Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቅድስት ድንግል ማርያም
••
የማልከፋው ስላለኝ ሳይሆን አንቺ ስላለሽኝ ነው ፤ በዚህች ምድር የሚያጓጓ ምንም ነገር የለም። ድንግል ሆይ! የአንቺ እናትነት ግን ከሁሉም ይበልጣል ፤ የተወደድሽ እመቤቴ ሆይ! ሰላሜ በአንቺ ነውና ምልጃሽ አይለየኝ! የፈተና ማዕበል ከተነሳባችሁ ፣ ነፍሳችሁ ከተረበሸ ፣ የጭንቀት ዓለት ካጋጠማችሁ እናቴ ማርያም ነይለኝ በሏት! ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢን ምህረት እና ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ለምኚልን አሜን!
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ገብርኤል ማርያምን እንዲህ ብሎ አበሠራት
ለሰላሙ ፍጻሜ የለው በዳዊት መንግሥት
መንበር ላይም መንግሥቱ ስልጣኑ ትፀናለች፡፡

••
በዚህች ዕለት ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችን እና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና እንደምትወልድ ያበሠራት ዓመታዊ በዓል ነው። የጌታችን ቸርነት ፣ የእመቤታችን አማላጅነትና የመልአኩ ጠባቂነት አይለየን።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 የዛሬዋ ቀን የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው እንኳን አደረሳችሁ!
•••
❤️ ነቢይ ናቸው እንደ ነቢያት ትንቢት ተናግረዋልና አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግን መወለድ አስቀድመው አብስረዋል።
••
❤️ ሐዋርያቸው ናቸው ኢትዮጵያን ከዳር እስከዳር ዞረው ወንጌልን አስተምረዋል።
••
❤️ ሰማዕት ናቸው በድንጋይ እየተወገሩ፣ በብረት በትር እየተደበደቡ፣ በብረት አለንጋ እየተገረፉ፣ በገደል እየተጣሉ ጣዖትን አጥፍተው ወንጌልን አስተምረዋል ለጽድቅም አንድ እግራቸውን ተቆርጠዋል።
••
❤️ ባሕታዊ ናቸው ንጽሕናቸውን ጠብቀው ከዓለም ርቀው በአንድ ዋሻ ተወስነው በቅድስና አሸብርቀው የብሕትውናን ሥነ ሥርዓት ፈጽመዋልና። በረከታቸው ከኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይኹን አሜን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ‼️ መልካም በዓል‼️
••
Baga Guyyaa Ayyaana Dhaloota Iyyasuus Kiristoosin Ishin gahe‼️ AYYAANA GAARII‼️
••
እንኳዕ ንባዓል ልደተ ክርስቶስ ብሰላም ኣብፀሐኩም‼️ ርሑስ በዓል ልደት‼️
••
“ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ”
ሉቃስ 2፥11
🔔 መልካም በአል 🔔
••••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ❤️

"… ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።

"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።

"…በዓለ ጌናን ስናከብር በሀዘን በመከራ ፣ በጭንቅ ፣ በረሃብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት ፣ በወኅኒ ቤት ፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ ፣ በየጎዳናው ፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን ፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ ፣ በመንከባከብ ፣ በመጠየቅ ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሃገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን ፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።

"እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 የአእላፋት ዝማሬ በድሬዳው
👉 28-4-2017ዓ.ም
👉 በጥቂቱ ይህንን ይመስል ነበር
•••
" በድጋሚ … እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Video
ጥር 4 - ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
••
ቅዱስ ዮሐንስ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት መካልከ አንዱ ነው በመጀመሪያ ለደቀ መዝሙርነት የተመረጠው ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ እንድርያስ ጋር  ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ስሞች አሉት ፦
••
👉 ጌታ ይወደው የነበረ ሐዋርያ ( ፍቁረ እግዚእ )
💚 ወልደ ዘብዴዎስ
💛 ወልደ ነጎድጓድ
💛 ነባቤ መለኮት ( ታኦሎጎስ )
❤️ አቡቀለምሲስ
❤️ ቁጹረ ገጽ እየተባለ ይጠራል

••
ቅዱስ ዮሐንስ ጌታን በመከራው ሰዓት ሳይሸሽ እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ የተከተለ ፣ እኛን ወክሎ የእመቤታችንን እናትነት አደራ የተቀበለ ፣ የዕለተ ዓርቡን የጌታን መከራ እያሰበ ቀሪ ዘመኑን በዕንባ የኖረ ሐዋርያ ነው ።
••
ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እየጠበቀ ለ16 ዓመታት ተቀምጧል ከኢየሩሳሌም ርቆ ያልሄደው እርሷን የመጠበቅ አደራ ስለነበረበት ነው ፤ በ49 ዓ.ም እመቤታችን አርፉ እንደ ልጇ በሦስተኛው ቀን ተነስታ ካረገች በኃላ ወደ ኤፌሶን ከተማ ገብቶ አስተምሯል በዚያም በአርጤምስ ቤተ መቅደስ የሚካሄደውን አምልኮ ጣኦት በመቃወሙ በጭካኔው በሚታወቀው በንጉሥ ድምጥያኖስ ዘመን ( ከ81 - 96 ዓ.ም ) በጣኦት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ በድምጥያኖስ ፊት ቀረበ እርሱም በፈላ ውኃ በተሞላ በርሜል ውስጥ ካሰቃየው በኃላ ወደ ፍጥሞ ደሴት አጋዘው።
••
ቅዱስ ዮሐንስም በጠባብ ዋሻ ውስጥ ለሰባት ዓመታት ( ከ88 - 96 ዓ.ም ) ያህል በግዞት ተቀምጦ ሳለ ነው ራእዩን ያየውና የጻፈው።
••
በ96 ዓ.ም ድምጥያኖስ ሲገደል ቅዱስ ዮሐንስ ከግዞት ተመልሶ ነው ሦስቱን መልእክታቱንና ወንጌሉን የጻፈው።
••
ከሐዋርያት ሁሉ ቀድሞ ሰማዕት የሆነው ታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ያዕቆብ ሲሆን ከሐዋርያት ሁሉ ረዥም እድሜ ( 99 ዓመት ) በምድር ላይ የቆየው ሐዋርያ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ ነው።
••
በመጨረሻም ጌታ በገባለት ቃልኪዳን መሠረት ዮሐ 21 : 22 እንደ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያይ ተሰውሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተወስዷል።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አባታችን ጻዲቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የአቡዬ ረድኤት፣ በረከትና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 ጾመ ገሀድ
👉 እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ አደረሰን

ጾመ ገሀድ ( ጾመ ጋድ ) ዛሬ ማለትም ቅዳሜ ጥር ፲ የጥምቀት ዋዜማ የከተራ ቀን ጾመ ገሃድ ( ጋድ ) ነው እናም ከጥሉላት ( ከፍስክ ) ምግቦች ጾመን እንዋል።
••
እለቱ ቀዳሚት ሰንበት ( ቅዳሜ ) ስለሆነ በባዶ ሆድ ጾሞ መዋል አይቻልም ነገር ግን ከፍስክ ምግቦች ተቆጥበው ይውሉ ዘንድ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን ።
••
በቅዳሜ ቀን ግን መጾም አይገባም ፤ በቅዳሜ ቀን ፀሐይ እስኪገባ መጾም የሚገባ ስራ አይደለም ፤ የሚገባ ጊዜ አለ እንጂ ፤ እስከ ስድስት ያም ባይሆን እስከ ሰባት ። ( ሐይማኖተ አበው ምዕራፍ ፳፩ )
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 ከተራ ምንድን ነው?
•••
ከተራ ' ከበበ ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር ፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
••
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ ( ይገድባሉ ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ ( ለጥር 11 ) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የልቤ ብዬ የምጠራው
ሚካኤል ለእኔ አባቴነው

••••
የዛሬ 88 ዓመት - በዛሬዋ ቀን የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ፋሽስት ኢጣልያ የከፋውን የበቀል እጇን በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ነዋሪዎች ላይ አነሣች፡፡ በሦስት ቀን ውስጥ ብቻም ወደ 30 ሺኽ ኢትዮጵያውያን አለቁ። ይኽ ክስተት ዘንድሮ 86ኛ ዓመቱን ይዟል።
••
አባቶች ሲናገሩ የ1929 ዓመተ ምሕረቱን የካቲት ወር የሚያኽል ለሀገራችን ለኢትዮጵያ የመከራና የጽልመት ወር ኖሮ አያውቅም። በጣም የሚገርመው በዚኹ በወርኃ የካቲት 1888 ዓመተ ምሕረትም ከሰባ ሺኽ በላይ ወገኖቻችንን መሥዋዕትነትን ከፍለዋል።
••
የግፈኛው ኡምቤርቶ ጦር በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ሃይማኖት ሊቀለብስ - መሬት ሊቆርስ - ነፃነታችንን ሊገስ መጥቶ ማጭድና ጎራዴ - ጦርና ጋሻ የያዙትን በመድፍና በዘመኑ መሣሪያዎች ፈጃቸው።
••
ከአርባ አንድ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ለወረራ የመጣው በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራው የፋሺስት ጦር ፣ ከየካቲት 12 ቀን እስከ የካቲት 14 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ከሠላሳ ሺኽ በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን ገደላቸው።
••
ዛሬ እነርሱን እንዘክራለን! ሃይማኖትን እና ሃገርን አጽንተው አሻግረውልናልና - ለዛሬው ነጻነታችን ከፍለውልናልና!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 ዘወረደ
👉 የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
••
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
••
👉 ሕርቃል ማን ነው?
👉 ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
••
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺህ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺህ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገ*ደ*ለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡
•••
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡
••
በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
•••
« #ዘወረደ » ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም « የወረደ » ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡
••
ሳምንቱ #ሙሴኒ ይባላል። ይህ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡
••••
መልካም ፆም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንደቸርነትህ
••
እንደቸርነትህ አቤቱ ማረን//2//
እንደምረትህም ይቅርታን ስጠኝ//2//
ከኃጢአቴም አንፃኝ ከክፉ በደሌ//2//
ከዚያች ክፉኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ//2//

አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እንደክፋታችን
እንደበደላችን ሳይሆን እንደቸርነትህ ማረን ይቅር በለን
••
አሜን አሜን አሜን!!
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 የምትጠብቀኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ‼️
••
ከዲያብሎስና ከዓለም ጋር በማደርገው ውጊያ ፈጥነህ ደርሰህ አድነኝ ፤ አእምሮዬን አብራልኝ። ኃጢአትን እንድንቅ ፣ በማንም ላይ እንዳልፈርድና ከክፉ ስራዎች ሁሉ እንዳልተባበር ጠብቀኝ። በችግሬ ግዜም ኃይልህና እርዳታህ አይለየኝ።
••
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል በምልጃው ከክፉ ሁሉ ነገር ይጠብቀን አሜን!
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ጾም - ቅድስት
•••
የአብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል። በዚህ ሳምንት ስለ እግዚአብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቿን ታስተምራለች።
••
እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ የተቀደሰ ነገር ያስፈልገዋልና ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግስቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ በማለት ስለማስተማሩ ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል።
••
እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰን እና ልጅነት እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል።
••
መልካም ጾም
••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ሃያ ሦስት በዚህች ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን ዓድዋ ላይ የረዳበት ነው።
••••
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለእኛም የሰማዕታት ጽናታቸውን አድሎ ከበረከታቸው ይክፈለን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማረኝ /3/ መመኪያዬ
አርጅቻለሁ እኔስ በኃጢያት ጎስቁዬ/2/
••
ከፊቴ ናትና ኃጢያቴ ሁል ጊዜ
ተዉጫለሁ እኔስ በሐዘን በትካዜ
በፊትህ ክፋትን አድርጌያለሁ እኔ
ምንም ጽድቅ አልሰራሁ በሕይወት ዘመኔ
#አዝ
ከፊትህ መቅበዝበዝ መሰደድ ፈለኩኝ
ኃጢያት ከኋላዬ እያሳደደችኝ
ወዴት እሄዳለሁ መሸሸጊያም የለኝ
ምህረትህ መጠጊያ ዋሻ ካልሆነችኝ
#አዝ
የተሰባበረዉ አጥንቴ እንዲጠገን
በምህረት እና በቸርነት ዳሰኝ
የቀና መንፈስን አድስ በልቤ ዉስጥ
ነፍሴ በእልልታ በተስፋ ትለወጥ
#አዝ
ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትዉሰድ
በንስሐ ድኜ በተስፋ እንድራመድ
አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ እና
በደስታ ልስገድ በፍቅርህ ልፅናና
••
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መድሃኒአለም
•••
ብታመም መድኃኒቴ ብደክም ብርታቴ ፣ ብፈተን ጽናቴ ፣ ብወድቅ ጉልበቴ ፣ ቢጨልም መብራቴ ፣ ብሞትም ህይወቴ ፣ ብቸገር እረዳቴ ፤ የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ መድኃኔዓለም አንተ ነህ አባቴ ፣ ሀገሬን አስባት የይቅርታ ፊትሕን አዙርልን የምህረት በሮችህን ክፈትልን በድለንሀልና የሆነብንን ሁሉ አስብ አቤቱ አምላካችን መድሃኒአለም የአለም ሁሉ መድሃኒት ከአንተ ዘንድ ያለውን እውነተኛ ሠላም ላክልን ‼️
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
2025/06/27 16:33:11
Back to Top
HTML Embed Code: