Telegram Web Link
💜Happy Jumea💜

የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያዳምጥ ሱረቱል ካህፍ📖


«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡
✏️ካህፍ 109

@astentn
Forwarded from 🌹❀"የፍቅር ጥግ"❀🌹 (Hayat)
💜 እዝነት ከፍቅር የበለጠ ይጠነክራል
እዝነት ፍቅርን, ርህራሄን, ይቅር ማለትንና
ውዴታን አቅፋ የያዘች ናት
⇨ ሁላችንም ማፍቀር ስንችል
ግን ጥቂቶቻችን ናቸው 
ልባቸው ውስጥ እዝነት ያላቸው ።

እዝነት እና ፍቅር ካለህ ደሞ እድለኛው ሰው አንተ ነህ!

የሮም ምዕራፍ الروم 30:21

وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም #ፍቅርንና_እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡
@Astentn
💔ከምታየውና ከምትገናኘው
ሰው ጋር ሁሉ ግንኙነትህን አሳምር
በሰዎች ሕይወት ዉስጥ ፈገግታህ ጥለህ እለፍ
ደግመህ ባታገኛቸው እንኳን አንተን ሲያስታዉሱ ሳቅህ ትዝ ይበላቸው እነሱም ያኔ ሳያስቡት ፈግግ ይላሉ ምነው ባላወኩት የሚባል አይነት ሰው አትሁኑ

አደራ ሰዎች በሰዎች ሕይወት ዉስጥ ጠባሳ
ወይም ጥላቻን ጥላችሁ አትለፉ

⇨ የመጨረሻ ግንኙነታችሁ
መች እንደሆነ አታውቁምና::
የልብ ድርቀት ላለብን

@Quran_hadiis
❤️ ሰዎች ቢሳሳቱ ይታረማሉ
ስህተታቸው በህይወት ዘመናቸው
ሁሌም አብሮአቸው እንደሚኖር
አድርገህ አታስብ/አትገምት ።

4any comment @Astentnbot

:¨·.·¨: ❀
 `·. 💜
https://www.tg-me.com/Astentn
የረመዳን ፆም ነገ ይጀምራል።

1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ መጋቢት 24  ይጀምራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አረጋግጧል!

አልሃምዱሊላህ በሰላም ላደረሰን ጌታ♥️

#ረመዳንኩም_ሙባረክ!❤️

@Astentn
Forwarded from 🌹❀"የፍቅር ጥግ"❀🌹 (Hawi)
እንኳን ለ1443ኛው አ. ሂ ፆም ፍቺ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አልሃምዱሊላህ ክብር ምስግና በሰላም አስጀምሮ በሰላም እንድንጨርስ ላደረገን ጌታችን ይሁን! ፆማችንን ሰላታችንን ዱዓችን መልካም ሥራችንን ሁሉ አላህ ይቀበለን! ይቀበላችሁ!
🌺ተቀበለላህ ወሚና ወሚንኩም!🌺

♥️መስጂዶቻችን በተክቢራ ደምቀውዋል::
አስጀምሮ ላስጨረሰን አላህ ምስጋና ይገባው።
አልሐምዱ ሊላህ!

የምወዳችሁ ሕዝበ ሙስሊም ሆይ!
በዋናነትም የጎንደር ከተማ ሙስሊሞች! እንኳን ለዚህች ቀን ደረሳችሁ።

አላህ ሁለመናችሁን ያክም፤ ቶሎ የምታገግሙ ሁኑ።
ዒዱኩም ሰዒድ😘
ኩሉ ዓሚን ወአንቱም ቢኸይር!

ኢድ ሙባረክ ያ ኡመተ ሙሀመድ!🥰

عيد مبارك

@astentn
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ዛሬ ይጀምራሉ::

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

ስለዚህ ቤተሰብ መልካም ሥራ እናብዛ ጌትዬ ድርብርብ እጥፍ አድርጎ ይፅፍልናል

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን። አሚን
23:115 - «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)

23:116 - የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡

23:117 - ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡

23:118 - በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት:- የአረፋን ቀን የፆመን ሰው አላህ የሁለት ዓመት ወንጀሉን ይምርለታል:: ያለፈዉን አንድ ዓመት ወንጀል እና ወደፊት የሚመጣዉን የአንድ ዓመት ወንጀል::

ነገ ማለትም ዕለተ ጁምአ 9ነኛው የዙል ጂጃህ ቀን ነው አረፋ በመባልም ይጠራል::

ኢንሻ አላህ ነገ ሁላችንም እንፁም ያጀማዐ ለቀጣዩ ዓመት እንድርስ አንድረስ ምናውቀው ነገር የለም::
እየፆማችሁ ነው?

አዎ♥️

አይ 😞

ሁለት ምርጥ ቀኖች አንድ ላይ ዉለዋል ጁምዐ + አረፋ💞

የዱዐ ቀን ነው ወንድሜ ማግባት ትፈልጋለህ?ሥራ የለህም የጤና ችግር አለ? እግዲያዉስ ዛሬ ጌታችን ከምንግዜውም በላይ ዱዐን ሚቀበልበት ቀን ነው በርታ እኔና አንቺስ እህቴ ስንት ስንት ሃጃዎች አሉብን አላህን እንጠይቅ:: ሁላችንም ብዙ ችግሮች አሉብን መፍትሄው ዱዐ ነው ውዶች በዱዐ እንጠክር:: አላህ በድብቅም በግልፅም የጠየቅነውን ይስጠን አሚን::
♥️ልብን እንድታፈቅር አደርጎ
የፈጠራት ጌታ ይመስገን♥️

ያፈቀሩትን ማግባት መታደል ነው
ያገቡትን ማፍቀር ደሞ ይበልጥ መታደል ነው::

@Astentn
መራራ እውነታዎች አንብቡት ውዶቼ😘

ምንም ነገር ለዘላም አይቆይም ፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች ስራህ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ

ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ

ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም ፡፡ 20% ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80% ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል

ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ

ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ

የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደ ኋላ አይልም ።

98 % ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም 2 % ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም ፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!

የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም ፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ

ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ

ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡

አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ

ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡

ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም ፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ ፡፡ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡

የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል ፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም ፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ

ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት

ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡

ህይወት እኩል አይደለችም ፡፡ በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት ፡፡
🌹
@Eslamik_Tube||ኢስላሚክ Tube
2024/04/26 06:56:59
Back to Top
HTML Embed Code: