Telegram Web Link
" ወደ 54 እንስሳት ነው የምናሳድነው፤ ኢንደሚክ የሆኑ ለምሳሌ ጭላዳ ዝንጀሮንም፣ የምኒልክ ድኩላንም እናሳድናለን " - የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን

በአራት ክልሎች ኢንደሚክ የሚባሉትን ጨምሮ ወደ 54 የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳትን በውጪ ዜጎች እየታደኑ በዶላር እየተሸጡ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ።

በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ባለሙያ አቶ ፋንታዬ ነጋሽ በሰጡን ገለጻ፣ ለምሳሌ " አንድ ኒያላ 15 ሺሕ ዶላር ነው የሚሸጠው፤ ይሄ ይበቃል? አይበቃም? የሚለው ገና እየታየ ነው በሕግ፤ አልጸደቀም እንጂ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረስ ገብቷል ረቂቁ። ዋጋው በቂ አይደለም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ እንዲህ አይነት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳት መታደናቸው ልክ አይደለም የሚሉ ቁጣዎች እየተሰነዘሩ ነው፤ ለዚህ ትችት ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ሲል አቶ ፋንታዬን ጠይቋል።

" ኢንደሚክ እንስሳት ይታደናሉ፤ ያም ደግሞ ዝም ብሎ በዘፈቀደ ሂዶ ማደን ሳይሆን ሳይንሳዊ በሚሆን መንገድ ተጠንቶ፤ ተቆጥረው ይህን ያክል ቢገደል ተብሎ በሚሰጥ ኮታ መሠረት ነው። የእንስሳቱን የመኖር ህልውና ምንም አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ተጠንቶ ነው ያ የሚደረገው፤ ያም ሲደረግ ደግሞ ከፌደራል፣ ከክልል የተውጣጡ ባለሙያዎች አጥንተው ሳይንሳዊ የሆነ ሪሰርች ቀርቦ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ወደ 54 እንስሳት ነው የምናሳድነው፤ ሁሉም የየራሳቸው ዋጋና ኮታ አላቸው። ኢንደሚክ የሆኑ ለምሳሌ ጭላዳ ዝንጀሮንም፣ የምኒልክ ድኩላንም እናሳድናለን " ብለዋል ባለሙያው።

ይህ የሚሆነው አንድ እንስሳ ምን ያህል ቢገደል ነው የእንስሳቱን ቁጥር የማይጎዳው? ተብሎ ቀንዱ ተለክቶ እድሜው ታውቆ እንደሆነ አስረድተው፣ "ለምሳሌ ኒያላን ከ29.5 ኢንቺ በታች ቱሪስቶች በስህተት እንኳ ከገደሉ የእንስሳውን እጥፍ ነው የሚከፍሉት። ማንኛውንም ሴት እንስሳ ቢገድሉ ደግሞ የዋጋውን እጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል " በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በሌሎች ሀገራት የሌሉ ኢትዮጵያ ብቻ የምትታወቅባቸው ብርቅዬ እንስሳት እየታደኑ የሚሸጡ ከሆነ በአንድ ወቅት ህልውናቸው ሊጠፋ ስለሚችል ጭራሹንም መጠሪያ ማጣትን አያስከትልም ወይ? ከጠፉ ደግሞ የቱሪስት ፍሰት አይኖርምና ከሚገደሉ ይልቅ በቱሪስት የሚያስገኙት ገቢ አይሻልም ወይ? በሚል ለሚነሳው ስጋት ምላሽ እንዲሰጡም አቶ ፋንታዬን ጠይቀናቸዋል።

ምን መለሱ?

" ያልከው ስጋት ምናልባት ስፓርታዊ ሃንቲንግ ምንድን ነው? ብለው በትክክል ካለመረዳት የመጣ ነው። መስጋታቸው ምንም ሊደንቅ አይገባም፤ ግን ደግሞ ሳይንሱን ቢያውቁት ግልጽ ይሆንላቸዋል።

ሲቀጥል እንስሳቱ የሚታደኑት ፓርክ ላይ አይደለም። ይልቁንም ለእነርሱ ተብሎ የተከለለ የአደን ቀበሌ አለ፤ ከፓርኮቻችን ቢያንስ 5 ኪሎ ሜትር የራቀ ቦታ እንጂ ብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ አደን አይፈቀድም። ነገር ግን ዓለም አቀፍ ህግ በሚፈቅደው መልኩ የአደን ቀበሌ ተብሎ ይቋቋልማል፤ እዚያ አደን ቀበሌ ላይ ነው ኮታ የሚሰጠው።

ኒያላ ብቻ ሳይሆን ወደ 54 እንስሳትን እናሳድናለን፤ አንድ ቱሪስት ደግሞ ኒያላ ብቻ ብሎ አይመጣም። ሌሎች እንስሳትን (የምኒልክ ድኩላ፣ ተራ ድኩላ፣ የቆላ አጋዘን...) አብሮ ይገዛል። ሁሉም በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንተው ኮታ ተሰጥቷቸው ነው የሚታደኑት " ብለዋል።

በዚሁ አደንም ከፍተኛ ገቢ እንደሚገኝ፣ 85 በመቶው ገቢ እንስሳው ለታደነበት ክልል፣ 15 በመቶው ለፌደራል መንግስት እንደሚገባ፣ አደኑ በኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሶማሌና አፋር ክልሎች እንደሚከናወን፣ የታደኑትን እንስሳትን ትክክለኛ ቁጥር ለጊዜው ባያስታውሱም በዚህ ዓመት ወደ 177 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደተገኘ ገልዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡874560😭39💔21🤔20🙏10🕊9👏8🥰6😱5
ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ለቀናት ህመም ላይ እንደነበረ የተነገረ ሲሆን ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ጋዜጠኛው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጋዜጠኝነት እስከ የዜናና ወቅታዊ መረጃ ዳይሬክተር በመሆን አገልግሏል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን " #የሚዲያ_ዳሰሳ " በሚል ርእስ ሲያቀርበው በነበረው ትንታኔ በአድማጭ ተመልካቾች ዘንድ ይታወሳል።

ወደ አሜሪካ በመሄድም በPhD ተመርቋል።

ከትምህርቱ ጎን ለጎንም እስከ ህልፈቱ ድረስ TBS በተባለው የትግርኛ ቴሌቪዥን በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ወቅታዊና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ሲያቀርብ ነበር። 

በ1963 ዓ/ም በትግራይ ውቕሮ ከተማ የተወለደው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  የጋዜጠኝነትን ኮሙዩኒኬሽንን ክፍል በዲግሪ ተመርቋል። በጋዜጠኝነት ሙያ ለረጅም አመታት ሰርቷል።

መረጃው የቲቢኤስ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
😭1.2K509😢124🕊80💔53🙏47😱10🤔8🥰7👏6😡3
#Houthis

የየመን ሁቲዎች በጉዞ ላይ የነበረ የጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ እና መርከቡ ቀይ ባህር ውስጥ ከሰጠመ በኋላ 6 መርከበኞች መትረፋቸውን እና ቢያንስ 3 ሌሎች ሰዎች መሞታቸውን የአውሮፓ የባህር ኃይል ተልዕኮ አስታወቀ።

የላይቤሪያን ባንዲራ የሚያውለበልበው እና በግሪክ የሚንቀሳቀሰው 'ኤተርኒቲ ሲ' የተባለው የጭነት መርከብ 25 ሠራተኞችን ይዞ እየተጓዘ ነበር።

መርከቡ ሰኞ ዕለት ከትንሽ ጀልባዎች በተተኮሱ የሮኬት ቦምቦች ከተመታ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በዚህም የመንቀሳቀስ አቅሙን እንዳጣ የእንግሊዝ የባሕር ንግድ ሥራዎች ኤጀንሲ (UKMTO) ገልጿል።

ጥቃቱ ማክሰኞ ዕለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን መርከበኞቹን የማዳን ሥራ የተጀመረው ሌሊት ላይ ነው።

በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች፤ ኤተርኒቲ ሲ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ወደ እስራኤል እየተጓዘ ስለነበረ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ቁጥራቸው ያልታወቀ ሠራተኞችንም " ደህንነቱ ወደ የተጠበቀ ቦታ " እንደወሰዱ ተናግረዋል።

በየመን የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሁቲዎች " በሕይወት የተረፉ የቡድን አባላትን አፍነው መውሰዳቸውን " ገልጾ፤ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርቧል።

የፊሊፒንስ ባለስልጣናት ከቡድኑ አባላት ውስጥ 21 ያህሉ ዜጎቻቸው እንደሆኑ ተናግረዋል።

ከቀሪዎቹ መካከል አንዱ የሩስያ ዜግነት ያለው እንደሆነ እና በጥቃቱ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት እግሩን እንዳጣም ተገልጿል።

ሁቲዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህንን ዓይነቱን ጥቃት ሲፈጽሙ ይህ ሁለተኛቸው ነው።

ቡድኑ እሁድ ዕለት 'ማሲክ ሲስ' በተባለ ሌላ የላይቤሪያን ባንዲራ የሚያውለበልብ የግሪክ የጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።

የእሁዱን ጥቃት የፈጸሙት መርከቡ፤ " በተወረረው የፍልስጤም ግዛት ውስጥ በሚገኙ ወደቦች ላይ የተጣለውን የጉዞ ክልከላ የጣሰ ኩባንያ ንብረት በመሆኑ " ነው ብለዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
901😭126👏65😡54🕊37😢15🤔7🙏7🥰6😱5💔4
#USA #VISA

" የቪዛው የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር አጥሯል ፤ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትም ተከልክሏል " - ኤምባሲው

የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታውቋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ኤምባሲው ገልጿል።

በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ " ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ " እንደሚኖረው አስታውቋል።

ኤምባሲው ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውስጥ ይካተታል።

እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።

አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።

በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ቪዛ የቆይታ ጊዜን ወደ ሦስት ወራት ማሳጠሩን ትላንት ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ሀገራት መካከል ናይጄርያ እና ጋና ይገኙበታል።

#USEmbassyAddisAbaba #BBCAmharic

@tikvahethiopia
990😭400😡107🤔61👏37😢36🙏26🕊19😱12🥰11
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በተማሪነትም ሆነ በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎቻችን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ቆይታ ጊዜ በላይ በአሜሪካ መቆየት በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የሌለውና ከፍተኛ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን መገንዘብ ያሻል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የአሜሪካ ቪዛ የያዙ ኢትዮጵያውያና የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቆዩ ቅጣት እንደሚከተላቸው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ይህን ያሉት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።

በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሜሪካ መንግስት የቪዛና አገልንሎትና ኢምግሬሽን ጉዳዮችን በሚመለከት አዳዲስ አሰራሮችንና አካሄዶችን ይፋ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለዜጎች ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

"በተማሪነትም ሆነ በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎቻችን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ቆይታ ጊዜ በላይ በአሜሪካ መቆየት በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የሌለውና ከፍተኛ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን መገንዘብ ያሻል" ሲሉ ተናግረዋል።

"ወደፊትም ለትምህርትም ሆነ ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል ያላቸው ዜጎች እነኝህን የተቀመጡ የቪዛ ቆይታ ጊዜዎች ካላከበሩ ለተለያዩ ችግሮች ሊጋለጡ የሚችሉ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንደረግ ማሳሰብ እንፈልጋለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ወደ አሜሪካ ለመጓዝ፣ ቪዛ ለማግኘት ለአሜሪካ ኤምባሲ ማመልከቻ የሚያስገቡ ከመንግስትም ሆነ ከግል ተቋማት የሚመነጩ ሰነዶች ትክክል ስለመሆናቸው እያረጋገጡ እንዲሆን አሳስበዋል።

በአጠቃላይ የአሜሪካ መንግስት የቪዛ አገልግሎትን የኢምግሬሽን ጉዳዮችን የሚያወጣቸውን አዳዲስ አሰራሮች በመከታተል ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አምባሳደሩ፣ "ከአሜሪካም ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ የአሜሪካ ፓስፓርት የያዙ ኢትዮጵያውያን፣ የሌሎች ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የኢትዮጵያን ቪዛ ለማግኘት ወደ አገራችን ሲመጡ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ በሀገራችን ሕግ መሠረት ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንወዳለን" ሲሉም ተናግረዋል።

አምባሳደር ነብያት፣ "ይህ አሰራር የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ያልያዙትን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ይጨምራል" ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvaEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.32K😡191🤔63👏56😭32🕊27💔19🥰17😢17🙏11😱4
#DStvEthiopia

ከ32 ቡድን 2 ብቻ ቀሩ! የዓለም ምርጡ ክለብ ማነው?

እሁድ ሀምሌ 6 ከምሽቱ 04፡00 ሰዓት
Chelsea vs PSG
📺 Channel 223 SS FIFA Club World Cup በጎጆ ፓኬጅ

⚽️ አንድም የጨዋታውን ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ሁሉንም ጨዋታዎች በጎጆ ፓኬጅ ላይ በቻናል 223 ይመልከቱ! 📺

📣 አዲሱን የዲኤሲቲቪ ስጦታ እየተጠቀማችሁ ነው?

🎊 እስከ ሐምሌ 24 ድረስ ባሉት ቀናት በመረጡት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ የአንድ ወር ሙሉ ክፍያ ሲከፍሉ ዲኤስቲቪ ያለተጨማሪ ክፍያ ከፍ ወዳለው ፓኬጅ ከተጨማሪ ቻናሎች ጋር በስጦታ ያገኛሉ!

ደንበኝነትዎን አሁኑኑ አራዝሙ ስጦታ ያግኙ!
⬇️
https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #FIFACWC
239😡14🙏10😢5🥰4🕊1
" የትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ማሽን ጭነን ቅድሚያ ስጡን ብለን ብንጠይቅም የሚሰማን አላገኘንም ፤ ተሰልፈን መንገድ ላይ ለማደር ተገደናል " - አሽከርካሪዎች

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል በቤንዚን ላይ ብቻ ይስተዋል የነበረው ሰልፍ ከቅርብ ጊዜያት ወዲ በናፍጣ ላይ ጎልቶ መታየት የጀመረ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያም አሽከርካሪዎች አነጋግሯቸዋል።

ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ጭነዉ በነዳጅ ሰልፉ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ማሽነሪዎቹ በየመንገዱ ባደሩ ቁጥር የሚሰራዉ ፕሮጀክት ከመጓተቱም በላይ የክረምት የጎርፍ ሙላት ፕሮጀክቱን ያበላቸዋል ይህን ለማደያ ባለሙያዎች ብንገልፅም ከሰልፉ ወጪ ለመቅዳት የንግድ ቢሮ ትዕዛዝ እንደሚያስፈልግ ነግረውናል " ብለዋል።

" በከተማ ሁሉም ማደያዎች ለመንግስት አምቡላንሶች እንጂ ለሌሎች የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ እየተሰጠ አይደለም " ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ደግሞ " ይህ ተገቢነት የለዉም " ብለዋል።

በአንድ ማደያ የናፍጣና ቤንዚን ረጃጅም ሰልፎች በተመሳሳይ ሰዓት መመደባቸዉ ለእግልታችን ሌላኛዉ ምክንያት ነዉ ያሉት በሰልፉ ላይ ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች " የከተማ አስተዳደሩ ንግድ መምሪያ ጉዳዩን በአግባቡ መምራት አለመቻሉንና እንደዉም በተቃራኒው ምሳ ሰዓት ዘግቶ በመዉጣት ለሚፈጠሩ መጨናነቆች ምክንያት እየሆነ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

" ተመዝግበዉ ያደሩ ናቸዉ " በሚል በየሰልፉ መሃል እንዲገቡ የሚደረጉ ተሽከርካሪዎች አሽከርካሪዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ እያደረገ ስለመሆኑ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" በነዳጅ ማደያዎች ሀዋሳ ከተማን የሚመጥን መስተንግዶ አላገኘንም " ሲሉም ወቅሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ የእጅ ስልክ ደጋግሞ ቢደውልም ስልክ ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
496😭74🤔21😡21👏12🙏11🕊8🥰5😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ! " - ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሁንም የእንስት ዘወዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ ሌላ ቀጠሮ ተይዞለታል። የግድያ ወንጀሉ ከተፈፀመ የፊታችን ነሀሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ 2017 ዓ.ም በዓል ሁለት ዓመት ይሞላዋል። አሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የአሸንዳ በዓል በሚከበርበት ወርሃ ነሀሴ 2015 ዓ.ም ነበር የተፈፀመው።   የእንስት ዘውዱ…
#Update

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ቀጠሮ ሰጠ።

ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በእስር የሚገኙ ተከሳሽ ተጠርጣሪዎች ለውሳኔ ማቅለያ የሚሆን የህክምና ማስረጃ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ለዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ችሎት ላይ የቀረቡት የተከሳሽ ጠበቆች " የመቐለ ዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ አርብ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህክምና ማስረጃ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶናል " ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም ይህን አድምጦና ተቀብሎ የመጨረሻ ቀነ ቀጠሮ ለነገ ሰጥቷል።

በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት የተበዳይና ተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ በርካታ ሚድያዎች ፣ በሴት ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስቪክ ማህበራት አመራሮችና አባላት ተገኝተው ነበር ።

ሁለት አመት ያስቆጠረው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ነገ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ መቋጫ የፍርድ ውሳኔ ያገኝ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የችሎቱን ውሳኔ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትጵዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
546😭157🙏34😡30🕊19🤔17😢15💔13🥰6👏6
2025/07/13 13:34:02
Back to Top
HTML Embed Code: