Telegram Web Link
" ከልጅ ልጄ ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ በመብቃቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል" - የዕድሜ ባለፀጋዉ አቶ ማኖ ማገሶ

➡️ " ከአምስተኛ ክፍል የወረዳ አልፎም የአዉራጃ አስተዳዳሪ ሆኜ ነበር ፤ ትክክለኛዉ ዕድሜዬ 91 ነዉ ! "

አቶ ማኖ ማገሶ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ዘንድሮ በሁለተኛዉ ዙር የፈተና ፕሮግራም ከካቻ ካሻሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካቀኑ የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዉስጥ አንዱ ናቸዉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በልጃቸዉ በኩል አግኝቶ አነጋግሯቸዋል።

ከልጅ ልጃቸዉ ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸዉን ገልፀዉ " ትምህርት በዕድሜ ሊገደብ አይገባም " ሲሉ ሃሳባቸው አጋርተዋል።

የ5 ወንዶችና የ6ሴቶች የ11 ልጆች አባት እንደሆኑ የገለፁት አቶ ማኖ በንጉሱ ዘመን በሁለት ዓመት ዉስጥ በነበራቸዉ ቀልጣፋ የትምህርት አቀባበል ክፍል እያጠፉ 5ኛ ክፍል መድረሳቸዉንና ከ5ኛ ክፍል ተወስደዉ የቦንኬ ወረዳ አመራር ተደርገዉ ተሹመዉ እንደነበርና ባሳዩት ጠንካራ አመራርም የቀድሞው የጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በጋርዱላ አውራጃ የገበሬ ማኅበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ይሰሩ እንደነበር አስታዉሰዋል።

በኋላም ደርግ መንበረ ስልጣኑን ሲይዝ ለእስር ተዳርገዉ ለ21 ዓመታት በአርባምንጭ ማረሚያ ታስረዉ መቆየታቸዉንና ደርግ ከወደቀ በኋላ ከማረሚያ ወጥተዉ ልጆቻቸዉን በማስተማር ቦታ ቦታ ካስያዙ በኋላ አቋርጠዉ የቆዩትን ትምህርት በመቀጠል ዘንድሮ በትምህርት መረጃ ላይ 85 ዓመት እሳቸዉ " ትክክለኛ ዕድሜዬ ነዉ " በሚሉት 91 ዓመታቸዉ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ከልጅ ልጃቸዉ ጋር አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸዉን ገልጸዋል።

ለትምህርት ካላቸዉ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በአመራርነት ዘመናቸዉ በርካታ ትምህርት ቤቶችን እንዳስገነቡ የገለፁት አቶ ማኖ እሳቸዉ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት አግብተዉ ትምህርታቸዉን አቋርጠዉ የነበሩ ልጆቻቸዉን ጭምር ከተፈቱ በኋላ ከባሎቻቸዉ ጭምር እንዲማሩ አድርገዉ በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ስራ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

" ከልጅ ልጄ ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ በመብቃቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ጥሩ ዉጤት አምጥቼ ዩኒቨርሲቲ እገባለሁ " ብለዋል።

" ትምህርት በእድሜ የማይገደብ የሕይወት ምግብ ነዉ " ሲሉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአቶ ማኖ ማገሶን ፅናታቸውን እያደነቀ መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ይመኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
👏1.38K1.04K🤔68🙏39😭37🥰22😱18😡18🕊15💔12😢6
" ፈጣሪ ጠብቋቸዉ እንጂ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር " - የብርብር ከተማ ፖሊስ

ሀገር አቀፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ መኪና የትራፊክ አደጋ አጋጥሞት በሰዉና በንብረት ጉዳት መድረሱን የብርብር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ምትኩ ፉላሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ ከቦሮዳ ወረዳ ሀገር አቀፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚሄዱ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይዞ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-09846 ደሕ የሆነ FSR መኪና ከአርባምንጭ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ ይጓዝ ከነበረ ኮድ 3-32326 ኦሮ ከሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ጋር በመጋጨቱ እንደሆነ አዛዡ አስታዉቀዋል።

በአደጋው በ5 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ23 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የገለፁት አዛዡ ተጎጅዎችም በብርብር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና መወሰዳቸዉን ገልፀዋል።

" ከቦታዉ ዳገታማነትና ከመኪኖቹ ፍጥነት አንፃር ሊደርስ ይችል የነበረዉ አደጋ ዘግናኝ ይሆን ነበር " ያሉት ፖሊስ አዛዡ " ፈጣሪ ጠብቋቸዉ የሞት አደጋ እስካሁን አልተከሰተም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.14K😭1.13K🙏239😢90😡65🕊56💔30👏25😱14🤔7🥰5
ቶምቦላ ዛሬ እስከ 11 ሰዓት ብቻ!

አዎ! "በ11ኛው ሰዓት ገዝቼ ዛሬ በ11 ሰዓት አሸነፍኩ!" ሊሉ ይችላሉ።

አፍሪካ ህብረት አጠገብ ጃምቦ ሪል ስቴት ያስገነባው ባለ 12 ፎቅ ህንጻ ውስጥ ያሉትን እጅግ ዘመናዊ ባለ ሶስትና ሁለት መኝታ አፓርትመንት ቤቶች እንዲሁም ተወዳጆቹን ቮልስዋገን ID.6 እና BYD Song Plus SUV መኪናዎችን የራስዎ ማድረግ አይፈልጉም?

የቤቶቹ አድራሻ https://maps.app.goo.gl/mgqFwSerUqyBnrZL6?g_st=aw ይሄ ነው። ተገንብተዋል ይገቡባቸዋል! መኪኖቹም ተዘጋጅተዋል ያሽከረክሩዋቸዋል!

እንግዲያውስ ዛሬ እስከ 11 ሰዓት ብቻ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሚወጣውን የቶምቦላ ሎተሪ በ100 ብር በቴሌብር ሱፐር አፕ ሰዓቱ ሳይደርስ አሁኑኑ ይግዙ!

ይቅናዎ!

ለበለጠ መረጃ በ +251977717272 ፣
+251950189808 እና
+251950199808 ይደውሉ!

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
402🙏70🥰21😭21🕊19🤔14😢8😱3
" የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ድምጽ አልባ በመሆናቸው ራሳቸውን በድምጽ ከአደጋ የሚከላከሉ በተለይም ዓይነ ስውርና መስማት የተሳናቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ትልቅ አደጋ ላይ ናቸው " - ማኅበሩ

የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ከአዲስ አበባ ብስራት ፕሮሞሽን ጋር በማበር፣ የመንገድ ላይ ደኅንነትን፣ የትራንስራንስፓርት ተሽከርካሪዎች እና የአገልገሎት መስጫ ተቋማት ተደራሽነት ችግር አካቶ የያዘ "ከቤት እስከ ጎዳና" በሚል ያዘጋጀውን ዶክመንትሪ ፊልም ለመንግስት አካላት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አቅርቧል።

በዚህም የትራንስፖርትና ሎጂስቲ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንትና ሌሎች ተቋማት ታድመው የነበረ ሲሆን፣ ማኀበሩም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናታዊ ፅሑፍ ጭምር እነዚሁ አካላት ባሉበት አቅርቧል። ባለድርሻ አካላቱም የተለያዩ አስተያየቶችን በመስጠት የተነሱትን ክፍተቶች ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል።

በመርሃ ግብሩ የተነሳው አንዱ ዋነኛ ጉዳይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተለይ ለዓይነ ስውራን አደጋ የደቀኑ በመሆናቸው ሕግና ፓሊሲ በማውጣት መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ የሚያሳስብ የነበረ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በዓይነ ስውራን የሚያስከትለው ጉዳት ምንድነው? ምንስ መደረግ አለበት? ያለው ክፍተትስ ምንድን ነው? ሲል ማህበሩን ጠይቋል፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ረታ ምን መለሱ ?

" መንግስት በጣም የሚደነግበት ቦታ ቢኖር እዚህ ኤሪያ ላይ ነው፡፡ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ይሄንን ጉዳይ ስናወራቸው ምንም ያላሰቡበት ነገር እንደሆነ ነው የነገሩን።

የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ድምጽ አላባ/ድመጽ አልባ አድርጎ መንዳት የሚችሉ ናቸው፡፡ ይሄ ሲሆን ግን እይታ የሌላቸው ነገር ግን ራሳቸውን በድምጽ ከአደጋ የሚከላከሉ በተለይም ዓይነ ስውርና መስማት የተሳናቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ትልቅ አደጋ ላይ ናቸው።

መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለመቀየር እቅድ ይዟል። ይሄንን እቅድ ሲይዝ ግን ቀጥታ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን ዓይነ ስውራንን ያገናዘበው ፖሊሲም፣ ሕግም ስታንዳርድም የለም፡፡ ይሄ ጉዳይ በአሜሪካ ምክር ቤት ክርክር ተደርጎበት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሙሉ ለሙሉ ድምጽ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገዳጅ ሕግ ወጥቶለታል።

በኢትዮጵያ ግን ለነዳጅ የምናወጣውን የውጭ ምንዛሬ ስለሚያስቀርልን፣ ኢንቫይሮመንታሊ ፍሬንድ ስለሆኑ በሚል እሳቤ ተሸከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባናቸው ነው።

መግባቱን ይግቡ ግን ቴክኖሎጅው ሁሉም ነገር የተገጠመለት ነው፤ ነገር ግን እኛ ጋር የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ ስለሌለ ዝም ብለን አስገብተን በመንገድ ላይ ጥቅም እንዲሰጡ እያደረግናቸው ነው ያለነው፡፡ ይህ ለዓይነ ስውራን አደገኛ የሆነ አካሄድ ስለሆነ መንግስት ሊያስብበት ይገባል፡፡

ምክንያቱም ተሽከርካሪዎቹ ድምጽ ስለሌላቸው መጥተው ሲገጩን ብቻ ነው የምናውቀው፡፡ አንድ ዓይነ ስውር በሚጓዝበት ወቅት አደጋ መኖርና አለመኖሩን የሚለየው ድምጽ በመስማትና በነጭ ብትሩ በመዳበስ ነው" ብለዋል።

በአጠቃላይ በዘርፉ ስላለው ችግር ሲያስረዱም፣ "የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎቹ ድምጽ ስለሌላቸው ዓይነ ስውራን ራሱ ቢገቡባቸውና/ቢጋጩ የአሽከርካሪዎች ኃላፊነት ከፍተኛ ድርሻ ስለሚይዝ ሊጣል የሚገባው ካሳ ሊቀንስልኝ ይገባል በሚል ክርክር ውሳኔው ምንድን ነው? በሚለው ዙሪያ በዓይነ ስውራን ወገኖች ረገድ ሕግ የለም " ነው ያሉት።

የመፍትሄውን ሃሳብ በተመለከተ ለጊዜው መንግስት በዚሁ ረገድ ሰርኩላር በትኖ የቁጥጥር ስልቱን መንደፍና መተግበር፣ በዘላቂነትም የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ ሕግና ፖሊሲ እንዲያወጣም አሳስበዋል፡፡

(ተጨማሪ አለን በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
31.44K🤔169🙏81😢47👏45🕊21🥰15😡14😱11💔11😭8
TIKVAH-ETHIOPIA
" የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ድምጽ አልባ በመሆናቸው ራሳቸውን በድምጽ ከአደጋ የሚከላከሉ በተለይም ዓይነ ስውርና መስማት የተሳናቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ትልቅ አደጋ ላይ ናቸው " - ማኅበሩ የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ከአዲስ አበባ ብስራት ፕሮሞሽን ጋር በማበር፣ የመንገድ ላይ ደኅንነትን፣ የትራንስራንስፓርት ተሽከርካሪዎች እና የአገልገሎት መስጫ ተቋማት ተደራሽነት ችግር አካቶ የያዘ "ከቤት…
" ከ47 በመቶ በላይ አሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከፍጥነት ወሰን በላይ ነው የሚያሽከረክሩት ! "

የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኀበር ዘርፉን በተመለከተ አዘጋጅቶት በነበረው መድረክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጀመንት ባለስልጣን መጥተው የነበሩት አቶ ደረጀ የተባሉ አካል " በየዓመቱ ከ2000 እስከ 300ዐ ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ስልጠና እንደሚሰጡ፣ ኢንፍራስትራክቸር በተለይ ለአካል ጉዳተኞች በልዩ ሁኔታ ተይዞ መሰራት እንዳለበት፣ አቅም በፈቀደ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

" ነገር ግን የትራፊክ ግጭቱ ስታቲስቲክሱ ሲታይ በዓመት አዲስ አበባ ከተማ ብቻ 401 ሰው ይሞታል።  በአመት 401 ሰው ይሞታል ማለት በቀን ከ1 ሰው በላይ ይሞታል ማለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የሚፈጠረው ግጭት ደግሞ መቆጣጠር የሚቻል፤ በሰዎች ስህተት የሚፈጠር እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት "ብለዋል።

" አንድ ክርክር አለ የትራፊክ አደጋ ነው ወይስ ግጭት ነው? የሚል። ከ95 በመቶ በላይ በሰዎች ባህሪ ላይ ሰርተን ለውጥ ማምጣት፤ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎችን ማክበር የምንችል ከሆነ ግጭቶችን መቀነስ የምንችልበት እድል ሰፊ ስለሆነ አደጋ ተብሎ ሊያዙ የሚገባ አይደሉም የሚል መከራከሪያ ይነሳል " ነው ያሉት።

" እውነት ነው፤ አንደኛው በአዲስ አበባ ላይ የግጭት አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ፍጥነት ነው። ከ47 በመቶ በላይ አሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከፍጥነት ወሰን በላይ ነው የሚያሽከረክሩት " ብለው፣ " ስለዚህ አንድ አካል ጉዳተኛ ዜብራ መንገድ እያቋረጠ እያለ በፍጥነት የሚመጣ አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን ተቆጣጥሮ ከአደጋው ሊታደገው አይችልም " ሲሉም ተናግረዋል።

በመዲናዋ በመኪና አደጋ ግጭት ጭምር በየጊዜው የበርካቶች ሕይወት እንደሚያልፍ፣ በተለይ ዓይነ ስውራን ደግሞ ለዚህ ተጋላጭ እንደሆኑ ይነገራል፤ ጥናት አድርጋችሁ ነበር? ማኀበሩ ባለው መረጃ መሠረት ስንት ዓይነ ስውራን በዚሁ አደጋ ሞተዋል? ስንልም የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኀበርን ጠይቀናል።

የማበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ረታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ፣ " የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች ሰብዓዊ መብቶች ቃል ኪዳን አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ዳታ ሊኖራቸው እንደሚገባ በመንግስታት ላይ ግልጽ የሆነ ግዴታ ይጥላል። ነገር ግን በመንግስት በኩል እንደዚህ አይነት የተደራጀ አሰራር የለም " ብለዋል።

" እንደ ኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ከጥር 18 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ብዙ የመኪና ሞት አደጋዎች መድረሳቸውን ያለን መረጃ ያሳያል (ይህ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያጋጥሙትን የሚያካትት አይደለም)። አደጋው ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን " ብለዋል።

" በጥር 18/2016 ዓ/ም አንድ የሞት አደጋ ሁለት ከባድ የአካል ጉዳት፣ በመጋቢት ለሚኩራ አንድ የሞት አደጋ ደርሶ ነበር፣ በሚያዚያ ወርም የሞት አደጋ ደርሷል፣  በመስከረም 2017 ዓ/ም በዓይነ ስውራን ላይ የሞት አደጋ ደርሷል፤ በሚያዚያ 2017 ዓ/ም በኮየ ፈጬ አንድ የሞት አደጋ ተመዝግቧል። አደጋው ከፍ እያለ እንደሆነ ነው የሚያሳየው " ነው ያሉት።

የችግሩ ምክንያቶች ሁለት እንደሆኑ በጥናት መዳሰሱን ገልጸው፣ "አንደኛው የኢንፍራስትራክቸር ችግር፤ ሁለተኛ ደግሞ Unsafe የሆነ የአሽከርካሪዎች አነዳድ እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
562😡40😭22🙏16🕊9😢8🤔7🥰3😱3
#Ethiopia🇪🇹

የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ግብይት ሊጀምር እንደሆነ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ( ስቶክ ገበያ) በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ እርምጃ ለአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተነግሯል።

ገበያዉ በኖቬምበር 2023 በተደረገ የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘመቻ 1.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከታሰበው ግብ በ631% በልጧል። ይህ ገንዘብ ከ48 የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተገኘ ነው።

በሕዝብና በግል ሽርክና የሚሰራው አዲሱ የበይነመረብ ንግድ ልዉዉጥ መድረክን መንግሥት 25%፣ የግል ዘርፍ ደግሞ 75% ድርሻ አላቸዉ።

አሁን ላይ ገዳ ባንክ አ.ማ. እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. በገበያው ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 50 ኩባንያዎችን፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ90 በላይ ንግዶችን ለማካተት አቅዷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
592👏57🤔19🕊19🥰14💔12😭8😱7😢6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

19 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ታዳጊዋ አያንቱ ቱና ላይ የግበረስጋ ድፍረት የፈጸመው ግለሰብ በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ የ13 ዓመቷን ታዲጊ አያንቱ ቱና ላይ የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውና በፖሊስ ተባባሪነት ጭምር አምልጦ ከ1 ዓመት በላይ ተሰዉሮ የነበረዉ ወጣት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ መረጃው ከተሰራጨ በኋላ በተደረገ ክትትልና ፍለጋ ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ዉሎ ክስ ተመስርቶበት እንደነበር የአያንቱ ታላቅ ወንድም ወጣት ጴጥሮስ ቱና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ይኸው ግለሰብ አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ዉሳኔ እንደተላለፈበት የአያንቱ ወንድም ተናግሯል።

የሻፋሞ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ፉና ስለጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " የወረዳዉ ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ያቀረቡትን ጠንከር ያለ ምርመራ፣ የሰነድ እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎችን የተመለከተዉ የወረዳዉ ፍርድ ቤት ግለሰቡን ጥፋተኛ ነዉ በማለት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል " ብለዋል።

" ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በማቆያ ዉስጥ የምትገኘዉ አያንቱ ደፋሪዋ እንደተያዘ ከተነገራት በኋላ ጥሩ መሻሻል ታይቶባታል " የሚለዉ የታዳጊዋ ወንድም ጴጥሮስ " ከዚህ በኋላ ከማቆያ ወጥታ ወደ ትምህርት ገበታዋ ትመለሳለች " ብሏል

" የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ለታዳጊዋ ድምፅ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.65K😡1.15K👏340🙏159😭64💔60🕊45😢23🤔16🥰14
#SafaricomEthiopia

አሁንም በSMS ጨዋታ ፈታ💬🎊 እያልን በየቀኑ እንሸለም! 🎁

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 በመላክ  ወይም ወደ *799# በመደወል እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ!

#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
146😡10🕊7🥰5😭4👏2🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል። " ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም…
#Tigray

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " - የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን በተሳሳተ ውሳኔ  ትግራይ የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተናገሩ።

ፕሬዜዳንቱ " ሁሉም ነገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ብለን ስለምናምን በትግራይ በኩል የሚጀመር ትንኮሳ እና ጦርነት አይኖርም " ብለዋል። 

" በክልሉ ደቡባዊ ዞን ያለው ችግር የመላው ትግራይ እንጂ የአከባቢው ብቻ አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንት ታደሰ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ በዞኑ ካለው አስተዳደር በመነጋገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታዋል " ሲሉ ተናግረዋል ።

ራሱን " የትግራይ የሰላም ሃይል " በሎ ከሚጠራውና በዓፋር ክልል ሆኖ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ሃይል ጋር ያለውን ችግር " በሰላማዊ ውይይት ይፈታል " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ግን ህዝብን ለአደጋ የሚዳርግ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል " ብለዋል።

" የትግራይ ሉአላዊነት ተደፍሮ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ሁኔታ ላይ ተሆኖም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመንፍታት ጉዳይ አንደኛ አማራጫችን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው መመለስ  ከሁሉም ስራዎቻችን ቅድምያ የምንሰጠው ነው ጉዳዩ ጊዜ በወሰደ ቁጥር የሰላም በር እንዳያጠብ የፌደራል መንግስት የበኩሉን ሃላፊነት በመወጣት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
703🕊135😡21🥰19🤔16👏13💔9🙏8😱4😭3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ቡድኑ ትግራይን ለማተራመስና ኢትዮጵያን ለመውጋት ከኤርትራ መንግስት ጋር እየሰራ ነው " - ስምረት ፓርቲ

የኢፌዴሪ መንግስት ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የተሰረዘው ' #ህወሓት ' ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንጂ ማስታመም አይገባውም አለ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ።

በቀድሞ የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የትግል ጓደኞቻቸው በቅርቡ ከብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የቅድመ እውቅና ምዝገባ የተሰጠው ስምረት " ለህግ የማይገዛ ወመኔ " ሲል የገለፀው ህወሓት ትግራይን ለማተራመስና ኢትዮጵያ ለመውጋት ከኤርትራ መንግስት እየሰራ ነው " ሲል ከሶታል።

" ኋላ ቀር ቡድን " በማለት በገለፀው ህወሓት ምክንያት የትግራይ ህዝብ መልሶ ወደ ጦርነት  እንዳይገባ የፌደራል መንግስት ሃላፊነቱ እንዲወጣ አሳስቧል።

" ከአሁን በኋላ በትግራይ ላይ የሚፈፀሙ ጥፋቶች ብቸኛው ተጠያቂ ከዓለም አቀፍና አገራዊ ህጎች የተቃረነው ወመኔው ኋላ ቀር ቡድን እና መሰሎቹ መሆናቸው የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘብ አለበት " ሲልም ስምረት ፓርቲ ገልጿል።

" የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶች በአገር ውስጥና በመላ ዓለም የሚገኙ ትግራዎት ቡድኑ በስልጣን የሚቆይባቸው እያንዳንዱ ቀናት በህዝብ ላይ አስከፊ መከራና ስቃይ የሚያስከትሉ መሆናቸው በመረዳት ትግላችሁ አጠናክሩ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ፓርቲው ለታጠቀው ሰራዊት ባስተላለፈው ጥሪ " ሌት ተቀን የጦርነት ነጋሪት ከሚጎስመው ኋላ ቀር ቡድን  ራሳችሁን በማራቅ ከሰላም ፈላጊ ህዝብ ጎን ተሰለፉ " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈፀም ወንጅልም ይሁን የሚቀሰቀስ ጦርነት በዝምታ ማየት በህዝብ ላይ የሚያስከትለው ከባድ አደጋ መዘንጋት ነው " ያለው ስምረት ፓርቲ " አደጋውን አስቀድሞ ለማስቀረት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸው ከወዲሁ እንዲወጡ " በማለት ለአገር አቀፍና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጥሪውን አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.35K😡306🕊146👏51🤔45🙏29😭27💔20🥰18😱9😢4
2025/07/09 23:32:30
Back to Top
HTML Embed Code: