Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ገጣሚ ኬቢሻ
💚💛❤️
የእስራኤል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ስለ እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ማረን ይቅር በለን •• ወንድማችን ቃለ ህይወት ያሰማልንየአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

👉🏼 ጌታ ሆይ ቶሎ " ና "
👉🏼 ልሳነ ክርስቶስ መምህር ጳውሎስ መልክዐ ሥላሴ
••
በአማኑኤል ልጆች የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ትምህርቶችና መረጃዎች እንዲሁም ዝማሬዎች በፌስቡክ ሆነ በቴሌግራም እንዲሁም በቲክ ቶክ ገፃችን ይከታተሉ።
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos

🌿 እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሳችሁ! 🌿
════• 🌿🌿•═════
የኃጢአት ሸክም ያጎበጠህ ፣ በሁሉ የተናቅህ ፣ አላፊ አግዳሚው ምራቁን ጢቅ እያለ ስድብ የሚያዋጣብህ ጎስቋላ ትሆናለህ። ሌሎች እነርሱን ስላልመሰልክ ይንቁህና ያንቋሽሹህ ይሆናል። ነገር ግን በፈጣሪህ ዘንድ ያለህን ተፈላጊነት ሰዎች በሚያሳዩህ ዝቅ ያለ አመለካከት አትለካ። ዛሬ የሚሰድቡህና የሚያዋርዱህ ሰዎች በአንተ መፈጠርና ሰው ሆኖ መኖር ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ የላቸውም። የሕያውነት እስትንፋስ አልሰጡህም ሞተህ እንዳትቀር ስለ አንተ አልተሰቀሉልህም። ላንተ ሲሉ የከፈሉት ዋጋ ስለሌለ ለእነርሱ ከቁስ ያነስክ ልትሆን ትችላለህ።
••
ነገር ግን በእጁ የለወሰህ፣ ቁርበትና ሥጋ ያለበሰህ፣ በአጥንትና በጅማት ያጠረህ ሕይወት ሰጥቶ ሰው ያደረገህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚበልጥበት ሀብት የለውም። በፀሐይና በጨረቃ በሌሎች ብርሃናት ሁሉ ያላስቀመጠው በአንተ ውስጥ ብቻ የቀረጸውን መልኩን ፈጽሞ ሊረሳ የማይችል አምላክ ይፈልግሃል። ጥበቡን አፍስሶ ስለ ፈጠረህ ስትጠፋ ዝም አይልም። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ደሙን ስላፈሰሰልህ ፈጽሞ አይተውህም።
••
የሆሣዕና በዓል በሰዎች ፊት እንደ ምናምንቴ ለሆንን ለእኔ እና ለአንተ ነው። ጌታ ከኢያሪኮ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟቸው የመጣው እንደ በርጤሜዎስ ያሉ የተናቁ ነዳያንን፣ እንደ ዘኬዎስ ያሉ የተጠሉ ኃጢአተኞችን ነበር። "ሆሣዕና በአርያም" የሚለው መዝሙራቸውም እንደዚያ ያማረው በመገፋት እና በመጠላት ልባቸው የቆሰሉትን በፍቅርና በምሕረቱ ፈውሶ መድኃኒትነቱን ስላቀመሳቸው ነው።
••
ለጌታ እናስፈልገዋለን!

❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Photo
#ሆሳዕና
(የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት)
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡
በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
#ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡-
ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
#የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው
ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
#ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡-
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡
#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡…..
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።
#መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷ (ተጨማሪ ያንብቡ)
#ምስባክ
"ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
#ወንጌል
ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡

“ ፍቅርህ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም ፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል ፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል ፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡
••
ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡ ”
••
ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግም
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
••
ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡ ”
••
ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግም
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኃጢአት ያጎበጠኝ እኔን ሊፈውስ ፤ የበደል ሸክም ያጎበጠው ትከሻዬን ሊያጸና በመቅደስ ሰውነቴ ሊያድር መድኃኒቴ እርሱን እሸከም ሳያንቅ መረጠኝ ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎም እረኞችን ላከልኝ ፤ ወደ መቅደሱ አግብቶ አከበረኝ። መቅደስ ሰውነቴ እየተቀደሰ በመቅደስ ይኖር ዘንድ።
•••
የተናቅን እኛ በስሙ የከበርንበት ፤ ከእስራት የተፈታንበት የድኅነት በዓል። እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
•••
የተናቅን እኛ በስሙ የከበርንበት ፤ ከእስራት የተፈታንበት የድኅነት በዓል። እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
✝ ሰሞነ ሕማማት
••
••
👉 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት እንዲሁም
••
👉 ከምሽቱ 1ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት ናቸው
••
••
👉 አለመሳሳም አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም።
••
👉 መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም።
••
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
••
••
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳ
••
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም
••
👉 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት እንዲሁም
••
👉 ከምሽቱ 1ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት ናቸው
••
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ
••
👉 አለመሳሳም አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም።
••
👉 መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም።
••
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
••
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
••
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው።
••
የጌታችን ሕማማት የምናስብበት ሳምንት ይሁንልን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 ሰኞ || ሰሞነ ሕማማት
••
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦
••
🛑 መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ ” ( ማርቆስ 11፥11_14 ) በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።
••
🛑 አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ” ማቴ 21፥13 በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃች - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
••
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦
••
🛑 መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ ” ( ማርቆስ 11፥11_14 ) በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።
••
🛑 አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ” ማቴ 21፥13 በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃች - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏻 #ማክሰኞ || የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል
••
ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ስልጣኑ በጸሐፍተ ፈሪሳውያን ተጠይቋልና።
••
ጥያቄውም " ከምድራውያን ነገስታት ፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር ፣ ተአምራት ማድረግ ፣ ገብያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ። የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? " አላቸው።
••
እነርሱም " ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል። ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል ፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት "
••
እርሱም " በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው "። ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ስልጣን እንደሚያደርግ አጥተው አይደለም። ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው።
••
በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል። ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው።
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
•••
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ስልጣኑ በጸሐፍተ ፈሪሳውያን ተጠይቋልና።
••
ጥያቄውም " ከምድራውያን ነገስታት ፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር ፣ ተአምራት ማድረግ ፣ ገብያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ። የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? " አላቸው።
••
እነርሱም " ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል። ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል ፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት "
••
እርሱም " በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው "። ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ስልጣን እንደሚያደርግ አጥተው አይደለም። ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው።
••
በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል። ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው።
••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
•••
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው
••
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ
📌 የዕብራይስጥ ፣
📌 የቅብጥ እና
📌 የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
••
👉 ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ « ኪርዬ ኤሌይሶን » ነው፡፡ « ኪርያ » ማለት « እግዝእትነ » ማለት ሲሆን « ኪርዬ » ማለት ደግሞ « እግዚኦ » ማለት ነው፡፡

ሲጠራም « ኪርዬ ኤሌይሶን » መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ « አቤቱ ማረን »ማለት ነው፡፡ « ኪርያላይሶን » የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው « ዬ » ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ « ኤ » በመሳሳባቸው በአማርኛ « ያ »ን ፈጥረው ነው፡፡
••
👉 ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « መሐረነ ፣ ማረን » ማለት ነው፡፡
••
👉 እብኖዲ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « አምላክ » ማለት ነው፡፡ « እብኖዲ ናይናን » ሲልም « አምላክ ሆይ ማረን » ማለቱ ነው
••
👉 ታኦስ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ « ጌታ ፣ አምላክ » ማለት ነው፡፡ « ታኦስ ናይናን » ማለትም « ጌታ ሆይ ማረን » ማለት ነው፡፡
••
👉 ማስያስ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ « መሲሕ » ማለት ነው፡፡ « ማስያስ ናይናን » ሲልም « መሲሕ ሆይ ማረን » ማለት ነው
••
👉 ትስቡጣ፦
« ዴስፓታ » ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
••
📌 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም « ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ - አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ » ማለት ነው፡፡
••
📌 አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን « ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን » ማለት ነው፡፡
••
📌 አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም « ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ - የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን » ማለት ነው፡፡
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏻 https://www.facebook.com/terbinos

👉🏻 ረቡዕ || ሰሞነ ሕማማት
••
1. ምክረ አይሁድ ይባላል
••
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል።
••
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
••
2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ፦
•
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል።
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል
•
ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ ‼️
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
1. ምክረ አይሁድ ይባላል
••
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል።
••
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
••
2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ፦
•
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል።
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል
•
ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ ‼️
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Photo
👉🏻 ሐሙስ || ሰሞነ ሕማማት
••
📌 ከስቅለት በፊት ያለው #ሐሙስ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡ የተፈጸሙ #ምሥጢራት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡
••
1• ሕጽበተ እግር ፡-
••
••
2• ጸሎት ሐሙስ፡-
••
👉 የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/
3• የምሥጢር ቀን፡-
••
👉 ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው ፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡ በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
••
4• የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፡-
•
👉 ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ /ሉቃ. 22፤18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡:
••
5• የነጻነት ሐሙስ፡-
••
👉 ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና ፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ.15፤15/ ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ /ማቴ 26፤17-19/
••
6• አረንጓዴው ሐሙስ ፡- በዚህ ዕለት ጌታችን በአትክልት ቦታ መጸለዩን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በአትክልት ቦታ መጸለዩን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡
••
7• የትእዛዝ ሐሙስ ይባላል ምክንያቱም ፡-
••
📌 ከኅጽበተ እግር በኋላ ጌታችን ደቀመዛሙርቱን እናንተም እንዲሁ አድርጉ ብሎ ስላዘዘ
📌 በጌቴሴማኒ ‹‹ ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ›› ብሎ ያዘዘበት ዕለት በመሆኑ
📌 ሥርዓተ ቁርባንን ከሠራ በኋላ ‹‹ ከመዝግበሩ ›› መታሰብያን አድርጉ በማለት በዚህ ዕለት ያዘዘበት በመሆኑ ነው፡፡
••
8. የነፃነት ሐሙስ፡- ይኸውም ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወዳጆች ግን ብያችኋላሁ ያለውን የነፃነት ቃል ለማስታወስ

9. ፋሲካ በአልዓዛር ቤት ይባላል :- ጌታችን የአይሁድን የፋሲካ በዓል ያከበረበት ታላላቅ ምሥጢራትን የፈጸመበት በአልዓዛር ቤትበመሆኑ ነው፡፡በጠቅላላው በዚህ ሐሙስ ዕለት ቅዳሴ በለሆሳስ ይቀደሳል ፣ እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለው ጸናጽል ነው፡፡ ይህም
••
1. አይሁድ ጌታን ለመያዝ ሲመጡ በለሆሳስ እየተገጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ
2. በዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማጠየቅ ነው፡፡ በቅዳሴው ጸሎት ኑዛዜ አይደረግም ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 https://www.tg-me.com/Terbinos
👉🏻 https://www.facebook.com/terbinos
👉 https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi

👉
የጸሎተ ሐሙስ ዕለት ጌታ በፍጹም ትሕትና የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበት ፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ሕይወት ማኅተም የሆነውን ምሥጢረ ቍርባን ያከናወነበት ነው፡፡ እናንተም ለወንድማችሁ እንዲህ አድርጉ ሲል ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል፡፡ ይህ የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጠኋችሁ የተባለውን ነው። እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ፤ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም ፤ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ ( ዮሐ.፲፫፣፲፮-፲፯ ) በማለት ትሕትናውን አሳይቷል፡፡••
👉 ጌታ በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ ምሳሌውን አሳየኋችሁ፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም እኔ እሆን? እኔ እሆን? ተባባሉ፡፡ ጌታም ኅብስት ቆርሼ ፣ ከወጡም አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው አላቸው፡፡ ይሁዳን ማመልከቱ ቢሆንም ስለማን እነደተናገረ አልገባቸውም። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ትሕትናን አስተማራቸው••
2• ጸሎት ሐሙስ፡-
••
👉 የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/
3• የምሥጢር ቀን፡-
••
👉 ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው ፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡ በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
••
👉
በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡••