🚩 ከሐበሻ ምድር ፈልቆ ምዕራብ ህንድ ላይ በነገሠው ማሊክ አምባር ሕይወት ዙሪያ በኦማር ሑሴን ዐሊ ተዘጋጅቶ በኪዳኔ መካሻ ወደአማርኛ የተተረጎመው "ማሊክ አምባር፡ ከቀንበር እስከ መንበር" የተሰኘው መጽሐፍ የዛሬ ዳሰሳችን ርዕስ ነው። ከአንትሮፖሎጂ ምሁሩ ሙሐመድ አወል ሐጎስ ጋር የሚከተለውን የዳሰሳ ቆይታ አድርገናል።
.
🥎 Enjoy! | Like | Share | Subscribe👇
.
📚 [ https://youtube.com/live/_GBu5oSFZPg ]
.
#የመጽሐፍትዳሰሳ #ማሊክአምባር #የተዘለሉታሪኮች #ሕንድ #ዴካን #ዓዳል #ሐረርጌ #ቶክኢትዮጵያ
🍁 ባለፉት ሁለት ቀናት ለብሄርተኛ ንቅናቄ መሠረት ስለሆኑ 3 ተገቢ ዓላማዎች በአጭሩ አይተናል። አሁን ደግሞ ብሄርተኛ ንቅናቄዎችን የሚያበላሹና ዓላማ የሚያስቱ፣ ለሰብዓዊ ቀውስም የሚዳርጉ 6 መሠረታዊ ችግሮችን ማየት እንጀምራለን።
.
❶ በትምክህተኝነት ላይ ሲመሠረት
—————————
.
የብሄርተኝነት ንቅናቄዎችን ከሚያበላሹ ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው የትምክህትና የበላይነት አመለካከት ነው። ሰዎች ባህላዊ ማንነታቸውን ከሌሎች የበለጠና የተሻለ እንደሆነ ማሰብ መጀመራቸው፣ ሌሎችን በንቀትና በዝቅተኝነት መገምገም መጀመራቸው እጅግ ግዙፍ ችግር ነው። ምክንያቱም ከትምክህት ቀጥሎ የሚመጣው የአመለካከት በሽታ "የፖለቲካ ሥልጣን የሚገባው ለእኔና እኔን ለመሰሉ ሰዎች ብቻ ነው" የሚል ነውና።
.
ይህ ዓይነቱ አመለካከት እንደኢትዮጵያ ባለ የብዝኃነት አገር ውስጥ የብሄርተኝነት ንቅናቄዎችን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ማለቂያ የለሽ ፀብ ውስጥ የሚከት፣ የጭቆና ዑደትንም እየቀያየረ አገሪቱን መፍትሄ በሌለው የፖለቲካ ቁልፋት ውስጥ የሚቀረቅር ነው።
.
ለማመን ፈለግንም አልፈለግንም የኢትዮጵያ ማኅበረ ፖለቲካ እንዲህ ስንክልክል ብሎ የቀረው በትምክህታዊ አመለካከቶች ምክንያት ነው። የአገሪቱ የፖለቲካ ንቅናቄዎች ዋና ማጠንጠኛ የራስ ገዝነት ትግል መሆኑም የዚህ እውነታ ማሳያ ነው። ትምክህት የራስ ገዝነት ዋና ጠላት ነው። የትምክህት በሽታ የተጠናወተው የትኛውም ንቅናቄ የሕዝቦችን የራስ ገዝነት መብት ሊያከብር አይችልም — ኢምፖሲብል!
.
ይቀጥላል... (ተከታታይ ጽሑፎቹን በአንድ ላይ በቪዲዮ ማየት ለምትመርጡ ሊንኩ እነሆ ➽ https://www.youtube.com/live/NQqBMoaRZ7Y?si=T8XHFrh2ssAmKElK )
.
#ብሄርተኝነት #ዘረኝነት #ጽንፈኝነት #የብሄርፖለቲካ #የደቦጥቃት #ኢትዮጵያ #ቶክኢትዮጵያ
2024/04/27 16:10:14
Back to Top
HTML Embed Code: