Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እመብርሃን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም
••
እለት እለት አፌን ሞልቼ የጌታዬን እናት እመቤቴን ሳመሰግናት ልቤ ደስ ይሰኛል ፤ በእሷ የተጎበኘ የተደረገለት ደግሞ ክብሯን የበለጠ ከፍ ያደርጋል። ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር አሜን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤል
••
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።
••
ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ ፥ ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው። ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው ፥ ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው።(ዕዝ፲፫፥፴፱)
••
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
••
ኃያሉ ሰማዕት ሆይ እኔን ምስኪኑን አገልጋይህን ከሃይማኖት መራቆት ከምግባር እጦት ታድነኝ ዘንድ እማልድሃለሁ ••• ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሽ በመከራ ጊዜ ፈጥኖ ይድረስልን አጥንታችንን ለመፍጨት ደማችንን ለማፍሰስ የተነሱትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያፍዝዝልን ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛችን ጠብቅልን ቅድስት ሃገራችንን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን የመድኃኔዓለም የስቅለት በዓል በደማቁ ይከበራል። እንኳን ለፈጣሪያችን መድኃኔዓለም እየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
••
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም እውነት ነው ፤ እራስን ነፍስን አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ? መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለሁላችን ድኀነት ሲል ራሱን ወዶና ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። ቸሩ መድኃኔዓለም በምህረቱ ይጎብኘን ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን አሜን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለአምላክ ወሰብእ ለቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ በዓል አደረሰን።
••
ጥቅምት 28 || " የምስራቁ ነፋስ አንበጣዎችን አመጣ። " ዘጸአት 10፤13
••
የበዓሉ መሰረትና ታሪክ ይህ ነው በወርሐ ጥቅምት እንዲህ ሆነ በሱዳን በኩል የመጣ አንበጣ የኢትዮጵያን ምድር ከል መስሎ ወረሳት የተዘራው ሳይሰበሰብ  የአንበጣ እራት ሊሆን ሆነ። ንጉሠ ሸዋ ሣህለ ሥላሴ
ወደ ታላቁና ተአምረኛው ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል  ደብር ሄደው እንባቸውን በእጃቸው አቁተው አዝነው  ቅዱስ አማኑኤል ፈጣሪዬ አምላኬ ሆይ የመጣው የአንበጣ መንጋ ከጠፋ ሕዝቤ ከሰቀቀን ድኖ የዘራውን አጭዶ ከጎተራ ከገባ በአዋጅ ነጋሪት ጎስሜ ቀንደ መለከት አስነፍቼ ድብ አንበሳ ነጋሪት አስመትቼ ታቦትህን በካህናቱ አስወጥቼ አከብራለሁ ብለው ስዕለት ያደርጋሉ የአንበጣው መንጋ ሰማይ ያርግ ምድር ይስረግ ሳይታወቅ አንድ ሰብል ሳያጠፋ ከኢትዮጵያ ምድር ይጠፋል በዓሉም በዚያ ምክንያት ተጀመረ የአባቶቻችን ስም ላለመጥራት ታሪክ አናድበስብስ መሰረቱ ይህ ነው።
••
በበዓሉ የሚከብረው ስሙ የሚወደሰውም  ወሰብእ ቅዱስ አማኑኤል ነው ቸርነቱ የተገለጠበት ተአምራቱ የታየባት እምርት እለት። በአባቶቻችን መዲና አዲስአበባ መርካቶ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ደብር ሁላችንም ተገኝተን እናክብር።
••
አምላካችን በቸርነቱ ይመልከተን ምድራችንን የወረረውን የዘረኝነት አንበጣ ያጥፋልን በየልቦናችን ያቆምነውን የዘረኝነት ጣኦት በኃይለ መለኮቱ ያቅልጥልን አስተዋይ ለሕዝብ የሚያስብ መሪ አይንሳን እኛንም ገባርያነ ሰላም ያድርገን ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከክሕደት አሽክላ ይሰውረን በፈቃዳቸው ላበዱ ፈውስን ብረት ላነሱ ትዕግስቱን ያድልልን አሜን አሜን አሜን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እንወድሻለን‼️
••
ሰላም ለኪ አምላክን የወደለድሽ በስጋም በነፍስም ድንግል የሆንሽ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢልን ምህረትና ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ለምኚልን
••
ልደታ ማርያም  በዕለተ ቀኗ ጨለማውን ብርሃን ሃዘናችንን በደስታ ትቀይርልን አሜን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለበዓለ ደብረ ቁስቋም በሰላም አደረሰን /አደረሳችሁ
💚💛❤️
እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ጋር ከስደት ወደ ሀገሯ
የተመለሰችበት ቀን ነው
••••••••
ህዳር 6 በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ፤ ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር
••
እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት ፤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል ፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡ በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን ፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡
••
እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።
••
ቁስቋም ማርያም - እናቴ ማርያም ምልጃሽና ምህረትሽ አይለየን አሜን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና
አደረሳችሁ አደረሰን ‼️
💚💛❤️
ወበዓለ መራኄ ፍኖቱ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
•••••••••
ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡
•••
በዓለ ሢመቱ ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም ( ሳጥናኤል/ሰማልያል/ ) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል ፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም ( 99ኙም ) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡
•••
ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 ( የአእላፍ መላእክት ) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡
•••
ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 ( የአእላፍ መላእክት ) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡
•••
እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡  እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው ፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡
•••
የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች ፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ  አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች ፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች ፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡
•••
የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡
•••
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 ( ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡   ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡ ››
•••
ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን ( የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን ) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/
•••
ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡
•••
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡
•••
ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር ፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን ፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን ፤ አሜን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
" እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ "
••
ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው። ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤
••
፩. ጾመ አዳም:- አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡
••
፪. ጾመ ነቢያት:- ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::
••
፫. ጾመ ሐዋርያት:- ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡
••
፬. ጾመ ማርያም:- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡
••
፭. ጾመ ፊልጶስ:- ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡
••
፮. ጾመ ስብከት:- የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡
••
፯. ጾመ ልደት:- የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡
••
ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
••
በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።
••
በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ማዕተብ በኩል 70 ወጣቶች ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በልጅነት ጥምቀትና በቄደር ጥምቀት ተመለሱ:: ጃን ማዕተብ ሥራ ከጀመረ ጊዜ አንሥቶ በአንድ ለአንድ (የገፅ ለገፅ) የትምህርት መንገድ የተማሩት እነዚህ ንዑሰ ክርስቲያን ከእስልምና ከፕሮቴስታንት ከካቶሊክ እና እምነት የለሽነት የተመለሱ መሆናቸውን የጃን ማዕተብ የንዑሰ ክርስቲያን ክትትል አስተባባሪ ዶ/ር ቤተልሔም ገልጻለች::
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጠፋው በግ ተገኝቷል እና እንኳን ደስ አላችሁ
••
#ዘማሪ_ሐዋዝ_ተገኝ ስንጠብቅህ የነበረ ወንድማችን ወደ ቤትክ እንኳን ደህና መጣህ የእናት እጅ ልጆቿን ለማቀፍ ትናፍቃለች
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቅዱስ ገብርኤል አባቴ
••
ቅዱስ ገብርኤል አባቴ ከአምላካችን ከእየሱስ ክርስቶስ ምህረትና ቸርነትን ለምንልን አማልደል ፤ የራማው መላአክ ገብርኤል ከመጣብን ክፉ መቅሰፍት በምልጃህ ጠብቀን ይቅርታውን ምህረቱን ይልክልን ዘንድ ለምንልን አሜን! 🙏🏿
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ህዳር 21 አክሱም ጽዮን ማርያም
❤️ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ

••
ህዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦
••
👉🏼 ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤
••
👉🏼 የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤
••
ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ለማሰብ፤
••
👉🏼 በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤
••
👉🏼 አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን። ከእመቤታችን ረድኤትና በረከት ይክፈለን!!!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ አማኑኤል ሆይ
••
በክንፍህ መዘርጋት ይህን ትውልድ አንተ ጋርድ። በዚህ ዓለም ሹሞች ሳይሆን ማመኔን በአንተ አድርግልኝ። ልቤን በአንተ አሳርፍልኝ! ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሳትፈን እግዚአብሔር አምላካችን አሜን!
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ቅዱስ ሚካኤል
•••
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘውትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኛንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልን።
•••
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ምልጃው ጥበቃና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን‼️
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ኪዳነ ምህረት
••
ርግብየ ርግብየ እያለ የሚያመሰግንሽ የጥበበኛው ሰሎሞን ርግብ ነሽና ድንቁርና ረኃብ እንዳይጸናብኝ እህል ጥበብን መግቢኝ። እመቤቴ ሆይ ፤ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው።
••
ስለዚህ ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡ መልክአ ኤዶም Rየኪዳነምህረት ምልጃ አይለየን🙏
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Video
❤️ ታኅሣሥ 19
❤️
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
•••
ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡
••
ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
••
‹‹ ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡
••
በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡
••
የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡
••
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡
••
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም መልአኩ በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
2025/06/27 10:42:56
Back to Top
HTML Embed Code: