Telegram Web Link
#Ethiopia🇪🇹

በግለሰቦች፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል " ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል " ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ።

ቦርዱ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን " ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደናቀፈ " የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰድ ስልጣንም በአዋጅ ማሻሻያው ተሰጥቶታል።

ላለፉት አምስት ዓመታት በስራ ላይ የቆየውን " የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ " ያሻሻለው የህግ ረቂቅ ለፓርላማ ቀርቧል።

ዛሬ በአዋጅ ማሻሻያው ላይ የፓርላማ አባላት መታየት ያለባቸውን ጉዳዮች በጥቂቱ ካቀረቡ በኋላ በዝርዝር እንዲታይ ለምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርተውታል።

ያለምንም ተቃውሞ እና ድምጸ ተዐቅቦ ለቋሚ ኮሚቴ የተመራው ይህ የአዋጅ ማሻሻያ ከተዘጋጀባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስፈጸመው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት የተስተዋሉ " የህግ ክፍተቶች " እንደሆነ የህግ ረቂቁን ለማብራራት በቀረበ ሰነድ ላይ ተጠቅሷል።

በዝርዝር ያንብቡ : https://ethiopiainsider.com/2025/16239/

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#OFC

" በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ የምንወስነው እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ በማግኘታቸው ላይ የተመሰረተ ነው " - ኦፌኮ


የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በዋና ፅ/ቤቱ መወያየቱን ገለጸ።

ፓርቲው ውይይቱ የነበረው በ2018 ዓ/ም የሚካሄደው 7ኛው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

" ምርጫው ቁልፍ እና ወሳኝ የተባሉ ጥያቄዎችን አቅርቢያለሁ " ብሏል።

ኦፌኮ " ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገባቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን እንዲሁም የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ አስመልክቶ ዝርዝር እና የማያዳግም ግምገማ አቅርበናል " ብሏል።

በውይይቱ ላይ እነማን ተገኙ ?

ኦፌኮን በመወከል ፦
- የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም ተገኝተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ልዑካን ቡድን አራት አባላት የያዘ ሲሆን ፦
- በተመድ የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን
- በኢትዮጵያ የተመድ የነዋሪ አስተባባሪ ጽ/ቤት የሰላምና ልማት አማካሪ ዶ/ር ዘቡሎን ሱይፎን ታክዋን እንዲሁም ሌሎች ሁለት ቁልቅ የተመድ ልዑካን አካትቷል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምን አሉ ?

" ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች ላይ የተመሰረተ ነው።

ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ቴክኒካዊ ሂደት ብቻ አይደለም፤ የዲሞክራሲያዊ ሂደት ውጤት ነው። ይህ ሂደት ዛሬ በኢትዮጵያ የለም። በጦርነት እና በፖለቲካ ስደት ውስጥ ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ አይቻልም። " ብለዋል።

ኦፌኮ፣ ተመድ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖውን ተጠቅሞ እንዲያስፈጽም በማሳሰብ ለመንግስት የሚቀርቡ ዝርዝር ጥያቄዎችን አቅርቧል።

በኦፌኮ የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

➡️ በኦሮሚያና በመላ ኢትዮጲያ ሰላም ፣ በክልሉ ያለውን አውዳሚ ግጭት ለማስቆም በመንግስት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) መካከል በአለም አቀፍ ታዛቢዎች የሚረጋገጥ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ።

➡️ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች መፍታት፣ የኦፌኮ አባላትን፣ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ጨምሮ በመላ አገሪቱ የታሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ።

➡️ በነጻነት የመንቀሳቀስ ዋስትና፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማስፈራራት፣ ወከባና እስራት እንዲቆም። ኦፌኮ የፓርቲ ጽ/ቤቶችን በነጻነት የመክፈትና የማንቀሳቀስ እንዲሁም ከሃገር ውስጥ አስተዳዳሪዎችና ከጸጥታ ኃይሎች ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር ህዝባዊ ስብሰባዎችን የማድረግ መብት እንዲከበርለት ጠይቋል።

በተጨማሪ፦

➡️ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች አመራሮች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ለመሆናቸው በይፋ ቃል የሚገቡበት እና ጥሰቶችን የሚመረምር ገለልተኛ አካል የሚቋቋምበት ስምምነት እንዲፈረም።

➡️ ከምርጫ በፊት የሁሉም ፓርቲዎች ውይይት፣ በገዥው ፓርቲ እና በሁሉም ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግልጽ የሆነ የምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ ለመስማማት የሚያስችል ይፋዊ ውይይት እንዲካሄድ።

➡️ የምርጫ ቦርድን እንደገና ማቋቋም፣ ገለልተኝነቱን ለማረጋገጥ ሁሉም ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ግልጽና አካታችነት ላይ በተመሰረተ ሂደት ኮሚሽነሮችን በመሾም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) እንደገና እንዲዋቀር።

➡️ አሁን በስራ ላይ ያለውንና አሸናፊ ሁሉን የሚወስድበትን የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ሥርዓት መሠረታዊ በሆነ መልኩ መከለስ። ሁሉም ማህበረሰቦችና የፖለቲካ ቡድኖች በፓርላማ ውስጥ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግ ወደ ተመጣጣኝ ውክልና (MMP) የምርጫ ሥርዓት እንዲሸጋገር።

➡️ ገዥው ፓርቲ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያለውን የበላይነት በማስቀረት ሁሉም የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግስት ሚዲያዎች (EBC, OBN የመሳሰሉት) ላይ ፍትሃዊ እና እኩል የአየር ሰዓት እንዲያገኙ የሚያስችል በገለልተኛ አካል የሚመራ ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲዘረጋ።

➡️ በሂደት ላይ ያለው ብሔራዊ ምክክር ሁሉንም የፖለቲካና የትጥቅ ቡድኖችን ያካተተ እንዲሆንና እንደ ፌዴራሊዝምና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ባሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች አስገዳጅ እንዲሆኑ ማድረግ።

የሚሉትን ጥያቄዎች በይፋ አቅርቧል።

የተመድ ልዑካን ቡድን የምርጫውን ቅድመ-ሁኔታዎች የመገምገም ኃላፊነት የተሰጠው መሆኑን ያመለከተው ኦፌኮ ቡድኑ የቀረበለትን ሃሳብ በትኩረት እንዳዳመጠው ገልጿል።

ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ የሚያደርገው ውሳኔ እነዚህ " መሠረታዊ " ያላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በማግኘታቸው ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አሳውቋል።

መረጃውን የላከው የኦፌኮ የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
24 ሰዓታት ቀሩት!

ዛሬ-የዕድል ትኬትዎን ይግዙ-ነገ ይሽለሙ!

ባለ 3 እና ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ ለዓመታት ከሚቆዩ የገንዘብ ሽልማት ጋር!
ቮልስዋገን ID 6 እና BYD–SUV መኪናዎች በተጨማሪ ለዓመታት ከሚቆዩ የገንዘብ ሽልማት ጋር!
ሌሎችም በርካታ ሽልማቶች እርስዎን ይጠብቃሉ፡፡

እንዳያመልጥዎ! ዕጣው ነገ ይወጣል!
ነገ እሁድ የሚወጣውን ቶምቦላ በ ethiolottery.et ላይ እና በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አሁኑኑ ይግዙ!
ለበለጠ መረጃ በ +251977717272፣
+251950189808 እና
+251950199808 ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
#SafaricomEthiopia

🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል 🙌

💨 እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰  ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የክረምት ስልጠናዎች ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራሉ።

የስልጠናዎቹ ዓይነት:
👉 Modern Accountancy (ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ)
👉 Import and Export
👉 Mern Stack Website and Mobile Application Development
👉 Computer Programming and Database
👉 Advanced Graphic Design, Video Editing, Motion Graphic and Digital Marketing
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Journalism
👉 Interior Design
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram
Tiktok
Linkedin
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በኦሮሞ አርት ውስጥ በዓመቱ ጉልህ አሻራን ያኖሩ እና በተለያዩ ጊዜያት በአርቱ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦች በመርሃግብሩ እውቅና አግኝተዋል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ፎቶ ክሬዲት ፦ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን እና ኦኤምኤን @tikvahethiopia
" ስለተፈጠረው ስህተት ህዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን። ለአርቲስት አንዷለም ጎሳ የሰጠነው ሽልማት ተሰርዟል ! " - ፋውንዴሽኑ

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ባዘጋጀው 4ኛው የሃጫሉ አዋርድ ላይ በምርጥ ወንድ ድምጻዊ ዘርፍ አሸናፊ አድርጎ የመረጠውን የአርቲስት አንዷለም ጎሳን ሽልማት መሰረዙን ገልጿል።

ሽልማቱ በተለይም የወጣት ቀነኒ አዱኛ ጥቃትን የሚያመለክቱ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከተለቀቁ በኋላ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

በዚህም ሽልማቱ እንዲነሳ የ24 ሰዓት የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄዎች ሲካሄዱ ነበር። ውሳኔውም ይኸው የሰዓት ገደብ ካበቃ ከሰዓታት በኋላ የተላለፈ ነው።

ፋውንዴሽኑ በመግለጫው ሽልማቱን ጉዳዩን ከሚመለከተው የህግ አካል የተጻፈ ደብዳቤ ይዘን የሸለምን ቢሆንም ከህዝብ በደረሰን አስተያየት ውሳኔያችን ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል ሲል ገልጿል።

አክሎም " ስለተፈጠረው ስህተት ህዝባችንን ይቅርታ እየጠየቅን ለአርቲስት አንዷለም ጎሳ የሰጠነው ሽልማት የተሰረዘ መሆኑን እናሳውቃለን " ሲል አስታውቋል።

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአሁኑ ጥቃት ከከዚህ ቀደሙ ከበድ ያለ ነበር " የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " በሰጠው ቃል ፤ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና 3 የአካባቢው ነዋሪዎች…
" ወደ 80 ሚሊዮን ብር የሚመት ንብረት ነው በታጣቂዎቹ የወደመው። ይሄ ለፋብሪካችን ቀላል ሀብት አይደለም " - ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ

" ታግተው የነበሩ 17 ሠራተኞች ተለቀዋል ! "

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ሱሉለ ፊንጫ ወረዳ ታጣቂዎች የፋብሪካውን ሠራተኞች አታግተው ወስደው እንደነበርና በተሽከርካሪዎቹ ላይ ቃጠሎ እንዳደረሱበት ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
 
ታጣቂዎች በፋብሪካው ፈጸሙት ስለተባለው እገታ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ኃይለማርያም፣ " 17 ሰዎች ትላንትና ማታ ተለቀው ወደ ቤተሰባቸው ገብተዋል። ጥቃቱ ትክክል ነው ተፈጽሟል። ሥራ ቦታ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ናቸው አግተው የወሰዷቸው" ሲሉ ነግረውናል።

" በአንድ ሎደር እና ሀይሉክስ ቶዮታ ተሽከርካሪዎች ነው ውድመት የደረሰው " ያሉ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ የእገታ ጥቃቱና የንብረት ውድመቱ ያደረሱት ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ መሆኑ ተመልክቷል።

የንብረት ውድመቱ በገንዘብ ሲተመን ምን ያክል እንደሆነ ላቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ መንግስቱ፣ " ወደ 80 ሚሊዮን ብር የሚመት ንብረት ነው በታጣቂዎቹ የወደመው። ይሄ ደግሞ ለፋብሪካችን ቀላል ሀብት አይደለም " ሲሉም የጉዳቱን ክብደት አጽንኦት ሰጥተውበታል።

" የሚያሳዝን ነገር ነው። ድርጅቱ በደንብ ወደ ሥራ ተመልሶ እየሰራ ባለበት ወቅት ባልተጠበቀ ሁኔታ ነው ይሄ ጉዳት የደረሰው " ሲሉም ሁነቱን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ታጋቾቹን በምን መልኩ ነው ከእገታ ማስለቀቅ የተቻለው? አጋቾቹ ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቁ እንደነበር ተሰምቷል፤ ሠራኞቹ የተለቀቁት ገንዘብ ተከፍሎ ነው ? ሲል ሥራ አስኪያጁን ጠይቋል።

እሳቸውም፣ " የኛም ሠራተኞች ሥራ ላይ ነበሩ፤ ጉዳቱ እንደተሰማ የጸጥታ አካላት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል።  የፌደራል ፓሊስና ኮማንዶ ኃይልም ሰፊ ርብርብ አድርገው በሄዱበት ቦታ ሂዶ ሰዎቹን ለማዳን ተሳትፈው ነበር በእለቱ ግን ማግኘት አልቻሉም " ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

" በማግስቱ የመከላከያ ኃይልም ተጨምሮ ሰፊ የሆነ ውይይትና ሰፊ አሰሳም አድርጓል። ግን ታጋቾቹ በራሳቸው ጊዜ ተለቀዋል የሚል መረጃ ስላገኘን የፋብሪካው አመራሮች ሰዎቹ አለን ካሉበት ቦታ ላይ ሂደው በመኪና ይዘዋቸው መጥተዋል " ሲሉም አክለዋል።

የገንዘብ ጥያቄውን በተመለከተ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ " እሱን ማጣራት ይፈልጋል። እኔም እንዲህ አይነት መረጃ ሰምቼ ነበር፤ ግን ሰዎቹ ድንጋጤ ላይ ስለነበሩ እንኳን ደኀና ገባችሁ ከማለት ውጪ እንደከፈሉና እንዳልከፈሉ መጠየቅ/ማረጋገጥ አልተቻለም " ብለዋል።

" በድርጅቱ ሀብት ጉዳት የሚያደርሱ፣ አገዳን የሚያቃጥሉ ኃይሎችን ህዝቡ ከራሱ ነጥሎ ማውጣት አለበት። ሰላም ሆኗል ብለን ተስፋ ስናደርግ ችግር ያጋጥማል። ከህዝቡ ውስጥ ሆኖ መሳሪያ ታጥቆ ብቅ ጥልቅ እያለ የድርጅቱን ሀብት የሚያወድመውን ኃይል ተው ሊል ይገባል " ሲሉም ማህበረሱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🕊#Peace

" የትግራይ ፓለቲከኞች ሃላፊነት ከጎደለው የመተላለቅ እንቅስቃሴ ተቆጠቡ " - ጉባኤው

" በትግራይ የእርስ በርስ መተላለቅ የሚጋብዝ ፕሮጀክት የተወገዘና ተቀባይነት የሌለው ነው " አለ የትግራይ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ።

ጉባኤው የትግራይ ፓለቲከኞች ሃላፊነት ከጎደለው የመተላለቅ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ሲል በፅኑ ተማፅኗል።

" ህዝብን በማሳተፍ ለሰላም ፣ ለፍቅር ለፍትህና ለአንድነት እሰራለሁ " ሲል ያሳወቀው ጉባኤው " በመሪዎች መካከል የተፈጠረው ተግባብቶ ያለመስራት ችግር ህዝቡ ለስደት፣ ለመፈናቀልና ለሞት የዳረገ የሚወገዝ ተግባር ነው " ብሏል።

" ገና ከጦርነት ባለገገመች ትግራይ ትግራዋይ ከትግራዋይ ለመተላለቅ ያለመ ፕሮጀክት ተደግሷል " ያለው  ጉባኤው " ይህ አደገኛ ፕሮጀክት ለትግራይ ህዝብ ታሪክ የማይመይጥን ነው " ብሎታል።

በአገር ውስጥና በመላ ዓለም የሚገኝ ትግራዋይ ሆደ ሰፊና አስተዋይ እንዲሆን መክሮ " በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በጋራ እንቁም " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ከልጅ ልጄ ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ በመብቃቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል" - የዕድሜ ባለፀጋዉ አቶ ማኖ ማገሶ

➡️ " ከአምስተኛ ክፍል የወረዳ አልፎም የአዉራጃ አስተዳዳሪ ሆኜ ነበር ፤ ትክክለኛዉ ዕድሜዬ 91 ነዉ ! "

አቶ ማኖ ማገሶ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ዘንድሮ በሁለተኛዉ ዙር የፈተና ፕሮግራም ከካቻ ካሻሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካቀኑ የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዉስጥ አንዱ ናቸዉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በልጃቸዉ በኩል አግኝቶ አነጋግሯቸዋል።

ከልጅ ልጃቸዉ ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸዉን ገልፀዉ " ትምህርት በዕድሜ ሊገደብ አይገባም " ሲሉ ሃሳባቸው አጋርተዋል።

የ5 ወንዶችና የ6ሴቶች የ11 ልጆች አባት እንደሆኑ የገለፁት አቶ ማኖ በንጉሱ ዘመን በሁለት ዓመት ዉስጥ በነበራቸዉ ቀልጣፋ የትምህርት አቀባበል ክፍል እያጠፉ 5ኛ ክፍል መድረሳቸዉንና ከ5ኛ ክፍል ተወስደዉ የቦንኬ ወረዳ አመራር ተደርገዉ ተሹመዉ እንደነበርና ባሳዩት ጠንካራ አመራርም የቀድሞው የጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በጋርዱላ አውራጃ የገበሬ ማኅበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ይሰሩ እንደነበር አስታዉሰዋል።

በኋላም ደርግ መንበረ ስልጣኑን ሲይዝ ለእስር ተዳርገዉ ለ21 ዓመታት በአርባምንጭ ማረሚያ ታስረዉ መቆየታቸዉንና ደርግ ከወደቀ በኋላ ከማረሚያ ወጥተዉ ልጆቻቸዉን በማስተማር ቦታ ቦታ ካስያዙ በኋላ አቋርጠዉ የቆዩትን ትምህርት በመቀጠል ዘንድሮ በትምህርት መረጃ ላይ 85 ዓመት እሳቸዉ " ትክክለኛ ዕድሜዬ ነዉ " በሚሉት 91 ዓመታቸዉ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ከልጅ ልጃቸዉ ጋር አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸዉን ገልጸዋል።

ለትምህርት ካላቸዉ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በአመራርነት ዘመናቸዉ በርካታ ትምህርት ቤቶችን እንዳስገነቡ የገለፁት አቶ ማኖ እሳቸዉ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት አግብተዉ ትምህርታቸዉን አቋርጠዉ የነበሩ ልጆቻቸዉን ጭምር ከተፈቱ በኋላ ከባሎቻቸዉ ጭምር እንዲማሩ አድርገዉ በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ስራ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

" ከልጅ ልጄ ጋር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ በመብቃቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ጥሩ ዉጤት አምጥቼ ዩኒቨርሲቲ እገባለሁ " ብለዋል።

" ትምህርት በእድሜ የማይገደብ የሕይወት ምግብ ነዉ " ሲሉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአቶ ማኖ ማገሶን ፅናታቸውን እያደነቀ መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ይመኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
" ፈጣሪ ጠብቋቸዉ እንጂ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር " - የብርብር ከተማ ፖሊስ

ሀገር አቀፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ መኪና የትራፊክ አደጋ አጋጥሞት በሰዉና በንብረት ጉዳት መድረሱን የብርብር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ምትኩ ፉላሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ ከቦሮዳ ወረዳ ሀገር አቀፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚሄዱ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይዞ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-09846 ደሕ የሆነ FSR መኪና ከአርባምንጭ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ ይጓዝ ከነበረ ኮድ 3-32326 ኦሮ ከሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ጋር በመጋጨቱ እንደሆነ አዛዡ አስታዉቀዋል።

በአደጋው በ5 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ23 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የገለፁት አዛዡ ተጎጅዎችም በብርብር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና መወሰዳቸዉን ገልፀዋል።

" ከቦታዉ ዳገታማነትና ከመኪኖቹ ፍጥነት አንፃር ሊደርስ ይችል የነበረዉ አደጋ ዘግናኝ ይሆን ነበር " ያሉት ፖሊስ አዛዡ " ፈጣሪ ጠብቋቸዉ የሞት አደጋ እስካሁን አልተከሰተም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2025/07/06 01:46:38
Back to Top
HTML Embed Code: