Telegram Web Link
" የትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ማሽን ጭነን ቅድሚያ ስጡን ብለን ብንጠይቅም የሚሰማን አላገኘንም ፤ ተሰልፈን መንገድ ላይ ለማደር ተገደናል " - አሽከርካሪዎች

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል በቤንዚን ላይ ብቻ ይስተዋል የነበረው ሰልፍ ከቅርብ ጊዜያት ወዲ በናፍጣ ላይ ጎልቶ መታየት የጀመረ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያም አሽከርካሪዎች አነጋግሯቸዋል።

ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ጭነዉ በነዳጅ ሰልፉ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ማሽነሪዎቹ በየመንገዱ ባደሩ ቁጥር የሚሰራዉ ፕሮጀክት ከመጓተቱም በላይ የክረምት የጎርፍ ሙላት ፕሮጀክቱን ያበላቸዋል ይህን ለማደያ ባለሙያዎች ብንገልፅም ከሰልፉ ወጪ ለመቅዳት የንግድ ቢሮ ትዕዛዝ እንደሚያስፈልግ ነግረውናል " ብለዋል።

" በከተማ ሁሉም ማደያዎች ለመንግስት አምቡላንሶች እንጂ ለሌሎች የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ እየተሰጠ አይደለም " ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ደግሞ " ይህ ተገቢነት የለዉም " ብለዋል።

በአንድ ማደያ የናፍጣና ቤንዚን ረጃጅም ሰልፎች በተመሳሳይ ሰዓት መመደባቸዉ ለእግልታችን ሌላኛዉ ምክንያት ነዉ ያሉት በሰልፉ ላይ ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች " የከተማ አስተዳደሩ ንግድ መምሪያ ጉዳዩን በአግባቡ መምራት አለመቻሉንና እንደዉም በተቃራኒው ምሳ ሰዓት ዘግቶ በመዉጣት ለሚፈጠሩ መጨናነቆች ምክንያት እየሆነ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

" ተመዝግበዉ ያደሩ ናቸዉ " በሚል በየሰልፉ መሃል እንዲገቡ የሚደረጉ ተሽከርካሪዎች አሽከርካሪዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ እያደረገ ስለመሆኑ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" በነዳጅ ማደያዎች ሀዋሳ ከተማን የሚመጥን መስተንግዶ አላገኘንም " ሲሉም ወቅሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ የእጅ ስልክ ደጋግሞ ቢደውልም ስልክ ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
504😭74🤔21😡21👏12🙏11🕊8🥰5😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ! " - ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሁንም የእንስት ዘወዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ ሌላ ቀጠሮ ተይዞለታል። የግድያ ወንጀሉ ከተፈፀመ የፊታችን ነሀሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ 2017 ዓ.ም በዓል ሁለት ዓመት ይሞላዋል። አሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የአሸንዳ በዓል በሚከበርበት ወርሃ ነሀሴ 2015 ዓ.ም ነበር የተፈፀመው።   የእንስት ዘውዱ…
#Update

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ቀጠሮ ሰጠ።

ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በእስር የሚገኙ ተከሳሽ ተጠርጣሪዎች ለውሳኔ ማቅለያ የሚሆን የህክምና ማስረጃ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ለዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ችሎት ላይ የቀረቡት የተከሳሽ ጠበቆች " የመቐለ ዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ አርብ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህክምና ማስረጃ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶናል " ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም ይህን አድምጦና ተቀብሎ የመጨረሻ ቀነ ቀጠሮ ለነገ ሰጥቷል።

በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት የተበዳይና ተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ በርካታ ሚድያዎች ፣ በሴት ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስቪክ ማህበራት አመራሮችና አባላት ተገኝተው ነበር ።

ሁለት አመት ያስቆጠረው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ነገ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ መቋጫ የፍርድ ውሳኔ ያገኝ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የችሎቱን ውሳኔ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትጵዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
549😭157🙏34😡30🕊19🤔17😢15💔13🥰6👏6
#ግብር

" የቤተክርስቲያን ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመለከተው ይገባል " - አባቶች

➡️ የሃይማኖት ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ባሻገር የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ሲሳተፉ ታክስ መክፈል እንዳለባቸው መወሰኑ ይታወቃል !

ቤተ ክርስቲያን የተጨማሪ ገቢ ግብር መክፈል እንዳለባት በተላለፈ ውሳኔ ላይ ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለጸች።

ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተካሄደ ሲሆን፦
- ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣
- ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የደቡብ ምስራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
- ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ እና የሐድያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
- ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ፕሬዘዳንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ነበር።

ከመንግሥት በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች እና መጋቢ ታምራት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ በውይይቱ ተካፍለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ባሻገር የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ሲሳተፉ ታክስ መክፈል እንዳለባቸው የሚደነግገውን አዋጅ ላይ በከተማ አስተዳደሩ የተጋበዙ የሥራ ኀላፊዎች ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።

ከቤተክርስቲያን ወገን የተገኙ መሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች ፤ ጉዳዩ ዙሪያ መለስ ውጤቶችን ከግምት ባስገባ መልኩ ተጨማሪ ምክክር ሊደረግበት የሚገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

በተጨማሪ የቤተክርስቲያን ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመለከተው እንደሚገባ መጠቆማቸውም ተገልጿል።

ውይይቱ ቀጣይነት እንዳለው ተጠቁሟል።

መረጃው የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
952😡357👏68🤔36😢30😱21😭17💔15🕊12🥰6🙏3
" አንድ ሃገር ለመብረር ፈቃድ ያስፈልጋል ያንን ፈቃድ ጠይቀን ሲፈቀድልን ነው የምንበረው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደርገውን የመጀመሪያውን በረራ በዛሬው ዕለት ምሽት ያስጀምራል።

አየር መንገዱ አፍሪካን ከ ኤዥያ ጋር ያገናኘው የዛሬ 52 አመት እ.ኤ.አ በ 1973 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ በመብረር  እንደነበር የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤዢያ 27 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን ወደ ቬትናም ሃኖይ ከተማ የሚያደርገው በረራ 28 ኛው መዳረሻው ይሆናል።

አቶ መስፍን " 190 በረራዎች በሳምንት ወደ ኤዢያ እናደርግ ነበር የአሁኑ በረራ በሳምንት ለ አራት ቀናት የሚከናወን በመሆኑ በአህጉሩ በሳምንት የምናደርገውን በረራ ወደ 194 ከፍ አድርገነዋል " ብለዋል።

ሃኖይ ለንግድ እና ለቱሪዝም የምትመረጥ መዳረሻ በመሆኗም የቀጥታ በረራ በመጀመሩ 120 የሚሆኑ አፍሪካውያን በዛሬው ምሽት ወደ ቬትናም ሃኖይ እንደሚጓዙ ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው " አየር መንገዱ በየጊዜው የሚጨምራቸው መዳረሻዎች በምን መስፈርት የተመረጡ ናቸው ? አፍሪካን እርስ በእርስ የማገናኘት ሥራስ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ? " ሲል ጠይቋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ወደ አንድ ሃገር እና ከተማ የበረራ መስመር ከመክፈታችን በፊት የአዋጭነት ጥናት እናካሄዳለን።

አዋጭነት ማለት ገበያው አለ ወይ በረራ ብንጀምርስ በቂ መንገደኛ እናገኛለን ወይ የሚለው ላይ ጥናት እናካሂዳለን።

ያ ጥናት በቂ መንገደኛ አለ ሲለን በረራውን እንጀምራለን።

እድገት የሚመጣው አዳዲስ የበረራ መስመሮችን በመጨመር ወይም ባሉት ላይ የበረራ ምልልሱን በመጨመር ነው።

አፍሪካ ውስጥ በአሁኑ ሰአት በ 40 ሃገራት ወደ 61 ከተሞች እንበራለን።

ወደ ፊት እያየን የምንበርባቸው ሃገሮች ተጨማሪ ከተሞችን አዋጭ ሆነው ስናገኛቸው ፈቃዱን እንዳገኘን እንበራለን።

በተጨማሪም የማንበርባቸው ሃገሮችም ፈቃድ እንዳገኘን አዋጭነት እያየን እንበራለን በዚህ መንገድ አፍሪካ ውስጥ መዳረሻችንን እና የበረራ ምልልሱን እንጨምራለን።

አንድ ሃገር ለመብረር ፈቃድ ያስፈልጋል ያንን ፈቃድ ጠይቀን ሲፈቀድልን ነው የምንበረው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
1.05K👏54🕊21😡16😭13🙏11🤔9🥰8😱1
" ሦስት 5Lሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት ፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት አንዱ ጥበቃ አብሮ ጠፍቷል " - ባለንብረቶቹ

ትላንት (ረቡዕ ለሐሙስ) ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ ፓርክ ከተደረጉበት ሦስት 5L ሚኒባሶች እንደተወሰዱባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቹን ያየ ሁሉ እንዲጠቁማቸው በአጽንኦት ተማጽነዋል።

ባለንብረቶቹ " ሦስት 5L ሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት አንዱ ጥበቃ አብሮ ጠፍቷል። ሁለቱ 'ተኝተን ነበር' አሉ። ከተቀጠረ ሦስት ቀናት የማይሞላው ጥበቃ ነው ከተሽከርካሪዎቹ ጋር አብሮ የጠፋው " ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

" ጥበቃው የተቀጠረው በኤጀንሲ ነበር። ኤጄንሲው ተመሳጥሮ እንዳይሆን የሚል ጥርጣሬ አለን። ምክንያቱም ኤጀንሲው የተሟላ ዶክሜንት አልያዘም ጥቃውን ሲቀጥረው፤ ዋስትና አልያዘም 'መጣል' በሚል" ብለዋል።

አክለው፣ "ኮሚቴዎች ደግሞ 'አይቻልም' ብለው ሲመልሱ አማላጅ ፓሊስ ጠርቶ 'ፓሊሱ እኔ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ፤ በሦስት ቀናት ያመጣል ይስራ' እንዳላቸው ነው ኮሚቴዎቹ የነገሩን። የኤጀንሲው ሰውም፣ ፓሊሱም፣ ሁለቱ ጥበቃዎችም ተይዘዋል" ነው ያሉት።

ሦስቱም ተሽከርካሪዎች ከአንድ ፓርኪንግ ከቆሙበት እንደተወሰዱ፣ የተወሰዱትም ቃሊቲ ቶታል ጨፌ ኮንዶሚኒየም እንደሆነ፣ አንዱ መኪና ኦሮ ኮድ 03 34021 መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላኛው የጠፋው ተሽከርካሪ ኦሮ ኮድ 03 ኦሮ 41867 እንደሆነ፣ ከጠፉት ከሦስቱ አንዱ እንደተገኘ በዚህ ዘገባ ታርጋቸው የተገለጹት እንዳልተገኙ ገልጸው፣ ተሽከርካሪዎቹን ያየ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች እንዲጠቁማቸው ተማጽነዋል።

የባለንብረቶቹ ስልክ ቁጥሮች 0912049042፤ 0965206720
ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አዲስ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
 
@tikvahethiopia
1.34K😢242🙏79😱62💔62🤔41😭37🕊22🥰21😡13
💎 ትልቁ ይገባዎታል!

በፀሐይ ባንክ "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" ተጠቃሚ ይሁኑ!

9.5% እስከ 10% የሚደርስ የወለድ መጠን የሚያስገኝ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ!

እርስዎ በርትተው ይቆጥቡ፤ እኛ ዳጎስ ባለ የወለድ ምጣኔ እንደግፍዎታለን! አሁኑኑ የፀሐይ ባንክ "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" ይክፈቱ!

ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ ወይም ወደ 921 ነጻ የጥሪ ማዕከላችን ይደውሉ፡፡

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!


የፀሐይ ባንክ የቴሌግራም ገጽን ይቀላቀሉ 👇 https://www.tg-me.com/tsehaybanksc
200🙏9🥰5😡4😢2🤔1😭1
" በአነስተኛ ጀልባዎች ለመሻገር የሚደረጉ ሙከራዎች ከንቱ ይሆናሉ "- የዩናይትድ ኪንግደም ጠ/ሚ

ዩናይትድ ኪንግደም ከፈረንሳይ በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አዲስ በተወጠነ እቅድ መሰረት መመለስ እንምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታመር መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በእቅዱ መሰረት አገር ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ ሲመለሱ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸውን ጥገኛ ጠያቂዎች የደኅንነት ፍተሻ አድርጋ ትቀበላለች።

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለንደን ይገኛሉ።

መሪዎቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ስታመር " በአነስተኛ ጀልባዎች ለመሻገር የሚደረጉ ሙከራዎች ከንቱ ይሆናሉ " ብለዋል።

እቅዱ በሳምንት እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎች እንዲመለሱ እንደሚያደርግ የተዘገበ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አሃዙን አላረጋገጡም።

" ለውጥ አምጪው " እቅድ የሰዎች ዝውውር ላይ የተመለደውን አካሄድ ለመስበር የሚያግዝ እና ውጤታማ ከሆነ በስፋት የሚሰራበት ነውም ብለዋል።

ሕገ-ወጥ ስደት " ዓለም አቀፍ ቀውስ፣ የአውሮፓ ሕብረት ቀውስ እና የሁለቱ አገሮቻችን ቀውስ ነው " ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
396😭51🙏16😢11💔8🕊5🤔3
አዲሱ የዩትዩብ ሞኒታይዤሽን መመሪያ ምን ይዟል ?

ከፊታችን ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ዩትዩብ፤ ዩትዩብን ተጠቅመው ገቢ በሚያስገቡ ላይ ጥብቅ መመሪያ አውጥቷል።

መመሪያው ምን ይላል ?

- ከአሁን በኋላ ዩትዩብ ክፍያ የሚፈጽመው አዲስና የራሳቸው ፈጠራ ብቻ ለሆኑ ፤ በብዛት ወይም በድጋሚ በዩትዩብ ላይ ላልዋሉ ስራዎች ነው።

- ክፍያ የሚፈጸምላቸው ቪድዮዎች እውነት እና የራስ ስራ ላይ የተመሰረቱ ብቻ መሆን አለባቸው።

- አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ተጠቅመው የሚሰሩ ሰዎች ክፍያ አይከፈላቸውም።

- በድምፅና ትንሽ የቪድዮ ስራ ብቻ ተጨማምሮባቸው የሚቀርቡ የሌላ ሰዎች ስራዎች ክፍያ አያገኙም።

- በተለያዩ ተንቀሳቃሽ ቪድዮዎች ወይም የሰው ቪድዮዎች ላይ reaction መስጠት እና የሰው ቪድዮዎችን እየሰበሰቡ ማቅረብ ከዩትዩብ ክፍያ ውጭ ይደረጋሉ።

- የራሳቸው ስራ ያልሆነ ቪድዮ ማለትም እዛው ዩትዩብ ላይ በሌሎች የተሰሩ ቪድዮ የሚያቀርቡ ሰዎች የራሳቸውን ሃሳብ እንዲጨምሩና እንዲሰሩ የሚጠየቁበት መንገድ ቢኖርም ያለማስጠንቀቂያም ሊታገዱ ይችላሉ።

ዩትዩብ በአዲሱ መመሪያው ኦሪጅናል ለሆኑ እና ሰዎች በራሳቸው ጥረት ለሰሯቸው ስራዎች ክፍያ ይከፍላል። ክፍያ ለማግኘት የራስን የፈጠራ ስራ ዩትዩብ ላይ መጫን ግዴት ይሆናል።

ዩትዩብ ይህን ወደማድረግ የገባው ሰዎች የራሳቸውን የፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ለማበረታታ ነው።

ዩትዩብ ክፍያ ለመክፈል ከዚህ ቀደም ያስቀመጠው አስገዳጁ 1 ሺህ ሰብስክራይበር እንዲሁም 4,000 የዕይታ ሰዓት በ12 ወራት ውስጥ ማግኘት አሁንም እንደ ግዴታ ይቀጥላል ተብሏል።

#YouTube #TheVerge

@tikvahethiopia
1.04K😢131👏125🙏27😱16😡16😭13🤔8🕊8🥰6
2025/07/14 15:31:23
Back to Top
HTML Embed Code: