TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። የሲዳማ ክልል ከሰሞኑ በፀጥታዉ ዘርፍ እየወሰደ እንደሆነ በተገለፀዉ ተቋማዊ ሪፎርም ዛሬ የቀድሞ የክልሉ ኮሚሽነር የነበሩትን ሽመልስ ቶማስ በዛሬዉ ዕለት ከስልጣን ማንሳቱ የተሰማ ሲሆን ማምሻዉን ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል። አዲሱ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ሲዳማ በዞን…
" ' ከእነ እገሌ ጋር ናችሁ ትፈለጋላችሁ ገንዘብ አምጡ ' በማለት የሚያስፈራሩ ተረኛ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እንዳሉ መረጃ ደርሶኛል " - ኮሚሽነሩ
በቅርቡ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት ተስፋዬ ኤቢሶ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት በክልሉ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ይስተዋሉ የነበሩ ህገወጥነትና ሥርዓት አልበኝነትን ለማስተካከል የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አቋም ወስዶ በመስራት ላይ መሆኑን ገለጹ።
" ስልጣንን መከታ በማድረግ ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈጸሙና ሲያስፈጸሙ የነበሩ ባለሥልጣናት፣ ደላሎችንና ኮንትሮባንዲስቶችን እንዲሁም በጸጥታ ተቋም ውስጥ የጥቅም ትስስር በመፍጠር በተደራጀ መንገድ የሌብነት መረብ ከላይ እስከ ታች በመዘርጋት ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ የማቅረብና ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ነው " ብለዋል።
" ለዚህም ስራ የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብር በጣም አስፈላጊ ነዉ " ብለዋል።
ኮሚሽነሩ ' ወሮበሎች ' ሲሉ የጠሯቸው የተወሰኑ ግለሰቦች " የህግ ማስከበሩን ተግባር ሽፋን በማድረግ የህግ አስከባሪዎች በመምስል ግለሰቦችን ' ከእነ እገሌ ጋር ናችሁ ትፈለጋላችሁና ገንዘብ አምጡ ' በማለት ሰዎችን የሚያስፈራሩ ተረኛ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እየተንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው መረጃ ደርሶኛል " ሲሉ አስታውቀዋል።
ኮሚሽነር ተስፋዬ ደቢሶ በወንጀል የተጠረጠረና በህግ የሚፈለግ ሰው ካለ በህጋዊ መንገድ እንጂ የሚያስፈራሩ ሰላዮችን በማሰማራት የሚሰራ እንዳልሆነ ታውቆ ማህበረሰቡ እንዲህ ዓይነት ተግባር ከሚፈፅሙ አካላት እንዲጠነቀቅ እና እንዲህ አይነቱ ተግባር ቢያጋጥመዉ ለፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል በፀጥታው ዘርፍ እያካሄደ ባለ ሪፎርም ከዚህ ቀደም በየደረጃው ለሰላምና ፀጥታ ተቋማት ተጠሪ የነበረዉን የፖሊስ መዋቅር ለየመዋቅሩ አስተዳዳሪዎች እንዲሆን በማድረግ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ መብት አስነስቶ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉ ሲሆን የቀድሞ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነር ከስልጣን ማንሳቱ አይዘነጋም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

❤686👏54🕊27😭17😡11🤔8😢7💔5😱2🥰1
" አብዛኛዎቹ አሰሪዎች ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚገለጹ፤ ትላልቅ ህንጻችን በእንጨት ስካፍሆልዲንግ ሥራ የሚያከናውኑ ናቸው " - ኢሠማኮ
የኮንስትራክሽን ሠራተኞች በሥራ ቦታ በሚገጥማቸው አደጋ በተደጋጋሚ ሞትና ጉዳት እንደሚደርስባቸው ፤ አሁንም አደጋው እንዳልቆመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በየቀኑ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ከእንጨት መወጣጫ ላይ ወድቀው የሚሞቱበትና የሚቆስሉበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፣ ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጥ ተማጽነዋል።
ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ፌደሬሽን (ኢሠማኮ) የኢንደስትሪ ግንኙነትና ማደራጃ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት አቶ ደርቢሳ ለገሰ፣ በአሰሪዎች የጥንቃቄ ጉድለቶች፣ በተቆጣጣሪዎች ደግሞ ክፍተት እየተስተዋለ መሆኑን ገልጸዋል።
ምን አሉ ?
" ከሙያና ደህንነት ጋር በተያያዘ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በግልጽ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች አሉ። ሆኖም ይህንን ለመከታተል የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ተስርቷል ማለት አይቻልም፡፡ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ከመስራት ይልቅ በሚደርሰው አደጋ መዘገብ ነው እንደ ልምምድ የወሰድነው።
የቁጥጥር ባለሙያዎች ቢመደቡም የሚቆጣጠሩባቸው መሳሪያዎች በብዙ ቦታዎች የሉም፡፡ እርምጃዎችን በመውሰድ ሂደትም በሚፈለገው ልክ አልተሰራበትም። ቅድመ ክትትልና እርምጃ መውሰድ ላይ ቢተኮር ኖሮ አሁን እየደረሱ ያሉ ጉዳቶች ባልደረሱ ነበር።
በአሰሪዎችም የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ጥንቃቄ አለማድረግና ቸልተኝነት አለ፡፡ በአንዳንድ ቦታ ይህን ለመከላከል የሚጠይቀውን ወጪ በማስላት የሰውን ጉዳት ቸል የማለት ሁኔታዎች አሉ።
ቀድሞ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ወጪን በመፍራት በሰዎች ሕይወት የሚደርስን አደጋ በዜና ማስተናገድን እንደ አማራጭ እንደ መውሰድ የሚቆጠርበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ትልቅ ችግር አለ። አብዛኛዎቹ አሰሪዎችም ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚገለጹ፤ ትላልቅ ህንጻዎችን በእንጨት ስካፍሆልዲንግ ሥራ የሚያከናውኑ ናቸው" ብለዋል።
በሥራ ቦታ የሚደርሱ አደጋዎች የሚከሰቱት እርምጃ ባለመወሰዱና የቅድመ ክትትል ሥራ ባለመሰራቱ መሆኑን ገልጸው፣ “ይህንን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል፣ መሳሪያዎች ሊኖሩ ይገባ ነበር፡፡ ነገር ግን መሳሪያዎች ለጥቅም ውለው አገልግሎት እየሰጡ ነው ማለት አይቻልም" ብለዋል።
ፌዴሬሽኑ ባለው መረጃ በሥራ ቦታ ላይ ስንት ሰራተኞች እንደሞቱ ስንጠይቃቸውም፣ "አብዛኛዎቹ አባሎቻችን ስላልሆኑ መረጃዎቻቸውን ማግኘት አንችልም” ብለው፣ ፌዴሬሽኑም መረጃ የሚያገኘው ከሥራና ክህሎት በሚቀርብ ሪፓርት መሆኑን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1❤803😭98👏29😢24🙏17😡10💔9🤔8😱4🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ማእከላይ ዞን ፍርድ ቤት የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከነሂጃባቸው እንዲማሩ ወሰነ። የወረዳ ፍርድ ቤት በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ ያስቀመጠው የገንዘብ መቀጮም እንዲቀር ወስኗል። የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 30/2017 ዓ.ም በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ፤ ከአሁን በፊት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች…
#Axum
" የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ በመልበሳቸው ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " - የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት
➡️ " ፈተና ማእከል ደርሳ ሂጃብ በመልበስዋ ምክንያት የተባረረች እንዲት ሙስሊም ተማሪ የለችም ፤ የፈጠራ ወሬና ጥላሸት መቀባት ይቁም " - የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
የአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ ወራትን አስቆጥሯል።
ዛሬ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ሲጀመር የአክሱም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ተነስቷል።
የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት ፥ " የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ክልከላ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " በማለት አስተያየታቸውን በማህበራዊ የትስስር ገፆች አሰራጭተዋል።
" ሂጃብ ከመልበስ ጋር ተያይዞ እንዲት ሙስሊም ተማሪ ከፈተና ማእከል የተባረረች የለችም " በማለት ለተሰራጩት ፅሁፎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) " ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡት 24 ሴት ተማሪዎች በራሳቸው ፍላጎት ሳይመጡ ቀርተዋል " ብለዋል።
" ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ የመፈተን ፍላጎት ካላቸው ሀሙስ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በሚጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና መፈተን ይችላሉ ፤ ከዚህ ውጪ ተማሪዎቹ እንዳይፈተኑ በመከልከል ሆን ተብሎ የሚፈጠረው የማጠልሽት ተግባርና ውሸት ለህዝብና አገር አይጠቅምም " በማለት አክለዋል።
ዛሬ በተጀመረው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 36 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

4❤1.65K😡668💔205😭141👏105🕊60🤔55🙏30🥰28😢25😱24
ቴሌብር ሐዋላ ምርቃቱ ብቻ ያጠግባል!
በቴሌብር ሐዋላ ከባህርማዶ ገንዘብ ስንቀበል፤ ከዋናው በተጨማሪ 7% የገንዘብ ስጦታ እናገኛለን!
በቴሌብር ገንዘብ ስናስልክ እንዲህ ነን! *127# ደውለን ወይም ቴሌብርን በስልካችን በዚህ ሊንክ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!
#ቴሌብር_ሬሚት
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

❤144🕊11😡11🙏6😢5🥰3👏1😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዋንጫው ከሲዳማ ቡና ተነጥቋል፤ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳታፊ ይሆናል " - ፌዴሬሽኑ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ባካሄደው ስብሰባ ላይ የየግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል።
ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው መቻል ስፖርት ክለብ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ህጉን ጥሰዋል ብለዋል።
ምን ውሳኔ ተላለፈ ?
- በእግድ ላይ የነበሩ ተጫዋቾች አሰልፈው የተጫወቱባቸው መርሐ ግብሮች በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆኑ
- የሲዳማ ቡና በእግድ ላይ የነበሩ ተጫዋቾችን አሰልፎ ያገኘው የ ኢትዮጵያ ዋንጫ ለወላይታ ድቻ እንዲሰጥ
- ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳታፊ ይሆናል።
- በ2017 የውድድር ዘመን በፕርሚየር ሊጉ የነበሩ ክለቦች በሊጉ እንዲቆዩ (መቐለ 70 እንደርታ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፣ ስሁል ሽረ)
- የ2018 የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በሀያ ክለቦች መካከል እንዲካሄድ ውሳኔ ተሰጥቷል።

❤969😭157🤔80😡67👏59🕊21🥰11😱11😢11🙏10
#Ethiopia
የንብረት ታክስ በክልሎች በሚቀጥለው በጀት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች የንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ " አሉ።
ይህን ያሉት በህዝብ ተ/ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
" ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዳ እየከፈለ የሚገኘው መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ገቢ እያገኘ መምጣቱን መጥቷል " ያሉ ሲሆን " ገቢ የማያስገኝ አገልግሎት አክሳሪ ነው " ብለዋል።
በአዲስ አበባ የንብረት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ መደረጉን በማስታወስ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀመራል " ነው ያሉት።
#ኤፍቢሲ

😡552❤330😭24💔19😱12👏9😢4🕊4
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ መሬትን በሊዝ በባለቤትነት መያዝ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል። የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት " ባለቤት ' ወይም " ባለይዞታ " የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ይህ " የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት " ወይም " ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የሚያገኙበትን…
#Ethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጽድቋል።
በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ " መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም " ብሏል።
የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ሲል ገልጷል።
የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።
የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል ተብሏል። #HoPR #FMC

❤420😭197😡164🤔20😱14🕊13😢8💔8🙏3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትናንት የተሰጠውን የእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ሌሎች ትምህርት ፈተናዎችን ከወሰዱ በኋላ ይፈተናሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ትናንት በተሰጠው የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ላይ የተወሰነ የኃይል እና የሲስተም መቆራረጥ አጋጥሞ እንደነበር የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
" ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን በፍጥነት በመፍታት ፈተናውን ማስቀጠል ተችሏል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" በሲስተምና በኃይል መቆራረጥ ችግር ትናንት የተሰጠውን የእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ሌሎች ትምህርቶችን ከተፈተኑ በኋላ ይፈተናሉ " ብለዋል።
Via @tikvahuniversity

❤678😡241😭79🙏64💔37🕊22👏19🤔18😱8🥰4😢4
" የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም "- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ፍቃዱን በተረከበ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአገሪቱ ዙሪያ ያሉት የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር 10 ሚሊዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል።
የግል የቴሌኮም አቅራቡ ድርጅት የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የአራተኛ ትውልድ ኔትወርክ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ተደራሽ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ለዚህም ከመቶ ሃምሳ በላይ በሆኑ ከተሞች 3,141 የኔትወርከ ማማዎችን መገንባቱን ገልጿል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቺፍ ኤክስተርናል አፌርስ ኦፊሰር አቶ አንዷለም አድማስ "ሳፋሪኮም የመጠንከር የመወዳደር እና ቀና ብሎ የመጓዝ ሂደት ላይ" ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
አቶ አንዷለም አድማስ በዝርዝር በሰጡት ሃሳብም ምን አሉ ?
" 10 ሚሊየን ንቁ(Active) ደንበኞች ማለት ባለፉት ዘጠና ቀናት ውስጥ የደወለ ወይም መልእክት የተቀበለ ማለት ነው።
ባለፉት 90 ቀናት ካልደወለ ወይም ካርድ ካልሞላ ከእኛ ዳታ ቤዝ ውስጥ ይወጣል ከደወለ ወይም ካርድ ከሞላ ወደ ዳታ ቤዛችን ይገባል ስለዚህ 10 ሚሊየን ንቁ ደንበኛ ስንል ገንዘብ የምናገኝበት ትክክለኛ ደንበኛችን ማለት ነው።
3141 ታወሮች በጣራ ላይ እና ግሪን ፊልድ ላይ አሉን የተወሰኑ ሳይቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ነው የምንጠቀመው ለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ጥሩ ገቢ ያገኛል።
ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞች አዳርሰናል ከዚህ በኋላ ወደ ሌሎች ከተሞችም እንዳረሳለን ለዚህም ከ 1.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ኢንቨስት እናደርጋለን።
በአሁኑ ሰአት ከኮሪደር ልማት ጋር በተገናኘ የ Fiber መቆረጥ አለ እሱ መፍትሄ በሚሰጥ መልኩ እየተሰራ ነው።
በመላ ሃጋሪቱ ነው የምንንቀሳቀሰው እቃዎች ተጭነው ነው የሚሄዱት በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንደማንኛውም ሰው እክል ሊገጥመን ይችላል ነገር ግን የተጋነነ ነገር አለ ብዬ አላስብም።
የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

❤1.39K👏207😡41🙏32🥰19🕊15🤔11😱11😭11😢9💔3