♥♥♥ ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
♥♥♥ የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡
♥♥♥ “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ
መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡
♥♥♥ በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡
♥♥♥ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኽ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኽ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠኽ ክብርኽን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫላይቱ ላይ ተቀምጠኽ ወደ ሰማይ ሰራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ ርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡
♥♥♥ የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ሕፃናትን ጨምሮ ዘንባባ ሰሌን በያዙት ኹሉ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ታላቁን በዓል ከኹሉም ዓለም አስበልጣ በታላቅ ክብር የምታከብርና የምታስተምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
♥♥♥ ይኸውም ታላቁ የምስጋና ዕለት ሊደርስ ሲቃረብ ስንዱዋ እመቤት አስቀድማ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቊርባን ምስጋና፦
✍ “ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት…” (የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ ርሷ ገባ፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነኽ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ኹሉ ጌትነቱን አሳየ፤ የሆሳዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡርክ ርሱ በታላቅ ቃል እየጮኻችኊ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከዚኽ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚኽም በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና መንክራትን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም... ) በማለት መድኀኒትነቱን ስትሰብክ፤ ካህናትና ምእመናንም በአንድ ድምፅ በዚያ ዘመን የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሰገነበት በዚኽ ልዩ ምስጋና “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ በመዘመር፤ ፈጣሪያቸው ክርስቶስን ያመሰግናሉ፡፡
♥♥♥ ከዚያም በዋዜማው፦
✍ “በዕምርት ዕለት በዓልነ ንፉሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ሆሣዕና በአርያም ቡሩክ አንተ ንጉሠ እስራኤል”
(በታወቀች በበዓላችን ዕለት በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በመቅደሴ ተራራም ስበኩ ይኽቺ ዕለት የእግዚአብሔር በዓል ናት፤ በአርያም መድኀኒት የተባልኽ የእስራኤል ንጉሥ አንተ ቡሩክ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የምታርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል) ነኽ) በማለት ልዩ ምስጋናዋን ጀምራ እስከ ሌሊቱ ድረስ በልዩ ምስጋና እየሰበከችው በኋላም ቤተ መቅደሱን በውርጫዋ ተቀምጦ እንደዞረ በአራቱ መኣዝን የጌትነቱ ወንጌል እየተነበበ፤ ካህናቱን ምእመናንም በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ያመሰግኑታል፡፡
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
መልካም በዓል ይኹንልን።
የቴሌግራም ቻናሌ https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w

Telegram
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
👍89❤57👏7🥰3
ስለ ሥውሩና ድብቁ ዓለም የተራቀቁት የት ገቡ? ማግሰኞ ማታ 2:22 ላይ ይጠብቁ
https://youtube.com/watch?v=rHQoxhZ7l7Q&si=YevajljhIE3MdF5-

YouTube
ስለ ሥውሩና ድብቁ ዓለም የተራቀቁት የት ገቡ? ማግሰኞ ማታ 2:22 ላይ ይጠብቁ
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
👍63❤27👎1🔥1
“ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን፤
ሞገሶሙ ለጻድቃን፤
ብርሃኖሙ ለፍጹማን፤
መርዐዊሃ ለቤተ ክርስቲያን፤
ተንሥአ አቡሁ ለአቡነ አዳም፤
ቤዛ ብዙኃን”
(የጻድቃን ሞገሳቸው፤ የፍጹማን ብርሃናቸው፤ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ በገናና ኀይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ የብዙኃን ቤዛ የአባታችን አዳም አባቱ (ፈጣሪው) ከሞት ተነሣ) (ድጓ ዘፀአተ ሲኦል )
እንኳን አደረሳችኹ

❤99👍22👏5🥰2
💥 Mary in the Old Testament (Genesis – Malachi)
Unveiling 144 Symbols of the Mother of God
✍️ By Dr. Rodas Tadese
A groundbreaking theological exploration revealing 144 symbolic prefigurations of the Virgin Mary throughout the Old Testament—from the Garden of Eden to the prophetic books of Malachi.
👉 562 pages
👉 21 chapters
👉 In English
Available in Hard Copy and Kindle on Amazon
💥 https://a.co/d/f2HUowh
A must-read for theologians, researchers, and spiritual seekers.
Unlock the ancient mystery. Discover Mary’s presence from the beginning.
የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 30ኛ መጽሐፍ በ562 ገጾች በ21 ምዕራፎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ ከኦሪት ዘፍጥረት - ትንቢተ ሚልክያስ የተገለጹ 144 የእመቤታችን ምሳሌዎች ለዓለም ዐቀፍ የቴዎሎጂ ሊቃውንት፣ ተመራማሪዎች፣ ወጣቶች፣ ዐዋቂዎች ቀርቧል። በውጪ ካሉ ከአማዞን ሀርድ ኮፒውን ይዘዙ።
https://a.co/d/f2HUowh

👍59❤33🥰6👏6
💥 The burning Bush💥
✍️ By Dr. Rodas Tadese (Mary in the Old Testament pp 151-152)
The account of Moses and the burning bush, found in Exodus 3:1 5, holds profound theological significance. The narrative describes Moses’ encounter with a bush engulfed in flames yet not consumed — a prefiguration of the Incarnation and a symbol of the Blessed Virgin Mary.
👉 The profound insight of St. Yared, in his Degua and Zimare (Hymns), sheds a radiant light on the mystery of the burning bush as a Marian symbol. He writes with unparalleled reverence,
✍️ "Moses saw the bush, Mary, whom the Divine Fire did not consume; and Moses trembled, unable to comprehend the Divine Power within it. He who blessed Aaron's priesthood descended from heaven and came to save Adam."
St. Yared’s vision reveals Moses not merely witnessing a bush but encountering a prophecy of Mary, the Theotokos, who would bear the Divine within her yet remain untouched, just as the bush was unburned by the flame.
In his Zimare (Hymns), St. Yared continues to draw upon the mystery, adding,
✍️ "This fire flaming on it is our Savior; just as in the bush, fire was contained in the Virgin's womb; neither was Her womb burned, nor was Her virginity damaged."
The beauty of St. Yared’s words lies in their poetic reverence and theological depth, portraying the bush as a living symbol of Mary’s unblemished purity and the mystery of the Incarnation. In his inspired teachings,
👉 Abba Giorgis draws upon the symbol of the burning bush to reveal the divine mystery of the Incarnation. He venerates the Blessed Virgin Mary as the “spiritual bush” that withstands the holy fire, explaining,
✍️ "O spiritual bush that could withstand the fire; the fire was not extinguished, nor was the bush consumed; and this foretold incarnation, from You, of the Son without separation or alteration."
👉 In his Arganon (Hymns of Mary), he further reflects on this profound image, exclaiming,
✍️ "I call You the bush, for the God of Abraham, Isaac, and Jacob was revealed in the bush to Moses, and sent him to the children of Israel to announce the tidings of their freedom. The Begotten Son of God, the incarnate Word, Who was born of You, sent the apostles to all the ends of the earth to preach to the whole world the freedom from evil’s slavery."
Here, he sees in Mary a new burning bush, through which God reveals His salvation, not only to one people but to all nations, sending forth the apostles as heralds of freedom and redemption
👉 The reflection by Abba Tsigie and Abba Gebre Mariam in their Mahlete Tsigie (Songs of Flower) unveils a beautiful and profound interpretation of the burning bush as a symbol of the Mother of God. They poetically write,
✍️ "When You, the burning bush, united with the Divine, O Mary, Your miracle was proclaimed in the Torah. O You, the green bush that the Chief Prophet saw, cover me under Your branches. May the fire of Your flower burn away my sinful thorns."
Their words capture both the reverence for Mary as the bearer of the Divine and a plea for her intercession to purify and protect, much like the sheltering branches of the miraculous bush.
💥 The book available on Amazon – Hardcover & Kindle.
https://a.co/d/dDMwQfS

❤30👍17🔥2
ለረዥም ጊዜ በማለቁ ምክንያት ተወዳጁ የአንድሮሜዳ መጽሐፍ ባለመኖሩ በድጋሚ እንደታተም እጅግ ተደጋጋሚ ጥያቄ አንባቢዎች ያቀርቡ ነበረ። አሁን ግን በጣም ሰፈ ኢትዮጵያዊና ሳይንሳዊ የሥነ ፈለክ (Astronomy) ዕውቀት የያዘው ታላቅ መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለአንባብያን ቀረበ።
መጽሐፉ በሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
ስልክ 0911006705/ 0924408461
መጽሐፉ በሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
ስልክ 0911006705/ 0924408461
👍34❤15😁2
አልፋ እግዚአብሔር አመሰግንኻለኹ። በዚኽች ሚያዝያ 22 ቀን ከእናቴ ማሕፀን ወጥቼ 33 ዓመት ከ3 ወራት ተረማምደኽ የቀደስካት የከበረች ምድርን እንዳይ ፈቅደኻልና አልፋ አዶናይ እግዚአብሔር ምስጋና ይግባኽ። ባለፈው የአንተ ስጦታ ብቻ በኾነው የዕድሜዬ ዓመት ዑደት ውስጥ
💥 ከመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ
ታላላቅ የአምላክ እናት ጉባኤን
👉 በቨርጂኒያ መካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ
👉 በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል
👉 በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በማድረግ።
👉 በጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ውዳሴና ቅዳሴ በመተርጎም
👉 በዐዲስ ዓመት ባሕረ ሐሳብ በማውጣት
👉 በሰሙነ ሕማማት ትምህርተ ኅቡአትንና መጽሐፈ ኪዳንን በመተርጎም
💥 በትምህርት
👉 የቀመረ ፊደለ ግእዝ ትምህርት በኦን ላይን ለ400 ደቀ መዛሙርት በማስተማር
👉 በሚዲያዎች ዕውቀትን ለትውልድ በማሸጋገር
💥 በድርሰት ሥራ
👉 The Sun of Righteousness፡ Ethiopia a sacred doorway to the light of Christ
እና 30ኛ መጽሐፌን
👉 Mary in the Old Testament፡ Unveiling 144 symbols of the Mother of God
አዘጋጅቼ እንድፈጽም ያደረከኝ የሕይወት እንጀራዬ፣ የሕይወት መጠጤ፣ የክብር ልብሴ፣ የሕይወት እስትንፋሴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እወድኻለኹ።
👉 በቀንም በሌሊትም ምልጃሽ ፍቅርሽ ጣዕመ ፍቅርሽ ያልተለየኝ መቼም ሊለየኝ የማይችል ብቸኛ እናቴ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እወድሻለኹ።
በልደቴ ከእናንተ ከወዳጆቼ ለቀረበልኝ መልካም ምኞት ከልቤ አመሰግናለኹ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
https://www.tg-me.com/+xN518gdGKvswNzE0

❤220👍35😁8👏2