Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tax ዩትዩብ ወይም ቲክቶክ የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ገንዘብ የሚያገኙ ግለሰቦች እና ተቋማት ታክስ እንዲከፍሉ ሊደረግ ነው። በክፍያ የሚቀርቡ ወይም በሚያቀርቡት አገልግሎት ገንዘብ ከሚያገኙ የድረገጽ እና የመተግበሪያ ውጤቶች ላይ መንግሥት ታክስ ሊሰበስብ መዘጋጀቱን አሰራሩን ለመተግበር ከወጣው የመንግሥት ሰነድ መመልከቱን ዋዜማ ሬድዮ ዘግቧል። በድረገጽ የሚቀርቡ የሚዲያ አገልግሎቶች ፖድካስት፣…
#Ethiopia🇪🇹

ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።

በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች "  በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው። #CAPITAL

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.18K😭440😡310👏110🤔72🕊30😱23🙏19💔15🥰13😢9
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል !

በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የጭካኔ የግድያ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኞች ተብለው የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።

ተከሳሾቹ ለፍርድ ውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል በማለት " የቆየ ህመም አለብን " ቢሉም የመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሃኪሞች የምርመራ ማስረጃ " የቆየ ህመም የለባቸውም " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የመቐለ ማእላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ ግድያ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?

የተጠርጣሪ ጠበቆች ትናንት ሀምሌ 3 " ደምበኞቻችን የቆየ ህመም አለባቸው ይህንን ለማረጋገጥ የህክምና ማስረጃ ለአርብ ሀምሌ 4 እናቀርባለን " ብለው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ይህን ተቀብሎ ለዛሬ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

ዛሬ አርብ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም ከመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰዓት በፊት ቤተሰብ የሚገኙባቸው የሚድያና የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች በፍርድ ቤቱ በራፍ ደርሰው ተሰባስበዋል።

ተከሳሾች ለውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል ብለው የጠየቁት የህክምና ማስረጃ የቆየ ህመም እንደሌለባቸው አረጋግጧል።

ዳኞችም ይህን ካረጋገጡ በኋላ በተከሳሾች ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል።

አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ያሬድ ገብረስላሰ በላይ እና ኣንገሶም ሃይለማርያም በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመርካታቸው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች የወንጀል ደርጊቱን ከማጠራት እስከ ምርመራና ውሳኔ ድረስ በችግሮች የተተበተበ እንደነበር በመግለፅ ማረሚያ ቤት የፍርድ ውሳኔውን በጥብቅ እንዲተገብረው ጠይቀዋል። 

" የጭካኔ ግድያው የሞት ፍርድ ያሰጥ ነበር " ያሉ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የተበዳይ ቤተሰቦች ወደ ቀጣዩ የፍርድ ቤት ይግባኝ ይጠይቁ " ብለዋል።

ከነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም የተጓዘው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ በዚሁ ተቋጭቷል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን ልኳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የእንስቷን ግድያ ከመነሻው እስከ ፍርድ ሂደቱ ሲከታተል ቆይቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
2.07K👏447🙏117😡69😭53🕊43😢17😱15💔13🥰6🤔2
ባለንበት ሆነን ወርሃዊ የውሃ ፍጆታችንን በቀላሉ በቴሌብር በመክፈል ጊዜያችን መቆጠብ እንችላለን።

ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ ክፍያ ➡️ የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ➡️ ክፍያ
*127# ደውለን ወይም ቴሌብርን በስልካችን በዚህ ሊንክ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
150🙏11👏7😢3🕊1💔1
#AmazonFashion

ሙሉ ልብስ ሽያጭና ኪራይ   የአመቱ የማጣሪያ ሽያጭና ታላቅ ቅናሽ ሙሉ ልብስ(ሱፍ) ሽያጭ ከ 12 ሺ -15 ሺ ብቻ፤ በርካታ አማራጭ ስላለን ለብዛት ፈላጊዎች ለሚዜዎች ለተመራቂ ተመራቂዎች በብዙ አማራጭ አለን። በተጨማሪም የሙሉ ልብስ ኪራይም  በሌላኛው ብራንቻችን አለን።

አድራሻ: ፒያሳ downtown ህንፃ ምድር ላይ 

☎️ 0919339250 / 0911072936 /0939721321

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
150😭12🙏3😡2
“እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” - ባለስልጣኑ

➡️ከ2015 እስከ ሰኔ 24/2017 ዓ/ም በሥራ ላይ የ142 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል!


የአዲስ አበባ ከተማ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2015 እስከ 24/10/2017 ዓ/ም ድረስ በመዲናዋ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች 121 ወንዶች፣ 21 ሴቶች በድምሩ 142 ሰዎች በህንጻ ሥራ ላይ እያሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

42 ወንዶችና 10 ሴቶች በድምሩ 52 በለሚኩራ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በንፋስ ስልክ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በቦሌ፤ 13 ወንዶችና አንዲት ሴት በድምሩ 14 ሰዎች በቂርቆስ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ህወታቸው ማለፉን የባለስልጣኑ መረጃ በዝርዝር ያስረዳል፡፡

ባለስልጣኑ ህንፃች አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ “እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” ብሏል፡፡

ባለፉት አስር አመታት በአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በስፋት እየተገነቡ እንደሚገኙ፣ ለአብነትም በ2017 ዓ/ም በከተማዋ 11 ሺሕ 748 አዳዲስና 12 ሺሕ 322 ነባር ግንጻዎች ክትትል እንደተደረገባቸው፣ ግንባታዎቹ ከ581 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳላቸው የባለሥልጣኑ መረጃ ይገልጻል፡፡

በከተማዋ በግንባታ ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ የአደጋ መንስኤዎች እና ስጋቶች ምንድን ናቸው?

-ከከፍታ ላይ መውደቅ
-የኤሌክትሪክ አደጋ
-የእቃ መውደቅ
-የግንባታ መዋቅር ችግር
-የሠራተኞች በቂ ስልጠና አለመውሰድ
-የግል ደህንነት መጠበበቂያ መሳሪያዎች ያለመጠቀም
-የቁጥጥር ችግር፣ የበጅት እጥረት
-ህግ የማስከበር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ “በአስር አመት አማካኝ የኢንዱስትሪው እድገት 10%"፣ “በቀጥታና በተዘዋዋሪ በየዓመቱ በአማካኝ የሚፈጠረው የሥራ እድል 1.2 ሚሊዮን” መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ “በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፈጣን ኢንዱስትሪው እድገት በሠራተኞች የሥራ ላይ ደንነነት ተመሳሳይ ለውጥና መሻሻል እየታየበት አይደለም” ብሏል፡፡

“አልሚዎች ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጭ ለመጨረስ በሚያደርጉት ጥረት የሥራ ላይ ደህንነት ትኩረት በመሆኑ አደጋና ጉዳት እየጨመረ ይገኛል” ብሎ፣ የኮንስትራክሽን እድገት በአጭር ጊዜና በዝቅተኛ ዋጋ ግንባታዎችን ለመጨረስ የሥራ ላይ ደህንነትን አቀናጅቶ መተግበር እንደሚገባ አሳስቧል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ የተያያዘ ሲሆን፣ ተጣለ የተባለውን ቅጣት የተመለከተ ተጨማሪ አለን)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
483😭70👏12🕊11😡9😱5😢5🤔3🙏3💔3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
“እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” - ባለስልጣኑ ➡️ከ2015 እስከ ሰኔ 24/2017 ዓ/ም በሥራ ላይ የ142 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል! የአዲስ አበባ ከተማ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2015 እስከ 24/10/2017 ዓ/ም ድረስ በመዲናዋ በ11ዱም…
ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።

እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።

ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።

ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።

ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡

(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
599😡114👏44🙏14😢13🤔10🕊10🥰8💔1
2025/07/14 09:34:48
Back to Top
HTML Embed Code: