Telegram Web Link
የጌታዬ እናት ድንግል ማርያም እጄን ይዛ ነው ከመከራዬ ያወጣችን ... ከዘፋኝነት ያወጣችን እርሷ ናት ‼️
••
የቀድሞ ሙዚቀኛ አሌክስ ኦሎምፕያ
በሰይፉ ሾው ላይ ከተናገረው የተወሰደ
••
ወዳጄ የድንግል ማርያምን አማላጅነት ከቀመሰ ሰው በላይ ምልጃዋን ማን ይመሰክራል። እንደተባለው ያወቀውን መስክሯል ፣ ያየውን ተናግሯል።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይቀላቀሉ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይቀላቀሉ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ዮሐ 3፥11"
እንደተባለው ያወቀውን መስክሯል ፣ ያየውን ተናግሯል
••••
የጌታዬ እናት ድንግል ማርያም እጄን ይዛ ነው ከዘፋኝነት ያወጣችን እርሷ ናት
« በእመቤቴ በቅድስት ድንግል ማርያም አማካኝነት ድኜ አሁን ለምስክርነት መጥቻለሁ ፣ ያለፈው የፈተና ጊዜ ከባድ ነበር ፣ እመቤቴ ከአንድ ሁለት ጊዜ መጥታ አድናኛለች ፣ አንድ ጊዜ ቤት መጥታ ኦፕራሲዮን አድርጋ አድናኛለች ፣ ኪዳነምህርትም አብርታ ቤቴ መጥታ ዳብሳ አይዞ ልጄ አሁን ድነሃል ብላኝ ሄደች ፣ አዲስ አልበም ሰርቼ ጨርሼ ነበር ከአርቱ ወጣለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ፣ እኔ የፅድቅ ስራ አልሰራውም እግዚዓብሔር ቸር ስለሆነ በእናቱ ሊያድነኝ ስለፈለገ እሱ የፈቀደው አደረገ ከሙዚቃው ስራ ሙሉ በሙሉ ወጣው »
•••
የቀድሞ ድምፃዊ አሌክስ ኦሎምፒያ ••• ክብርና ምስጋና ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ እናት ለድንግል ማርያም ይሁን መጨረሻህን ያሳምርልህ አሌክስ ኦሎንፒያ
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቅዱስ ቂርቆስ ❤️
••
ቅዱስ ቂርቆስ ሆይ በሚንቀለቀል እሳት ፊት ቆመህ የራማውን ልዑል ቅዱስ ገብርኤልን ለማረከ አንደበትህ ሰላም እላለሁ። እናትህን ቅድስት ኢየሉጣን ለሰማዕትነት እንድትጨቅን ልቧን ላበረታ አንደበትህ ሰላም እላለው። ቅዱስ ቂርቆስን እና ቅድስት ኢየሉጣን የታደከው ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ማኅተመ ባሕርዩ ቃልህ ለሚሆን አንደበትህ ሰላም እላለሁ። የባቢሎንን የእሳት ግለት ወደ ቀዝቃዛነት የለወጠ ለእስትንፋስህ ጠልም ሰላም እላለው። ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ጻድቃኖችን ሁሉ ለመራዳት የታመንክ ነህና አስቀድሞ ህጻኑን ቂርቆስን እና እናቱን እየሉጣን እንዳዳንካቸው እኔንም የመከራው ቁስል እንዳይጠዘጥዘኝ ፣ እንዳይነዘንዘኝ ከእሳት ነበልባል አድነኝ። አሜን በእውነት ይሁን።
••
የቅዱስ ገብርኤል ፣ የቅዱስ ቂርቆስ እና
የቅድስት ኢየሉጣን በረከት ይደርብን።

•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
በቅርብ ነው ወደ ኦርቶዶክስ ቤት የመጣውት። ዳግም እንዳልጠፋ እና እንዳልባክን ሽምግልናዬን ሳታዩ እንደ ህፃን ልጅ በጸሎታችሁ ታስቡኝ ዘንድ ተንበርክኬ እማጸናችዋለው •• አርቲስት ሰለሞን ተካ
••
በይርጋጨፌ ከተማ በተደረገው መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የተገኘው አርቲስት ሰለሞን ተካ በቅርብ ወደ ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ልጅ ሆኖ እንደመጣ ይፋ ያደረገ ሲሆን ማህበረ ምዕመናንን በጸሎታቸው እንዲያስቡ በአውደምህረቱ ተንበርክከው ተማጽነዋል።
••
👉 #በቤቱ_ያጽናዎት - በአረጋዊ ዘመንዎ የመረጦት አምላክ ይመስገን‼️
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኪዳነምህረት እናቴ ❤️
••
ኪዳነ ምህረት እናቴ
ፈጥነሽ ደራሽ ነሽ በሐዘኔ (፪)
የከበበኝ ጭንቀት ተወግዷል
ፍቅርሽ እመ አምላክ እኔን ማርኳል (፪)
የችግሬ ደራሽ የጭንቀቴ
ነይ እናቴ ነይ እናቴ
እናቴ ባንቺ ሰው ሆኛለው
ከሞት አፋፍ ላይ ተርፌያለው
ስምሽን ስጠራ ቀን ሌሊት
ትሆኚኛለሽ መድኃኒት
••
አንቺን ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው። ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ እናመሰግንሻለን። ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንቺን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ ••• ከእግዚአብሔር ዘንድ ድኀነትንና ሕይወትን ፤ ፀጋና በረከት ፣ ክብርን እያማለደች የምታሰጥ ፣ የእኛነታችን መመኪያ የህይወታችን ቋንቋ ኪዳነምህረት ከሁላችን ጋር ትሁን ባለንበት ሁሉ አትለየን ምልጃዋ ልመናዋ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሐዋርያት ሹም የወንጌል ገበሬ
የዘራኸው ትምህርት ደረሰ ለፍሬ
ሊቀ ዲያቆናት የሐይማኖት ዐምድ
ድል አድርገኸዋል የዓለምን ፈቃድ
•••
አይሁድ አማጽያን ሊሞግቱት በሸንጎ ተሰበሰቡ መጽሐፍ እንደመሰከረው እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር ፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም ይላል ፤ “ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ ” ብሎ በግልጽ ዘለፋቸው ስለ ጌታችን መሰከረ በዚህም ተቆጡ ድንጋይ ጨበጡ በግፍ ገደሉት ይቅር በላቸው እያለ ነፍሱን ሰጠ ••• ከቀዳሜ ሰማዕት ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋና በረከት ያድለን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይቀላቀሉ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይቀላቀሉ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ‼️
••
👉 አዲስ የምስጋና ዝማሬ 👈
❤️
ገብርኤል መጥቷል ❤️
••
አዲስ ቅኔም ተቀኙለት ፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ ••• መዝ 33 : 3
https://youtu.be/ABPimOD3UmM
••
እቶኑ በእጥፍ ቢነድብንም
ለጣዓት ከቶ አንሰግድም
መልአኩን ልኳል እግዚአብሔር
በፍርሃት ላንጎድል ስንመክር
የአማልክት ሌጁን መስሎ ይታየው
አራተኛው እርሱ ገብርኤል ነው
https://youtu.be/ABPimOD3UmM
በሚፈሩት ዙሪያ የሚሰፍረው
ሰውን ለመርዳት የሚላከው
ገብርኤል መጥቷል ሊያረጋጋን
እንዳንፈራ ሊያጸናን
https://youtu.be/ABPimOD3UmM
ዛሬ የተለቀቀውን የወንድማችን ዲ/ን ኢንጅነር ካሳሁን ወልዴ #ገብርኤል_መጥቷል አዲሱን መዝሙር በLink ገብተው ያገኙታል።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በአል
በሰላም በጤና አደረሳችሁ

💚💛❤️
የቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በርከት አያለየን
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሔር ሥራው ግሩም
እሳቱን በእሳት ያጠፋል

••
ሐመልማሉን ሳያቃጥል እሳት ያነድዳል በእሳት መኻል በማኅሌት ዜማ ይመሰገናል። ከሰማይ እሳት ያወርዳል። በእሳት ሠረገላ ይነጥቃል። በእሳት መጋረጃ ይጋርዳል። በእሳት መንበር ይቀመጣል። እሳታዊ መልአክ ይልካል። ለእኛም እሳቱን በእሳት ያጥፋልን።
••
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
በዓል አደረሳችሁ

••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ድንግል_ሆይ ❤️
••
ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም ፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤
••
ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤
••
ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም ፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ፤
••
ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ።
••
ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኦርቶዶክሳዊያንን መተሀራ ላይ
በጥይት ደብድበው በእሳት አቃጠሏቸው

••
ከቁሉቢ የቅዱስ ገብር ኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል አክብረው አንግሰው በሚመለሱ መነሻቸው አዲስ አበባ አቃቂ ቅሊቲ የሆኑ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ታጣቂዎች መተሃራ ላይ በከፈቱት ጥቃት ኦርቶዶክሳዊያን በጥይት ተደብድበውና ተገድለው አስክሬናቸው እንዲቃጠል ተደርገዋል። ከእነርሱም ጋር አብረው የተጓዙ 13 ኦርቶዶክሳውያን ታግተው እስከ አሁን የት እንዳሉ አይታወቁም።
••
👉🏼 ይህን በጭካኔ የተሞላ አረመኔነት
እስከ መቼ ነው ዝም የምትለው⁉️

