Telegram Web Link
#Axum

የአክሱም ከተማ ፖሊስ በከተማው ክንደያ በተባለ ቀበሌ ሁለት ተጠርጣሪዎች አደገኛ ኬሚካል በመጠቀም የወርቅ ማጣራት ተግባር ሲያከናውኑ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አሳውቋል።

ፖሊስ ከህብረተሰብ በደረሰው ጥቆማ የፍ/ቤት የፍተሻ ትእዛዝ በመያዝ የተለያዩ የፍትህ አካላት ፣ የአገር ሽማግሌዎችና የጤና ባለሙያዎች በማሳተፍ ነው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፡፡

የከተማዋ አቃቤ ህግ የህበረተሰብ የጤና ጠንቅ የሆነውን አደገኛ ኬሚካል በመጠቀም ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ተጠርጣሪዎቹ በአጭር ጊዜ አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ከባለ ድርሻ አካላት በመሆን ይሰራል ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

Photo credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
300👏38🤔12🙏9😡9🕊5😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት " ስጋት ላይ ጥሎናል " ያሉት አዲስ መመሪያ ምን ይዟል ? የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አሰራር ስርዓት ለማስያዝ በሚል ዳግም ምዝገባ በማካሔድ ላይ መሆኑን ከዚህ ቀደም በሰጣቸው መግለጫዎች አስታውቋል፡፡ በዚህ ሒደት 85 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲሱ መስፈርት መሰረት ዳግም ለመመዝገብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እንደሚዘጉም…
" መንግስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የመዝጋትም ሆነ የማዳከም ፍላጎት የለውም " - የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዋናዮች በዳግመ ምዝገባው ዙርያ ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ፣ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ መንግስት ተቋማቱን የማጥፋት እቅድ አለው እየተባለ ለሚቀርበው ቅሬታ በሰጡት አስተያየት፣ " ይሔ አስተያየት ስህተት ነው፣ እነዚህን ተቋማት የማዳከም አላማ የለም " ብለዋል፡፡

" ይልቁንም መንግስት እነዚህን ተቋማት የማጠናከር አላማና ፍላጎት ነው ያለው፣ የዳግመ ምዝገባና ምዘና ሒደቱ ትኩረትም ይህን እውን ማድረግ ነው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የዳግመ ምዝገባና ምልከታ ሒደቱ በአዲስ አበባ መጠናቀቁን ተናግረው፣ በቀጣይ የትኞቹ ተቋማት ይቀጥላሉ፣ የትኞቹ አይቀጥሉም የሚለውን ለመግለፅ ሪፖርት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባው የዳግመ ምዝገባና ምዘና ስራ በመጠናቀቁ፣ በቅርቡ በክልሎች ይህንን ስራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ?

" አሁን እየተከናወነ ባለው ዳግመ ምዝገባና ምዘነና ሒደት የተፈለገው፣ የትምህርት ተቋማቱ መሰረታዊ በሆነ መንገድ ራሳቸውን እንዲያድሱ ነው፡፡

ባለቤትነታቸው እንኳ የማይታወቅና አጠራጣሪ የሆኑ ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች የማጥራት ስራ ነው እየተሰራ ያነው፡፡መዝጋት የምትፈልገውን ተቋም ይህን ያህል ጊዜ ማቆየት አያስፈልግም፡፡ በፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጠህ ከገበያ እንዲወጡ ማድረግ ይቻላል፡፡ ግን እሱ አይደለም አላማችን፡፡

የእኛ አላማ፣ ትናንሽ ቢዝነሶች ሆነው የጀመሩት ተቋማት ወደ አንድ ተደራጅተውና ተጠናክረው እንዲመጡ ነው፡፡ ካልቻሉ ደግሞ ከገበያው መውጣት አለባቸው፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ (ፕሮፌሰር ብረሀኑ ነጋ) ከዚህ በፊት የተናገሩት ነገርም (50 ተቋማት ይበቃሉ ማለታቸው ይታወሳል) ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ጠንከር ጠንከር ያላችሁ ተቋማት ሁኑ፡፡ ጥቂት ተቋማት ይበቃሉ፡፡ ይህ ሁሉ ተቋም አለ ማለት፣ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ነው ያሉት፡፡ ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ተቋም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ የእኛም አላማ ይኸው ነው፡፡

ከዚህ በፊት ወጣ የተባለው፣ ' አብዛኞቹ ተቋማት መስፈርቱን አያሟሉም ተብለዋል ' የተባለው ዘገባ ስህተት ነው፡፡ ሚድያዎችን ለመተባበር ብለን የሰጠናቸውን መረጃ አዛብተው ዘገቡት፡፡ ከዛም፣ ሁሉም የግል ትምህርት ተቋማት መስፈርቱን አያሟሉም ተባለ ተብሎ ተስተጋባ፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡

በወቅቱ ያልነው፣ አብዛኞቹ ተቋማት ለዳግመ ምዝገባ የሚሆን የተሟላ ሰነድ አላቀረቡም ነው፡፡ ሰነድ አስገቡ ስንላቻው ስለነበር ማለት ነው፡፡ ሰነድ አላሟሉም ማለትና ያስገቡትን ሰነድ ገምግሞ መስፈርቱን አላሟሉም ማለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡

ቀደም ሲል ሒደቱ በጣም ቀላል ነበር ኮሌጅ ለመክፈት፣ ትንሽ ገንዘብ ካለህ አንድ ሁለት ክፍል ተከራይተህ መክፈት ነበር፡፡ በዚህ መሰሉ ሒደት መቀጠል አይቻልም አሁን፡፡ ይህን ቀላል አካሔድ የለመዱ ተቋማት መቀጠል አይችሉም፡፡ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው በትንሹ ኮሌጅ የሚያስብል ስራ ሰርተው ነው ይህንን ቢዝነስ መጀመርና ማስኬድ ያለባቸው፡፡

አሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በተቀመጠው መስፈርት መሰረት እንደ ኮሌጅ መቀጠል እችላለሁ የሚሉት ተቋማት ናቸው የተመዘገቡት፡፡ ከተመዘገቡት መካከል ደግሞ፣ አሁን ግምገማ ተደርጎ፣ ሰነዶቻቸው ተፈትሸው፣ የመስክ ምልከታም ተደርጎ፣ በትክክል መስፈርቱን ያሟላሉ የሚባሉትን ውጤት እንገልፃለን፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የአዲስ አበባን ተቋማት ምዝገባና ምልከታ ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል፡፡ ውጤቱን ለመግለፅ ሪፖርቱን በማዘጋጀት ላይ ነው ያለነው፡፡ ጎን ለጎን ደግሞ በክልሎች ይህንን ስራ ለመጀመር ቅድመ ዘግጅት እያደረግን ነው፡፡ ስራው በአዲሱ የበጀት አመት የሚጀመር ይሆናል፡፡

እስካሁን ከዘርፉ የወጡ ተቋማትን በተመለከተ የተለያየ አሀዝ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ መጀመሪያ ላይ 84 ተቋማት ሳይመዘገቡ ቀሩ፡፡ በኋላ ላይ ግን ዘግይተው የመጡ አሉ፡፡ ከነሱ ውስጥ በቂ ምክንያት ያቀረቡትን መዝግበን እየገመገምን ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተመዝግበው ከነበሩት ውስጥ ለመውጣት ሒደት ላይ ያሉ አሉ፣ ጎንለጎን ማለት ነው፡፡ ይህ የእነሱ ገባ ወጣ ማለት፣ ከዘርፉ የወጡ ተቋማት ብዛት በየጊዜው እንዲለያይ አድርጎታል፡፡ እንደዛም ሆኖ፣ አሁን የምዝገባና የግምገማ ሒደት ላይ ስለሆንን ትክክለኛ ቁጥሩን ማስቀመጥ ቢያስቸግርም ቢያንስ 80 የግል ትምህርት ተቋማት፣ ስራቸውን አቋርጠው ከዘርፉ ተሰናብተዋል፡፡

የዳግመ ምዝገባው መመሪያ ላይ በቂ ውይይት አልተደረገበትም፣ ከዘርፉ ተዋናዮች ግብአት አልተወሰደም የሚለውም ጉዳይ ትክክል አይደለም፡፡ ከተቋማቱ ባለቤቶች በሁለት መንገድ ግብአት ተቀብለናል፡፡ አንደኛው፣ ከውይይት መድረክ የተገኘው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በፅሑፍ የተቀበልነው ነው፡፡ በዚህ መንገድ በአዲስ አበባ በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ከተደረገ ውይይትና በፅሑፍ ከቀረቡልን ሀሳቦች ግብአት ወስደናል፡፡አስፈላጊ የሆኑትንና ያስኬዳሉ የምንላቸውን ሀሳቦች በግብአትነት ተጠቅመንባቸዋል፡፡

ለምሳሌ ፦ ከእነሱ ተቀብለን ካካተትናቸው ሀሳቦች አንዱ፣ በመውጫ ፈተና ቢያንስ 25 በመቶ ያላሳለፈ ተቋም መቀጠል የለበትም የሚለው መስፈርት መቼ ተግባራዊ መሆን ይጀምር የሚለው ላይ የእነሱን ሀሳብ ተቀብለን የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጥ አድርገናል፡፡

ይህ መስፈርት መተግበር የሚጀምረው፣ መመሪያው በወጣበት ጊዜ ትምህርት በጀመሩ ተማሪዎች ላይ እንጂ፣ በነባር ተማሪዎች ላይ መሆን የለበትም የሚለው ሀሳብ ከነሱ የመጣ ነው፡፡ ይህ ሀሳባቸው አሳማኝ በመሆኑ ተቀበልነው፡፡ አሁን ለትግበራው ሁለት አመት ገደማ አላቸው፡፡ በ 2019 ዓ.ም ገደማ ነው መተግበር የሚጀምረው ይህ መመሪያ፡፡ ሌሎችም የተቀበልናቸው ሀሳቦች አሉ፡ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
701😡103🙏26🤔22😭17🕊14🥰8😢5😱3
#SafaricomEthiopia

⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ዘና ፈታ እንበል! 🥳

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

#1wedefit
#Furtheraheadtogether
62😡13🥰4😭4
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ ባለሥልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ 1,227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደለቸው መዘገቡ ይታወሳል። ጭማሪውን ተከትሎ የአዲስ…
#AddisAbaba

የትምህርት ቤት ክፍያ !

20 በመቶ ትምህርት ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ላይ ከወላጆች ጋር አለመስማማታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቅርቡ ባጸደቀው የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርአት ደንብ ቁጥር 194/2017 መሰረት በ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት ክፍያ ላይ ከ ተማሪ ወላጅና አሳዳጊዎች ጋር ካልተስማሙ መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መካሄዱን የከተማው ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በውይይት መርሃ ግብሩ ፦
- የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ፣
- የትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች
- የግል ትምህርት ቤቶች አሰሪዎች ማህበር ፣
- የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች እና የተማሪ ወላጅ ኮሚቴ ተወካዮች እንደ ተሳተፉ ቢሮው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።

ውይይቱ የተካሄደው በጭማሪው ላይ መስማማት ላይ ያልደረሱ ትምህርት ቤቶች ደንቡ በሚያስቀምጠው መሰረት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ አስተሳሰብ ለመያዝ እንዲቻል መሆኑን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ "በደንቡ መሰረት 80 ፐርሰንት ያህል ትምህርት ቤቶች ከወላጆችና አሳዳጊዎች ጋር በመስማማት የአገልግሎት ክፍያ መጨመራቸው የሚበረታታ ተግባር ነው" ብለዋል።

እንደ ትምህርት ቢሮ ሃላፊው ገለጻ 20 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች እና አሳዳጊዎች መስማማት ላይ አለመድረሳቸውን አመላክቷል።

የትምህርትና ስልጠናና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢዘዲን ሙስባህ "በደንቡ ላይ በመግባባት ወደ ስራ መገባቱን በዚህም መሰረት በርካታ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በመስማማት መጨመራቸውን ፣ መመሪያውን መሰረት በማድረግም ባለስልጣኑ በተቀሩትና መስማማት ባልቻሉት ላይ  ውሳኔ መስጠቱን" አሳውቀዋል ።

ባለሥልጣኑ ምን ውሳኔ እንዳሳለፈ በዝርዝር ባይገለጽም የወላጆችን የመክፈል አቅም እና የትምህርት ተቋማቱን የግብአት አቅርቦት ታሳቢ አድርጎ ተግባራዊ የሆነ መሆኑን ስለመናገራቸው ትምህርት ቢሮው አሳውቋል።

#AddisAbabaEducationBureau

@tikvahethiopia
219😭40😡25🕊5🤔2😢2😱1
" በወረዳዎቹ በቂ የጸጥታ ኃይል የለም። ጥቂት የጸጥታ ኃይሎችም ታጣቅዎቹ ጥቃት ካደረሱና ዝርፊያ ከፈጸሙ በኋላ ይመጡና ወዲያው ይመለሳሉ " - ፓርቲው

ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፣ " የ'ሸኔ' ታጣቂዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይ በመተከልና ካማሺ ዞኖች እያደረሱት ያለው ጥቃት ቀጥሏል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ፓርቲው ሰሞኑንም በወንበራ ወረዳ ጥቃት መድረሱን ገልጾ፣ " የክልሉ መንግስት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት በመስጠት በቂ የጸጥታ ኃይል በመላክና በአከባቢው የመከላከያ ካምፕ በማቋቋም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት እንዲያስጠብቅ " ጠይቋል።

" በካማሺ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች፣ በመተከል ዞን በቡለን፣ ድባጢና ወምበራ ወረዳዎች ታጣቂዎቹ የሚያደርሱት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ፓርቲው፣ " ታጣቅዎቹ ንጹሐንን እና የጸጥታ አካላትን ይገድላሉ፣ የግልና የመንግስት ሀብት፣ ንብረት፤ የመንግስት ተቋማትን ይዘርፋሉ፤ ያወድማሉ " ሲልም ከሷል።

" ባለፈው ወር ቡለን ከተማ፣ ድባጢ ወረዳ በርበር ከተማ ሁለት ጊዜ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን፣ በቡለን ከተማ በአንድ ሌሊት ብቻ የአረፋ በዓል በማክበር ላይ የነበሩ 11 የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትን ከመግደል ባለፈ በርካታ ንጽሐንን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችንና የጸጥታ አካላት ገድለዋል፤ ንጽሐንን አግተዋል " ብሏል።

ታጣቂዎቹን ተቋማትን " ዘርፈዋል፤ አውድመዋል " ሲል የከሰሰው ፓርቲው፣ " ሰሞኑን በወምበራ ወረዳ ወግዲና ሌሎች ቀበሌዎች ተመሳሳይ ጥቃቶችን ፈጽመዋል። ይህ ታጣቂ ቡድን በድባጢ ወረዳ ከ60% በላይ፣ በቡለን ወረዳ ከ30% በላይ ቀበሌዎችን በራሱ ቁጥጥር ስር በማደርግ ሰሞኑን ደግሞ በወንበራ ወረዳ በወግዲ ቀበሌ ግዛቱን ለማስፋፋት እየጣረ ይገኛል " ሲል ጠቁሟል።

ፓርቲው፣ " የሸኔ ታጣቂዎች በየወረዳዎቹ በሚኖሩ በሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ነው ጥቃት የሚያደርሱት " ብሎ፣ " በዚህ ምክንያት ነዋሪዎቹ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። በርካቶችም ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞችና ወረዳዎች እየሄዱ ይገኛሉ " ብሏል።

" ታጣቂዎቹ በወረዳዎቹ ይህንን ሁሉ ጥቃት ሲፈጽሙና ወረዳዎች ‘ካቅማችን በላይ ነው’ እያሉ ለክልሉ መንግስት ሲያሳውቁ የክልሉ መንግስት ግን ለምን በቂ ትኩረት መስጠት እንዳልፈለገና ህዝቡን መከላከል ለምን እንዳልቻለ ለእኛ እንቆቅልሽ ሆኗል " ነው ያለው።

ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ " ህዝቡም በተደጋጋሚ ለክልሉ መንግስት የይድረሱልኝ ጥሪ ቢያቀርብም ሰሚ አላገኘም። በወረዳዎች በቂ የጸጥታ ኃይል የለም። ጥቂት የጸጥታ ኃይሎችም ታጣቅዎቹ ጥቃት ካደረሱና ዝርፊያ ከፈጸሙ በኋላ ይመጡና ወዲያውኑ ወይንም በነጋታው ይመለሳሉ " ሲል ነው የገለጸው።

" ህዝቡ ከፍተኛ ስጋት ላይ ይገኛል። ከሁሉም በላይ ይህ ሁሉ ጥቃትና በደል በህዝቡ ሲደርስ ክስተቱ በየትኛውም የመንግስት ሚዲያ አለመዘገቡና ሽፋን አለማግኘቱ ህዝቡን አሳዝኗል " በማለትም ወቅሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
227😡38😭15🙏12🕊7😢4💔4🤔3😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Sidama

ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዲስ ፖሊስ አዛዥ ተሹሟል።

የምስራቅ ሲዳማ ዞን ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆነዉ ተሹመዋል።

በፀጥታ ዘርፉ ዉስጥ ሪፎርም ዉስጥ እንደሆነ በሚነገረው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ተቋም ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በተፃፈ ደብዳቤ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ ከዛሬ ሐምሌ 2/2017ዓ/ም ጀምሮ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆነዉ ተሹመዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኮማንደር መልካሙ አየለ በምን ምክንያት እንደተነሱ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
313😢18🕊16💔14🙏12🤔10😡10😭7😱5🥰4
" ካምፓኒዎቹን መቀመቅ የሚከት እብደት እንዲቆም የሚመለከተው አካል ሃላፊቱን ይወጣ " - አቶ በየነ ምክሩ

አሁን ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙትና የትእምት (EFFORT) ዋና ስራ አስፈፃሚ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ በየነ መክሩ ' ላዛ ትግርኛ ' ለተባለ የዩቱብ ሚድያ ቃለ መጠይቅ ሰጥተው ነበር።

በዚህም " ህገ-ወጥ " ሲሉ የጠሩት የደብረፅን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት በትእምት ካምፓኒዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ እንዲያንዣብብ እየተንቀሳቀሰ ነው በማለት ከሰዋል።

መጋቢት 2017 ዓ.ም በትግራይ በወቅቱ በነበረው ጊዚያዊ  አስተዳደር ላይ በተከሰተው ከፍተኛ የፓለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መውጣታቸው የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው የሳቸውንና የባለ አደራ ቦርድ ሰብሳቢ ቴድሮስ ሓጎስ የሚጠቀሙበት ማህተም ከህግ አገባብ ውጪ በማስቀረፅ " ህገ-ወጡ ቡድን " አደገኛ ተግባራት በመፈፀም ላይ ይገኛል ብለዋል።

" ዋና ስራ አስፈፃሚ ፣ ቦርድና የባለ አደራ ቦርድ በስራ እያለ ቡድኑ የራሱ  ህገ-ወጥ  ቦርድና የባለ አደራ ቦርድ በመሰየም ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመቅጠር ማስታወቅያ በማስነገር ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ በየነ " ካምፓኒዎቹን መቀመቅ የሚከት  ይህንን መሰል እብደት እንዲቆም የሚመለከተው አካል ሃላፊቱን ይወጣ " ብለዋል።

" የቡድኑ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ካምፓኒዎቹ ከስራ ውጭ  እንዳያደርግ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተከታታይ ምክክሮች እያካሄድን ነው " ያሉ ሲሆን " ጉዳዩ በህግ-ማእቀፍ እንዲታይ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ክስ መመስርተናል " ሲሉ አስታውቀዋል።

ይህን ሳይሳካ ከቀረ ግን የፌደራል መንግስት በትእምት ካምፓኒዎች ላይ በጦርነቱ ጊዜ ያስቀመጠው እግድ መልሶ ለማየት የሚገደድበት ሁኔታ ዝግ አይደለም ብለዋል። 

በተጨማሪ ምን አሉ ?

- " የትእምት 60 በመቶ ሃብት በጦርነቱ ወድሟል ፤ መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ አርጅቷል ፤ ትራንስ ኢትዮጵያ ከነበሩት 500 መኪኖች አሮጌ 100 መኪኖች ብቻ ነው የቀሩት ፤ አልመዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ  በአውሮፕላን ቦንብ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። "

- " የፌደራል መንግስት ከጥቅምት 2013 እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም በትእምት ካምፓኒዎች ላይ አኖሮት የነበረው እግድ ለጊዜው ሲያነሳ ካምፓኒዎቹ ከህወሓት ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው መስራት እንዳለባቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስጥቶ ነው ያስረከበን። " 

- " የፌደራል መንግስት በትእምት ካምፓኒዎች ያስቀመጠው  እግድ ሙሉ በሙሉ ባለነሳበት ሁኔታ ሆነን ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው እንዲያንሰራሩ ስንሰራ ነበር፤ ህገወጡ የህወሓት ቡድን ከካምፓኒዎቹ ላይ እጁ የማያነሳ ከሆነ የፌደራል መንግስት እግድ ሊቀጥል ይችላል። "

- " ህገ-ወጥ ቡድኑ በሃይል ካስቀመጣቸው አመራሮች የተደረገ ርክክብ የለም ፤ ዋና ስራ አስፈፃሚና ቦርድ የነበረው ነው ያለው። "

ትእምት ኢንቨስትመንት በስሩ 15 ካምፓኒዎች እንዳሉት ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
456🤔39🕊21🥰12😡11😭10🙏6😢2😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" መንግስት ሁሉን አቀፍ እና አካታች ፖለቲካዊ ውይይት ማድረግ አለበት " - የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ከአምስት አመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አካሄደ።

በዚህ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የኦነግ በማዕከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ምን አለ ?

- መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት ያድርግ፤

- የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ካሉ አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮች ይፍታ፤

- የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ እና ነፃ እንዲሆን ይሁን ሲል መጠየቁን አቶ ለሚ ተናግረዋል ።

ፓርቲው ላለፉት አምስት አመታት በየደረጃው ያሉ አመራሮቹና አባላቶቹ በመታሰራቸው እንዲሁም ከዋናው ጅምሮ በዞን እና ወረዳዎች ያሉት ጽህፈት ቤቶቹ በመዘጋታቸው የፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ማሳለፉን የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አስታውሰዋል።

በፓርቲው በውስጥ የገጠሙትን ችግሮች እና ክፍተቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ኮሚቴ መዋቀሩንም አቶ ለሚ ገልፀዋል።

ፓርቲው በሀምሳ አመት የትግል ጉዞው ያስመዘገባቸው ድሎች እና ድክመቶች በዚህ ጉባኤው ይገመግማል ያሉት አቶ ለሚ የወደፊት የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ በቀጣይ ጉባኤው እያደረገ ያለው ሰላማዊ ትግል ፀንቶ እንደሚቀጥል የተናገሩት አቶ ለሚ " መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዴሞክራሲን መለማመድ አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘብ ከወዲሁ እናሳስባለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamliyNekemte

@tikvahethiopia
279😡89🕊22🤔12👏5😢3🙏3🥰2😱2
#AddisAbaba

ሽንኩርት ፣ ድንችና ሌሎች የአትክልት ምርቶች #ከቫት ነጻ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው " ማህበረሰቡ ዕለት በዕለት የሚሸምታቸው ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርገዋል " ሲል ገልጿል።

ከሰሞኑን ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በወረደው ሰርኩላር ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች የአትክልት ምርቶች ከቫት ውጭ መደረጋቸውን አመላክቷል።

በሰርኩላሩ ላይ " የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 አንቀፅ 10 እና አዋጅን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 570/2017 ዓ.ም መሰረት ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች ያሉ ምርቶች ወደሀገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ ተመርተው ለግብይት ሲቀርቡ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መደረጋቸውን ተደንግጓል " በሚል ተቀምጧል።

በዚህም መሰረት ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች ብቻ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ መሆናቸው ታውቆ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ተገቢው ክትትል በማድረግ እንዲፈፀም አዟል።

ይሁንና በአዋጁ ከታክስ ነፃ ከተደረጉ ውጪ የፍራፍሬ ምርቶች በሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች የቫት አሰራሩ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
985🙏133👏72🤔41😡31😱10😢9🕊9🥰8😭1
2025/07/10 03:08:48
Back to Top
HTML Embed Code: