Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት  የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ነሐሴ 24 ነው
••
አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡
••
የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፤ ነፍሳቸውንም ‹‹የጠራሽ፣ ንጽሕት ነፍስ ሆይ ወደ እኔ ነዪ›› ብሎ በክብር ተቀብሏታል፡፡ በመጽሐፈ ገድላቸው እንደ ተጠቀሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው።
••
በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በይፋት ፱ ወር፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት፤ በትግራይና በኢየሩሳሌም ገዳማት ፩ ዓመት፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር፤ በደብረ አስቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል (ገ.ተ.ሃ ፶፱፥፲፬-፲፭)፡
•••
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው አይለየን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሠማያዊ
በአደባባይ ተተክለሀል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሀል 👏
••
የመነኮሳት መመኪያ ፣ የምእመናን ሁሉ አባት ፣ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ሐዲስ ሐዋርያ፣ አጋንንትን የሚያሳዱ ጣዖታትን የሚያርዱ፣ እልፍ አእላፋትን በወንጌል መረብ የሚያጠምዱ፣ በምድር ተወልደው እንደ መልአክ የኖሩ ጻድቁ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት ያረፉበት እለት ዛሬ ነው። እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት የቤታቸውን በር እንደ ተከፈተ ጥለው የወጡትን አባት፣ የገነትን ደጅ ወለል አድርጎ ከፍቶ በታላቅ ክብር የተቀበለበት እለት ነው።
••
እንኳን አደረሳችሁ!
አባ ጸሊ በእንቲአነ!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሞቼ ነበር ተቀብሬ
ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
ወዴት ነበር የእኔ እጣ
ከንቱ ነበር ማንነቴ
ተሽናፊ ለዚች ዓለም
••
ግን አንተ የያዝከው
አባቴ የያዝከው
ይኖራል ዘላለም
••
አኑሮኛል ቸርነትህ ልክ የሌለው ደግነትህ(2)
እንዳንተ አይነት ከዬት ይገኛል
ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል(2)
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ አማኑኤል ሆይ!
••
ስፍራ ሳይርቀው የሚረዳ ፣ ዘመን ሳያልፍበት የሚያጽናና ፣ የጠቆረውን ፊት የደስታ ዘይት የሚቀባ ፣ የምህረት አባት ፣ የይቅርታ ጥላ ማን አለ እንደ አማኑኤል በያለንበት ይጠብቀን አሜን!
••
የሚያጽናናኝ የለም እኔ እንዲህ ስከፋ
ህልምም ሆኖብኛል የሰው ሁሉ ተስፋ
ቃልህን የማታጥፈው አንተ ከኔ አትጥፋ /፪/
••
አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ /፪/
••••
#አማኑኤል
#photoeditingchallengesstoday
#ortodoncia
#እመቤታችን
#orthodoxchurch
#እግዚአብሔር
#ortodox
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
••
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከ ሐዲስ ኪዳን አበው አንዱ የሆነ ንፁሓን ነብያት ቅዱስ ገብርኤል እና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት ከህፃንነቱ ጀምሮ ቅኑዕት እንደ ገበሬ ጽሙድ እንደ በሬ ሆኖ እግዚአብርን ያገለገለ በፍፁም ልቡ አለምን የናቀ ከተድላዋም ከደስታዋም የተለየ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ ፣ መምህር ፣ ሰማዕት ፣ ባህታዊ ነቢይ ጻድቅ ነው።
••
ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤቱ በረከቱ በኛ ላይ
በእውነቱ ይብዛልን ይደርብን አሜን !!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቅዱስ ሩፋኤል መላዕክት
•••
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወርኃ ጶግሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፣ በዚህ የተነሳ ምዕመናን በጾምና በጸሎት (በሱባኤ) ያሳልፏታል፡፡ በተለይም በቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ሰማያት የሚከፈቱበት (ርኅዎተ ሰማይ) መሆኑን በማመን ምዕመናን ጸሎታቸውን ከምንግዜውም በበለጠ ያቀርባሉ፡፡ ወደ ወንዞች በመሄድም በሚዘንበው ዝናብ ይጠመቃሉ፡፡ ወርሃ ዿግሜን የጌታችን ምጽአት የሚታሰብበት በመሆኑ የሚዘመረው መዝሙር፣ የሚነበቡ ምንባባትና ቅዱስ ወንጌል እንደዚሁም የሚሰበከው ምስባክ ይህንኑ ምስጢር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በወርሃ ዿግሜን ከሚታሰቡና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ዿግሜን 3 ቀን የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በዓል የሚከበርባቸው ምክንያቶችም ሁለት ናቸው፣ እነርሱም አንደኛው በዓለ ሢመቱን ምክንያት በማድረግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤቱ ነው፡፡ ‹ሩፋኤል› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ‹ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን፣ የዋህ› ማለት ነው፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቆረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላዕክት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ ›› እንዲል (መጽሐፈ ጦቢት)
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዮሐንስ ተሽሮ ማቴዎስ ሊሾም ነው።
እንኳን አደረሳችሁ! የአማኑኤል ልጆች
🌼🌼🌼
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላም አደረሰን!! "

አዲሱ ዓመት ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የተሰጠን ሌላ አዲስ እድል ነው። አማኑኤል ከእኛ ጋር ለመሆን የእኛን ሥጋ ተዋሕዷል፣ አምላክነቱ ሳያሳስበው የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አድርጉዋል። በደሃ ቤት አድሯል ፣ በበረት ተወልዷል፣ ከብርድ መከለያ ጨርቅን ፈልጓል ፣ ፍጥረትን የሚመግብ እርሱ ከእናቱ የድንግልናዋን ወተት ለምኖ አልቅሷል ፣ እንደ ሕፃናት በጉልበቱ ድኋል፣ ለእናቱ እየታዘዛት ጥቂት በጥቂት አድጓል። ከአደገም በኋላ ራሱን የሚሰውርበት ጎጆ ሳይኖረው በተራራ ተንከራቷል ፣ ተርቧል ፣ ከኃጢአተኞች በደረሰበት ተቃውሞ ተሰድቧል ፣ ተገፍቷል። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ሆኗል።

ከእኛ ጋር ለመሆን ብቻ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ለመኖር በእለተ አርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ተሰጥቶናል። እኛስ ወደ እርሱ ሊያቀርበን ይህን ሁሉ ከሆነልን አምላክ ጋር ለመኖር ምን አደረግን? ንስሐ ገባን? ሥጋ ወደሙን ተቀበልን?

ከእግዲህስ በኃጢአት ያረጀ ማንነታችንን እንተው። አዲሱን ዓመት " ማለዳ ማለዳ አዲስ " ከሆነው ፈጣሪያችን ጋር ለመኖር ለራሳችን ብሩህ ተስፋ እንሰንቅ። እስኪ አምና ወድቀን ከተሰበርንበት የዘር ፣ የጥላቻ ጉድጓድ ወጥተን ዘንድሮን ተዋድደን ፣ ተፋቅረን በሰላም እንኑር። እስኪ ደግሞ ወደ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርበን ይህችን ዓመት በሰላም ጀምረን እንፈጽማት።

አዲሱ ዓመት የሰላምና  የፍቅር  እግዚአብሔርን  በቅንነት የምናገለግልበት ዓመት እንዲሆንልን እንመኛለን
••
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጨው የሞላብሽ አዲስ ማሰሮ
አለም ጣፈጠ ምሬት ተሽሮ
ተለውጠናል አዲስ ሆነናል
ድንግል ለክብርሽ እጅ ነስተናል
••
አክሊላችን ነሽ ውበታችን
ትምክህታችን ነሽ መፅናኛችን
ስምሽን ጠርተን ከሞት ድነናል
ምልጃሽ እረድቶን ቀና ብለናል
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በልዩ መንበሯ ሃገሯ ግሸን ማማሯ
💚💛❤️
እንኳን ለንጽሕተ ንጹሐን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊት ጎሎጎታ የመስቀሉ መገኛ ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
••
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ ማረፉን አስበን በዓሉን እናከብራለን። ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን አሜን!
••
የግሸኗ ማርያም በጦርነት ውስጥ ያሉትን መከራ የከበባቸውን ደጅሽ መርገጥ ያልቻሉትን ልጆችሽን አስቢያቸው አሜን! እኔን የሰማችኝ ወላዲተ አምላክ የእናንተንም ጸሎት፣ ልመናችሁን የልብ መሻታችሁን ሰምታ ለደጇ ታብቃችሁ አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
••
የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸውና አማላጅነታቸው አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
ወርኃ ጽጌ - ( ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 )
••
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን ( ዘመነ ጽጌን ) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልላክነት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ፡፡
••
በዚህ በወርኃ ጽጌ ( በዘመነ ጽጌ ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ ( የፈቃድ ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ ( ሉቃ. 7፡47 ) እንዲል፡፡
የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ " ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ " (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እረኛዬ መድኃኔዓለም
••
ጥቂት ስምህን ማወቅ ብዙ መረጋጋትን ታጎናጽፋለች ፤ በተሳዳቢ ዓለም ዝምታን አስተማርከኝ። እየተገፉ መደሰትን ፣ እያጡ ማመስገንን ፣ ነገን እያሳይህ ዛሬ ማኖርን ፣ ባንተ ማረፍን በስምህ ተማርኩ። መድኃኔዓለም እረኛዬ የምታሳጣኝ የለም ፣ ያጣሁትም የለም።
••
እረኛዬ ሆይ! ካላንተ አባትም እረኛም ጠባቂም የለኝም። አሁንም ስለ ስምህ ጠብቀኝ አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የድንግል ልጅ አማኑኤል ይጠብቀን አሜን
••
አማኑኤል ሆይ - በክንፍህ መዘርጋት ይህን ትውልድ አንተ ጋርድ። በዚህ ዓለም ሹሞች ሳይሆን ማመኔን በአንተ አድርግልኝ። ልቤን በአንተ አሳርፍልኝ!! ለተጨነቁ መጽናናትን ፣ ለተረበሹ ሰላምን ፣ ላጡት ማግኘትን ፣ ለታመሙት ምህረትን ይስጥልን አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ድንግል ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው‼️
••
እነሆ የብርሃናት ንጉስ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች፤
••
ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፣ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ተወለደች፤
••
የአለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፤
••
ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ ( የፀሐይ እናት ) ቅድስት ድንግል ተወለደች፤
••
ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው ፣ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው ፤ የመድኃኒአለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።
••
በእውነት እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት!
••
የእናታችን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ ፣ አማላጅነቷ፣ ጥበቃዋ ፣ በረከቷ ፣ ረድኤቷ ፣ ይደርብን
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለአባታችን አቡነ አረጋዊ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
•••
❤️ #አቡነ_አረጋዊ_ዘደብረ_ዳሞ
•••
በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው። በ5ኛው ክ/ዘ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ አቡነ አረጋዊ መጨረሻቸውን በደብረ ዳሞ፣ ትግራይ ቢያደርጉትም በወሎ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በደቡብ ታሪክ ውስጥ ግን አሉ፡፡ ደቡብ ጎንደር ውስጥ ጥንታዊው ገዳማቸውና የዝማሬ መዋሥዕት ማስመስከሪያው ዙር አባ አረጋዊ አለ፡፡
•••
ጣና ቂርቆስ፣ አዲስ አበባ አጠገብ የሚገኘው የረር፣ እንዲያውም ከዚያ ተሻግሮ ጋሞጎፋ የምትገኘው ብርብር ማርያም ታሪካቸውን ከእርሳቸው ጋር ያገናኛሉ፡፡ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ድንበር ጠባቂ ሆኖ ሞያሌ ላይም ይገኛል፡፡
•••
ደብረ ዳሞ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ ትግራይ በ535 ዓ.ም. የታነፀ ገዳም ነው፡፡ መጠርያ ስሙንም ያገኘው ከአምባው ሲሆን፣ ከባሕር ወለል 2216 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ ዳሞ ገዳም እስካሁን ህልውናው የተጠበቀ ከ1400 ዓመት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡
•••
ደብሩን ለማየት ማናቸውም ሰው ወደ ደብሩ ሲወጣ ርዝመቱ 16 ሜትር ከሆነው ገመድ ተንጠልጥሎ ከላይ ተስቦ ይወጣዋል፡፡ “የሊፍት” ፍልስፍና በደብሩ መነኮሳት የታቀደ ይመስላል፡፡ በገድል በቱሩፋት 99 ዓመት ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 14 እንደ ሄኖክ እንደ ኤልያስ እንደ ፍቁረ እግዚ ዮሐንስ ተሰውረዋል:: የአባታችን የአቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከት አይለየን !
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ #ኪዳነምህረት የምህረት እናት‼️
••
የሁሉንም እንባ አባሽ፣ የሃዘኔ ደራሽ፣ የጭንቅ አማላጄ፣ ሳዝን መፅናኛዬ፣ ስደክም ጉልበቴ፣ በቃልኪዳንሽ ጠብቂኝ አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
(ጥቅምት 17)
••
ዛሬ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ በዓል ነውሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከሰባት ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስትያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይገኝበታል
••
እስጢፋኖስ ማለት 'መደብ' ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ 'አክሊል' ማለት ነው።
••
ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ትውልዱ ከነገድ ብኒያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ ።
የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከት አይለየን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የምትጠብቀኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ‼️
••
ከዲያብሎስና ከዓለም ጋር በማደርገው ውጊያ ፈጥነህ ደርሰህ አድነኝ፤ አእምሮዬን አብራልኝ። ኃጢአትን እንድንቅ፣ በማንም ላይ እንዳልፈርድና ከክፉ ስራዎች ሁሉ እንዳልተባበር ጠብቀኝ። በችግሬ ግዜም ኃይልህና እርዳታህ አይለየኝ።
••
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል በምልጃው ከክፉ ሁሉ ነገር ይጠብቀን አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
2025/06/28 20:41:24
Back to Top
HTML Embed Code: