TIKVAH-ETHIOPIA
“ ዜጎች ብዙ ወጪ ወጥቶ ከያሉበት ተሰባስበው ወደ ሀገር እንዲመጡ ጥረት ይደረጋል የዛኑ ያክል ደግሞ በተለያየ ቀዳዳ ሰዎች ሲወጡ ይታያል ” - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በማይናማር ከእገታ ወጥተው በካምፓኒ የሚገኙ፣ አሁንም በእገታ ያሉ ወገኖች መንግስት ጓደኞቻቸውን እንደመለሰው ሁሉ እነርሱንም እንዲመልሳቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እየተማጸኑ ይገኛሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር…
" የወጣቶቹ ህይወት በአደጋ ላይ ነው " - አስተባባሪ
ማይንማር ውስጥ አሁንም በአጋቾች እንደተያዙ ነው የተባሉ 42 ኢትዮጵያውን እጣ ፈንታ አለመታወቁን በማይንማር የተጎጂ ወጣቶች ቤተሰቦች አስተባባሪ ተናግረዋል።
" ከአጋቾች ነጻ ከወጡ 751 ኢትዮጵያውያን የመጨረሻዎቹ 49 ዜጎች አገራቸው ገብተዋል " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የተናገሩት አስተባባሪዋ ወ/ሮ አበበች ሲመል " ሆኖም ከአጋቾቻቸው ካምፕ መውጣት ያልቻሉ 42 ኢትዮጵያውያን ግን አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ " ብለዋል።
" ከአጋቾች እጅ መውጣት እየፈለጉ ከዚህ ቀደም ሌሎች ሲወጡ አጋቾቹ ያስቀሯቸው 42 ወጣቶች አሁን ላይ በሶስት ኩባንያዎች ውስጥ በጉልበት ብዝበዛ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
በፖሊስ እጅ ያልገቡ የእነዚህ ወጣቶች ህይወት በአደጋ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ወጣቶቹ የመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ያላቸው እንዲሁም ከመካከላቸው የህክምና ዶክተሮች እንደሚገኙበትም የተጎጂ ቤተሰብ አስተባባሪዎቹ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። ወደ ማይናማር የሄዱትም " ከፍተኛ ደመወዝ ታገኛላችሁ " ተብለው ተታለው ነው።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba #እንድታውቁት
ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ሴንተር ወይም በሜክሲኮ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር ላይ አስቸኳይ የጥገና ሥራ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
በዚህም ምክንያት ፦
- በሜክሲኮ፣
- በአፍሪካ ህብረት፣
- በቄራ፣
- በገነት ሆቴል፣
- በደንበል፣
- በመስቀል ፍላወር፣
- በወሎ ስፈር፣
- በመስቀል አደባባይ በባምቢስ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጦ እንደሚቆይ አሳውቋል።
የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ነዋሪዎች ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
#EEP

Photo
" ሰባት አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል። አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ተገድሏል፤ ተሳፋሪዎችም ታግተዋል " - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
በአማራ ክልል ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም፣ "ከ20 በላይ አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገደሉ" በተባለበት የጎንደር መስመርና በአካባቢው ከጥቃቱ በኋላም በታጣቂዎች የግድያና እገታ ጥቃት መፈጸሙን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማኀበሩ በሰጠን ማብራሪያ፣ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ/ም፣ " አምስት ሹፌሮች ታግተዋል። ስድስተኛው በዚሁ እለት ከእገታ አምልጦ ነበር ከመሪው ተደብቆ፤ 100 ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ ግን ሌላ ቦታ ገደሉት " ብሏል።
" ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ/ም ከጎንደር መተማ መንገድ ሁለት ሹፌሮች ታግተዋል። በቀን 16 የግድያ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ" ያለው ማኀበሩ፣ "ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ታግተዋል። አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ተገድሏል። ተሳፋሪዎችም ታግተዋል " ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ሁለቱ ሹፌሮች የታገቱት ሰሞኑን ከ20 በላይ ሹፌሮች ተገደሉ የተባለበት መንገድ፣ አምስቱ ሹፌሮች በሌላኛው በአብራሂጅና ሶረቃ መካከል፣ አንዱ ሹፌር የተገደለውና ተሳፋሪዎች የታገቱት ደግሞ ደለሎ አካባቢ መሆኑን ማኀበሩ ገልጿል።
" አሽከርካሪዎችን 'ችግር ባለባቸው አካባቢዎች አትሂዱ' ብለናቸዋል፤ አለመሄድ ቢቻል ውጤት ይመጣ ነበር። በቀን 16 ሹፌሮች ተገድለው እያለ በማግስቱ ሄደው ነው የታገቱት። በአሊ ዶሮ መንገድ ግድያ የቀረው ማታ መንጓዝ ቀርቶ ነው " ሲልም ገልጿል።
በሌሎች አካባቢዎች ያለው እገታና ግድያ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ስንጠይቀውም፣ "ከደብረታቦር ጋይንት ባለው መንገድ ቀድሞ መሻሻሎች አሉ እየተባለ ነው። ኦሮሚያ ክልልም የሌሊት ጉዞ ስለቀረ ብዙ ነገሩ ሴፍ ሆኗል" ሲል መልሷል።
በቀን 16 የግድያ ጥቃት የተፈጸመበት መንገድ በጸጥታ ችግር ለወራት ተዘግቶ አሽከርካሪዎች ለ140 ኪሎ ሜትር መንገድ አላስፈላጊ ጉዞ ተዳርገው መቆየታቸውን ማኀበሩ አስታውሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ጋምቤላ
" አራት ሴቶች በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነዉ ተወስደዋል " - የጋምቤላ ክልል ፖሊስ
➡️ " በአንድ ዓመት ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በታጣቂ ቡድኑ ተወስደዋል ! "
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በትናትናው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አከባቢ በአኝዋክ ብሔረሰብ ዞን በጎጊ ወረዳ ተዶ በሚጠራዉ አከባቢ የሙርሌ ታጣቂዎች አራት ሴቶችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉን ተናግረዋል።
" ሙርሌ" የተሰኘዉ የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድኑ ከ14 እስከ 27 ዓመት ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ አራት ሴቶችን ወደ ፒኝውዶ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተኩስ በመክፈት አፍኖ እንደወሰዳቸዉ የገለፁት ኮሚሽነሩ አስቀድሞ በአከባቢዉ የነበሩ የጎግ ወረዳ ፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎችን በኋላም የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ መዋቅር የጋራ ግብረ ሃይል ታፍነዉ የተወሰዱትን ለማስመለስ ቡድኑን እየተከታተሉ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል።
በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሰው የሙርሌ ታጣቂ ቡድን ከጋምቤላ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በተደጋጋሚ ሰዎችን እያፈነ እንደሚወስድ የተናገሩት ኮሚሽነር ኦጉሉ በፀጥታ ሃይሎች ኦፕሬሽን ከተመለሱት በስተቀር አብዛኞቹን እንደሚገድልና ሱዳን ወስዶ ለጉልበት ስራ እንደሚሸጣቸዉም መረጃዎች እንደሚደርሷቸዉ ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ አክለዉም በ2017 ዓ/ም ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በነዚህ የታጠቁ ቡድኖች ተዘርፈዋል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

ወጋገን ባንክ !
በ4% ጉርሻ ከወጋገን ባንክ ይመንዝሩ! ይቀበሉ!
ከውጭ ሀገር በሃዋላ ድርጅቶች በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከወጋገን ባንክ ሲቀበሉ እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ከዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ ላይ የ4 በመቶ ጉርሻ በማከል ገንዘብዎን በፍጥነት እናስረክብዎታለን፡፡
💰 ይፍጠኑ የጉርሻው ተቋዳሽ ይሁኑ!
☎️ ለበለጠ መረጃ ወደ ወጋገን ባንክ የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ 866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ!
ከስር የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀሉ!
𝖩𝗈𝗂𝗇 ➥ Telegram 📲 Facebook
🌍 https://linktr.ee/WegagenBank
📩 [email protected]

#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
የቴክኒካል ስራዎች (Technical Skills) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
ስልጠናዎቹ:
👉Building Electrical Installation, CCTV Camera Installation and Security Solutions
👉 Computer Maintenance, Networking, Office Machine Maintenance and Home Appliance
👉 Mobile Maintenance
👉 Industrial Machine Installation and Maintenance
ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Instagram Telegram Tiktok Linkedin

ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም #የአረንጓዴ_አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia