እንደ አምናው

ዘወትር በቀዳሚት  ሥዑር ሰንበት ት/ቤታችን በዚህች ቀን የምታሰባስበን የራቅነውን አቅርባ ፤  የጠፋነውን ፈልጋ ካለንበት ጠርታ እርስ በእርስ የናፍቆት ሰላምታ አድላ ቀደምቱን ከአዳዲስ አንድ አድርጋ  አልፎም   ከሞያ ጨዋ ለሆንን  ሞያ ከባለሞያዎች ሞያ አስተምህራን እንኳን አደረሳችሁ አባብላን የምትሸኘን የናፍቆት ዕለታች ናት  የቅዳሜ የነድያንን ጾም ማስፈቻ የግብር ቀን። 

ኑ እንደ አምናው እንደ ካቻአምናው በፍቅር በአንድነት በትጋት በበረከት ስራ እንሳተፍ
በጠዋት ነው የተጀመረው ቀኑንም ማታውንም ይቀጥላል።


ትንሳኤ በመራሔ ድኅነት በበረከት ስራ እናሳልፍ ዛሬ ሚያዝያ ፳፮/፳፻፲፮ ዓ.ም
የመራሔ ድኅነት ሰንበት ት/ቤታችን ሥራ አመራርና የንዑስ ክፍላት ተጠሪዎች ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ሲዳማ ክልል ሊቀ ጳጳስና የፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ መኖርያ ቤት በመገኘት የሰ/ት/ቤታችንን በመወከልም ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሶት መልክቱን  ለብጹነታቸው  አስተላለፈ።

ሰኞ ሚያዝያ ፳፰/፳፻፲፮ ዓ.ም

በዕለቱም የገዳማችን አስተዳዳሪ መ/ፀ/መ/ር/ቆ/አባ ኪዳነማርያም አብረውን በመገኘት የሰንበት ት/ቤቱን አገልግሎት በጥልቀት ያስረዱ ሲሆን ቀጥሎም ብጹነታቸውም
በመልዕክታቸው የሰንበት ት/ቤቱን አገልግሎት ዘወትር እንደሚከታተሉና ከየገዳማችን አስተዳዳሪ  እንደሚሰሙ ተናግረውና  አድንቀውም አስከትለው የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት በአሐት አብያተ ክርስትያናት የጳጳሳት ፤ የካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የተለያዩ ምሁራን መፍለቂያና የምዕመናን በሃይማኖት መጽኛ ነው እናም እንደ ሰንበት ት/ቤት የእነርሱን አርአያነት በመመልከት ከፍ ላለው አገልግሎት እንድንፋጠን አስገነዝበዋል። አክለውም ከታች ላሉት ተተኪ አባላት በተለይም ለሕጻናት መንፈሳዊ ሕይወት የቃልና የሕይወትም የተግባር መምህር መሆን እንዳለብን ተናግረዋል።

የሰንበት ት/ቤታችን ሰብሳቢ ታምራየሁ ግርማም የሰንበት ት/ቤቱን አገልግሎት እና መርሐ ግብራት በዝርዝያ ለብጹነታቸው በማስረዳት በፈጣሪ ቸርነት በእመቤታችን ረድኤት በቅዱስ ገብርኤል ጠብቆትና በብጹዕነታቸው ቡራኬ ጸሎት እርዳታ ታግዘን በዕለቱ  የተሰጠንን ኋላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በሰንበት ት/ቤቱ ስም ቃል እንገባለን በማለት የሰ/ት/ቤቱን  በመወከል መልእክቱን ለብጹዕነታቸው አስተላልፏል ።

በመጨረሻም ብጹዕነታቸውም ቡራኬ ሰጥተው እና ማጠቃለያ ጸሎት አድርገው የመርሐግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

   👉 መራሒ ሚዲያ 👇

@SaintGebrielSundaySchool
2024/05/08 09:56:50
Back to Top
HTML Embed Code: