነት ተናግሯል፡፡

🔰 ኢየሱስ ክርሰቶስ ከዘፍጥረት መፅሀፍ ጠቅሶ የተናገረውን ቃል እንመልከት ፡፡

(ማቴ 19 )
------------
4 እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥

5 አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?

6 ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
_______

አያችሁ ቅደምተከተሉን

⭕️ መጀመሪያ አባትና እናትን መተው
️ቀጥሎ ከሚስት ጋር መተባበር (መተባበር ማለት በሌላ ቋንቋ ጋብቻ ማለት ነው፡፡ )
⭕️ መጨረሻውስ? ወደፊት ሁለት ላይሆኑ አንድ መሆን

🚫 አስተውላችሁ ከሆነ አለም የምትለው መጀመሪያ ከመጋባታቸው በፊት 'መሞካከር'
ቀጥሎ ውጤቱን አይቶ ወይ ወደ ጋብቻ መሄድ አልያም ሌላ አጋር ፍለጋ አሁንም በሃጢያት መዘፈቅ

💯 ይህ መፅሐፍ ቅዱስ ከሚለው ፍፁም ከዚህ የተገላቢጦሽ ነው፡፡

የመፅሐፍ ቅዱስ አቋም ግልፅ ነው
አቋሙም ግልፅ ነው ፡፡

👇
#ወሲብ_ለጋብቻ_ብቻ_የተወሰነ_ነው !!

ደግሞም መፅሐፍ ቅዱስ በሌላ ቦታ ሲናገር እንዲህ ይላል ፡፡

🔰 " ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና።"
(1 ቆሮ 6: 16)

👉 ከዚህ ቃል በግልፅ እንደምንረዳው ሁለት ሰዎች ወሲብ ሲፈፅሙ ደስታቸውን እየፈፀሙ ብቻ ሳይሆን ውህደትንም ጭምር ነው ፡፡

👉 ሁለት በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በቤተክርስቲያን ያልተጋቡ ጥንዶች ወሲብ ሲፈፅሙ ዝሙት እንጂ የፍቅር መገለጫ አይደለም ፡፡

🔑 ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው የክርስቲያን ህይወት መመሪያ የሆነው መፅሀፍቅዱስ የሚያስተምረው ከወሲብ በፊት ጋብቻ መሆን እንዳለበት ነው፡፡


.......... ይቀጥላል

#General
#Singles
#couples

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛 ቅድመ ጋብቻ ወሲብ 📛

ከዚህ ቀደም ባሉት ክፍሎች ስለ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ
1) አለም ምን ትላለች ? እና
2) መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ?

በሚሉ ርዕሶች ተመልክተናል ፡፡

በዛሬው ክፍል ደግሞ ስለ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ መዘዞች እናያለን

🚫 መዘዞቹ ምንድን ናቸው

የቅድመ ጋብቻ ወሲብን መዘዞች በሶስት ከፍለን ለማየት እንሞክራለን

1⃣ ስነ-ልቦናዊ ጠንቅ

👉 ብዙ ጊዜ ያልተጋቡ ጥንዶች ወደ ወሲብ የሚያመሩት ' መጋባታችን እንደሆነ አይቀርም ' ብለው በማሰብ ነው ፡፡

ያልተጋቡ ጥንዶች የቱንም ያህል እንዋደዳለን ብለው ቢያስቡም የሆነ ያህል ደግሞ 'ምናልባት ይህ ሰው አስከ መጨረሻው የህይወት አጋሬ ባይሆንስ !? ' የሚል ጥርጣሬ ወይም ፍራቻ አላቸው ፡፡

ታዲያ ወሲብ ከፈፀሙ በኋላ

👉 አንድ የህይወት አጋራቸው ለማይሆን ሰው ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸውን በመገንዘብ ወደ #ቁጭት ወይም #ድብርት ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል ፡፡

👉 በሌላ በኩል ደግሞ መንፈሳዊ እውቀት ያላቸው ከሆኑ የሰሩት ነገር ሃጢያት እንደሆነና እግዚአብሄርንም እንደበደሉ ስለሚያውቁ #ሃይለኛ_ፀፀት ውስጥ ይወድቃሉ ፡፡

👉 ብዙ ጊዜ ደግሞ ይሄን ድርጊት ከፈፀሙ በኋላ ያን አብሯቸው የተኛውን ሰው እነሱም በማይገባቸው መልኩ ሲጠሉት ይስተዋላል ፡፡

👉 ስለዚህ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ #የስሜት_መዋዠቅንም ያስከትላል ማለት ነው፡፡

2⃣ ማህበራዊ ጠንቅ

🔸 ይህን ድርጊት የሚፈፀሙ ሰዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ስለሚያውቁ ነገሩን የሚፈፅሙት #በመደበቅና ትክሻቸውን ባለማመን ነው ፡፡

በተለይም በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህ ነገር የተለመደ ነው ፡፡

🔴 ሌላው ደግሞ #እርግዝና ነው ፡፡

✔️ አንዲት ሴት ሳታገባ ካረገዘች በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ #ትችትና_ዘለፋ ይደርስባታል ፡፡ ይህም አንገቷን እንድትደፋ ያደርጋታል ፡፡

🔴 ከዚህም የተነሳ አሁን አሁን በጣም አሳሳቢ በሆነ መልኩ ሳያገቡ ያረገዙ ሴቶች አማራጭ አድርገው የሚወስዱት ነገር #ውርጃ ነው ፡፡

📣📣#ውርጃ የህይወት ዘመን #ፀፀትን ያዘለ ጊዜያዊ 'መፍትሄ ' ነው ፡፡

⚫️ ብዙዎች ውርጃን ከፈፀሙ በኋላ በፀፀት ሲሰቃዩ ኖረዋል ፡፡

🔑 ስለዚህ መፍትሄ የተባለውም ነገር ከችግሩ የባሰ ችግር ካመጣ ምኑን መፍተሄ ሆነ መልሱን ለናንተ


.......... ይቀጥላል

#General
#Singles
#couples

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛 ቅድመ ጋብቻ ወሲብ 📛

ክፍል ሶስት

በቀደመው ክፍል ስለ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ጠንቆች ጠቅለል ባለ መልኩ በሶስት ከፍለን ማየት ጀምረን ነበር፡፡

በዛሬው ክፍል የመጨረሻው ግን ደግሞ ትልቁን የቅድመ ጋብቻ ወሲብ መዘዝ እንነጋገራለን ፡፡

3⃣ መንፈሳዊ ጠንቅ

🔶 በዚህ ልምምድ ውስጥ የገቡ ሰዎች ሁሉ በተለይም ክርስቲያኖች አንድ የጋራ ኪሳራ ይገጥማቸዋል ፡፡

👉 ይህም ኪሳራ መንፈሳዊ ኪሳራ ነው ፡፡

📛 አስተውሉ ይህ የአንዳንዶች ብቻ ሳይሆኑ የሁሉም የጋራ ታሪክ ነው፡፡

🔸 ይህን ሃጢያት የፈፀሙ ሰዎች ሃጢያቱን ከፈፀሙበት ቅፅበት ጀምሮ ወደ እግዚአብሄር ፊት መቅረብን ይፈራሉ ፡፡

🔹 መፀለይም ሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብን እርግፍ አድርገው ይተዉታል፡፡

🔴 ምክንያቱም የሰሩት ነገር ሃጢያት እንደሆነ በቅድመ ዕውቀታቸው ስለሚረዱ ወቀሳውን አይችሉትም ፡፡

👉 ስለዚህ መንፈሳቸው ምግብ የሆነለትን ፀሎትንና የእግዚአብሔር ቃል ስለሚያጣ መንፈሳዊ መቀጨጭን ያስከትላል ፡፡

🔑 ይህ ሲሆን ደግሞ ነፍስ ወደ ስጋ መሻት ማድላት ትጀምርና ወደ ቀደመው ሃጢያት ተመልሰው ማለቂያ በሌለው የህይወት ዝቅጠት ውስጥ ይጨመላለቃሉ ፡፡

ይህ መንፈሳዊ ኪሳራ ከዚህ ቀደም ላየነው የስነልቦና ጠንቅ መሰረት ይሆናል ፡፡

👉 ከዚህም በተጨማሪ በቅድመ ጋብቻ ወሲብ ልምምድ ውስጥ የገቡ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ከክርስቲያን ወገኖች ጋር ህብረት ማድረግን ያቆማሉ ፡፡

👉 ይህ ከህብረት መለየት ደግሞ ለሰይጣን ዒላማ ተጋላጭ ስለሚያደርጋቸው ጠንቁ በክፉ መንፈስ ቁጥጥር ስር እስከ መውደቅ ሊያደርሳቸው ይችላል ፡፡

🔴 እነዚህ ሰዎች ምናልባት ወደ ቤተክርስቲያን ቢሄዱ እንኳን ህብረታቸው #የማስመሰል ስለሚሆን ሰላም ከህይወታቸው ይጠፋል ፡፡

🚫💯ከላይ ያየናቸው ጠንቆች እመኑኝ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡

ስለዚህ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ ልምምድ ውስጥ የገቡ ሰዎች ከዚህ ክፉ ወጥመድ እንዴት ማምለጥ ይችላሉ

♨️ለዚህ ጥያቄ መልስ በሚቀጥለው ክፍል ይዘን እንቀርባለን ፡፡

........ ይቀጥላል


#General
#couples
#Singles


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛 ቅድመ ጋብቻ ወሲብ 📛

ክፍል አራት

ዛሬ ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍል በይደር ትተነው በነበረው ጥያቄ ማለትም

⁉️"በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ ልምምድ ውስጥ የገቡ ሰዎች ከዚህ ክፉ ልምምድ እንዴት ማምለጥ ይችላሉ ? "

ለሚለው መልስ እንሰጣለን ፡፡

ምን እናድርግ

👉 ማንም ሰው በተለያየ አጋጣሚ በማወቅም ይሁን በድፍረት ሃጢያትን ቢሰራ ልቦናውን ገዝቶም ወደ እግዚአብሄር መመለስን ቢፈልግ

💯በመጀመሪያ ማድረግ ያለበት ነገር ንሰሃ መግባት ነው፡፡

🔑 ንሰሃ ማለት በአንዳንድ የእምነት ተቋማት እንደሚደረገው የሃጥያት ዝርዝርን ለእግዚአብሔር ማቅረብ #አይደለም! ፡፡


ትክክለኛው የንሰሃ ትርጉም በሰራነው ሃጥያት ከልብ መፀፀት ሲደመር ያን ሃጢያት ዳግመኛ ላለመፈለግ የሚደረግ እርምጃ ነው ፡፡

👇 መፅሃፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይናገራል

" ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።

እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤

እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። " ኢሳ 1 ፦ 18-20

ከዚህ ቃል የምንረዳውን መሰረታዊ ነገር እንመልከት ፡፡

📌1) እንዋቀስ ፦ ይህ ማለት የሰራነው ነገር በእርግጥም በደል እንደሆነ ማወቅ ከዛም ወቀሳን መቀበል ወይም መፀፀት

📌2) ስርየት ፦ እግዚአብሄር በእርግጥም እንደበደልነው ካመንንና ንሰሃም ከገባን እንደገና ንፁህ ሊያደርገን በተደጋጋሚ በቃሉ በኩል ተናግሮናል ፡፡
( 1 ዩሐ 1: 7 )
(ኢሳ 43: 25)

📣 ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ንሰሃ መግባት ማለት ያለምንም የበደል ሪከርድ የአዲስ ምዕራፍ ጅማሬ ማለት ነው ፡፡

👉 ሰው ደግሞ ወደ እግዚአብሄር በተመለሰ ጊዜ ሰይጣን እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፡፡

ይልቁንም በተለያዩ መንገዶች ወደ ቀድሞ ሃጢያት እንዲመለስ አማላይ መስህቦችን ያቀርባል ፡፡

💯 ነገርግን ሰው በራሱ አቅም ይህን ማታለያ ማሸነፍ ላይችል ይችላል ፡፡

👇 ነገርግን መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል

" እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።" ዕብ 4፥16

📌 አያችሁ የሰይጣንን አባባይ ሽንገላ ማሸነፍ የምንችለው በሰው ጥበብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ነው ፡፡

⭕️ ከላይ ካየናቸው ማምለጫ መንገዶች በተጨማሪ ከዚህ ክፉ ልምምድ ለመውጣት ሰው በራሱ ማድረግና መወሰን ያለበት የተወሰኑ ነገሮች አሉ ፡፡

📌1) መፀለይና መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ
ምክንያቱም አንድ ክፉ ነገር ስንጥል ማንሳት ያለብን መሳሪያ እነዚህ ናቸውና፡፡

📌 2) ወደዚህ ልምምድ የሚገፋፋንን ሰው መራቅ ወይም ወደዚህ ነገር ከሚገፋፉ ሁኔታዎች መራቅ ፡፡

ለምሳሌ ከተቃራኒ ፆታ ጓደኛ ጋር ሰው በሌለበት ጭር ያለ ቦታ አለመገናኘትና የመሳሰሉት ፡፡

አለቀ

ይህን መልዕክት ሌሎች እንዲማሩበት #ሼር ያድርጉ

#couples
#Singles
#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💁የኔ አለባበስ የኔ ጉዳይ እንጂ የወንዶች አይደለም፡፡ እግዚአብሄርንም ቅር አያሰኘውም

👆ከላይ ያነበባችሁት የአንዳንድ እህቶች ድምፅ ነው፡፡

👉 ነገርግን በሳይንስም ሆነ በመፅሃፍቅዱስ የተረጋገጠ እውነት ይህ ነው ፡፡

👁 ወንዶች በብዛት ለዝሙት የሚጋለጡት በአይናቸው በሚያዩት ነገር ነው፡፡

🤔ታዲያ ከላይ የተባለውን አይነት አስተሳሰብ እህቶች የሚኖራቸው ለምን ይሆን?

ምክንያታቸው ልዩ ልዩ ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን የብዙዎቹ ምክንያት ከነዚህ ከሁለቱ አይዘልም ፡፡

1⃣ ወንዶች በእነሱ አለባበስ እንደሚሰናከሉ አለማወቃቸው

2⃣ ቢያውቁም ለወንዶች ከመጠንቀቅ ይልቅ ፋሽን ለመከተል መወሰናቸው

🗝 ነገርግን ሴቶች በመገላለጣቸው ምክንያት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ወንዶች ማሰናከላቸው አይቀሬ እሰከሆነ ድረስ ሁለቱም ምክንያቶች #ከተጠያቂነት_አያድኗቸውም ፡፡

👇እስኪ ከታች ያለውን ጥቅስ እንይ

(ሉቃ 17 )
------------
1 ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤

2 ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።

--------------

💯 አየሽ? ለአንዳንዶቹ የቀለለውን ያህል ይህ ጉዳይ በእግዚአብሔር ፊት ቀላል አይደለምና በአግባቡ በመልበስ እና እርቃንን በመሸፈን ወንዶችን በዝሙት እንዳይወድቁ ማገዝ እራስሽንም ከተጠያቂነት ማዳን ያንቺ ሃላፊነት ነው፡፡

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Grand AYS ላይ
Flood is coming ሚለውን እንዴት አየነው።

💯 ጎርፍ ሲመጣ ገበሬ ቦይ ቀዶ ማሳውን እንደሚያፀድቅ የደረቀውንም እንደሚያለመልም

ፅድቅና ቅድስናን ለተጠማ ሁሉ እንዲደርስ ታስቧል::
😊

💯 ጎርፍ በባህሪው ቤተሰብ እንደሚበትን ይታወቃል። ወላጆች ልጆችን ያጣሉ ልጆችም እንደዛው። ዘመድ ይበተናል።


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 10)
----------
35፤ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤

. . .
37፤ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

እንዳለ ጌታችን ኢየሱስ በዚህ መንፈስ ለክርስቶስ ወጣቱ ጨካኝ እንዲሆን ጉባዔው ተሰርቷል።
😍

💯 በኖህ ዘመን በጎርፍ ምድር ስትጠፋ ኖህና መርከቡ ከፍ ብለው እንደተንሳፈፉ በዛው መጠን ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ የተነሱ ሁሉ እንደጠፉ ሁሉ

እግዚአብሔር ማያከብር ነገራችሁን ጎርፉ እንዲበላው። መንፈሳዊ ሀሳባችሁ ሁሉ ከፍ ብሎ ሳታፍሩበት እንዲታይ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።

❤️

💯 ጎርፍ ሲመጣ አሮጌ ነገሮችን እንደሚያሶግድ አዲሱ ብቻ ፀንቶ እንዲቆም ሁሉ

ማለዳ ማለዳ አዲስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን አስቀርቶ ተቀጥላውን ቆሻሻችሁን ምታፀዱበት ነው።

😉
#youth

ፕሮግራሙ ዛሬ ተጀምሯል ነገ ይቀጥላል። ለወጣቱ A4P telegram ይጋብዛል። አንደኛ ፕሮግራም ነው።

ነገ ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ELIANA hotel 8 ሰዓት እንገናኝ።


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🏃‍ ‍ትቶላት ሸሸ

ዮሴፍ የጌታው ሚስት ከኔ ጋር ተኛ ብላ ባስገደደችው ጊዜ

አጠገቧ ቆሞ ስሜቱን ለመግዛት አልሞከረም

ወይም ልብሱን በያዘች ጊዜም ልብሴን ልቀቂ ብሎ አልተጨቃጨቃትም

ለምን

👉 ምክንያቱም ዮሴፍ ወጣት ስለሆነ ስሜቱ አእምሮውንና እውቀቱን አሸንፎ ትክክል ወዳልሆነ ተግባር ወይም ወደ ዝሙት ሊመራው እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡

📌 ስለዚህ መሸሽን እንጂ መጋፈጥን አማራጭ አላደረገም ፡፡

👉 ምንንም ነገር ከመሸሽ አላስቀደመም እርቃንን መሸፈንንም ቢሆን ይህን በማድረጉ ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል በግዞት እስከ መጣል ድረስ

💫 ነገርግን እግዚአብሄር የመጨረሻው ሽልማቱን መከራውንና ነቀፌታውን ሁሉ እስኪረሳ ድረስ ሀገረ ገዢ በማድረግ ካሰው ፡፡

ዛሬ ዛሬ ብዙዎች በጣም ብዙዎች በፍቅር ስምና በውለታ ታስረው ወደ ዝሙት አልጋ ሲጋበዙ እምቢ አሻፈረኝ ብለው ከመሸሽ ይልቅ በሃጢያት ወድቀው እግዚአብሄርን ይበድላሉ ፡፡

ለምን

ምክንያቱም ዛሬ የሚያጡትን ጥቂት ነገር እንጂ ለነገ እግዚአብሄር ያዘጋጀላቸውን መልካም ነገር ማየት ስላልቻሉ ነው ፡፡

🙏 እግዚአብሄር ማስተዋልን ይጨምርልን !

#singles
#couples
#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
2025/07/08 13:04:32
Back to Top
HTML Embed Code: