Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን ደስ አላችሁ ! Class of 2017 Commencement! በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው። ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡ ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡…
#AAU #JIGJIGA #KABRIDAHR

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ፦
➡️ 3 ሺህ 334 የመጀመሪያ ዲግሪ፣
➡️ 2 ሺህ 859 የሁለተኛ ዲግሪ፣
➡️ 304 የሦስተኛ ዲግሪ እና 352 የስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ በአጠቃላይ 6 ሺህ 849 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተገኝተው ነበር።

በሌላ በኩል በዛሬው እለት የጅግጅጋ እና ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,500 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የመጡ 13 ተማሪዎች ይገኙበታል።

ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከ1,100 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

እንኳን ደስ አላችሁ !

ፎቶ፦ AAU (FMC)

@tikvahethiopia
795👏106🙏27😡21🥰19🕊15😭6😢1
#ነዳጅ

ከሰሞኑ በተለያዩ ከተሞች ረጃጅም የነዳጅ ሰልፍ በስፋት እየታየ ይገኛል። አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ተሰልፈው እየዋሉ ፤ የስራ ጊዜያቸውም እየባከነ ፤ ስራዎችም እየተስተጓጎሉ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሀዋሳ ከተማ ያለውን ሁኔታ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በሀዋሳ የነዳጅ ረጃጅም ሰልፍ በማደያዎች ለቀናት የቀጠለ ሲሆን ከወትሮዉ በተለየ መልኩ በሰልፉ ውስጥ የነበሩ የውጪ ሀገራት ተሽከርካሪዎችና የመድሐኒት ማመላለሻዎች እንዲሁም የእርሻ ትራክተር አሽከርካሪዎች አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

አሽከርካሪዎቹ ምን አሉ ?

ሳራዋ ማቡዋ ከኬንያ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለመጫን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አሽከርካሪ ሲሆን በነዳጅ እጥረት ምክንያት ከዕቅዱ ዉጪ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ለመቆየት መገደዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግሯል።

" ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመጫን የመጣሁትን ምርት ከጫንኩ በኋላ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ማደያ ብመጣም ረጅም ሰልፍ በመኖሩ እንድሰለፍ ተነግሮኝ ሰልፉ ሲቀል እመለሳለሁ ብዬ ወደ ማደሪያዬ በመሄድ በማግስቱ ስመለስ ሰልፉ ብሶበት ተሰልፌ ለማደር ተገድጃለሁ " ብሏል።

" ኢትዮጵያ ዉስጥ መቆየት ሰላም የሚሰጠኝ ቢሆንም በነዳጅ ምክንያት የዘገየኋት ሶስት ቀን በካምፓንያችን አሰራር መሰረት ለቅጣት ይዳርገኛል " ሲል ገልጿል።

ሮባ መሐመድ እና ሬድዋን ሀሰን የትራክተር ሹፌሮች ናቸው።

ድርጅታቸዉ በጌዴኦ ዞን ዲላ አከባቢ ካለዉ የእርሻ ኢንቨስትመንት ወደ አርሲ ዞን ወዳለዉ የእርሻ ቦታ እንዲሄዱ አዟቸው እየሄዱ ነዳጅ ስላለቀባቸዉ በሀዋሳ ሶስት ማደያዎች ተዟዝረዉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ቢጠይቁም እንዳተፈቀደላቸዉና በዚህም ምክንያት ስራ እንደተስተጓጎለባቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" በእርሻ ወቅት አንድና ሁለት ቀን ትልቅ ዋጋ አላቸዉ " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በነዳጅ ምክንያት ዘር ለመዝራት የተያዘዉ ቀጠሮ መስተጓጎሉን አስታዉቀዉ እንደሁኔታዉ ቅድሚያ ሊሰጣቸዉ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በመለየት ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ማድረግ ቢቻል መልካም ነዉ ብለዋል።

" ለልዩ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅዲሚያ መስጠት አለበት " ያለን ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የመድኃኒት ማመላለሻ መኪና ሹፌር " ይህ ካልሆነ የነዳጅ ምርቶች እጥረት በሚኖርበት ወቅት ችግሩን ያባብሰዋል " ሲል ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ባሰባሰባቸውን መረጃዎች በየማደያው ከፍተኛ የነዳጅ ሰልፍ አለ።

አንዳንድ ማደያዎች ደግሞ " ነዳጅ የለም " የሚል መልዕክቶችን ለጥፈው እየተስተዋሉ ነው።

ከዚህ ቀደም በተሻለ ሁኔታ የሚገኘው ናፍጣ አሁን ላይ ማግኘት ከባድ ሆኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
635😢53🕊25🙏21😭21🥰5😡5💔4🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
" በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ፤ ነዳጅ እያለ ዋጋ ይጨምራል በሚል እሳቤ ' የለም ' በሚሉ ማደያዎች ላይ  እርምጃ እንደሚወሰድ ገለጹ። " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ' ነዳጅ ይጨምራል ' በሚል አገልግሎት አቁመዋል። ነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል። መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ…
" የነዳጅ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ሚኒስቴሩ

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
21.21K🙏277🤔60😡59👏42🕊34😢24
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በእጀባ ተማሪዎችን የጫኑ 6 የሚጠጉ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ደርሰው በሰላም ተመልሰዋል " - ሹፌሮች

ከሰኔ 16/2017 ዓ/ም በኃላ ተዘግቶ የሰነበተው የጎንደር መተማ መንገድ ዛሬ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ፤ በከባድ ጥበቃ ታጅበው ደርሰው እንደተመለሱ ሹፌሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በቦታው የነበረው አሽከርካሪ ከጥቃቱ በኃላ መንገዱ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከጎንደር መተማ ከመተማ ወደ ጎንደር ማመላለስ እንደቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ሌላው ለደህንነቱ በመስጋት ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን አሽከርካሪ " እጀባው የተካሄደው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲሆን ብዛት ባላቸው እንደ ስናይፕርና መትረየስ የመሳሰሉ የቡድን መሳሪያዎችን በጫኑ ተሽከርካሪዎች ነው " ብለዋል።

ይህው አሽከርካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገረው  " እኔን ጨምሮ ሌሎች ሹፌሮች በዚህ መስመር አንሄድም ብለን ብናምጽም የጎንደር ከተማ መናህሪያ  ስምሪት ክፍል በግዳጅ እንድንሄድ ስለታዘዝን ለመሄድ ተገደናል " ብሏል።

በእጀባ ተማሪዎችን የጫኑ 6 የሚጠጉ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ደርሰው በሰላም መመለሳቸውን አሽከርካሪዎቹ አክለው ገልፀዋል።

በዚሁ መንገድ ሰኔ 16/2017 ዓ/ም እና 18 2017 ዓ/ም በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 16 አሽከርካሪዎች ፣ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችና ንፁሃን መገደላቸውን የዞኑን አስተዳደርና የአይን እማኞችን ጠቅሰን መረጃ ማካፈላችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
768🙏104🕊59😢37😡19🤔13😱10😭10🥰2
🕊#Peace

" ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም "  - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር 

➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " - የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር 


በአዲስ አበባ ከተማ " ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎችና ፈተናዎች " በሚል ርእስ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

የውይይት መድረኩ CENTRE FOR RESPONSIBLE AND PEACEFUL POLITICS (CRPP) የተባለ ተቋም ከአዲስ አበባ ዪኒሸርስቲ በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እድሪስ " ከመነጋገር እናተርፋለን " ብለዋል።

" ሃሳብ ነው ሃገርን የሚገነባው ስለሆነም ለሃሳብ ክብርና ልዕልና እንስጥ ፤ ጠመንጃንና ጦርነትን እንጠየፍ የትግራይ የፓለቲካ ምህዳር ለወጣቶች እድልና ቅድሚያ ይስጥ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' አንዋጋም ይበቃል ' ማለት ታላቅ ድፍረት ይጠይቃል ከተቻለ ግን ውጤቱ እጅግ አመርቂና ፍሬውም ጣፋጭ ነው። ስለሆነም እርስ በርስ መዋጋት ይብቃ ፤ ሳንገዳደል አሸናፊ የምንሆንበት ሰላማዊ መንገድ እናስቀድም የመገዳደል የመተላለቅ ታሪክ ልንዘጋው ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " የትግራይ ህዝብ አሁንም ከህልውና አደጋ አልወጣም " ብለዋል።

" ችግሮቻችን በውጭ ምክንያቶች እያሳሰበን ከመኖር ውስጣችን በደምብ በመፈተሽ የተወሳሰቡ ችግሮቻችን መፍታት እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ትግራይ ጥቂት አመራሮች ማረምና ማንሳት አቅተዋት በከባድ ፈተና ተዘፍቃ ትገኛለች ፤ ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ለማለፍ ወጣቶችን ወደ መሪነት ማምጣት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልው አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " በማለት አክለዋል።

ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ " ሰላምና ደህንነት ፣ ዲሞክራሲ ግንባታ ፈተና እና እድል " የሚሉና ሌሎች የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በመድረኩ ከትግራይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ስቪክ ማህበራት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ታዋቂ ሙሁራንን ፓለቲከኞች ተገኝተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
607😡104🕊50🙏18🤔13😱9😭9🥰7👏7😢2
2025/07/13 22:34:24
Back to Top
HTML Embed Code: