Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 " የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ነው ! " - የምክር ቤት አባል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ይገኛሉ። እስካሁን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ከኑሮ ውድነት፣ ከመንግሥት ሰራተኞች…
#HoPR🇪🇹

" በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው ? " - የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉና አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ምን ጠየቁ ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" የመንግሥት ሰራተኞች እና ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል በተደጋጋሚ በአሁን ሰዓት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዳቃታቸው ይገልጻሉ።

እንደመገለጫም ፦
- እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን አብልቶ ማሳደር
- የቤት ኪራይ መክፈል
- የልብስ እና የትምህርት ወጪዎችን መሸፈን ዳገት እንደሆነባቸው ይዘረዝራሉ።

ከዚህ ጋር በተገናኘ የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ መሰረታዊ የዳቦ ጥያቄያቸው እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሆኖም ግን መንግሥት ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ የፖለቲካ ስም በመስጠት ጥያቄያቸው ሳይፈታ ተዳፍኖ ቀርቷል።

ለመሆኑ መንግሥት ' ድሃ ተኮር ኢኮኖሚ ሪፎርም አራማጅ ነኝ ' እያለ የመንግሥት ሰራተኛውን እና ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል ስራ የሚጀምረው መቼ ነው ?

ከዚህ ጋር በተገናኘ አጠቃላይ የኢኮኖሚው አካሄድ ላይ ጥያቄ ይነሳበታል። የኢኮኖሚክ ባላንሱ ችግር እንዳለበት ይነሳል። የተለያየ ጥረት እየተደረገ ነው inflation (የዋጋ ግሽበት) ለመቀነስ ግን IMF እኛን የሚደግፍ ኢኮኖሚክ ሪፎርሙን፣ ዓለም ባንክ ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን  ሳይቀር በጣም ፈተናዎች እንዳሉ ከኢኮኖሚክ ሪፎርሙ ጋር በተያያዘ ይገልጻሉ። ለምሳሌ ፦
° ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዳለ፣
° ገበያ ተኮር ምንዛሬ በመጠቀማችን ምክንያት የብር ዶላር ልዩነት ከፍተኛ መሆኑ፣
° በህዝብ ስም የተበደርነው ዕዳ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ፣
° ከፍተኛ ስራ አጥነት እንዳለ በአሁን ሰዓት በየአመቱ 2 ሚሊዮን ስራ አጦች እንደሚቀላቀሉ ይገለጻልና ይሄንን ችግር እንዴት ነው የምንፈታው በተለመደው አዙሪት ውስጥ ነው ወይ የምንቀጥለው ? ከኢኮኖሚ ችግሩ ለመውጣት ምን የታሰበ ነገር አለ ?

ሁለተኛ በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ የሰማይ ቤትን ታሳቢ ያደረጉ መናኞች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈጸመ ለሞት፣ ለድብደባ እና እንግልት ሲዳረጉ ይታያል። ለመሆኑ መንግሥት እንደዚህ ያለ ተደጋጋሚ የንጹሃን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት ፣ ከድብደባና እንግልት ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ኃይል የማይመድበው ለምንድነው ?

ሶስተኛ መንግሥት ከፋኖ ፣ ከሸኔና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ጋር ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ (ከፖለቲካ እስረኞች ጋር ለተገናኘ በተደጋጋሚ ያቀረብነው ጥያቄ ነው) ጅምላ ጭፍጨፋ የመሩ የህወሓት ባለስልጣናት በቶሎ ነበር የተፈቱት ነገር ግን እንደዚህ አይነት ተሳትፎ (involvement) የሌላቸው የአማራ ፖለቲከኞች ፣ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች ከታሰሩ 2 ዓመት ሞልቷቸዋል።

የፍትህ ስርዓቱ በጣም ዘገምተኛ ነው፤ ቶሎ እየተፈታ አይደለም ፤ ምንም ምስክርም እየተሰማባቸው አይደለም በጄኖሳይድ ወይም በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሆኑ የሚያመለክት ነገር የለም ግን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። አማራ ክልል ብቻ አይደለም ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከተለያዩ የምክር ቤት አባላት ጋር ባደረግነው ንግግር እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ችግር አለ። ቶሎ ፍትህ የማግኘት ችግርን በኢትዮጵያ መቼ ነው የምንቀርፈው ? የረፈደ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራልነውና።

ሌላው ድሮንን ጨምሮ በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጭምር ንጹሃን እንዳይጠፉ የምክር ቤት አባላት፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ፣ኃያላን መንግሥታት አሜሪካን ጨምሮ ስንወተውት ቆይተናል። የተለያዩ መግለጫዎች ኃያላን መንግሥታት ጭምር ሲያወጡ ይታያል። ሆኖም ግን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የመሳሰሉ ክልሎች ላይ የጸጥታ ችግሩ እስካሁን አልተቀረፈም።

ከዚህ ጋር በተገናኘ ' አግዙን ' ባሉን መሰረትም ሰላሙን ለማምጣት ወደ እርሶ ቢሮ መልዕክተኛ ብንልክም አልተሳካልንም። እንጂ እኛ ፖለቲከኞች፣ ተቃዋሚዎች ችግር መፍጠር ሳይሆን ችግሩ እንዲፈታ ቀረብ ብለን መነጋገር እንፈልጋለን ነገር ግን ያን መድረክ ልናገኝ አልቻልንም። ከዚህ ጋር በተገናኘ ምን የሚሉን ነገር አለ ሰላሙን ለማምጣት።

አራተኛ በተለያዩ አዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሎች ትላልቅ የክልል ከተሞች ላይም ይሄ ችግር አለ ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ መኖሪያ ቤት ሰርተው ፣ ውሃና መብራት አስገብተው፣ በርካታ የልማት ስራዎችን የሰሩ፣ መንግሥትዎን በድጋፍ ያገለገሉ ዜጎችን ያለምንም ምትክ ቤት ፣ መሬትና የገንዘብ ካሳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አቤቱታቸውን ይዘው የተለያዩ ቢሮዎች ቢሄዱም ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኗል።

እነዚህ ሰዎች የሚያመለክተት ' ነገር ከ1998 ጀምሮ ነው ህገወጥ ከሆንን እናፍርስና በኮንዶሚኒየም እንደራጅ ' ስንል አይ ' እናተ ሰነድ አልባ ናችሁ እንጂ ህገወጥ አይደላችሁም በቅርቡ ህጋዊ እናደርጋችኃለን ' ተብለው እንደነበር ነው የሚያስታውሱት። በቅርቡ ያወጣነው አዋጅ አለ ከከተማ መሬት ጋር በተገናኘ ከ2004 ዓ/ም በፊት የተሰሩ ህገወጥ ቤቶች ህጋዊ እንደሚሆኑ የሚያመለክትና እነዚህን ሰዎች ለምድንነው በአግባቡ የማይስተናገዱት። የተለያዩ ቢሮዎች ሄደዋል አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም እርሶን እንድጠይቅላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሁለት ቀበሌ የተፈናቀሉ ከሰነድ ጋር ነው ያቀረቡልኝ። አመሰግናለሁ። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2❤2.22K👏267🙏97😭35😡21🤔14🥰11🕊11😢8😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 " በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው ? " - የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉና አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ምን ጠየቁ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማዕድን አቅም ያላት ሀገር ናት፤ በአፍሪካ ውስጥ ትላልቅ የማዕድን አቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት ፤ እስካሁን የትክረት የአመራር፣ የዕይታ ማነስ ስለነበረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማገዝ ይችል ነበር። አሁን እያነቃቃነው ነው።

ወርቅ ባለፈው ዓመት በዚህ ዓመት 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገነዋል። 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ዓመት ያገኘነውም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ስለሰራን ነው። ይህ በየትኛውም ዘመን ያልነበረ ስኬተ ነው። ሌላው ጋዝ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ ላይ የሚሰማሩ ኩባንያወች ፈቃድ አውጥተው ወደ ተጨባጭ ስራ አይገቡም ነበር።

ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዚህም ሰርቶ አዳሪ እንጂ አውርቶ አዳሪ አለመሆናችንንም በተከታታይ እያሳየን እንቀጥላለን። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል። "

Credit : PMO Ethiopia

@tikvahethiopia
😡917❤714😭54👏33🤔31🙏15🕊14😱13💔10🥰8😢5
" በዚህ ዓመት ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ አግኝተናል !! "

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦

" ዩኒቲ ፓርክ ፣ ፍሬንድሺፕ ፣ ሳይንስ ሙዝየም ፣ ናሽናል ፓላስ ብቻ በዚህ ዓመት 1.5 ሚሊዮን ሰው ጎብኝቷል። ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል።

አስቡት ' ዩኒቲ ፣ ፍሬንድሺፕ ለምን ይሰራል ? ' ሲባል የነበረበትን ዘመን። በአንድ አመት 1.5 ሚሊዮን ሰው መሄጃ አዘጋጀንለት ማለት ነው። ያ አንድ ሚሊዮን ሰው ዩኒቲ ባይኖር ፣ ፍሬንድሺፕ ባይኖር ወይ ጫት ላይ ነው ወይ ድራፍት ላይ ነው።

ባለፉት ጥቂት አመታት በነዚህ ቦታዎች 13. 5 ሚሊዮን ሰው ጎብኝቷል። ሳይንስ ሙዝየም፣ ፍሬድሺፕ እና ዩኒቲ። ይሄ የተመዘገበና ብር የሚከፍል ነው። የሚታወቅ ቁጥር ነው።

አዲስ አበባ ላይ ባለው ዳታ በዚህ ዓመት ያለው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስት እድገት በጣም ከፍተኛ ነው። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡1.27K❤774👏67🤔51😭41😱27😢13🕊13🥰10💔7🙏4
TIKVAH-ETHIOPIA
" በዚህ ዓመት ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ አግኝተናል !! " ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦ " ዩኒቲ ፓርክ ፣ ፍሬንድሺፕ ፣ ሳይንስ ሙዝየም ፣ ናሽናል ፓላስ ብቻ በዚህ ዓመት 1.5 ሚሊዮን ሰው ጎብኝቷል። ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል። አስቡት ' ዩኒቲ ፣ ፍሬንድሺፕ ለምን ይሰራል ? ' ሲባል የነበረበትን ዘመን። በአንድ አመት 1.5 ሚሊዮን ሰው መሄጃ አዘጋጀንለት…
#EthiopianAirlines🇪🇹

የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ተጨማሪ 13 አውሮፕላኖችን መግዛቱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

አሁን ላይ አየር መንገዱ ያሉት አውሮፕላኖች ብዛት 180 መድረሱን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ብቻ 6 አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ መዳረሻውን ወደ 136 ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በዚህ ዓመት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከ19 ሚሊዮን ሰው በላይ ማጓጓዙን አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.07K😡409👏67😭43🕊21🙏19😱13🤔12🥰6💔5😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ተጨማሪ 13 አውሮፕላኖችን መግዛቱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። አሁን ላይ አየር መንገዱ ያሉት አውሮፕላኖች ብዛት 180 መድረሱን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ብቻ 6 አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ መዳረሻውን ወደ 136 ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል። አየር መንገዱ በዚህ…
#HoPR🇪🇹

" 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዚህ ቀደም የነበሩ መንግስታት የተበደሩትን ገንዘብ ያለፉትን ሶስት እና አራት አመታት ተደራድረን የእዳ ሽግሽግ እንዲኖር አድርገናል የገንዘብ ሚንስቴር በትላንትናው እለት በፈረንሳይ ተፈራርሟል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

የበጀት አመቱን አፈጻጸም በየዘርፉ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣በፋይናንስ እና በቱሪዝም ዘርፍ ተመዘገቡ ያሏቸውን ለውጦች ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነፈው አመት የ8.1 በመቶ እድገት ኢትዮጵያ ማስመዝገቧን በመግለጽ ዘንድሮ 8.4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በየዘርፉ አስመዘገብናቸው ስሏሏቸው ለውጦች ምን አሉ ?

ግብርና

- በግብርና ዘርፍ 6.1 በመቶ እድገት እንዲያመጣ ታቅዶ ነው እየተሰራ ያለው።

- ባለፈው አመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ችለን ነበር ዘንድሮ 31.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል።

- ባለፈው አመት በሁሉም አይነት የእርሻ ምርቶች 1.2 ቢሊየን ኩንታል ምርት ነበር የሰበሰብነው ዘንድሮ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ችለናል ይህም 24.7 በመቶ ጭማሪ አለው።

- ከ100 በላይ አነሰተኛ እና መካከለኛ ግድቦች ይሰራሉ።

- 50 ሺ ሄክታር አሲዳማ መሬት ታክሞ ወደ እርሻ ገብቷል።

ኢንዱስትሪ

° 12.8 በመቶ እድገት እንደሚያመጣ ታስቦ እየተሰራ ነው።

° የኢንዱስትሪው ሴክተር የኢነርጂ ፍላጎት 40 በመቶ ጨምሯል።

° የሲሚንቶ ምርት 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

° የብረት ውጤቶች 18 በመቶ አድጓል።

° የመስታወት ፋብሪካ በቂ አልነበረም በአመት 600 ሺ ቶን የሚያመርት የመስታወት ፋብሪካ እየተሰራ ይገኛል ጥሬ እቃውንም ከሃገር ውስጥ ይጠቀማል ታህሳስ ወይም ጥር ላይ ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ማእድን

- ባለፈው አመት 4 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል ዘንድሮ 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል።

- አምና በወርቅ ኤክስፖርት 300 ሚሊየን ዶላር ዘንድሮ 3.5 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።

- ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥለው አመት የመጀመሪያውን የጋዝ ምርት ለገበያ ታቀርባለች።

- ምክር ቤቱ ከእረፍት ሳይመለስ ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ መስራት ትጀምራለች ከ 40 ወራት በኋላም ግንባታው ይጠናቀቃል።

- የማዕድን ዘርፍ በጋዝ ፣በወርቅ እና በማዳበሪያ የተለያዩ እድገቶችን እያመጣ ነው።

ቱሪዝም

° 1.3 ሚሊየን የውጭ ቱሪስት ኢትዮጵያን ጎብኝቷል።

° ዩኒቲ ፣ፍሬንድ ሺፕ ፣ ፓላሱን እና ሳይንስ ሙዚየምን ብቻ ከ 1.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጎብኝቶታል ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል።

° አየር መንገድ በሃገር ውስጥ እና በውጭ 19 ሚሊየን ህዝብ አጓጉዟል።

ፋይናንስ

- ብድር ከአምና 75 በመቶ ጨምሯል የግሉ ሴክተር 80 በመቶ ድርሻ አላቸው።

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 900 ቢሊየን ብር እዳ የነበረበት ተቋም ነበር እዳው ከባንኩ ወደ መንግሥት በመዘዋወሩ እና ለባንኩም 700 ሚሊየን ዶላር ድጎማ በመሰጠቱ ተቋሙንም ሆነ ሴክተሩም ማዳን ተችሏል።

- የሞባይል መኒ ተጠቃሚ 55 ሚሊየን ደንበኛ ደርሷል።

- ወደ 11 ሚሊየን ደንበኞች 24.5 ሚሊየን ብር ብድር በሞባይል መኒ አግኝተዋል።

ኤክስፖርት

° 5.1 ቢሊየን ዶላር ከኤክስፖርት ገቢ እናገኛለን ብለን አቅደን 8.2 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.03K😡448🤔42🕊18😭17👏11🥰7🙏3💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 " 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዚህ ቀደም የነበሩ መንግስታት የተበደሩትን ገንዘብ ያለፉትን ሶስት እና አራት አመታት ተደራድረን የእዳ ሽግሽግ እንዲኖር አድርገናል የገንዘብ ሚንስቴር በትላንትናው እለት በፈረንሳይ ተፈራርሟል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። የበጀት አመቱን አፈጻጸም…
#Ethiopia 🇪🇹
#GERD 🇪🇹

" መስከረም ላይ ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴን እናስመርቃለን !!! "

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ህዳሴ አልቋል። ህዳሴን እናስመርቃለን። ህዳሴ ከመመረቁ በፊት ' ብንረብሽ ' ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ ፤ እናስመርቃለን።

ህዳሴን እንዳይመረቅ ለማድረግ የሚያስችል ነገር አሁን የለም። የሚመረቀውም አሁን ነው ነገ ክረምቱ ሲያልቅ።

ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ህዳሴ ለሱዳን ህዳሴ ለግብፅ በረከት ነው። በፍጹም ጉዳት አያመጣባቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልማት ልማታቸው ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኢነርጂ ለሁሉም ጎረቤቶች የሚዳረስ ነው።

የኛ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን የሚጎዳ ቢሆን ኖሮ ቱርካና አጀንዳ አይሆንም ነበር። ታስታውሳላችሁ ግቤ 3 ሲሰራ 'ቱርካና ይደርቃል የሚል ከፍተኛ ችግር ነበር። እንኳን ሊደርው ከግድቡ በኋላ ይኸው ሞልቶ እያስቸገረ ነው ያለው።

አሁንም ግብፅ ብትሄዱ የግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም። ወደፊትም ኢትዮጵያ እስከበለጸገች ድረስ እስካለች ድረስ የግብፅ ወንድሞቻችንን ጉዳት እኛ አናይም ተባብረን ከወንድሞቻች ጋር ማደግ እንፈልጋለን።

ግብፅ እንድትጎዳ ፣ ሱዳን እንድትጎዳ አንፈልግም። ኢነርጂውን በጋራ እንጠቀማለን ውሃውን በጋራ እንጠቀማለን ልማት በጋራ ይመጣል። ንግግር ካስፈለገ እንነጋገራለን ችግር የለም።

እኛ ለረጅም ጊዜ ስናነሳ የነበረው ' አትስሩ ' አትበሉን ነው ያልነው እንጂ በኛ ገንዘብ በኛ ምድር የሚሰራውም ስራ አታግዱ ነው ያልነው እንጂ ያን እስካልከለከሉ ድረስ አሁንም ከግብፆች ጋር ለመነጋገር፣ ለመደራደር ፣ ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት፤ምንም ችግር የለብንም።

በእርግጠኝነት የምናገረው ህዳሴ ለግብፅም ለሱዳንም ጉዳት አያመጣም።

በዚሁ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የስልጣን ባለቤት ይህ የተከበረው ምክር ቤት ስለሆነ ለግብፅ መንግሥት ፣ ለሱዳን መንግሥት እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታት በሙሉ መስከረም ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ግብዣ አቀርብላቸዋለሁ።

የጋራ ሃብታችን ነው ፤ በጋራ እናስመርቀዋለን በጋራ እናየዋለን፣ የሚታዩ ጉዳዮች ካሉ በጋራ እናያለን።

ከድርቅ ጋር ተያይዞ ግብፅ የሚነሳው ነገር ' ድርቅ በሚሆንበት ሰዓት ግብፅ ትጎዳለች ' ነው ፤ ድርቅ የሚባለው ኢትዮጵያ ነው ኢትዮጵያ ከደረቀች ውሃዋ የለም  ማለት ነው እዛ አይደለም ድርቅ የሚባለው፤ ኢትዮጵያ ደግሞ እንዳትደርቅ Green Legacy (አረንጓዴ አሻራ) እየሰራን ነው እኛ አንደርቅም ማለት ነው እኛ ዝናብ ካገኘን እኛም ግብፅም ሱዳንም ሌሎቹም ይጠቀማሉ። በቅንነት አይተን በጋራ ለልማት እንድንሰራ አደራ እላለሁ። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2.37K😡337👏127🙏55🤔36🕊26😱17😭14🥰13😢9💔3
የፌዴራል መንግሥት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 ዓ/ም የፌዴራል መንግስት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር አድርጎ አፅድቋል።

@tikvahethiopia
😡1.13K❤509🤔133😭81😱46👏45🕊36🙏27😢26💔12🥰7
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia 🇪🇹 #GERD 🇪🇹 " መስከረም ላይ ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴን እናስመርቃለን !!! " የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ? " ህዳሴ አልቋል። ህዳሴን እናስመርቃለን። ህዳሴ ከመመረቁ በፊት ' ብንረብሽ ' ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ ፤ እናስመርቃለን። ህዳሴን እንዳይመረቅ ለማድረግ የሚያስችል ነገር አሁን የለም። የሚመረቀውም አሁን ነው…
" በዝቋላ አንድ አባት ተገድለዋል ማን እንደገደላቸው እየተጣራ ነው ያለው á‰°áŒŁáˆ­á‰ś ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ "- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባለው ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም “የሸኔ ታጣቃዎች” ባህታውያን አባቶች በሚኖሩባቸው ዋሻዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገዳሙ ማሳወቁ ይታወሳል።

ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ አባት መገደላቸውን እና ሟቹ አባት ባህታዊ አባ ኃይለሚካኤል እንደሚባሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከገዳሙ ባገኘው መረጃ መዘገቡ ይታወሳል።

በተደጋጋሚ በገዳሙ እያጋጠመው ስላለው የመነኮሳት ግድያ መንግስት ለምን ማስቆም ተሳነው ሲሉ በዛሬው እለት የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

የአብን አባሉ አቶ አበባው " በዝቋላ ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው " ሲሉ ጥያቄያቸውን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ በዝቋላ አንድ መናኝ መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝርዝር በሰጡት ምላሽ ምን አሉ ?

" ' መሻቴን ፍላጎቴን በሃይል ማስፈጸም እችላለሁ ' የሚሉ ሃይል በብቸኝነት የመጠቀም ስልጣን የመንግስት ብቻ መሆኑን የማይቀበሉ ሰዎች ናቸዉ።

እንዳሉት በዝቋላ አንድ አባት ተገድለዋል ማን እንደገደላቸው እየተጣራ ነው ያለው  ተጣርቶ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

የሃይማኖት ተቋማት የታጠቁ ሽፍቶች መሸሸጊያ ከሆኑ እንደዚህ አይነት አደጋ ሊፈጠር ይችላል የሃይማኖት ቦታ የሃይማኖት ብቻ መሆን አለበት ሲሸሹ የሚደበቁበት ከሆነ ሲከፋቸው ገድለው ሊሄዱ ስለሚችሉ።

የዝቋላው ምን ይገርማል 12 አመት ተምሮ ፈተና ሊፈተን የሚሄድ ሰው ላይ የሚተኩሱ ሰዎች ዝቋላ ላይ አንድ አባት ላይ ቢገድሉ ምን ይገርማል።

የግድያው እሳቤ ነው ችግር ያለው ፈተና አትፈተን፣ ማዳበሪያ አትውሰድ ፣ትምህርት አትማር ብሎ የሚገድል ሰዉ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ የትም ሞት አለ ማለት ነው።

'ልብ ሲያቅ ገንፎ ያንቅ ይባላል'  ልባችን ያውቀዋል እነማን እንደሆኑ፤ ድብብቆሽ አይደለም። እነማን ገዳይ እንደሆኑ ግልጽ ነው። 'ልብ ሲያቅ ገንፎ ያንቅ' የመባለው እያወቅነው የምናግበሰብሰው ጉዳይ ሲሆን ነው።

ግድያ ሽንፈት ብቻ ነው የሚያመጣው በመግደል አይሳካልኝም ብሎ ማመን ያስፈልጋል። ... በሃይል ፍላጎትን ማስፈጸም ማለቂያ የለውም መቆም አለበት። " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡3.24K❤1.36K😭192💔86🕊57🙏36🤔33😢32👏25😱18🥰7
TIKVAH-ETHIOPIA
" በዝቋላ አንድ አባት ተገድለዋል ማን እንደገደላቸው እየተጣራ ነው ያለው á‰°áŒŁáˆ­á‰ś ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ "- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባለው ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም “የሸኔ ታጣቃዎች” ባህታውያን አባቶች በሚኖሩባቸው ዋሻዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገዳሙ ማሳወቁ ይታወሳል። ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ አባት መገደላቸውን…
" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል።

" ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ ምሁራን እና ወጣቶች ምን ይጠበቃል ? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?

" የሁሉም እምነት አባቶች እዚህ ተወካይዎች አላችሁ፣ ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም።

ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ ኤምባሲዎች ውጊያ እንዳይጀመር አሁን ሚናችሁን ተወጡ ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ይበላሻል ነገር።

በእኛ በኩል በትግራይ ምድር እንድ ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለንም፣ ከቻልን ማልማት ነው የምንፈልገው።

ትግራይ ላሉ ሃይሎች ለትግራይ ህዝብም፣ ለኢትዮጵያ ህዝብም መታወቅ ያለበት ጦርነት አያስፈልገንም በሰላም እና በውይይት ጉዳያችንን መፍታት ይቻላል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
❤1.03K😡402🕊89😭24🤔23🙏14💔11👏10😢10🥰1
2025/07/13 15:17:18
Back to Top
HTML Embed Code: