Telegram Web Link
አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
••
ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡
••
እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!
••
(ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ )
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን -  https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ የለም ቤቤታችን
ቀዳሚ ነው ስሙ አልፋ ኦሜጋችን
ሕጉን ጠልፈንበት መጋረጃችን ላይ
ንጉስ ነው በኛ ቤት በከፍታ የምታይ
••
እግዚአብሔር በኛ ቤት ሁልጊዜ ምስጉን ነው
የአማልክት አምላክ አምነን የመረጥነው
ስሙ በማለዳ በቀን ይቀደሳል
እርሱ ራሳችን ነው በለልት ይነግሳል
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን -  https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ #ድንቅ_አድርጎልኛል
••
ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ (2)
አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ (2)
••
ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር
ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ረክሼ ሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ
ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ
አዝ ••••
ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ
ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት
ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል እንዲ ለወደደኝ
አዝ ••••
ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ
ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል
ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ኪዳነምህረት እናቴ
•••
አንቺን ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው። ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ እናመሰግንሻለን። ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንቺን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ አሜን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቅዱስ ገብርኤል
❤️ እንኳን አደረሳችሁ

••
በህይወታችን መልካሙን ነገር ያብስረን ፣ የታመሙትን ይፈውስልን ፣ ያዘኑትን ያፅናናልን ፍቅርና አንድነትን ያብዛልን አሜን! የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል በምልጃው ከክፉ ሁሉ ነገር ይጠብቀን አሜን!
••
መልካም ዋዜማ
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
👉🏼 ሐምሌ 19ቀን 2016 ዓ.ም
••
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከንፍር ውኃ ያዳነበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ኃይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በድምቀት ተከብሯል፡፡
••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
ጠባቂዬ አባቴ ቸሩ መድኃኔዓለም

መድኃኔዓለም የህይወት እስትንፋሴ፣ ለመኖሬ ምክንያት ነህ፤ እንደ አባቶቻችን አበርታን እነሱ ከያዙት ጦር ይልቅ አንተ ትበልጣለህ፤ ህዝብህን ጠብቅ ለጠላቶቻችን አሳልፈህ አትስጠን።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ አማኑኤል ሆይ

በክንፍህ መዘርጋት ይህን ትውልድ አንተ ጋርድ። በዚህ ዓለም ሹሞች ሳይሆን ማመኔን በአንተ አድርግልኝ። ልቤን በአንተ አሳርፍልኝ!!
••
ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሳትፈን እግዚአብሔር አምላካችን አሜን!
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
••
የቅድስት ኤልሳቤጥና የካህኑ ዘካሪያስ ልጅ በማሕፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት በበረሐ ያደገ በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ እስራኤልን ለንሰሀ ያጠመቀ የጌታችንን መንገድ የጠረገ ጌታውን ያጠመቀና ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ቅዱስ ካህን ሐዋርያ ሰማዕት ወንጌላዊ ባህታዊ ነብይ ነው።
••
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ጌታን ባጠመቅክበት ክቡራን እጆችህ ነብስና ስጋችንን እንዲሁም የወጣትነት ዘመናችንን በእጥፍ ባርክልን ለሀገራችን ፍፁም ሠላምን ይስጥልን አሜን መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ ይኹንል
••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለተከበረችው የሱባኤ እና የጾም ወቅት በሰላም አደረሳችሁ!
••
የእመቤታችን ፍቅሯን በረከቷን ያብዛልን ፤ በፍቅር ተሰባስበን ተዋደን ፣ ተፋቅረን የምንጾመው ጾም ይሁንልን። አዛኚቷ ልደታ ማርያም ሆይ! ሱባኤያችን የቤተክርስቲያናችን ዕረፍት የኃጢአታችንን ስርየት ሱባኤ አደርጊልን አሜን!
••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 የውሸት ዜና ነው እያላችሁ አታሞኙን‼️
••
በኮሪደር ልማት ስም የአፍሪካ ህብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ሊፈርስ ነው ‼️
••
የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለሌላ ቤተ እምነት ሲሰጦ " ስንጮኽ " ነበር  ህግ ይከበር ርቀት ይጠበቅ እያልን አሁን ደግሞ ጭራሽ የቤተክርስቲያኒቱን ግቢ ሊያፈርሱ ኑው። ይህ ሕዝብን መናቅ ነው።
••
በአዲስ አበባ ጠባብ ግቢ ካላቸው አብያተክርስቲያናት አንዱ አፍሪካ ሕብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ነው።
••
ይህ እየታወቀ ያቺንው ያለቺውን በኮሪደር  ምክንያት ግቢው ሊፈርስ  ነው።ይሄ መረጃው የደረሳችሁ የሚመለከታችሁ አካላት መፍትሔ ይደረግበት። ግቢው ፈረሰ ማለት እንደ መንገድ ላይ ሱቅ ቤተ መቅደሱ ብቻ ነው የሚቀረው ።
••
#ፍትሕ_ለእናት_ቤተክርስቲያን
መልእክቱን ሼር በማድረግ ያጋሩ።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 በሱባዔ ጊዜ
••
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
••
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ « በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ » እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
••
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት ፣ መዝሙረ ዳዊት ፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት ፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
••
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና (2)
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና (2)

እመቤታች ጉድለታችንን ሁሉ ትሙላልን !
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን
••
ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
💚 ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
💛 የከፍታዬ መሰላል
❤️ መነሻዬ ሆነሀል
••
ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል /2/
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል /2/
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 #ፍትህ_ለሔቬን
••
በሙሉ ዓይናችን ለማየት በምንሳሳላቸው ፤ ጠንካራ ቃላት በሚያስደነግጣቸው ሕፃናት ላይ እንዲህ ያለውን ግፍ መፈጸም መንፈሳቸው የተራቆቱ ሰዎች ድርጊት ነው።
••
እንዲህ ያለ ለመስማት የሚዘገንን ተግባር ለፈጸመ ግለሰብ ማስተማሪያ የሆነ ቅጣት ይሰጠው ስንል እንደ አማኑኤል ፔጅ እንጠይቃለን።
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 #በዓለ ደብረ ታቦር
••
በዓለ ደብረ ታቦር ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ  በቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል።
••
እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)

ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤ የደመቀ የጎላ ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው፡፡ የችቦ ማብራት ቱፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ተራራው ከገሊላ ባህር በስተ ምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል፤ መሳ.4 ÷6-14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤ ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ሌሎች ኤልያስ ነው፤ ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ ነው ይላሉ ብለውት ነበር፤ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ’’ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስደስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦሥቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርሀን አሳየኝ ብሎት ነበር (ዘጸ. 33÷17-23) ጌታችን ግን በሕይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል ፡፡

ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለአለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል፡፡ ከዚያም ደመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው አርሱን ስሙት" ሲል መሰከረ፡፡ ማቴ 17÷ 2 ሉቃ 9÷29፡፡

እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት የትንሣኤ
በዓል በሠላም አደረሳችሁ
💚💛❤️
#ዕርገተ_ማርያም || ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር።
••
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።
••
የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ።
••
የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት።

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው።
••
ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ።
••
ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን። በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
••
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
••
ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።
••
በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
••
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ።
••
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና።
••
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbino
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
••
በችግር ውስጥ ስከበብ አለው የምትይኝ ፣ ችግሬን ጭንቀቴን የሚሰማ ባጣሁ ጊዜ የውስጤን የምነግርሽ ፣ ዕንባዬን የሚያብስ ፈልጌ ባጣሁ ጊዜ የልቤን ሁሉ የምነግርሽ የማዋይሽ ድንግል እናቴ ሆይ! ጓደኛ ስፈልግ ጓደኛዬ ፣ ዘመድ ስፈልግ ዘመዴ ሁሉ ነገሬ ሆነሽ በመከራዬ ሁሉ ፈጥነሽ የምትደርሺ ባዶ ሆኜ ሳለ ሙሉ የምታደርጊኝ ፣ ሃዘኔን አይተሽ የማትርቂኝ ፣ በጊዜ በሁኔታ የማትቀያየሪ ዘውትር የልቤ አማካሪ
••
የልቤን የማዋይሽ እናቴ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ዘወትር በየጊዜው በየሰዓቱ ማርያም ማርያም ስልሽ ልኖር እመኛለሁና የእኔን የደካማው ባሪያሽ መሻት አንቺን ማመስገን ነውና መሻቴን ፈጽሚልኝ አሜን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
2025/06/28 10:26:33
Back to Top
HTML Embed Code: