"መቻል"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ልብሷ እላይዋ ላይ የተቀደደ ፥ አንገትዋ በመታነቅ የተነሳ የበለዘ ፥ ቡጢ አፍንጫዋን የሰበረባት... ድንግልናዋ በሀይል የተገረሰሰ ሴት እርቃን ሬሳዋ ተጋድሟል።
መብራት ከተማ ወደ ፍርስራሽ ተቀይራለችደ የመብራት ሀይቅ ከነዋሪው ደም ጋር ተቀላቅሏል። የከተማው እኩሌታ የደም ዝናብ አጨቅይቶታል፥ የሀይቁ ዙሪያ በደም ጎርፍ ርሷል።
ከተደፈሩ በኋላ የተገደሉ ሴቶች የሙት አካላቸው እርቃን በየመንገዱ ተጋድሟል ፥ የእናታቸውን ሬ*ሳ የታቀፉ ሙት ህፃናት በየቦታው ይታያሉ ፥ መፈነዳዳት የጀመሩ አስከሬኖች የመብራት ጎዳና ላይ ተበትነዋል።
ከተማዋ የሞት ሙዚየም መስላለች። በየአቅጣጫው የጭንቅላት ፍላጭ፥የተተረተረ ሆድ ፥ የአንጀት ዝርጋፊ፥ የገላ ቁርጥራጭ ፥ ይታያል።
መቻል ቆራጣ እግሩን እየላሰ ፥ ዝንቦችን ለማባረር ያላዝናል። የቆሰለ አካሉ ላይ የሚያርፉ ዝንቦችኝ በጥርሱ ለመንከስ በሞከረ አፍታ በውሸኛ "ኡኡ" ይላል። የእግሩን ቁስል በምላሱ ከላሰ በኋላ በውሻ ቋንቋ መከፋቱን ያወራል ፥ ያላዝናል።
ከጦርነቱ በፊት መቻል ከአንበሳ የተዳቀለ ውሻ ይመስል ነበር። ረጅም ሽንጡ ምገስ አልብሰውታል ፥ ገላው ምቾት ተጓድሎበት እንደማያውቅ ምስክር ነበር።
ከጦርነቱ በኋላ መቻል ገላው ተለወጠ። ከአንበሳ የተዳቀለ ይመስል እንዳልነበር ከድመት የተዳቀለ እንኳን የማይመስል ኮስማና ሆነ።
ከኋላ እግሩ አንዱ ተቆርጦ አንድ እግር አልባ ሆኗል። ግራ ጆሮው በከፊል ተቆርጦ ተንጠልጥሏል። አንድ አይኑ ፈሷል ፥ አፍንጫው ቆስሏል።
መቻል እርቃን አስከሬን አጠገብ በደረቱ ተጋድሞ ያቃስታል።
ልብሷ እላይዋ ላይ የተቀደደ ፥ አንገትዋ በመታነቅ የተነሳ የበለዘ ፥ ቡጢ አፍንጫዋን የሰበረባት... ድንግልናዋ በሀይል የተገረሰሰ ሴት እርቃን ሬሳዋ ተጋድሟል። አስከሬኑ አጠገብ መቻል በደረቱ ተጋድሞ ያቃስታል።
ሟች የመቻል አሳዳጊ ነበረች። መቻል ከተደፈረች በኋላ የተገደለች አሳዳጊው አጠገብ ተጋድሞ እንደ ሰው ያቃስታል።
ከጦርነቱ በፊት እንዲህ አልነበረም.....
@Tfanos

😢5👍1
  አንዳንዴ በጣም በቁም ነገር ዩቲዩብ ሰፈር ሄጄ ዘፈን እሰማለሁ። ታዲያ ለሰአታት አንድ ዘፈን ደጋግሜ እሰማለሁ።
የምሰማቸው ዘፈኖች የሆነ አይነት ትዝታ ፥ የጓደኞቼን ትውስታ ፥ የተረሱ ገጠመኞች ማስታወሻ ወዘተ ይሆኑኛል።
ለምሳሌ ዛሬ ደጋግሜ የሰማሁት ዘፈን "ከፍ እንበል በስራ" የሚለው ነው።
የሮፍናን ትውልድ አባላት ይሄን ዘፈን አያውቁት ይሆናል። ዘፈኑ ስለ ህዳሴ ግድብ የተዘፈነ ነው። ጥንት እኛ ወጣት እያለን የተፈዘነ ዘፈን ነው። የኛ ትውልድ እንደ ዘንድሮ ልጆች አይደለም። የሐገር ፍቅር ያለው ትውልድ ሰለሆነ ለአባይ የተዘፈነውን ዘፈን ከልቡ አጣጥሟል።
እንግዲህ የሆነ የሆነ ቀን ትውስ ብለውኝ ደጋግሜ የምሰማቸው ዘፈኖች አሉ። ለምሳሌ ዘፈኖቹ ለHiv ማስተማሪያ የተዘፈነው ማለባበስ ይቅር የሚለው ፥ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የተዘፈነው ፥ መለስ ሲሞት የተሰራው ምነው ሞት ወዘተ ናቸው። ደጋግሜ አደምጣቸዋለሁ።
ዛሬ "ከፍ እንበል በስራ" የሚለውን ደጋግሜ ሰማሁት። ዘፈኖች ከትዝታ ጋር ያላትሙኝ አይደል? ለምሳሌ የዛሬው ዘፈን አዘዋውሮ ወስዶኝ ጥንት ከተለየኋት ፍቅረኛዬ ትዝታ ጋር አላተመኝ።
አንዳንድ ሰዎች "ያ ዘፈን እና የፍቅር ታሪክ ምን አገናኘው?" ይላሉ። መልስ ከፈለጋችሁ ሲግመን ፍሮይድን ጠይቁት።
ይህ ከእናተ ህይወት ጋር ምን ያገናኘዋል? አውቃለሁ ምንም አይገናኝም።
ወላህ የፃፍኩት እና ልፅፈው ያሰብኩት አይገናኝም። የፃፍኩት እጅ እግር የለውም፥ ምክኒያቱም ርቦኛል።
"ከፍ እንበል በስራ ፥ ከፍ እንበል በዝና
እንደገና ክብር ፥ ሞገስ እንደገና
ከፍ ከፍ እንበል ፥ ከፍ ከፍ በሉ
ይቻላል ያልነው ፥ ይፈፀማል ቃሉ"
ፀዴ ዘፈን ነው 😎
ምንድነው መፃፍ የፈለግኩት? 🤔

😁6👍4🥰1🤔1