Telegram Web Link
😍😍የታላቁ የረመዳን ፆም ማክሰኞ 1 ብሎ እንደሚጀመር ተገለፀ!
እንኳን አደረሰን አላህ ረመዳንን ከሚፆሙ ፆመውም ከሚጠቀሙት ዉስጥ ያድርገን አሚን!❤️

ረመዳንን ስንፆም የረመዳን ፆምን መፆም የሃይማኖታችን አንዱ መሰረት መሆኑን እና ምንዳዉን ደሞ ከአላህ በመከጀል መሆን አለበት::
ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት ረመዳንን በኢማን እና በኢህቲሳብ (ምንዳዉን ከአላህ ፈልጎ) የፆመ ሰው አላህ ያለፈዉን ኃጥያቱን ሁሉ ይቅር ይለዋል::❤️❤️
አላህ ረመዳንን በኢማን በኢህቲሳብ ከሚፆሙት ዉስጥ ያድርገን❤️❤️አሚን
🌼ረመዳን ሙባረክ🌼
3:90
إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَمَاتُوا وَهُمْ كُفَّارٌ فَلَن يُقْبَلَ مِنْ أَحَدِهِم مِّلْءُ الْأَرْضِ ذَهَبًا وَلَوِ افْتَدَىٰ بِهِ ۗ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ وَمَا لَهُم مِّن نَّاصِرِينَ

እነዚያ የካዱና እነርሱም በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ ከእነሱ ከአንዳቸው በምድር ሙሉ የኾነ ወርቅ (ቢኖረውና) በርሱ ቢበዥበትም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይን አያገኝም፡፡ እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አላቸው፡፡ ለነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

99:7

فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

በዚህ ምድር ላይ የብናኝ ክብድት ያላት መልካም ነገር ብትሰራ አላህ ይቀበልሃል በ10 አባዝቶ ለፈለገው እስከ 700 መቶም ከዛ በላይም ያባዛል ነገር ግን ዕድሜህን እዚች ምድር ላይ ባልባሌ ነገር በክህደት ላይ አሳልፈህ ከትንሣዬ ቡሃላ እውነቱ ሁሉ ሲገለጥልህ ከአላህ ቅጣት ለማምለጥ ምድር ሙሉ ወርቅ እንኳን ቢኖርህ ተቀባይነትም ማምለጫም የለህም::
በሕይወት እያለህ በዉዴታ ወደ አላህ ተመለስ እሱ ፀፀትን ተቀብያለሁ ሩህሩህ አዛኝ ነውና
27:11
إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًا بَعْدَ سُوءٍ فَإِنِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

«ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ አዛኝ ነኝ፡፡
4:110

وَمَن يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمْ نَفْسَهُ ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رَّحِيمًا

መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይም ነፍሱን የሚበድል ከዚያም (ተጸጽቶ) አላህን ምሕረት የሚለምን አላህን መሓሪ አዛኝ ኾኖ ያገኘዋል፡፡
5:39
فَمَن تَابَ مِن بَعْدِ ظُلْمِهِ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ اللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

ከበደሉም በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከእርሱ ይቀበለዋል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ፆም የለ ሰላት የምግብ አድማ ብቻ ነው::
ሰላት ከእስልምና መሠረቶች ዉስጥ 2ኛው ሲሆን ፆም ደሞ 4ኛ ነው::

ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት በኛና በሌሎች እምነት መካከል ያለው መለያ ሰላት ነው ሰላትን የተወ በርግጥ ክዷል::
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
20:132
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ

ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአብራሃም ምዕራፍ 14:40-41
الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

«ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡

رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ

«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
4:157 - «እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን (ኢየሱስን) ገደልን»በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ #አልገደሉትም #አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በኢየሱስ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም #አልገደሉትም፡፡
4:158 - ይልቁንስ አላህ (ኢየሱስን) ወደርሱ አነሳው፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡

@Astentn
ነብዩ ሙሀመድ ﷺ ለይለቱል ቀድርን ከረመዳን መጨረሻው አስርት ቀናቶች ዉስጥ በጎዶሎዎቹ(21,23,25,27,29) ተጠባበቁ ብለዋል።ግን ይሄ 27 አጀብ አስብሎኛል።

97:1 - እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡

97:2 - መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?

97:3 - መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡

97:4 - በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ(ገብርኤል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡

97:5 - እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡

ከ 1000 ወር በላጭ የሆነቺዉን ለይለቱል ቀድር(የመወሰኛየቱ ሌሊትን) አላህ ይወፍቀን❤️ አሚን አላሁመ አሚን❤️
የረመዳን 27ተኛ ለሊት
★★★★★★★★★★★
በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ83 ዓመት ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ ሰሀባዎች ውስጥ፥ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም ለይለተል-ቀድር የረመዳን 27ተኛ ለሊት ላይ ልትሆን ትችላለች ይሉ ነበር!

ይህች ለሊትም ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ላይ ናትና እንበራታ!
እናታችን አይሻ ነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ አለይሂ ሰላም እንዲህ ስትል ጠየቀች ለይለተል ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓ ላድርግ ስትላቸው አላሁመ ኢነከ አፉዉን ቱህቡል አፍወ ፈዐፉ አኒ (አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ)❤️
የዘካ ግዴታዎን በጊዜው ይወጡ


◉ ዘካ መስጠት ውድና ዕንቁ የሆነ መንፈሳዊ ከንዝና ተግባር ነዉ. ዘካን በአግባቡ መስጠት ማህበራዊ ቀውስን ለመቅረፍና ድህነትን ለማንኮታኮት ታላቅ መፍትሔ ይሆናል።

_ዘካ ማውጣት ከእስልምና ማዕዘናት ሦስተኛው ማዕዘን ሲሆን ይህም የዘካን አስፈላጊነትና ግዴታነት ለማሳየት በቂ ነው፡፡ ለዚህም የሚከተለውን የአላህን (ሱ.ወ) ቁርኣናዊ አንቀፅ መጥቀሱ ማስረጃ ይሆናል፡፡

وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَارْكَعُوا مَعَ الرَّاكِعِينَ

ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም (ግዴታ ምጽዋትን) ስጡ፡፡ (ለጌታችሁ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ፡፡


ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ኢስላም የተመሠረተባቸውን ማዕዘናት ሲያስረዱ እንደሚከተለው ብለዋል፡

" بني الإسلام على خمس: شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمدا رسول الله وإقام الصلاة وإيتاء الزكاة" وحج البيت وصوم رمضان " متفق عليها


"ኢስላም በአምስት መሰረቶች ላይ ተገንብቷል። ከአላህ በስተቀር በእውነት ሊገዙት የሚገባው እውነተኛው አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ሰላትን አዘውትረው መስገድ፤ ዘካትን መስጠት፤ የረመዷንን ወር መም፤ ሐጅ ማድረግ የአላህን ቤት መጎብኘት/ ናቸው።

አላህ (ሱብሃነሁ.ወተዓላ) ዘካን ግዴታ ካደረገባቸው ምክንያቶች መካከል ጥቆቶቹ፡

► ዘካ የሚወጣበትን ሀብት ለማጥራትና ለማፋፋት፣

► ድሆችንና ሚስኪኖችን ለመርዳትና ለማገዝ፣
➢ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ፣

► ንጹሕና ሠላማዊ የሆነና የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ወዘተ በመሳሰሉት ምክንያቶችና አላማዎች ሃብትና ንብረት ባላቸው ሰዎች ላይ ዘካ መስጠት ግዴታ ተደርጓል።

አላህም (ሱ.ወ) ይህንኑ አስመልክቶ እንደሚከተለው ተናግሯል፡፡

خُذْ مِنْ أَمْوَالِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم بِهَا وَصَلِّ عَلَيْهِمْ ۖ إِنَّ صَلَاتَكَ سَكَنٌ لَّهُمْ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡ ለነሱም ጸልይላቸው፡፡ ጸሎትህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡



وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ

በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡


◉ አላህ (ሱ.ወ) ሁሉን አዋቂ ነውና በህብረተሰቡ ውስጥ ችግረኛና ደካማ የሆኑ ሰዎች መኖራቸውን ያውቃል። የሰው ልጆች ሁሉ ደግሞ እኩል በሆነ ሁኔታና መልኩ ሃብትና ንብረት አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህም ይህንን ክፍተት ለመሙላት፣ የድሆችን ችግር ለመቅረፍ፣ በሰዎች መካከል ሰላምና ፍቅርን ለማረጋገጥ በሃብታሞች ላይ ዘካ /ምፅዋት/ መስጠት በኢስላም ግዴታ ሆኖ ተደንግጓል።


○ሃብታሞች መደብ ፈጥረውና ተለይተው እራሳቸውን ከሌላው - ገድበው፣ ሃብታቸውን ቆልለው ለድሆች ምንም ነገር ሳይረዱና ሳይሰጡ ቢኖሩ አብዛኞቹ የህብረተሰብ ክፍሎች ይጎዱ ነበር፡፡ ማህበራዊ ቀውስም ይፈጠር ነበር፡፡ ሃብታሞቹም ቢሆኑ ሰላማቸው ይደፈርስ ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን ኢስላም የዘካን ሥርዓት ዘረጋ፡፡


◉ኢስላም በዘረጋው ሥርዓት መሠረት ዓለም ብትመራበት ኖሮ ይህ _ ሁሉ ዛሬ የሚስተዋለው ሰብአዊና መንፈሳዊ ቀውስ ባልተፈጠረ ነበር፡፡


_ አላህ /ሱ.ወ/ ለርስዎ ሃብትን በጥበቡ ለግልዎታል፡፡ እርስዎም ትዕዛዙን ለመፈፀም ቃል ኪዳን ፈፅመዋል፡፡ በመሆኑም ከሃብትዎ | ያልሰጡ ከሆነ አሁኑኑ በመስጠት ግዴታዎን ይወጡ! ጥቅሙም ለእርስዎ ነውና። እንዲሁም እርስዎ ውስጣዊ ሰላምንና ደስታን ለማግኝ ት ይፈልጋሉ፡፡ ነገ አላህ /ሱ.ወ/ ዘንድ ቀርበውም መልካም መስተንግዶውን ይመኛሉ፡፡ ታዲያ ይህ ይሳካ ዘንድ የዘካን ግዴታዎን በታማኝነትና በደስታ መስጠት ይጠበቅብዎታል፤ ጥቅሙም ለእርስዎ ነውና። (አላህ /ሱ.ወ/ ይፍቅዎት)

@Quran_Hadiis
@Quran_Hadiis
@abuhyder
@Wahidcom
@Islamawi_Metatf

6:54 «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው» በላቸው፡፡
"ቤተሰቤን ከማስጨንቅ ብሞት ይሻለኛል😭"
#አንዋር_ሁሴን
"እባካችሁን የሆነ ነገር አድርጉልን😭😭😭"
#ኢፍቱ_ሁሴን(እህት)
ከጅማ የዩንቨርስቲ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ኢዲስ አበባ የመጣው ወንድማችን #አንዋር _ሁሴንን ለመጠየቅ ትላንት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነበርን!!

የ22አመቱ ወጣት ጅማ ዩኒቨርስቲ የ1ኛ አመት ተማሪ
ሲሆን ለ 3አመታት የአጥንት መቅኔ ደም አለማሞረት ሲሰቃይ ቆይቶዋል😭አሁን ደግሞ የአጥንት መቅኔው 100% ማምረት አቁሞ በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ እየተሰቃየ ነው😭

እጁ በጣም ቆስሏል😭እግሩም መራመድ አቁሟል😭

የጥቁርአንበሳ የህክምናቦርድም አንዋር በአጭርጊዜ ውስጥ ወደ ውጪ ሄዶ መታከም እንዳለበት ፅፈዋል!!ለህክምናውም #2,500,000ብር ተጠይቋል😭

ምንም አቅም የሌላቸው ቤተሰቡ ለልጃቸው መድረስ ባለመቻላቸው እያለቀሱ ህመሙ ላይ ሌላ ጭንቀት ሆነውበታል😭እባካችሁን #እናድነው🙏 #እንርዳው!

ምንም ማድረግ ካልቻልን #በአላህ_በእግዚአብሔር #SHARE_ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስለት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-
#1000337570918_አንዋር_ሁሴን
ስልክ:-
0939504654_አንዋር_ሁሴን
0917322524_ኢፍቱ ሁሴን
0917001162_ዮናስ ስለሺ
0927708670_ሁሴን አባድንቁ
እረኛው በጎችን ይዞ ወደ ማደሪያቸው አስገብቶ በሮችን ሁሉ በሚገባ ዘጋው።
የተራቡ ቀበሮዎች በጎቹን ሊበሉ ሲመጡ በሮች ሁሉ በሚገባ ተዘግተው አገኙት።
በሮችን አልፈው መግባትን ተስፋ የቆረጡት ቀበሮዎችም፤ በጎቹን ከበሮች
ቁጥጥር ውጭ ለማድረግ ሴራቸውን ይጠነስሱ ጀመር።
በመጨረሻም ቀበሮዎቹ (የበጎች ነፃነት ይከበር) የሚል መፍክር ይዘው የበጎቹን
ማደርያ ዙርያ ለመዞር ወሰኑ።
በጎችም ለነሱ ነፃነት እንዲከበር ቀበሮዎች ትልቅ አብዮት እንዳቋቋሙ ሲሰሙ
ልባቸው ወደ ቀበሮዎቹ ይሸፍት ጀመር።
የነፃነት አብዮቱን ለመቀላቀል በርካታ በጎችም የግቢያቸውን አጥር በቀንዶቻቸው
ይነቀንቁ ጀመር። ከረጅም ግዜ ረብሻ እና ትርምስ በኋላ በጎቹ ማደሪያቸውን
አፍርሰው አብዮቱን ለመቀላቀል ወደ ጫካዎች ፈረጠጡ።
ቀበሮዎችም ከበጎቹ ኋላ ይሮጡ ጀመር፤ እረኛውም ከኋላ ኋላ እየሮጠ አንዴ
በድምፁ አንዴ በብትሩ ሊመልሳቸው ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም።
አብዮታዊ ሩጫው ቀጥሏል፤ በጎች ከፊት ቀበሮዎች ከኋላ....ብዙም ሳይርቁ
ቀበሮዎች እና በጎች ያለ እረኛ ያለ ከልካይ ሰፊ በረሃ ላይ ተፋጠጡ።
ያች ቀን የነፃነት አብዮትን ፍለጋ ለወጡት በጎች ጨለማ ስትሆንባቸው፤ ሴራን
ላሴሩት ቀበሮዎች ግን የደስታ እና የፈንጠዝያ ቀን ነበረች።
በማግስቱ እረኛው ተነስቶ ወደ አብዮት የወጡትን በጎች ፍለጋ ወደ በረሃው
ሲያቀና፤ የነፃነት መገለጫ የሆኑ ቀበሮዎች ነፃነትን ፍለጋ የወጡትን በጎች
ስጋዎቻቸውን በልተው፣ አጥንቶቻቸውን በመሰባበር ሜዳው ላይ በትነዋቸው
አገኘው።
_____________________________
ድሮ የሰማናት ተረት ናት አይደል!!!
ግን በአለማችን የሚገኙ የሴቶች የነፃነት አብዮትን እና ቀበሮዎችን ምን ያህል
እንደሚመሳሰሉ አስተውላችሁታል!!!?
የሴቶች ነፃነት አብዮት የሙስሊም ቁጥብ፣ ጨዋ እና እንቁ ሴቶችን በቀላሉ
ሊያገኝ አይችልም።
ምክንያቱም፦ አባቶቻቸው ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል።
ምክንያቱም፦ቤታቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘዋል።
ምክንያቱም፦ ሂጃብ አድርገዋል።
ለዝያም ነው የሰው ቀበሮዎች <የሴቶች ነፃነት> የሚል መፈክር ይዘው
ሚስተዋሉት። አላማው ግን <የሴቶች ነፃነት> ሳይሆን <ወደ ሴቶች መድረሻ
ነፃነት> ነው።

©Al kewser
https://www.tg-me.com/Quran_Hadiis
የኦቶማን ስረወ መንግስት የትዳር ህጎች
ፈገግ በሉ ሡና ነው

1፦ በራስ ፍቃድ ትዳር የመያዝ መብት ከ18-25 ነው። ከ25 እድሜ በላይ የሆነ ሰው አፍንጫው ተይዞ ትዳሩን ይይዛታል።

2፦ ከ25 እድሜ በላይ ሁኖት በበሽታ አመካኝቶ ትዳር ያልያዘ ጎረምሳ ካለ፤ የህክምና ምርመራ ይደረግለታል። በሽታው የመዳን ተስፋ ካለው እስኪድን እርዳታ ይደረግለታል፤ ካልዳነ ዐፉ ይባላል።

3፦ጎረምሳው 25 እድሜ ሞልቶት ትዳር አልይዝም ብሎ ቢገግም፤ ከቀን ገቢው 1/4 ለመንግስት ገቢ ያደርጋል። ይሄ ቅጣት ተሰብስቦ ትዳር ፈልገው ብር ለሌላቸው ወጣቶች ጀባ ይባላል።

4፦እድሜው 25 ሞልቶ ያልተዘወጀ ወጣት በፍፁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር አይፈቀድለትም። የሚሰራበት የመንግስት መስሪያ ቤት ካለም 25 ሞልቶት ካልተዘወጀ ይባረራል።

5፦ እድሜው 50 ሞልቶት ሁለት ሚስት የማግባት economically ም Physically ም አቅም እያለው 2 ሚስት ካላገባ፤ የተለያዩ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ድርጅቶች ላይ እንዲሳተፍ ይገደዳል። አልያም ከ1-3 የቲሞችን እንዲንከባከብ ይታደላል።

6፦ ከ 18-25 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁኖ ምንም ሳይኖረው የሚዘወጅ ማንኛውም ወጣት ከሀገሪቱ የመሬት ባንክ 900 ካሬ ይሰጠዋል።

7፦ ወጣቱ የንግድ ወይም የሙያ ልምድ ካለው ሰርቶ እንዲለወጥ የብድር አገልግሎት ይመቻችለታል።

8፦ ጎረምሳው ለወላጆቹ የሚካድም ሌላ አካል በሌለበት ሁኔታ ትዳር ቢይዝ ለግዳጅ የመዝመት ድንጋጌው ውድቅ ይሆንለታል።

9፦ ጎረምሳው ከ18-25 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁኖ 3 ልጆችን ቢወልድ በሽልማት መልኩ ልጆቹ አዳሪ ትምህርት ቤት በነፃ እንዲማሩ ይፈቀዳል።

10፦ ተማሪ ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ትምህርቱን በመከታተል ባለበት ሁኔታ ላይ ተገዶ ትዳር እንዲይዝ አይገደድም። (ምስኪን)

11፦ ሰውዬው በስራ ጉዳይ ከሀገር ለተወሰኑ አመታት ሊወጣ ካሰበ ሚስቱን ይዟት እንዲሄድ ይገደዳል፤ አልያም አሳማኝ ምክንያት ያቀርባል።

#የታደለ_ትውልድ_ነበር☺️ credit ሰፍዋን አህመዲን
ለምን በሙስሊሞች ላይ በረታን❗️
የማስተማር ጥበብን ዘነጋን
ከወቅታዊ ሁኔታችን ጋር የተያያዘ


የመጀመርያ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሳለው በእንግድነት እየመጣ የሚያስተምረን መምህር ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የማካካሻ ትምህርት እየሰጠን ይገኛል የመግሪብ ሰላት ከመድረሱ በፊት ይጨርሳል ብለን ብንጠብቅም ማስተማሩን ቀጠለ የመግሪብ አዛን ሲያስተጋባም ብርሃን በጨለማ ቦታዋን እየተነጠቀች ነበርና ከዚህ በኋላ ብዙ አይቆይም በሚል እሳቤ የመግሪብ ሰላትን አስፈቅደን ወጥተን ለመስገድ እያመነታን ነው።በመሃል ግን አንዲት ሴት ልጅ እጇን አውጥታ ይቅርታ መምህር የሰላት ሰዐት እያለፍብን ስለሆነ 5 ደቂቃ ፍቀድልን ሰግደን እንመለስ ስትል ጠየቀች መምህሩ ደነገጠ ምላሽ ሳይሰጣት ለጥቂት ሰከንዶች አትኩሮ ተመለከታት።ተማሪውም ተገርሞ አትኩሮ እየተመለከታት ነው። ሙስሊም ነሽ? ሲል ጠየቀ መምህሩ በአግራሞት ይህ ጥያቄ የመምህሩ ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው።ልጅቷ ስሟ የሙስሊም ቢሆንም ገፅታዋ ግን የሙስሊም ሴት አይመስልም።ሂጃብ ለብሳ አታውቅም።ሙስሊምነቷ ያጠራጥር ነበር። ቆንጆ ስለሆነች ነው መሰለኝ መጥፎ አመለካከት ነበር ለሷ ያለን ዝምተኝነቷ እና ከማንም ተማሪ ጋር አለመቀላቀሏን እንደ አስመሳይነት ነበር የምንቆጥረው።አረ እንደውም ምናለ ስሟን በቀየረችው እያልን በተደጋጋሚ በመጥፎ እናነሳት ነበር።ሙስሊም ነሽ ሲል መምህሩ ጥያቄውን ደገመው ሙስሊም ባልሆን ለሰላት አስፈቅድህ ነበር ስትል መለሰችለት። ጥሩ መስገድ ምትፈልጉ ወጥታችሁ መስገድ ትችላላችሁ አለ። በክፍል ውስጥ ካለው።6ወንድ 5ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል 3ወንዶች እና ይህችው ለሰላት ያስፈቀደችው እንስት ብቻ ለመስገድ ወጣን ከመማርያው ህንፃ ጀርባ በሚገኝ ሳር ውስጥ ለመስገድ ገባን።ይህች ልጅም ከቦርሳዋ ውስጥ አባያና ሂጃብ አውጥታ ለበሰች።ትንሽዬ ተጣጣፊ መስገጃዋን አንጥፋ ከእኛ ኋላ ፈንጠር ብላ መስገድ ጀመረች ኢቃም ብለን መስገድ ብንጀምርም ሃሳቤ ግን ልጅቷ ጋር ነው። እንዴት ገፅታዋን ብቻ አይተን እንደዛ በመጥፎ ሳልናት!ለምንስ ቀርበን ልናናግራት አልሞከርንም።ከእኛ ተሽላ የሰላት ሰዓት አሳስቧት ማስፈቀዷ ለምን ግርምት ፈጠረብን እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች በአእምሮዬ እየተመላለሱ ሰላቱን ሰግደን ጨርሰን ወደ ክላስ ተመለስን ክላስ ገብቼ ትምህርቱን ከመከታተል ይልቅ ሃሳቤ ልጅቷ ጋር ነበር ብዙ ሳይቆይ መምህሩ ትምህርቱን ጨርሶ አሰናበተን።ከኋላ ስለነበር የምቀመጠው ልጅቷ ቀድማኝ ስለወጣች እየሮጥኩ ተከተልኩና ስሟን ጠርቼ አስቆምኳት።እህት አለም በአላህ አውፍ በይኝ ስላንቺ በጣም መጥፎ ነገር አውርቻለው።ድንበር አልፌብሻለው አልኳት። መሬት መሬቱን እየተመለከተች በለመጣ ፈገግ አለችና አንተ ብቻ አይደለህም ይህን አይነት አመለካከት ያለህ ሙስሊሙ በሙሉ እንዳንተ ነው።አልያም ከአንተ በከፋ ነው የሚያስበኝ አለች።ጥቂት ዝም ካለች በኋላ ሳግ እየተናነቃት ይገርመሃል አያቶቼ ስለ እስልምናፕምንም አያቁም እኔም የተማርኩት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነው። የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በሙሉ ሙስሊም ያልሆኑ ናቸው በእርግጥ አካባብያችን ሙስሊም ስለሚበዛ ሂጃብ ሲለብሱ እመለከት ስለነበር የሙስሊሞች የማንነት መገለጫ ነው ብዬ ሳስብ መልበስ ጀምሬ ነበር።ቤተሰቦቼ ግን አልፈቀዱም የእራሴ ክላስ ስላለኝ እዛ ገብቼ በመቆላለፍ ሰላቴን እሰግድ ነበር።ወደ ዩንቨርስቲ ስገባ የተወሰነ ነፃነቴን ስለማገኝ በተቻለ መልኩ ስለ እምነቴ ለማወቅ እና ለመተግበር ምኞቱ እና ፍላጎቱ ነበረኝ።ግና ዶርሜ ውስጥ የነበሩት ሙስሊም እህቶቼ ጥሩ አልተቀበሉኝም የጁምዓ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ ሳቀና ሰላቱ ምን ያደርግልሻል።ወይ ጥቅልል ብሎ መግባት ወይ መውጣት ሲሉ ተናገሩኝ የሚያቀርበኝ ጠፋ የሚያስተምረኝ ከጎኔ ሆኖ የሚያበረታታኝ አጣው።በተቃራኒው የሚሰድበኝና የሚተቸኝ ግን በርካታ ነው። ኢስላምን የማያውቅ ቤት ውስጥ እንደማደጌ በአንድ ጀንበር ውስጥ ለውጥ ማምጣት ለኔ ከባድ ነው።ይሁን ቢባል እራሱ ስለ ለውጥ ለኔ ቀርቦ የሚያስረዳኝ የለም
በጣም የሚገርመው ሰላታቸውን በትክክል የማይሰግዱ በየፓርቲ ቤቱ በሙዚቃ የሚጨፍሩና በየበግ ተራው ከወንድ ጋር ሲላፉ የሚያመሹ ሁሉ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከእኔ የተሻሉ እንደሆኑ በማሰብ በንቀት አይን ይመለከቱኝ ነበር።ሂጃብ መልበስ በጣም ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ መላበስ ግን ከባድ ነው።ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃባቸውን ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ከቤተሰቤ ስርቅ ሂጃቤን ስለመልበስ ነበር የማስበው ግና...አለችና በረጅሙ ተነፈሰች...

እቴዋ ሰልመሽ ያደርሽው ሙእሚኗ የተከበርሽው
ሰብአዊ ክብርሽን አጥተሽ ደም እንባ ያንቆረቆሽው
ስልጡን ዘመን ላይ ተፈጥረሽ እግር
ስር የተረገጥሽው
የኑሮሽ አሻራ በዛ ላይፋቅ ወይ ላይነሳ
ለፆታሽ መብት ተነፍጎ
ለጥቅምሽ ነጋ ደግድጎ
ለጎዳሽ ማረግ ፈልጎ
ላትሰለጥኚ ተጠልፈሽ በሰለጠነ ተልፈሽ
ሃፍረት ማረግሽን ተዘርፈሽ መብትሽ
መብትሽ ለቆጨሽ ተገድፈሽ

ለምታሰሚው ኡኡታ እርቃን አልሆንም ስሞታ
አታድሙኝ ላልሽው አታጥቁኝ በእውቀት አክብሩኝ አትናቁኝ

የሃዋ ዘር ነኝ እወቁኝ!!!


ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠች ሄደች።


....ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠችኝ ሄደች።

ለደቂቃዎች በድንዛዜ ውስጥ ቆሜ ሳስብ ሳስብ እራሴን ነቅንቄ ወደ ዶርሜ መመለስ ጀመርኩ

"ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃብ ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ሂጃብን ለመልበስ ከቤተሰቤ መራቅን ነበር የማስበው ሂጃብ መልበስ ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ ግን መላበስ ግን ከባድ ነው።"

እነዚህ ቃላቶችን ደጋግሜ እያሰብኩ ዶርም ደረስኩ ጓደኞቼ ምንም አላሉም ምን ሆንክ እያሉ ሲጮሁብኝ ነበር ከአይኖቼ እንባ እየፈሰሱ እንደነበር ያወቅኩት።ዛሬ ይሃንን ትዝታዬን የቀሰቀሰው ክስተት ደግሞ ይህ ነበር።የፌስቡክ ኖትፊኬሽኔን ስመለከት በርካታ የፌስቡክ ጓደኞቼ ኮሜንት የሰጡበትን ፖስት አገኘው ምን ይሆን ብዬ ወደፔጁ ጎራ አልኩ

#ሃሊማ #አብዱረህማን የምትባል ዘፋኝ ፔጅ ነው።ኮሜንቶቹን ማንበብ ጀመርኩ ሙስሊሞች የሰጡት ኮሜንት በአጠቃላይ እጅግ የሚያሳዝን ነው።
ለምን አንደኛውን አትከፍሪም?ለምን ስምሽን አትቀይሪም?ወደ እሳት ተጣሪ!የሰይጣን ተላላኪ!
መሰል እጅግ ከባባድ ኮሜንቶችና ሌሎች አስቀያሚ ስድቦች ሞልተውታል።

አስደነገጠኝ በተለይም ልጅቷ ለአንዳንድ ኮሜንቶች የሰጠችው ምላሽን ሳነብ የበለጠ ደነገጥኩ።አሁን ይቺ ልጅ ብትከፍር ተጠያቂው ማነው⁉️
የሚገርመው ደግሞ በኮሜንት ውስጥ አንድም ሊያስተምራት የሞከረ የለም።አረ እንደውም የአንዳንድ ተሳዳቢዎችን አካውንት ስመለከት የሂጃብ ትርጉም የሌለው ጨርቅ እራሳቸው ላይ ጣል አድርገው በሜክአፕ ሌላ ፊት ደርበው ጭብጨባ ፍለጋ በርካታ ፎቶዎችን ለጥፈዋል። እጅግ በጣም የሚገርመው የበርካታ ዘፋኞችና የዘፈን ፔጆችን ሳይቀር ላይክ አድርገዋል።👇👇👇
እስልምና ኢቅረዕ በሚል አንቀፅ የሚጀምር እምነት ነው። መጀመርያ መማር ከዚያ ልሎችን ማስተማርን የእምነቱ አስኳል ተጣሪዎች እንጂ ፈራጆች እንዳንሆን ያዙናል።ወደ ኢስላም በመልካም ግሳፄና በጥበብ በመጣራት ሌሎች ወደ ኢስላም እንዲቀርቡ ማድረግ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ሆኖ ሳለ እኛ ግን ሰዎች ላይ በመፍረድ በመስደብና በማሸማቀቅ እያራቅናቸው እንገኛለን ለመሆኑ ግን እኛ ከእነሱ እንደምንሻል በምን ይሆን ያረጋገጥነው!

የአላህ ቃልስ
"ነፍሶቻችሁን አታጥራሩ ከእናንተ ውስጥ አላህን ፈሪ ማን እንደሆነ እርሱ ብቻ ነው የሚያውቀው"
አይደል እንዴ የሚለው!

 یَا أَیُّهَا الَّذِینَ آمَنُوا لا یَسْخَرْ قَومٌ مِنْ قَوْمٍ عَسَى أَنْ یَکُونُوا خَیْرًا مِنْهُمْ وَلا نِسَاءٌ مِنْ نِسَاءٍ عَسَى أَنْ یَکُنَّ خَیْرًا مِنْهُنَّ وَلا تَلْمِزُوا أَنْفُسَکُمْ وَلا تَنَابَزُوا بِالألْقَابِ بِئْسَ الاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الإیمَانِ وَمَنْ لَمْ یَتُبْ فَأُولَئِکَ هُمُ الظَّالِمُونَ﴿١١﴾


"49:11 - እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡"
ሱረቱል ሁጁራት አንቀፅ 11

ኢስላም እንዲኖረን የሚሸው ስብእና ባማረ ስነምግባር ላይ የተገነባ ነው።እራሳችንን አክብረን ሌሎችን እንድናከብር ያዘናል።የኢስላም አላማዎች
"መቃሲደል ሸሪዓ" ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሙስሊሙን ክብር መጠበቅ ነው።

የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱም ከእጁም ሰላም የሆኑለት ሰው ነው ብለዋል ።

ኢብኑ መስዑድ (ረድየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሌላ ሃዲስ ደግሞ
ሙስሊምን መስደብ ወንጀል ነው።መጋደሉ ደግሞ ክህደት ነው ይላሉ መምህራችን አሽረፈል ኸልቅ!

ሌሎችን በስነ ምግባራችን ጠርተን ወደ ኢስላም ማምጣት ሲጠበቅብን ያሉትን ስህተቶቻችንን እንዲያርሙ በጥበብ ከመንገር ይልቅ በስድብ እንገፋቸዋለን! ከመነሻው እነርሱ እንዲስተካከሉ ቢሆን ኖሮ ደግመን ደጋግመን ጥሪ ባረግንላቸው እና ባስታወስናቸው ነበር።

ግና እኛ ከሌሎች መሻላችንን ማንፀባረቅ ስለሆነ የምንሻው ከማስተማር ይልቅ ስድብና ነቆራን መርጠናል ይህ ሙስሊሞች ላይ ስህተት ስንመለከት ብቻ አይደለም።ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችንም ስለ ኢስላም አንድ ነገር ሲፅፉ አልያም ሲጠይቁ በስነ ስርዓት ከመመለስና ከማስረዳት ይልቅ ስድብን እንመርጣለን። በአንድ ድንበር ውስጥ አብረን የምንኖር የድንበር ወንድሞቻችን ላይ ድንበር በማለፍ እኛንም እስልምናንም እንዲጠሉና እንዲጠራጠሩ በር እንከፍታለን።በእርግጥ ይህ ነገር ከግንዛቤ እጥረት ተነስቶ ሊሆን ይችላል የሚደረገው ግና ፍፁም ስህተት ነው።ሌሎች ወደ ቀናው እንዲመጡ ምክንያት መሆን ባንችል እንኳ ከኢስላም እንዲርቁ ገፍታሪ መሆን የለብንም።ሰዎች ኢስላም ምን ይላል ሚለውን ሳይሆን ቀድመው የሚመለከቱት ሙስሊሞች ምን ይላሉ የሚለውን ነው።ንግግራችንም ሆነ ተግባራችን ኢስላምን የሚወክል በመሆኑ ከኢስላማዊ አስተምሮ የተቀዳ ይሁን አልያም ተናገሩ ብሎ የሚያስ ገድደን የለምና ዝም እንበል

"መድሃኒት ስለወሰድነው ሳይሆን ፈውስ የሚሰጠው በአግባቡ ስንጠቀመው ነው"

እስልምናም ምሉእነት ነው ብለን ስለፎከርን ሳይሆን ውብ ሆኖ የሚታየው በእኛ ህይወት ውስጥ ስጋና ደም ለብሶ ሲከሰት ብቻ ነው።እየናረ የሚገኘውን የስድብ ፍጆታችንን መቀነስ ካልቻልን ስለ ኢስላም የምንፈጥረው ገፅታ በጥላሸት የተሞላ ነው የሚሆነው!

ይህን ፅሁፍ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!!

በድምፅ የደረሰኝን መጣጥፍ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘውት በፅሁፍ ገልብጬ አቀርብኩላችሁ።

እኔም ሰዎችን የማስተማር ጥበብ የጎደለን ይመስለኛል!
በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጊዜ አንድ እእራቢይ(ዘላን ወይም የገጠር ሰው)
በሚሰግዱበት መስጂድ ውስጥ ወደ አንድ ጥግ ዞር አለና ሽንቱን መሽናት ጀመረ።ሰሃቦችም በጣም ተቆጥተው እና ገንፍለው አደነባበሩት የአለም እዝነት የሆኑት ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግን ሰሃቦችን አስቆሟቸውና ተውት ይጨርስ አሏቸው። ሸንቶ እንደጨረሰ ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀረብ ብለው የሚሰገድበት ቦታ ውስጥ እንዲህ እንደማይደረግ በጥበብ አስተማሩት ያ አእራቢይም እንዲህ ነበር ያለው!

"አላሁመ እርሃም አነ ወሙሃመዳ ወላ ተርሃም መዓና አሃዳ"

"አላህ ሆይ ለእኔና ለሙሃመድ እዘንልን ከእኛ ጋር ለአንድም አትዘን"

እዩት ያደረገው ዱዓን ምን ያክል በሰሃቦቹ ተከፍቶ እንደነበር ያሳየናል።ማስተማር፣ዳዕዋ ማድረግ እና የመሳሰሉት ኸይር ናቸው የምናስተምርበትን መንገድ አለማወቅ ግን አደጋ ነው!


አየህ የሃቢባችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጥበብ ልቡን እንዴት እንደማረከው!

በኢስላማዊ ጥበብ ህይወታችንን እናሳምር!!

በቪድዮ ለማየት ለምትሹ
👇👇
https://www.facebook.com/belachhizboch/videos/1712446248921929/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

#ደስ_የሚል_ዳዕዋ_በትርጉም

https://www.tg-me.com/Quran_Hadiis
2024/05/06 13:52:53
Back to Top
HTML Embed Code: