[ኅዳር 24 የየ24ቱ ካህናተ ሰማይ ዓመታዊ በዓል]]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 “በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር።”
— ራእይ 4፥4
💥 ዮሐንስ በራእዩ የጠቀሳቸው በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የቆሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ማን ናቸው? የሚለውን በዝርዝር የሚያስረዱን የቤተ ክርስቲያን የሥነ ፍጥረት መጻሕፍት አሉን። ይኸውም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡-
✍️ “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል።
💥 ከሰራዊተ ሩፋኤል 24ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪) እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ብሏቸዋል።
💥 የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል።
💥 ነጭ ልብሶቻቸው ንጽሕናን ስለሚያመለክቱ እና አክሊሎቻቸው ሥልጣንን ወይም ድልን ያመለክታሉ።
♥ ቁጥራቸው 24 መኾኑም በ24ቱ ሰዓት ጸልየው አመስግነው በጸሎታቸው ሌላውን ጠብቀው የሚኖሩ ናቸውና ነው፨
👉 በሰማይ አመስጋኞች በኾኑት 24ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል በ1ኛ ዜና መዋዕል 24 ላይ እንደተጻፈው የእስራኤል ካህናት የሆኑት የአሮን ዘሮች በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉበትን ቅደም ተከተል ለመወሰን በ24 ክፍሎች ተከፍለዋል። በ 1ዜና መዋዕል 25 ላይም ዘማርያን በ24 ክፍሎች ተከፍለው በቤተ መቅደስ ያመሰግኑ ነበር።
👉 በተጨማሪም በብሉይ ኪዳን የተጠሩት 12ቱ ነገደ እስራኤል በብሉይ ኪዳን ያሉ አማኞችን ሲወክሩ በሐዲስ ኪዳን ለክብር የተጠሩ 12ቱ ሐዋርያት የሐዲስ ኪዳን አማኞችን በመወከል በድምሩ 24 ናቸው።
♥ ዮሐንስም በራእዩ “ሀያ አራቱ ሊቃናት በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።” ይላል።
— ራእይ 4፥10-11
💥 እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል።
💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ምስጋናው ላይ እመቤታችን ምዕራገ ጸሎት ናትና በካህናተ ሰማይ ማዕጠንት መስሎ፦
✍️"ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ ማርያም በማዕጠንት ዘወርቅ ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ካህናት ሰማያውያን" (እመቤታችን ማርያም ሆይ የቅዱሳንና የምእመናንን ጸሎት ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች እጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን) ይላታል።
💥 ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦
✍️ "ማዕጠንተ ሱራፊ ዘወርቅ" (የሱራፊ የወርቅ ማዕጠንት) ይላታል እመቤታችንን።
💥 ጸሎት ሁሉ በመላእክት ማዕጠንት (ጽናሕ) ወደ ጌታ የሚቀርብ ነውና፦
✍️ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” ይላል ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡
💥 ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ፦
✍️ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” ይላል።
💥 ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡
✍️ “መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።”
— ራእይ 5፥8-10
💥 አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ፡- ✍️ “ወይምጽኡ ካህናት ሰማያውያን፣ ልቡሳነ ብርሃን ወጸወርተ ዕጣን፣ እለ ያቈርቡ ቅድመ ምሥዋዒከ ጸሎተ ቅዱሳን፣ እለ ይቀውሙ ዐሠርቱ ወክልኤተ እምይምን ወዐሠርቱ ወክልኤቱ እምፅግም፣ ወፍያላተ ያቄርቡ ለስብሐተ መለኮትከ፤ ዕሥራ ወአርባዕቱ ኊልቆሙ ዕሥራ ወአርባዕቱ መናብርቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ አክሊላቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ ማዕጠንታቲሆሙ”
(ብርሃንን የለበሱ ዕጣንንም የተሸከሙ የቅዱሳንን ጸሎት ወደ መሠዊያኽ ፊት የሚያቀርቡ ዐሥራ ኹለቱ ከቀኝ ዐሥራ ኹለቱ ከግራ የሚቆሙ ለጌትነትኽም ምስጋና ጽዋዎችን የሚያቀርቡ ሰማያውያን ካህናት ይምጡ፤ ቊጥራቸው ኻያ አራት ነው ወንበሮቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፣ አክሊሎቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፤ ማዕጠንቶቻቸውም ኻያ አራት ናቸው) በማለት ስለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ አስተምሯል፡፡
💥 ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ ሲያቀርብ፦
✍️ "ሰላም ለ፳ወ፬ቱ ካህናት ሰማያውያን እለ ዐውደ መንበሩ ለአብ፡፡ ወሰላም ለማዕጠንት ዘውስተ እደዊሆሙ ወሰላም ለአክሊላት ዘዲበ አርዕስቲሆሙ፤ ወሰላም ለአስማቲሆሙ፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል”፡፡
(በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ፳፬ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፨

❤91👍33🥰13
[የልዑል እግዚአብሔርን ዙፋን የሚያጥኑ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በማዕጠንታቸው ጸሎታችንን ወደ ጸባኦት ዙፋን ያድርሱልን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ የተለጠፈ]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ የተለጠፈ]
❤157👏22👍20
[ኅዳር 25 የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓለ ዕረፍት]
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 በእኛ አጠራር ቅዱስ መርቆሬዎስ በግሪክኛ Ἅγιος Μερκούριος በቅብጥ Ⲫⲓⲗⲟⲡⲁⲧⲏⲣ Ⲙⲉⲣⲕⲟⲩⲣⲓⲟⲥ; በሲርያክ ܡܳܪܩܘ̇ܪܝܘ̇ܣ ተብሎ የሚጠራው ይኽ ቅዱስ ሰማዕት የተወለደው በ225 ዓ. ም. በቀጶዶቅያ ኢስኬንቶስ ከተማ ነው። ቤተሰቦቹ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ሲኾን በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል።
💥 “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል።
💥 በዚኽ ምክንያት በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡
💥 “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ በውጊያው ውስጥ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት) Abu-Seifein (أبو سيفين) በቅብጥ ⲁⲃⲩⲥⲉⲫⲁⲓⲛ ተብሏል፡፡
💥 ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ ለጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ በዚኽ ምክንያት ንጉሡ አስጠርቶት “ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡
💥 ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ ብዙዎች ሥቃያትን አደረሱበት።
💥 ከዚያም ኅዳር 25 ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ የምሕረትን ቃል ኪዳን ከገባለት በኋላ በ250 ዓ.ም በ25 ዓመቱ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊልን ተቀዳጀ።
💥 የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታል፤ በተለይ በእስክንድርያ እና በኢትዮጵያ በስፋት ይከበራል፡፡ ከሊቃውንት መካከል ቅዱስ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በቃል ኪዳኑ ሲማፀኑ ከገዢው ዑልያኖስ emperor Julian the Apostate (361-363) በተራዳኢነቱ ጠብቋቸዋል።
💥 በተጨማሪም ቅድስት ድንግል ማርያም ከግንቦት 21-25 በደብረ ምጥማቅ ጉልላት ላይ ትገለጥ በነበረ ጊዜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል በጸሊም ፈረስ ሆኖ ቅዱስ መርቆሬዎስ ይመጣ ነበር።
💥 ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
✍️“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”
(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡
💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አመስግኖታል፡፡
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፡

❤185👍57👏13🔥1
The Sun of Righteousness p.24
Dr Rodas Tadese.
THE BOOK OF ENOCH
The Book of Enoch and its survival became widely known in the Western world during the 18th century, by the Scottish explorer James Bruce. Bruce arrived in Gondar, then the Ethiopian capital, on February 14, 1770, with the primary goal of studying the origins of the Nile. During his time in Ethiopia, he immersed himself in local culture, studied ancient Ge’ez manuscripts and gathered medicinal herbs to share with European monarchs. Among the manuscripts he acquired were three complete copies of the Book of Enoch. Upon returning to Europe, Bruce presented one copy to King Louis XV, which was added to the French National Library in Paris in 1773. A second copy was placed in the Bodleian Library at Oxford University in 1774 and Bruce kept the third, which was also later added to the Bodleian collections after his death in 1794. Through these manuscripts , the Book of Enoch was reintroduced to scholars, offering the Western world an extraordinary look at a text that had been safeguarded in Ethiopia for centuries. The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church’s preservation of the Book of Enoch reflects its dedication to a unique and sacred scriptural heritage. Alongside other texts like the Book of Jubilees, the Ethiopian canon remains one of the most extensive and historically rich collections in Christianity, preserving ancient beliefs and spiritual insights that connect Ethiopia’s faithful to some of the earliest traditions of biblical literature. Through the Book of Enoch, the Church offers a vision of cosmic justice, divine mystery and a world intricately connected to heavenly realms, affirming Ethiopia’s distinctive legacy as a custodian of holy wisdom and ancient scripture.
Order your copy on Amazon today and uncover profound mysteries that will deepen your understanding.
The Sun of Righteousness https://a.co/d/3sDda2j

❤52👍28👏3
[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።
♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::
♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።
♥❖♥ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡
♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::
♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡
ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦
፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”
(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥
♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”
(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]
♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)
♥ “እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ”
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)
♥ “ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ”
(ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)

👍47❤32👏6🥰3😁1
♥ “ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”
(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል
++++++++++++++
፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]
♥ “She was grave and dignifified in all her action…” (እመቤታችን በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች)
+++++++++++
፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ)
++++++++++++++++
፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]
♥♥♥ “At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አምባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም)
+++++++++++++
፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም)
+++++++++++++++++++
፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]
♥♥♥ “Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 እና ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)

❤108👍36🥰8👏3🔥1
❖ መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው፤ የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖✔💥 በ290 ዓ.ም. በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ስላረፈችው ስለ ቅድስት አርሴማ በአርሜንያ Հռիփսիմէ
ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በስሟ በተሰየመው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች ካለ ካታኮምብ ግበበ ምድር በአርመንያ አለ፡፡
❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨
❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨

❤54👍19
❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

❤70👍16
ከ37 አልፋ 73 መጽሐፍ የተወሰደ
✍️ በዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 በግእዝ ቀመረ ፊደል ዙሪያ በቀደሙ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ የተጻፉ እንደ "ህላዌ ዘአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ፤ ህላዌ መለኮት፣ መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ ..." የመሳሰሉና ሌሎችም በርካታ የግእዝ የፊደል ቀመር መጻሕፍት እና ጸሎታት ይገኛሉ፡፡
ፊደላቱን ወደ ቀመረ ግእዝ ስንለውጥ የሚመጡልን ቀመራት አስደናቂ ናቸው፡፡ ይልቁኑ በነዚኽ መጻሕፍት ውስጥ እንደምንረዳው ፊደላቱ በሙሉ “መለኮታዊ ስሞች” Divine Names የያዙ ናቸው፡፡
በመኾኑም በነዚኽ ፊደላት የተዋቀሩ የተቀደሱ ቃላት ታላቁን የእግዚአብሔርን ስሞች የያዙ ናቸውና በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰውን አእምሮ፤ በዕውቀት ብርሃን የሚያበሩ፣ ልቡናን የሚያነቁ፣ የማስተዋል ደጅን የሚከፍቱ በከፍታ ያሉ ረቂቅ ዕውቀቶችን ከአልፋ የሚያሰጡ ተብለው በሊቃውንት ይታመንባቸዋል።
ለምሳሌ ያኽል “ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ” (የሔኖክ የአእምሮ ደጃፍ) የተባለው የግእዝ መጽሐፍ ሲዠምር፡- “በስመ አብ ወወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ኆኅተ አእምሮ በጸፍጸፈ ሰማይ ጽሑፍ፤ ዝንቱ ፊደል ዘአለበዎ ለሔኖክ፤ ወከብደ እንግድዓሁ ወልቡናሁ፤ ወርእየ ኀዋኅወ ሰማይ …” (በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ በሰማይ ሰሌዳ የተጻፈ የዕውቀት በር፡፡ ይኽ ፊደል ሔኖክን የሚያስተውል ያደረገው ነው፡፡ አእምሮውና ልቡናው ከበረ (በረታ) የሰማይ ደጃፍ ተከፍቶ አየ …) በማለት በፊደል [አ] [በ] [ገ] [ደ] … የሚዠምር ሲኾን የእነዚኽን የፊደላትን ዕውቀት አካኼዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው ሔኖክ እንደተረዳው ይገልጣል፡፡
“መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ” የተባለው የቀመረ ፊደል የግእዝ መጽሐፍ ይኽነን የፊደል ቀመር ማወቅ ወደ ከፍተኛ የአእምሮ ልዕልና ስለማድረሱና ለእግዚአብሔር የቀረቡ ቀደምት ነቢያት ኹሉ ጠንቅቀው ይኽን ያውቁ እንደነበር ሲገልጽ፡- ....
በሚያልፍ ጊዜዎ የማያልፍ ዕውቀትን ቀድመው ያግኙ መጽሐፉን በሀሁ የመጻሕፍት መደብር 0911006705
ወይም በአማዞን 37 Alpha 73 (Amharic Edition) https://a.co/d/hzWq57M
ገዝተው ያንብቡ

❤45👍26🥰6👎2
[ታኅሣሥ 8 በዓሏ የሚከበረው ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ድንቅ ታሪኳ፤ በቀደምት ኢትዮጵያውያን የቀረበላት ውዳሴና ዓለም ዐቀፍ ክብሯ]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥❖♥ ከክርስቶስ የተቀበለችው ቃል ኪዳን ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው በመላው ዓለም ከጥንት ጀምሮ የምትታወቀው ከ273-306 ዓ.ም የነበረችው ሰማዕቷ ቅድስት በርባራ በሌሎች ሃገራት Αγία Βαρβάρα, Great Martyr Barbara በመባል ትታወቃለች።
💥 ከ305-311 በነገሠው በከሓዲው መክስምያኖስ (emperor Maximian) ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ ናት። እጅግ ውብ ስለነበረች ሰው እንዳያያት ጣዖት አምላኪ የነበረ አባቷ ለርሷም ለብቻዋ ሰገነት ያለው ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶላት አንድ አረማዊ መምህር ብቻ ወደርሷ እንዲገባ አደረገ።
♥❖♥ ያሠራላት ሰገነት ከፍ ያለ ስለነበር አበባዎችን ይልቁኑ በምሽት የሚያበሩትን ከዋክብት የምሽቱ አስደናቂ ግርማ እየተመለከተች መደነቅ ጀመረች። በዚህ ጊዜ እነዚህ የአባቷ ጣዖታት አስደናቂ ዓለማትን እንደማይፈጥሩ ተረዳች። በሕይወቷ የዓለማት ፈጣሪን ለማወቅና በድንግልና ሕይወት ለመኖር ወሰነች። ብዙ የጋብቻ ጥያቄን ውድቅ አደረገች። በዚህ ምክንያት አባቷ ውጪውን እንድትለምደው ከግቢ እንድትወጣ ፈቀደላት።
♥❖♥ በዚህ ጊዜ ከክርስቲያን ሴቶች ጋር በመገናኘቷ ስለ ምስጢረ ሥላሴ፣ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢርን አስረዷት። እውነተኛውን የድኅነት መንገድ በመረዳቷ ከእስክንድር ወደ ሄሊዎፓሊስ መጥቶ በነበረ ካህን በድብቅ ተጠመቀች።
♥❖♥ በዚያ ወቅት አባቷ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት መስኮቶችና ቅንጡ የሆነ መታጠቢያ እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ምስጢረ ሥላሴን አስባ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም አዳኝ የኾውን የመስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡
♥❖♥ አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም “ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ እስመ በሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ” ይላል ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም መስቀል ዓለሙ ኹሉ በርሱ በዳነበት በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት ተናገረችው፡፡
♥❖♥ አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና “ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ ሰማች፤ ከዚያም ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡
♥❖♥ በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤ ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የዳንኩት” አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡
♥❖♥ በዚያም የሂሊኦፓሊስ ነዋሪ ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን ሲያሰቃይዋት አይታ ከርሷ ጋር በክርስቶስ ስም መከራን ለመቀበል በመወሰን አብራት መከራ መቀበል ጀመረች። ሁለቱም ሰማዕታትን በምስማር ሰውነታቸውን እየወጉ ያሰቃይዋቸው ነበር። ለመዘባበት ዕርቃናቸውን በአደባባይ ሊወስዷቸው ቢሞክሩም በቅድስት በርባራ ጸሎት ጌታ መልአኩን ልኮ በአስደናቂ መጎናጸፊያ ሰውነታቸውን ጋርዶታል።
♥❖♥በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ብዙ ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ።
♥❖♥ ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤ በአባቷ ወደተዘጋጀው ወደመግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ (አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡
♥❖♥ ከዚያም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት።
♥❖♥ በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8, በ306 ዓ.ም. አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡ በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ ብልጭታ ይሣላል፡፡ ቅድስት በርባራም በዚህ ምክንያት በአማላጅነቷ ከጥንት ጀምሮ ባሉት ክርስቲያኖች ከመብረቅ አደጋና ከእሳት የምትጠብቅ እንደሆነች ይነገራል።
♥❖♥ ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በመስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡
♥❖♥ ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል ይዛ ይታያል፡፡ በዐዲስ አበባ በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ባሉት የግድግዳ ላይ ሥዕላት ላይ ቅድስት በርባራና ቅድስት ዮልያና ተሥለዋል። በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል::
♥❖♥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 8 በሚነበበው መዝገበ ቅዱሳን በሆነው ስንክሳር ላይ ቅድስት በርባራና ዮልያናን ታስባለች።
♥❖♥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅድስት በርባራን አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር፤ ለምሳሌ ያኽል ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ቅዱስ አርከ ሥሉስ እንዴት እንዳመሰገኗት ብናይ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-

❤42👍29👎2😁2
“ሰላም ለበርባራ ወዮልያና በፍኖተ ስምዕ እለ ቆማ፤
በድሮን እለ ፈጸማ
እለ ተጋደላ ከመ ሐራ
አርዑተ መስቀሉ ለክርስቶስ እለ ጾራ
መርዓዊሆን እስከ ረከባ
ድንግልናሆን እለ ዓቀባ”፡፡
(ሙሽራቸው ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ ድንግልናቸውን የጠበቁ፤ የክርስቶስ መከራ መስቀሉን የተሸከሙ፤ እንደ ጭፍሮች የተጋደሉ፤ ሩጫቸውንም የፈጸሙ፤ በምስክርነት ጐዳና የቆሙ ለኾኑ ለበርባራና ለዮልያና ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፡፡
♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ፡-
“ሰላም ለበርባራ እንተ አግሀደት ሃይማኖታ
እንዘ ታርኢ ሥላሴ በመስኮተ ቤታ
ኢያፍርሃ መጥባሕት ወሞሠርተ ሐጺን ኢያሕመመታ
ወሰላም ካዕበ ለዮልያና ካልዕታ
እንተ ሰቀልዋ በክልኤ አጥባታ”
(በቤቷ መስኮት የሥላሴን ምሳሌ እያሳየች ሃይማኖቷን የገለጠች ለኾነች ለበርባራ ሰላምታ ይገባል፤ ሰይፍም አላስፈራትም የብረት መጋዝም አላሳመመቻትም፤ ዳግመኛም በኹለት ጡቶቿ የሰቀሏት የርሷ ኹለተኛ ለምትኾን ለዮልያናም ሰላምታ ይገባል) በማለት የተቀበሉትን ጽኑ መከራ ጽፏል፡፡
♥❖♥ ቅድስት በርበራ እመቤታችንን ለምና የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁት ላይ ያደረገችውን የመስከረም 25 ተአምሯን ደግሞ፦
"ሰላም ለበርባራ ወለዮልያና አምሳላ
በዛቲ ዕለት ዘአስተርአየት ኀይላ
በክልኤ ዕደው ዘሰረቁ መጽሐፈ ገድላ
ፈደየቶ ለአሐዱ እንባዜ እምኀበ ማርያም ስኢላ
ወለዐይነ ቢጹ ካልዕ አጽለመት ጸዳላ"
(የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁ በሁለት ወንዶች ላይ በዚህ ዕለት ኃይሏን ያሳየች ለሆነች ለበርባራና ርሷን በተጋድሎ ለምትመስል ለዮልያና ሰላምታ ይገባል። ከእመቤታችን ማርያም ለምና ለአንዱ መቅበዝበዝ የሁለተኛው ጓደኛውን ዐይን ብርሃኑን አጨለመች) በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ ተመሳሳይ ተአምርን እንደሠራች ይጽፋል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስ በመስከረም 25 ስንክሳር አርኬ።
💥 ❖የቅድስት በርባራ ዐለም ዐቀፍ ክብሯ❖💥
♥❖♥ በእጅጉ የሚገርመው ከጥንት ጀምሮ በየክፍላተ ዘመናቱ እስከ ዛሬ ድረስ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በቅድስት በርባራ ከሚፈነዱ የጦር መሣሪያዎች፤ ከመብረቅ አደጋና ከድንገተኛ ሞት በቃል ኪዳኗ እንደምትጠብቅ ሲታመን፤ በጣሊያን የባሕር ኀይላችን ጠባቂ (the patron of the Italian Navy.) ይሏታል።
♥❖♥ በቃል ኪዷና በእጅጉ ከመታመን የተነሣ በጊዜያችን ያሉ በርካቶች ኀያላን ሀገራት ብሪታኒያ (Royal Artillery, RAF Armoures, Royal Engineers) በካናዳ (Explosiv Ordance Technicaians) በአውስራሊያ (RNZAF Armourers) በኒውዝላንድ፤ በስፔን፣ በአሜሪካ፣ በግሪክ የቅድስት በርባራን በዓል በዐየር ኀይላቸው፣ በጦር ካምፓቸው፣ በባሕር ኀይላቸው ዲሴምበር 4 ላይ እንደሚያስቡ ጥናቶች በግልጽ ያሳያሉ::
♥❖♥ በስፓኒሽና በጣሊያን ይታተም የነበረው መጽሔት መርከበኞች ከድንገተኛ አደጋ መርከባቸው ይጠበቅ ዘንድ ሥዕሏን ይይዙ እንደነበር ይጽፋል።
♥❖♥ በሰሜን አሜሪካ የጦር ኃይልም ቅድስት በርባራ የምትታሰብ ሲሆን በጦር ኃይሉ ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ለሠሩ ምርጥ ወታደሮች በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ የቅድስት በርባራ ሥዕል ያለበት ሜዳልያ (ANCIENT ORDER OF SAINT BARBARA) ይበረከትላቸዋል። (https://www.fieldartillery.org/awards)
💥 (United States Field Artillery Association, fieldartillery.org. retrieved 23 January 2010,) (Cyprus Army notes on Saint Barbara, Army)
♥❖♥ በሰሜን አሜሪካ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ 100 ማይልስ በሚገመት አግጣጫ ያለችው በቅድስተ በርባራ ስም ሳንታ ባርባራ Santa Barbara በመካከለኛው ካሊፎርንያ ከተማ ተሠይሞላታል፤ በተመሳሳይ መልኩ በስፔንና ፖርቱጋል ቦታ ላይ በብራዚል፣ በቺሊ፣ በኮሎምቢያ፣ በሆንዱራስ፣ በሜክሲኮ፣ በቬንዝዌላ፣ በፊሊፒንስ በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ አለ። በሊባኖስ ክርስቲያኖችም በጣም ትታሰባለች (Hammond Atlas of the World.1997.)፡፡
♥❖♥ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ሊቁ አርከ ሥሉስ ያወደሷት፤ ክብሯ በስንክሳር ላይ የተጻፈላት በርካቶች ቃል ኪዳናትን የተቀበለች ቃል ኪዳኗም ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ጥንታዊ ሥዕላት በብራና ላይ እንዳሉ ባውቅም በስሟ የተሰየመ ታቦት እንዳለ ግን ጥናቱ የለኝም።
💥 እኔ ከክብሯ በዐጭሩ በረከቷን ለመሳተፍ ያህል እንደጻፍኩ እናንተም ታኅሣሥ 8 በስሟ ለነዳያን በመመጽወት በቃል ኪዳኗ በመማጸን በረከቷን ተሳተፉ።
💥 ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።”
— (ሮሜ 13፥7) እንዳለ
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ ፓስት ያደረኩት)

❤150👍30👏20
♦️እነሆ መልካም እራት በሥላሴ እጅ ♦️ This Evening is nice With Holy Trinity♦️
https://youtube.com/live/TJUc-WCxWsI?si=DvrPjGyCG9lgbx0S

Youtube
- YouTube
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
👍49❤26🥰6👎1
12/24/24
,
In biblical and spiritual numerology, the date 12/24/2024 carries profound symbolism when broken down, especially considering its connections to key biblical numbers:
1. Month: 12
The number 12 in the Bible signifies divine governance, order, and completeness.
12 tribes of Israel symbolize God's chosen people.
12 apostles reflect the foundation of the Church.
12 gates of the New Jerusalem indicate God's eternal kingdom (Revelation 21:12).
In this context, 12/24 could represent the alignment of heavenly order and earthly events.
2. Day: 24
The number 24 is associated with priestly service and heavenly worship.
In Revelation 4:4, 24 elders surround God’s throne, representing divine worship and authority.
It reflects God's perfect leadership and unbroken connection with His people.
3. Year: 2024
Breaking the year down:
2024 = 2 + 0 + 2 + 4 = 8
The number 8 symbolizes new beginnings, resurrection, and eternal life.
Jesus rose on the 8th day (the first day after the Sabbath), marking the dawn of a new creation.
Circumcision, a sign of covenant with God, occurs on the 8th day (Genesis 17:12).
Thus, 2024 could signify a time of spiritual renewal and covenantal restoration.
4. Total Date: 12/24/2024
Adding the numbers: 12 + 24 + 2024 = 2060 → 2 + 0 + 6 + 0 = 8
Once again, the number 8 emerges, emphasizing renewal, rebirth, and eternal life.
This ties beautifully to Christmas Eve, symbolizing the imminent birth of Christ, the bringer of new life and salvation.
Spiritual Meaning
Harmony of Heaven and Earth:
The combination of 12 (heavenly order) and 24 (priestly worship) reveals the interconnectedness of God's divine plan for creation.
The overarching presence of the number 8 emphasizes that this date resonates with Christ's role as the light of the world, offering renewal, hope, and eternal life.
As this day precedes Christmas, it symbolizes the anticipation of God's promise being fulfilled through Jesus, connecting deeply with themes of hope, joy, and divine grace.
In conclusion, 12/24/2024 in biblical numerology represents a spiritually significant moment, highlighting the harmony of God's divine order, the fulfillment of His promises, and the renewal of life through Christ.

❤52👍24👎3
The list of books published by Dr. Rodas Tadese:
1. The Symbol of Mary in the Old Testament, Volume 1 (Amharic)
2. The Symbol of Mary in the Old Testament, Volume 2 (Amharic)
3. Mariology in the New Testament, Volume 1 (Amharic)
4. Mariological Thoughts of the Early Church Fathers (1st to 4th Century) (Amharic)
5. Mariological Thoughts of the Early Church Fathers (4th to 9th Century) (Amharic)
6. Christology, Volume 1 (Amharic)
7. Alpha and Omega (Amharic)
8. The Commentary on the Effigy of Mary (Amharic)
9. The Commentary on the Effigy of Mary, Second and Third Volumes (Amharic)
10. The Commentary on the Effigy of Jesus (Amharic)
11. The Commentary on the Effigy of the Trinity (Amharic)
12. The Commentary on the Effigy of the Passion of Christ (Amharic)
13. The Commentary on the Book of Hours (Amharic)
14. The Commentary on the Salutation of Saints (Amharic)
15. The Commentary on the Anaphora of Mary (Meaza Qeddase) (Amharic)
16. The Commentary on the Salutation of Mary (Amharic)
17. The Book of Fisalogos (Amharic)
18. The Philosophy of Hikar and the Revelation of Sabela (Amharic)
19. The Nativity of Jesus by Jacob of Serugh (Amharic)
20. The Perpetual Virginity of Mary and On the Mother of God by Jacob of Serugh (Amharic)
21. Bible and Medical Science (Amharic)
22. Andromeda 1 by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
23. Andromeda 2 by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
24. The Ethiopian Calendar by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
25. Mazzaroth (Amharic)
26. 888 (Amharic)
27. 37 Alpha 73 (Amharic)
28. The Sun of Righteousness (English)

❤82👍27🥰10