👉🏼 ዝምታው እስከመቼ ⁉️
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
የቀድሞ ዘማሪት ጽጌሬዳ ጥላሁን ከተ*ድሶ መናፍቅነት ተመለሰች‼️
••
በስምህ ታምኛለው እንዳትተወኝ
ለሚያሳድደኝ ጠላት ለሞት አትስጠኝ
•••
በሚለው ዝማሬዋ የምትታወቀው ዘማሪት ጽጌሬዳ ጥላሁን ••• ተወስዳ ከነበረችው የተ*ድሶ መናፍቅነት እንቅስቃሴ ወደ ቀደመው ርትዕት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መመለሷ ታውቋል።
•••
👉 ቤዛ ኩሉ የሁሉ ቤዛ ፣
👉 በወርቅ ቀለም ተጽፈሻል ፣
👉 ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ ፣ የሚሉ የነገረ ቅዱሳን ዝማሬዎችን  ያበረከተችው እና ••• አምናለው ብዙ ነው ኃጢያቴ በደሌ በሚለው የንሰኃ መዝሙር የምትታወቀው እህታችን ዳግም ህያው ሆና ወደ ቀደመው በረቷ ገብታለች።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
#ተክልዬ_አባቴ ❤️
••
የዛሬዋ ቀን የአባታችን የጻድቁ  አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው እንኳን አደረሳችሁ!
••
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ  ጸጋ ዘአብ  ካህኑና  እግዚእ ኃረያ  ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
••
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  #‎ቅዱስ_ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ ( ከአረማዊ ጋብቻ ) አድኗቸዋል። በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::
••
አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።
••
የአባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ፀሎትና ልመና  ይጠብቅልን!
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲቃጠል ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አረሳት ኢትዮጵያን በዕርፈ መስቀል
••
አረሳት ኢትዮጵያን በዕርፈ መስቀል
አባ ተክለሐይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው-ነው ተወዳጅ በሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ (2)
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ልደት ❤️
••
 " ብዙ ልደቶች በሰዎች ልጆች ሁሉ ትከብሯል። የኢየሱስ ግን ይለያል፤ ማንም ቢወለድ አልጋ ወራሽ ሆኖ ይወለዳል እንጂ ንጉስ ሆኖ አይወለድም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ንጉስ ሆኖ ተወልዷል። "
•••
ማንኛችንም ስንወለድ ቤተሰብ ተስፋ አርጎ የራሳችንን ህይወት እንድንመራ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለኛ ሊሞት ተወልዷል።
•••
ዛሬ ፅንሱ ከመወለዱ በፊት ፆታው ይታወቃል። ቀድመውም ልጁ ሳይወለድ የሚያስፈልገው አልጋ ፣ መመገቢያ ፣ ልብስ ይዘጋጅለታል። ጌታ በተወለደ ጊዜ ፆታን ቀድሞ የሚለይ ቴክኖሎጂ ባይኖርም ዘመን የማያልፍባቸው ከቴክኖሎጂ ከላይ የሆኑ መላዕክት ፆታውን ቀድመው አሳውቀዋል ግን ከድሀ ቤተሰብ ተወልዷልና ልብስና አልጋን አላዘጋጁለትም። ምድርን በአበባ አስጊጦ ሰማይን በሚያምሩ ከዋክብት አንቆጥቁጦ እርሱ ግን በጨርቅ ተጠቀለለ።
•••
በረት የእረኛ መዋያ የተናቀ ትኩረት የማይሰጠው ቦታ እንጂ ዝና ክብር አለን የሚሉ ሰዎች የሚውሉበት አይደለም። የመንግስት ባለስልጣን አንድ ግብዣ ላይ ሲጋበዝ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ወይ? ለክብሬ ይመጥናል ወይ? ይላል። ክርስቶስ ንጉስ ነው ግን ለደህንነቴ አያሰጋም ወይ? ለክብሬ ይመጥናል ወይ? ብሎ ሳይሰጋ በበረት ተወለደ።
•••
በዘመናችን ሁሉ ጋንዲ የተወለደ እንጂ በረት ተወለደ ተብሎ ሲተረክ አልሰማንም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እውነተኛ በግ ሆኖ በበረት ተወለደ። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ወር ያልሞላው አራስ ህፃን ሆኖ ስግደት ተቀበለ።  የጌታ ልደት የህፃን ልደት ሳይሆን የበረከት ፣ የደስታ ፣ የሰላም ፣ የእረፍት ልደት ነው።
•••
ይህ ጌታ ዛሬ በቤታችሁ በደስታ ይወለድ ፣ በጤና ይወለድ ፣ በስኬት ይወለድ ፣ በመከናወን ይወለድ ፣ በሰላም ይወለድ ፣ በለውጥ ይወለድላችሁ። አሜን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ❤️
••
"… ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።
••
"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
••
"…በዓለ ጌናን ስናከብር በሀዘን በመከራ ፣ በጭንቅ ፣ በረሃብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት ፣ በወኅኒ ቤት ፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ ፣ በየጎዳናው ፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን ፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ ፣ በመንከባከብ ፣ በመጠየቅ ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሃገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን ፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።
••
"…እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን
••
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
" የጌታ ልደት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "
••
ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡
••
መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡
••
እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት ፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡
2025/06/30 20:11:30
Back to Top
HTML Embed Code: