Telegram Web Link
❤️ ተመልከት ንዝረት የሆነ ፎቶ ❤️
💚💛❤️
ኦርቶዶክስ በመሆን አትኳራም ወይ⁉️
ኦርቶዶክሳዊ ውበት!!!

ወዳጅን በፍቅር ጠላትን በማስፈራት ያስደነግጣል። አንድ በር ሲዘጉ ሺህ በር ወደሚከፍተው እግዚአብሔር ዞር በል።

@terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማህፀንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አገኘነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡት ጋር ብፅሂት ብለና
••
ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር /2/
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር /2/

•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከአባቶቻችን ጎን ነን አይናችንም ልባችንም ከአባቶቻችን እና ቤተክርስቲያን ላይነው
••
ከጠቅላይ ቤተክህነት የተሰጠ መግለጫ
••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ
•••
“ ከፍ ብሎ የሚወጣ ከፍ ብሎም የሚጮህ የመለኮትን አናኗር የሚናገር የሚተረጉም ፤ የጥበብ ባሕር የስብከት ጥልቅ ዮሐንስ በንስር የተመሰለ ነው፡፡ ከወንድሞቹ ለይተህ የመረጥኸው እንደ መላእክት ኀጢአት የሌለበት ይሆን ዘንድ ” ( ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ )
••
በቅድስት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳት አንዱ ንስር ነው ፤ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ ንስር በእግሩ እንደሚሽከረከር ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏልና በንስር ተመስሏል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አምስት ቅዱሳት መጽሐፍትን የጻፈ ሲሆን እነዚህም ወንጌለ ዮሐንስ፣ ሦስት መልእክታት እና ራእይ ናቸው፡፡
••
የተሰወረብንን ነገር ሁሉ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ቀኑ ይፍታልን።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት ፣ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
••
ኢየሱስ ክርስቶስ ያጌጥንበት ማርዳ የሸተትንበት መአዛችን ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ጣፋጭ የሆነ መአዛ ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ የከበረ መአዛ ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን ያጣጣምንበት ያሸተትንበት የሕይወት መአዛ ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ የኑሯችን ዋስትና የቤታችን የሁለንተናችን ማስቀጠያ መልካም መአዛ ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መስዋእት አድርጎ ያቀረበ መአዛ መስዋእት ነው!
ኢየሱስ ክርስቶስ የዳንበት ያመንበት የማያሳፍረን ድፍረታችን የሆነ መአዛ ነው!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በእኔ ቢጠቁርም ሰማይ
በእኔ ቢጠልቅም ፀሐይ
በነፋሳት የማይጠፋ ፋኖሴ
ኢየሱስ ነው የመኖር እስትንፋሴ
••
መች ይሰጠኛል ለጠላት
አይሰለጥንም በእኔ ሞት
የሚጠብቀኝ ጌታ ነው
የትኛው ጠላት ሊደፍረው
በቤቴ መቃን ላይ ደም ይታያል
እኔን ከእግዚአብሔር ከቶ ማን ይለያል
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ ጥር 7 - በዓለ ሥሉስ ቅዱስ
••
ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው።
••
👉 #ሕንጻ_ሰናዖር - ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር። ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ።
••
ከጥፋት ውሃ ( ከኖኅ ዕረፍት ) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ። በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ።
••
ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ። ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል። ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል።

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል። ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው። ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን።
••
ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም። የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና። ይልቁኑ " ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ።
••
ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ። እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ። ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት። ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው " ባቢሎን (ዝሩት) " ሲባል ይኖራል።
••
👉 #ቅዳሴ_ቤት - ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች።
••
ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን ሠራዊት መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል። በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል። ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል ፣ ደግ ፣ ጥበበኛ ፣ አስተዋይ ፣ መናኝ ንጉሥ ነውና።
••
ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል። ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላቸው ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል። ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው።
••
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን።
••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 እንኳን አደረሳችሁ ለቅድስት ሥላሴ
••
ጥር ሰባት አጋዝተ ዓለም ሥላሴ ያን የትዕቢት የአመፃን ሠፈር የሰናኦርን ግንብ ያፈረሱበት ዕለት በቅድስት ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
••
አቤቱ ጾም ፣ ጸሎት ፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ መምህር ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ( ተክለ ማርያም ) አስገራሚ ግጥም ተገጠመለት
••
በነገር ሁሉ የቅዱሳን አምላክ ከፊት ከኋላ ይቁምልህ “ለቅኖች ምስጋና ይገባል”መዝሙር 33፥1 ታላቁ መጽሀፍ እንደሚል" የተከበርክ ወንድማችን መምህር ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ የቤተክርስቲያን የስስት ልጅ መድጏኔ ዓለም ክርስቶስ ስትወጣ ፣ ስትገባ ይጠብቅህ!
••
ፈጣሪ ባንተ እጅግ ይደሰታል በርታልን
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
••
እንደ ልደቱ ፣ እንደ ስቅለቱ።
እንደ ትንሳኤ ፣ እንደ እርገቱ፤
ሁሌ ይናፍቀናል ብርሃነ ጥምቀቱ።
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ ጥር 10 - ጾመ ገሃድ
••
ጥር አስር በዚህች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
••
እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
••
በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
••
በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
••
የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
••
መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው።
••
ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
••
( ስንክሳር ዘወርኀ ጥር )
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ - ሊቀ ዲያቆናት ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከሰባት ዲያቆናት መካከል በቅድስና ህይወቱ ለክርስቲያኖች አብነት የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይገኚበታል። እስጢፋኖስ ማለት መደብ ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው።
••
ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ሲሆን አባቱ ስምኦን እናቱ ሀና ይባላሉ። የሰማዕቱ የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን ፩፯ ❤️🙏
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 የድንግል ማርያም ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ
••
አስተርዮ _ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም ፦ መታየት ወይም መገለጥ ማለት ነው፡፡
••
👉🏼 ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት በሰማይና በምድር የተሰጣትን ፀጋና ክብር የገለፀችበት እለት ስለሆነ በዓሉም አስተርዮ ማሪያም ይባላል።
••
❤️ የድንግል ማሪያም ጥበቃ ምልጃዋ አይለያቹ
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🙏 #ሊቀ_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_አባቴ 🙏
               💚💛❤️
      የፈጣሪውን ስም ስለመሰከረ
      ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ
      የስቃይ መሳሪያ ያላዘናጋህ
      መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ።
••
👉 ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የልባችሁን ፍላጎት ያሳካላችሁ ፣
👉 ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን ፣
👉 ሀገራችንና ህዝባችንን በምልጃህ አስበን፣
👉 አቤቱ የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ማረን ፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ራራልን ፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ይቅር በለን አሜን🙏
••
የቅዱሣን ረድኤት በረከት ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ለሁላችንም ይድረሰን " አሜን "
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
ይህን ዓለም ንቀው ስጋቸውንና ነፍሳቸውን ለሰማያዊ መንግስት ያስገዙ ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
••
የቅዱሣን ረድኤት በረከት ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ለሁላችንም ይድረሰን " አሜን "
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉🏼 ድንግል ማርያም የሞት ዘመን መደምደሚያ ምልክተ ናት‼️
••
ድንግል ሆይ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍህም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ። ፍህም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው ፤ ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ( ቅዱስ ኤፍሬም )
••••
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
2025/06/30 15:08:03
Back to Top
HTML Embed Code: