Telegram Web Link
"ትምህርት ምን ያደርጋል? አንድ ሰው ተምሮ ስራ ቢይዝ የሚያገኘው ደሞዝ ጥቂት ነው። ቲክቶከር ፥ ዩቲዩበር ፥ ቪዲዮ ኤዲተር... ከተማረው ሰው በላይ ያገኛል" የሚል ይዘት ያለው ቪዲዮ አየሁ። ያው ቲክቶክ ላይ ነው ያየሁት።

ሃሳቡ ላይ የሚነሱ ብዙ ችግሮችን ለጊዜው እናቆያቸው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ሰዎች ብዙ ብር ያገኛሉ ነው አይደል አጀንዳው? እውነታው ፥ ማህበራዊ ሚዲያን የፈጠረው ራሱ ትምህርት ነው!


@Tfanos
👍8😁1
አዋቂን የመቅጣት መንገድ የት ያደርሰናል?
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *

አንድ ሰው በጉብዝናው መቀጣት አለበት? የታታሪነት ሽልማቱ በችግር መወቃት መሆን አለበት?

ገና ልጆች ሳለን በአእምሯችን የተሳሉ 3 የትምህርት ዘርፎች ነበሩ። ህልማችን ከሶስቱ አንዱን ማሳካት ነበር።

ህልማችን ኢንጂነር ፥ አሊያም ፓይለት ወይም ዶክተር መሆን ነበር። ሶስቱ መስኮች ለጎበዝ ተማሪዎች ብቻ የተፈቀዱ መሆናቸውንም እናውቅ ነበር። ከልጅነት ወደ ወጣትነት ስንሸጋገር ከሶስቱ ዘርፎች ሁለቱ ዋጋቸውን አጥተው ጠበቁን። ኢንጂነሪንግ የተማሩ ጓደኞቻችን ስራ አጥ ሆኑ። ህክምና ያጠኑቱ ልፋታቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን የማያሟላ ሆነ።

መሰረታዊ የሆነ የጤና ችግር ባለበት ሐገር ውስጥ እንኖራለን። የሰለጠኑ ሐገራት የቀረፉት የጤና ችግር ዛሬም ድረስ ለእኛ ስጋት ነው።
የጤና ተቋማት መሰረታዊ መገልገያዎችን አሏማሉም። ስለ ህክምና በቂ ግንዛቤ የለም።

የዶክተርነት ዋጋ ምንድነው?

የዛሬ ዶክተሮች ለዚህ ሞያ ጉርምስናቸውን ገብረዋል ፥ ልጅነታቸውን ሰውተዋል። በተማሪነት ዘመናቸው እንደ አቻዎቻቸው የመዝናናት ነፃነት አልነበራቸውም። ጥርሳቸውን ነክሰው ፥ አንገታቸውን ቀብረው ፥ ስሜታቸውን ገርተው መማር ነበረባቸው።
ህክምና ለማጥናት የላቁ ተማሪዎች መሆናቸውን ማስመስከር ነበረባቸው።

አንድ ሰው በጉብዝናው መቀጣት አለበት? የታታሪነት ሽልማቱ በችግር መወቃት መሆን አለበት?

ጎበዝ ተማሪዎች ተመልምለው ህክምና አጠኑ። ጎበዝ ተማሪ በመሆናቸው የተነሳ ዶክተር ሆኑ። የጤና ባለሞያ በመሆናቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት አቃታቸው። ይህ እንዴት ያለ ህመም ፈጣሪ እውነት ነው?

ጎበዝ በመሆን የተነሳ መቀጣት እንዴት ያለ ኢ ኢፍትሃዊነት ነው? በታታሪነት የተነሳ ባገኙት ሞያ ለችግር መዳረግ ምን የሚሉት ግምድልነት ነው?

የጤና ባለሞያዎች ጥያቄያቸው አይራበን የሚል ነው። በግልፅ አማርኛ በመማራችን የተነሳ አንቀጣ የሚል ጥያቄ ነው ያላቸው። ጥያቄው ህመም ይፈጥራል። የጤና ባለሞያ ራበኝ ስል መስማት ፥ ዶክተር የቤት ኪራይ ሲቸግረው ማየት ልብ ይሰብራል።

ጥያቄው የሃኪሞች ብቻ አይደለም። ከዚህ ጥያቄ ጎን መቆም ከሐገር እጣ ፈንታ ጋር መሰለፍ ነው። ዛሬ ዶክተሮች ተቸገርን ሲል የተመለከተ ቀጣይ ትውልድ ምን ይሰማዋል? ያለ ጥርጥር ትምህርት ላይ ተስፋ ይቆርጣል። የመማር ዋጋ ላይ ምራቁን ይተፋል። አዳጊ ልጆቿ ትምህርትን የሚንቁባት ሐገር እጣ ፋንታዋ ውድቀት ነው።
ለጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ክብር መስጠት ለትምህርት ክብር መስጠት ነው።
ለዶክተሮች ጥያቄ እውቅና መስጠት ለእውቀት ክብር መስጠት ነው።
ለሃኪሞች ጥያቄ ጅሮ መስጠት ለታታሪነት ክብር መስጠት ነው።

ሐገራችን ለጤና ባለሞያ የሚገባውን ክፍያ መስጠት ይችግራት ይሆናል። ነገር ግን ትንሽም ቢሆን ኑሯቸውን ለመደጎም የምትቸገር አይመስለኝም። የሀገር ሀብት የሚውልበት ቦታ ነው እጥረትን እየፈጠረ ያለው።

ሀብታችን የት ነው?

ኮርደር ልማት የሚባል ቅንጦት ቢሊዮን ብሮችን እየበላ ነው ፥ የቤተመንግሥት ግንባታ ላይ ብዙ ሃብት ተከስክሷል፥ ለአክቲቭስት እስከ 240 ሺ ብር የሚደርስ ወርሃዊ ድጎማ እንደሚደረግ የሰማነው በቅርቡ ነው፥ በስብሰባ ስም የሚወድም የሐገር ሀብት የትየለሌ ነው፥ ለጥይት መግዣ ብዙ ዶላር ይወጣል። በዚህ ሁሉ መሐል ግን የጤና ባለሞያዎች ተቸግረዋል።

ሃኪሞቻችን እየተራቡ ሊያገለግሉን ቃል አልገቡም።

ድምፃቸው ይሰማ!

@Tfanos
👍12
ለኢትዮጵያ ህዝብ ዋጋ መክፈል ይገባል?

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ይታወቃል። በእርግጥ ዋጋ መክፈል ይገባል?

በዛሬው ደርዘን ጥያቄ በዚህ ጉዳይ እንወያያለን። እንግዳዬ ሚስጥረ-ሥላሴ ታምራት ናት።

ተከታተሉ፥ ለሌሎች አጋሩ ፥ አስተያየት አካፍሉ

ሊንክ

https://youtu.be/l_OgtaXEpng
"የዶክተሮችን ጥያቄ ፖለቲከኞች እየጠለፉት ነው" የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረ ነው።

መፍትሔው በጣም ቀላል ነው። የዶክተሮችን ጥያቄ ፖለቲከኞች እንዳይጠልፉት ማድረግ የሚችለው መንግስት ነው።

መንግስት ለጥያቄው ምላሽ መስጠት ቀላሉ እና ትክክለኛው መፍትሔ ነው። ለጥያቄው መልስ ተሰጠ ማለት "የፖለቲካ ቁማር" የሚለው ስጋት ያከትማል

Nb፥ ፖለቲከኞች ለዜጎች ጥያቄ ድምፅ መሆናቸው ሃላፊነታቸው ጭምር ነው። ፖለቲከኛ ለህዝብ ጥያቄ ድምፅ መሆን ፥ ስህተትን መንቀስ ፥ አማራጭ ማቅረብ ስራው ነው!

@Tfanos
👍8
በቅርበት የሚያውቁኝ ሰዎች በሁለት መንታ ባህሪዎች ያውቁኛል። በማይጠበቅ መጠን ወግ አጥባቂ እና ግትር ደግሞም በተቃራኒው አፈንጋጭ እና ወግ አፍራሽ ሆኜ ያገኙኛል። ሁለቱ ባህሪ ለነሱም ለእኔም ይጋጭብኛል።

ወግ አጥባቂ የሆንኩባቸው ጉዳዮች በአንድ አሊያም በሌላ የወይዘሮ ምህረት ውጤት ናቸው። ምህረት እናቴ ናት።

ልጆች ሆነን አንድ እለት ጆተኒ ጨዋታ ጀመርን። በ50 ሳንቲም መድበን ቆመርን። ጨዋታውን መሐል ላይ አቋርጬ "ተሸንፌያለሁ" አልኩ። ከዛ በኋላ ቁማር ተጫውቼ አላውቅም። ምክኒያቷ ምህረት ናት። በአይነ ህሊናዬ ሲደብራት ታየኝ። እኔም መጫወቱ ደበረኝ።

ለአደንዛዥ እፆች ገና በልጅነቴ ተጋላጭ ነበርኩ። ኤለመንተሪ የተማርኩት ሻሸመኔ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ነው። አፈንጋጭ ልጆች ጓደኞቼ ነበሩ። ገና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ጋንጃ የሚጠቀሙ ጓደኞች ነበሩኝ። እኔም መጠቀም ፈለግሁ። ከወሰንኩ በኋላ ምህረት ሲከፋት አሰብኩ። ይቅርብኝ አልኩ።

ልጆች ሆነን ቤታችን ፀሎት ይደረጋል። የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን በልጅ ቋንቋ አስተምራለሁ። ጉባኤውንተ ተካፋይ የምትሆነው ምህረት ናት።

እንደመታደል ሆኖ ከፍተኛ ነፃነት ነበረኝ። ነፃነት ብቻ ሳይሆን ሊገባኝ ባልቻለ ምክኒያት እኔ ላይ ሀይለኛ እምነት ነበራት። በተለየ ሁኔታ መታመንን እና ነፃነትን አጎናፅፋኛለች። (ታናናሾቼ እኔ ያገኘሁትን እድል ያገኙ አይመስለኝም 😂)

እኔን መቆጣጠሪያ መንገዷ አንዲት ቃል ብቻ ነበረች። "ጌታ" በምትል ቃል ብቻ ነው የተቆጣጠረችኝ። በጣም ልጅ ሆኜ ልክ ያልሆነ ነገር ካደረግኩ በብስጨት "ጌታ ይሄን ይወዳል?" ትላለች። ትክክለኛ ነገር ሳደርግ "ጌታ ይባርክህ" ትላለች። በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ "ጌታ ኢየሱስ ያውቃል" ትላለች። በቃ! በለጋነቴ "ጌታ ኢየሱስ" የህይወት ስታንዳርድ እንደሆነ እንዲገባኝ አደረገች።

የተማረች አይደለችም። ነገር ግን ለእውቀት ክብር አላት። ዘመናይ ባትሆንም በሆነ መንገድ ተራማጅ አድርጋኛለች።

አንድ ቀን ከዘመዳችን ልጅ ጋር ተጣላሁ። ቁስ..ላም ብዬ ሰደብኹት። ሰውነቱ ላይ ቁ ስል ነበረበት። ይሄን ስትሰማ በጣም በሸቀኝ። "ሲሳይን ለምን ቁስ..ላም አልክ? እሱ ፈልጎ ነው ያመጣው? ይሄን ጌታ ይወዳል?" አለችኝ።

ቁማር ፥ ሱስ የሚያስይዝ ነገር ፥ ሰውን ማዋረድ ወዘተ ጌታ ኢየሱስ እንደማይወድ ልጅ ሆኜ አወቅሁ። ሱስ ለመጀመር እድሉን ሳገኝ ያልጀመርሁት ሰው ይቆጣኛል ብዬ ፈርቼ አልነበረም። እሷ ይከፋታል ብዬ እና ጌታ አይወድም ብዬ ነበር።

ከሆነ ጊዜ በኋላ "ኢየሱስ በዚህ ዘመን ቢኖር እንዴት ይመላለስ ነበር?" ብዬ ማሰብ ጀምሬ ነበር። ያን እንዳስብ እርሾ የሆነችው ምህረት ናት።

በኔ ህይወት ያሳደረችውን ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ታውቀው ይሆን? እንጃ!

በትዕቢት እና በኩራት መሓከል ሆኜ የምናገረው ነገር አለ። ብዙ ሰዎች "ልጆችሽ ጥሩ ልጆች ናቸው። ስነምግባር አላቸው" ይሏታል። እኔ በግሌ ገና በለጋነቴ ኢ-ስነምግባራዊ የሚባሉ ነገሮችን ማድረግ ከማልፈልግበት ምክኒያቶች መካከል ዋነኛው እሷን ላለማስከፋት ነበር።

አንድ ቀን ተኝቼ ነበር። ቤት መኖሬን አላየችም። ተንበርክካ ረጅም ፀሎት ፀለየች። ስትፀልይ ድምጿን ከፍ አድርጋ ነው። ፀሎቷን ሰማሁ። የልጆቿን ስም (የአራታችንንም) እየጠራች ፀለየች። በየግል ፀለየችልን። አሜን ብላ ጨረሰች። ስለ ራሷ ምንም አልፀለየችም። የፀሎት አጀንዳ ነበራት። እኔ የማውቀው ጉዳይ ነበረባት። አንድም ለራሷ አልፀለየችም። ያቺን ቀን "በህይወቷ ደስ እንድትሰኝ አደርጋታለሁ። አክብሬያት አስከብራታለሁ" ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ።


@Tfanos
12👍2🥰1
😥
😁5
"የእናት ውለታዋ..."
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ስለ እናት ሲወራ ሃዘን ይጫነናል። የእናትነት ምልክት ከሚባሉቱ መኻከል ብዙዎቹ ህይወታቸው መከራ የደቆሰው ነው።
ስለ እናት የተዘፈኑ ዘፈኖች ትራጃዲ ይበዛቸዋል። ስለ እናት የተገጠሙ ግጥሞች ከእንባ የተቀላቀሉ ናቸው።

በእርግጥ የዚህ ሰበብ ይታወቃል። በርካታ እናቶች ህይወታቸው የመከራ ነው። ልጆቻቸው እንዲጠግቡ ተርበዋል ፥ ልጆቻቸው ቀና እንዲሉ እናቶች ጎብጠዋል ፥ እናትነት እና መጎሳቆል ግዴታ እስኪመስል ድረስ ተዛምደዋል።

ይህ እስከመች ይቀጥል ይሆን?

እንጀራ ጋግራ ፥ ከሰል ሸጣ ፥ ልብስ አጥባ ልጆቿን ያሳደገች እናት ብዙ ናት። ቀላል ቁጥር የሌላቸው እናቶች ደግሞ ከባል ጭቆና ጋር መታገል እጣ ፈንታቸው ሆኗል።

እናትነት ሲባል ብዙ ሃዘን ወደ ልባችን ይመጣል። የድህነት ቡጢ ፥ የችግር አለንጋ ፥ የትዳር አለመመቸት... ወዘተ

ምኞቴ ሌላ ነው።

የነገ ልጆች ስለ እናታቸው ሲያወሩ ከሃዘን ይልቅ ኩራት ልባቸውን ቢዳስሰው እመኛለሁ።

"እናቴ ሽቅቅር ፥ በራስ መተማመን ያላት ፥ በቂ ገቢ የምታገ፥ የተማረች ... " ተብሎ የሚገለፁ እናቶች በዝተው ማየት እመኛለሁ።

እናት ምርጥ እናት ለመሆን መጎሳቆል አይጠበቅባትም። የእናትነት ፍቅሯ በቂ ነው።

የወደፊት እናቶች የቀደሙ እናቶችን መከራ የማይጋሩ ፥ የቀደሙ እናቶችን ቀንበር የማይሸከሙ እንዲሆኑ እመኛለሁ

@Tfanos
8👍1
ሦስቱ ትንቢቶች
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

"በኤዲስ ትሞታለህ፥ ከ10 አመት በኋላ ኤድስ ይይዝሃል"

የፍርሃት ቡጢ ነረተን። ባለንበት ደርቀን ቀረን። አስፈሪ አይኖቿን መመልከት ከብዶን አቀረቀርን።

"መዳፋችሁን አምጡ፥ እጣ ፈንታችሁን እነግራቸዋለሁ" ስትለን እየሳቀን ነበር የታዘዝናት። መዳፍ አንብባ የተሰማትን ስትነግረን ግን ድንጋጤ በጥፊ አጮለን።
የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ነበርን። ከትምህርት ቤት መልስ እንደ ዘወትር ልማዳችን ከአርሰናል እና ከማንችስተር ማን እንደሚበልጥ እየተከራከርን ፥ ስለ ሳምራዊት ጡት ውበት እየተማከርን ፥ በከድጃ መቀመጫ ግዝፈት እየተደነቅን ፥ ባዮሎጂ አስተማሪያችን ላይ እየተሳለቅን... ወደ ሰፈራችን ጉዞ ጀመርን።

የከተማችን ስመ ጥር እብድ አስቁማን መዳፋችንን እንደንዘረጋላት ጠየቀችን። ሳናመነታ ተስማማን።
ኤልሳ ስመ ጥር እብድ ናት። ግዙፍ ቁመቷ ፥ ረጅም ካፖርቷ ፥ በጀርባዋ ጣል የምታደርገው ሽመል ፥ ቀይ መልኳ ፥ በጨርቅ የተቋጠረ ቡቱቶዎቿ... መለያዎቿ ናቸው። " መዳፍ ተመልክታ እጣ ፈንታ ትናገራለች" ሲባል ሰምተናል።

አራት ጓደኛሞች እየተበሻሸቅን ወደ ሰፈራችን ስናዘግም አስቆመችን። የመተናኮል ልማድ እንደሌላት ስለምናውቅ ቆምንላት። መዳፋችንን እንድንዘረጋ ስትጠይቀን ታዘዝናት። ከሁላችንም ቀድማ የመሳፍንትን መዳፍ ተመለከተች። ለግማሽ ደቂቃ ያህል ብቻ መዳፉን እንደነገሩ ካየች በኋላ ፊቱን በጥንቃቄ መረመረች።

"ማነው ስምህ?" በጎርናና ድምጿ ጠየቀችው
"መሳፍንት" እየሳቀ መለሰላት
"ኤዲስ ይይዝሃል። ከአስር አመት በኋላ ኤዲስ ይይዝሃል። መሞቻህ እሱ ነው"
ሁላችንም እኩል ደነገጥን። ድንጋጤያችን ስሜት አልሰጣትም።

አጠገቤ የቆመውን ተባረክ መዳፍ አፈፍ አደረገች። መዳፉን በጥንቃቄ መረመረችው።
"ማነው ስምህ?" እንደ ቀደመው በጎርናና ድምጿ ጠየቀችው
"ተባረክ እባላለሁ" ድምፁ ተንቀጠቀጠ
"አተኩረህ ተመልከተኝ። አይኔ ስር ተመልከት"
እንደታዘዘው አደረገ።
"ስንተኛ ክፍል ነህ?"
"ስምንተኛ ክፍል ነኝ። ዘንድሮ ሚኒስትሪ እፈተናለሁ" ከፍርሃቱ እየታገለ እንደሆነ ድምፁ ያስታውቋል።
"ሚኒስትሪ አትፈተንም። ከፈተናው በፊት ትሞታለህ"
የተንገዳገደ መሰለኝ። ወይንም ተንገዳገደ።

ኤልሳ ግድ አልሰጣትም። የበሀይሉን መዳፍ አፈፍ አደረገች። ሊሸሻት ፈልጎ ነበር። አልተሳካለትም።

"ማነው ስምህ?"
"በሀይሉ"
"ከሁለት አመት በኋላ ታብዳለህ"

ልሸሻት ፈለግሁ። እጣ ፈንታዬን ማወቅ አስፈራኝ። ወዴት እንደምሸሽ ማሰላሰል ጀመርሁ። መሮጥ የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ባውቅም ባለሁበት ደንዝዤ ቀረሁ።

ትኬሻዬ ላይ እጇን አኖረች። ጉልበቴ ዛለ። መቆም ከበደኝ።
"ቀና ብለህ እየኝ"
እየፈራሁ አይኖቼን ወደ አይኖቿ ላክሁ።

"ፈርተኻል"
"አዎ ፈርቻለሁ"
ትታን ሄደች።እጣ ፈንታዬን ሳትነግረኝ ጉዞ ጀመረች። እፎይ አልኹ

ቀናት መደበኛ ጉዟቸውን ሲጀምሩ ሁሉም ነገር የተረሳ መሰለ። የኤልሳን አጀንዳ ዘነጋነው። ትኩረታችን ሚኒስትሪ አልፈን የሀይስኩል ተማሪ ለመሆን መመኘት ሆነ።

የሚኒስትሪ ፈተና ሁለት ቀን ሲቀረው ፥እኔ እና መሳፍንት እንዴት ባለ መንገድ እንደምንኮራረጅ ልንወያይ እነ ተባረክ ቤት ሄደን። ሰፈራቸው ስንደርስ መንደሩ ታውኳል። በማመንታት ወደ ቤታቸው ስንቃረብ የለቅሶ ድምፅ ሰማን።

መሳፍንት በቆመበት እንባው ፈሰሰ።
"የኤልሳ ትንቢት ተፈፀመ" አለኝ ከእንባ ጋር። ድጋሚ ጉልበቴ ዛለ። መቆም ተሳነኝ። ምድር በፍጥነት መሽከርከር የጀመረች መሰለኝ። ጓደኛችን ተባረክ ከሚኒስትሪ ፈተና በፊት ሞተ። ምን እንደገለው አናውቅም። "ለሊቱን ሞቶ አደረ" ተባልን

የተባረክ ሞት በሀይሉ ላይ የፈጠረውን ድንጋጤ ልዘነጋ አልችልም። "እኔም እንደማብድ ነግራኛለች" አለኝ እያለቀሰ። መሳፍንት በጭንቀት ከአጠገባችን ሸሸ። የምለውን አጥቼ ዝም አልኹ።

ወራት አለፉ፥ የበሀይሉ ቤተሰቦች ከተማ ቀይረው ወደ አዲስ አበባ ገቡ። ከበሐይሉ ጋር ተራራቅን። እኔና መሳፍንት "የውሾን ነገር ያነሳ..." ተባብለን የኤልሳን ትንቢቶች ላናነሳ ወሰነን።

ከእለታት በአንዱ መሳፍንት አይኑ ደም ለብሶ ቤት መጣ። እጁ ይንቀጠቀጣል።
"በኤድስ እንዳልያዝ ምን ላድርግ?" አለኝ። ጥያቄው ግራ አጋባኝ።
"ስለ በሐይሉ ሰምተሃል?" አለኝ
"ምን ሆነ?" ልቤ ደረቴን በጥሳ ልትወጣ ታገለች።
"የአእምሮ ህመም ገጥሞት አማኑኤል ሆስፒታል ገብቷል። ከድጃ ናት የነገረችኝ"
የድንጋጤ ቡጢ ነረተኝ። የመሳፍንት ጉንጮች ላይ እንባ ተራመደ

"የማለቅሰው ለራሴ ነው፤ እኔም በኤዲስ እንደምሞት ነግራኛለች" አለኝ። የማፅናኛ ቃል ስላልነበረኝ ዝም አልኹ።

አመታት እንደ ዋዛ አለፉ። ኤልሳም ተሰወረች። "ጅብ በልቷት ሞታለች" ይላሉ አንዳንዶች።ሌሎች ደግሞ "ተሽሏታል" ይላሉ። ከተማ ስለመቀየሯም የሚናገሩ አሉ።

እኔና መሳፍንት ከኤልሳ ትንቢቶች ጋር አለን።

መሳፍንት Hiv በደሙ ውስጥ እንዳለ ካረጋገጠ አምስት አመታት ተቆጥረዋል...


@Tfanos
😢6🤔32👍2
"ሀርሜ"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

"አባትሽ ይገድልሻል። እናትሽ ወደኔ ዘንድ መጥታ መፍትሔ ካልሰጠኋት በአሰቃቂ ሁኔታ ይገድልሻል"

ለደቂቃዎች አካሌን ማዘዝ አቃተኝ። አእምሮዬ በፍርሃት ደነዘዘ። ሽፈራው በነገረኝ ነገር ሰውነቴ ራደ።
ሽፈራው በአርሲ ነገሌ ከተማ ስመ-ጥር ጠንቋይ ነው። ለእናቴ ደግሞ የቅርብ ዘመዷ ጭምር። ቤቱ አስጠርቶኝ "እናትሽ እኔ ዘንድ መጥታ መፍትሔ ካልሰጠኋት ፥ አባትሽ አሰቃይቶ ይገድልሻል" አለኝ። በማግስቱ እኔና ሀርሜ መፍትሔ ፍለጋ ሽፈራው ቤት ሄድን።

አመሻሹን ነበር የደረስነው። እንደደርስን ጫት ሲቀርብልን ግራ ተጋባሁ።
"ጫት ልንቅም ነው?"
"አለሜዋ ለዛሬ ብቻ ነው" አለችኝ ሃርሜ በለሆሳስ
"አትፍሪ" ሽፈራው አበረታታኝ።
ከሽፈራው ትይዩ ያለች ፍራሽ ላይ እንደተቀምጠን የተሰጠንን ጫት አኝኬው በተነገረኝ መሰረት መራራውን የጫት ፈሳሽ ዋጥኩት።
"ጎበዝ ልጅ" አዳነቀኝ።
ሽፈራው በወሬ የምሰማውን አይነት ጠንቋይ አይመስልም።

ከቆይታ በኋላ ሃርሜ እየተንዘፈዘፈች ማጓራት ጀመረች። ግራ እጇን እና ቀኝ እግሯን ግትር አድርጋ በተቃራኒው ያለ አኳሏን እያወራጨች እንደ እንስሳ አጓራች።... እየጮሃች ተንደባለለች። ግድግዳውን ቧጠጠች። በመጨረሻም ተዘለፍልፋ ፍራሹ ላይ ወደቀች።

ከአንድ ሰአት ለሚበልጥ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ ስትሆን ምንም አይነት እርዳታ ለማድረግ አልሞከርኩም። ይልቅ እንደ ትርኢት ሙሉ እንቅስቃሴዋን እከታተል ነበረ።
የለበሰቺው ቀሚስ እስከወገቧ ተገልጦ፥ የፓንቷ ግማሽ አካል ታየ።... የእናቴን እንርቃን ለመሸፈን አልሞከርኩም። ፊቷን ስትቧጭር ፥ፀጉሯን ስትነጭ ፥ ደረቷን በሀይል ስትደቃ አልከለከልኳትም።... ልብ ሰቃይ ትያትር እንደታደመ ተመልከች በተመስጦ ተከታተልኳት።

ሃርሜ 'ራሷን ጥላ እንደሞተ ሰው ለግማሽ ሰአት ያህል ከተኛች በኋላ ቀስ በቀስ ወደ አእምሮዋ ተመለሰችና በሃፍረት አቀርቅራ ተቀመጠች።

"ነይ ወዲህ" ሽፈራው ጠራት

በእንብርክክ ወደ ሽፈራው ሄዳ ጉልበቱን ሳመች። ቀና አድርጎ አፏን ሳማት።... ለደቂቃዎች የእናቴን ከንፈር በልጇ ፊት መጠጠው።

"አለሜ" ሽፈራው የእናቴን ክንፈር ከመጠጠው በኋላ ጠራኝ
"አቤት" ልቤ ደለቀ
"ነይ ወዲህ"
ወደ ሽፈራው ማቅናት ከበደኝ። እናቴ ላይ ያደረገውን እኔ ላይ የሚደግም መሰለኝ። ከሰገድኩለት በኋላ አፌ ላይ እንዳይስመኝ ፈራሁ።
ሃርሜ በዝግታ መጥታ አጠገቤ ስትቀመጥ ሃፍረቷን አውቄዋለሁ። ድርጊቷ እንዳሸማቀቃት ተገንዝቤያለሁ። በእንብርክክ ወደ ሽፈራው ከማቅናቴ በፊት አይኖቼን ወደ ሃርሜ ስወረውር እንባዋን እንዳላይ አቀረቀረች። እያለቀሰች ነው።

'አታልቅሺ! ሳድግ እናት እሆንሻለሁ። ትልቅ ስሆን ማንም ለሃጢኣት አያስገድድሽም' አልኩ በልቤ።
የሽፈራውን ልጅ ስመለከታት የስላቅ በሚመሰል መንገድ ፈገገች። ዳግመኛ እናቴን ስመለከት የሃሰት ፈገግታ ፊቷ ላይ ረበበ።
"ነይ ወዲህ" ሽፈራው ተረጋቶ ጠራኝ
የሽፈራው ፈገግታ አስፈራኝ። ጥርሶቹ የሰይጣን ስለት መሰሉኝ።

"ነይ ወዲህ"

እጆቼ በላብ ርሰው ጉልበቱ ላይ ተደፋሁ። ጀርቦዬን በጫት ቅጠሎች ሲመታ አይኔ አጠገቡ ያለ አነስተኛ ስለት ላይ አረፈ።
'ቢያርደኝስ?' ድንገተኛ ድንጋጤ መታኝንና ልቤ ደረቴን ቀዳ ለመውጣት ትግል ገጠመች።
'ከሚያርደኝማ አፌ ላይ ቢስመኝ ይሻላል' አልኩ በልቤ።
"አለሜ"
"አ...ቤ....ት" እያንዳንዱን ፊደል የጠራሁት በመርበትበት ነበር
"አትፍሪ"

ስላታሙ ቢላ አጠገቡ ምን ይሰራል? ለባዕድ አምልኮ ልጆች እንደሚታረዱ ፀሐይ ለእናቴ መናገሯን አስታውሳለሁ።
ከፀሐይ እና ሃርሜ ውይይት ልጆች ለመስዋዕት የመታረዳቸው ነገር ትውስ ሲለኝ ተረበሽኩ።
እግሩ ላይ እንደተንበረከኩ ማጅራቴን ሲዳስሰኝ መታረዴ እርግጥ መሰለኝና ተስፋ ቆረጥኩ።
'ሽፈራው እግሩ ላይ እንደተንበረከኩ በማጅራቴ በኩል ሊያርደኝ ቢሞክር እናቴ ዝም ትለው ይሆን?'
'ሃርሜ ራሷን መቆጣጠር ተስኗት ስትወራጭ እንዳልረዳት ያደረገኝ አፍዛዥ ሰይጣን እኔም ስታረድ እሷንም ያፈዛት ይሆን?'

በእንብርክክ የነበርኩበት ጥቂት ደቂቃዎች የዘላለም ሲሶ ያህል ረዘሙብኝ።
ሽፈራው ማጅራቴ ላይ ያሳረፈውን እጁን ወደ ጉንጮቼ ልኮ አገጬን ይዞ ቀና ሲያደርገኝ በቅፅበት እድሜ መንታ ስሜት ውስጥ ገባሁ።
'ከመታረድ ስጋት ነፃ በመሆን መደሰትና አፌ ላይ ሊስመኝ ነው' በሚል መፍራት!
ጉንጮቼን በጠንካራ እና ትልቅ እጁ በሚያሳምም ሁኔታ ሲይዘኝ ድዴ አከባቢ የተሰማኝን ህመም ለማስታገስ አፌን በትንሹ ከፈትኩና ለንቦጬን ጣልኩ።

ግንባሬ፥ የታችኛው ከንፈሬ ውስጠኛ ክፍል፥ የአይኔ ሽፋሽፍት አከባቢ የምራቅ ጠብታዎች አረፉ። ሽፈራው እንትፍ አለብኝ።

"ወደ እናትሽ ሂጂ"
ባለማመን ስሜት ተነስቼ ልሮጥ ነበር። 'አፌ ላይ አትሰመኝም አይደል?' የሚል ንግግር ከአንደበቴ ያልወጣው በአንዳች ተአምር መሆን አለባት።.... ሃሳቡን ሳይለወጥ ፈጥኜ ከፉቱ ዘወር አልኹ። እናቴ አጠገብ ተቀመጥኩ።

"ምትኬ" ልጁን ጠራት
"አቤት"
"ላንቺና ለአለሜ መኝታ አንጥፊ"
እንደታዘዘችው ልታደርግ ወደ ጓዳ ገባች።
"አለሜ" በእርጋታ ጠራኝ
"አቤት"
"አንቺ ከምትኬ ጋር ትተኛለሽ። ..... እናትሽ ደግሞ እዚህ ትተኛለች"
ዞሬ እናቴን አየኋት
"ለዛሬ ብቻ ነው" አለችኝ ሃዘን ባሻከረው ድምፅ

"አለሜ ምትኬ ጋር ሂጂ" አነጋገሩ ትእዛዝ አዘል ሆነብኝ።... እናቴ እንባዋን እንዳልመለከት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች።
"አለሜ ሂጂ" የተናገረችው አቀርቅራ ቢሆንም ማለቅሷን ተገንዝቤያለሁ

አዘንኩላት እንጂ አላዘንኩባትም። ለእኔ ስትል የተራመደችበትን ፀያፍ ጎዳና በመመልከቴ በገዛ ራሴ አፈርኩ እንጂ በእናቴ አላፈርኩባትም። ራሴን ተቀየምኩ እንጂ እርሷን አልተቀየምኩም። የነውሯ ምክንያት በመሆኔ እኔነቴን ጠላሁ እንጂ ስለ ሃርሜ አንዳች አሉታዊ ስሜት አልተፈጠረብኝም።


@Tfanos
👍2
"ፖለቲከኞች ያልተማሩ ናቸው" የሚል ወቀሳ ይሰማል። ባለስልጣናት ድግሪ የሚገዙ ፥ሰነፍ ተማሪ የነበሩ ወዘተ ተብለው ሲወቀሱ እንሰማለን።

የዚህ ምክኒያት ውስብስብ አይደለም። አዋቂው ራሱን ከፖለቲካ ሲያገል አላዋቂው መንበር ላይ ይቀመጣል። የተማረው ፖለቲካን ሲሸሽ ያልተማረው እጣ ፈንታን ወሳኝ ሆኖ ይከሰታል።

"ከፖለቲካ ራስህን ባገለልኽ ጊዜ ፥ በእውቀት እና በስነምግባር ካንተ የሚያንሱቱ ይገዙሃል!"


@Tfanos
👍51🤬1
የቀበሌያችን ሹማምንት ሀዘኑ ላይ ዘሀን ደረቡበት።
የልብ ቁስሉ ሳይሸር በጦር ወጉት፥ ከህመሙ ሳያገግም ደጋግመው አደሙት።

ወርቁ እናቱ ሞታለች። ገና ከጉርምስና
ወደ ወጣትነት በሚሸጋገርበት እድሜ እናቱ ሞተች። አባት አልባነቱ ላይ እናት አልባነት ተከተለ። የሰፈር ማቲዎች ፥ የመንደሩ ህፃናት ጭምር ለወርቁ አዘንን። የህይወት ትርጉም ባይገባንም ፥ የወርቁን ሀዘን መረዳት አልከበደንም።

በሙት ልጅ ይጨከናል? ሀዘንተኛን ማፅናናት ባይቻል እንኳን ቁስሉ ላይ ጦር መስደድ እንዴት ይቻላል?
ቁስል ላይ ዘይት ማፍሰስ የአባት ነው። ይኸን ማድረግ ባይቻል ፥ እንዴት የቆሰለን ስፍራ በስለት ይወጉታል?

እናቱ ከሞተች በኋላ ወርቁ በፍጥነት መክሳት ጀመረ። የእናቱን ሞት ተከትሎ መኖሪያ ግቢያቸው ተሸነሸነ፥ ግዛት ማስጠበቅ ሳይችል ቀረ። የቀበሌ ሹማምንት የሀዘንተኛውን መኖሪያ ግቢ እየሸነሸኑ ለተለያዩ ሰዎች ማከፋፈል ጀመሩ።

"የእናቱ ሀዘን እስኪወጣለት ቢጠብቁ ምን ነበረ?" ብለው ነበር ወላጆቻችን።

ከእኩዮቼ ጋር ኳስ ልንጫወት ስንሰባሰብ ለወርቁ ከንፈር እንመጥለት ጀመር። የወላጆቻችንን የሀዘን ቃል እየተዋስን ተነጋገርን። "እናቱን እስኪረሳ ቢጠብቁ ጥሩ ነበር" ተባባልን።
የቀበሌ ሰዎችን ሳናውቃቸው ጠላናቸው። ሀዘንተኛ ላይ በመጨከናቸው ተፀየፍናቸው።

ድሮ ኳስ ስንራገጥ ወርቁ ቆሞ ያየን ነበር። "አቢቹ እንደ ሮናልዲኒሆ ነው ፥ አቡላ ደግሞ እንደ ጄራርድ ነው" ይለን ነበር። እናቱ ስትሞት ይሄን ማለት አቆመ። ግቢያቸው ሲሸነሸን ደግሞ እኛን ጭምር ዘጋን። ሃይማኖተኝነቱን ትቶ በአደባባይ ሲጋራ ሲያጨስ ታየ።
ለሱ አዘንን። ቀበሌዎችን ጠላናቸው።

ምርጫ 97 ደረሰ።

ሲመሽ ወርቁ እኛ ቤት ይመጣል። ሬዲዮ ይከፈትና ከአባቴጋ ዜና ይሰማሉ። የጀርመን ሬዲዮ ፥ የአሜሪካ ሬዲዮ ፥ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ፥ ገለመሌ ሬዲዮ ፥ ቅብርጥሶ ሬዲዮ እያፈራረቁ ይሰማሉ። በሬዲዮ የሰሙት ወሬ ላይ መሰረት አድርገው ከአባቴ ጋር ይወያያሉ

ዝርዝር ውይይታቸውን ማስታወስ ባልችልም ሁለቱም የቅንጅት ደጋፊዎች መሆናቸውን አስታውሳለሁ። "በዚህ አመት ኢህአዴግ ይወድቃል" ይባባሉ ነበር።

ምርጫ ሲቃረብ በሬዲዮ የምርጫ ቅስቀሳ መስማት ጀመርኹ። ያኔ ቅንጅትን ወደድኹት። ቅንጅትን የወደድኹት በሁለት መሰረታዊ ምክኒያት ነበር።

ምክኒያት አንድ፥ ስለ ቅንጅት የሚያወራው ሰውዬ ድምፁ ያምራል። በወርቃማ ድምፁ ቅንጅት እንዲመረጥ ይቀሰቅሳል። የሰውዬው ድምፅ አንበረከከኝ። ቅንጅት ካሸነፈ ባለ-ወርቃማ ድምፁ ሰውዬ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆን መሰለኝ።
የሰውዬውን ተክለ ቁመና በምናቤ ሳልኹት። ረጅም ፥ ፈርጣማ ፥ ቀይ ፥ ባለ ገብስማ ፀጉር... መልከ-ቀና ጎልማሳ በአእምሮዬ ሳልኹ። ያ ሰውዬ በመለስ ዜናዊ ፋንታ የሐገራችን ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆን መሰለኝ።

ባለ ድምፀ-መረዋው ሰው አርቲስት ደበበ መሆኑን ያወቅኹት ቆይቼ ነው።

ምክኒያት ሁለት፥ ወርቁ ቅንጅትን ይወዳል።

ወርቁ ተበዳይ ስለሆነ ያሳዝነኝ ነበር። ከእኩዮቼጋ ለወርቁ ከንፈር መጠን እናውቃለን። እኔ ፥ ዮናታን ፥ ሶፈኒያስ ፥ ዳግማዊ ፥ አቢቲ ፥ አቢቹ... እኛ በር ላይ ኳስ እንራገጣለን። ከኳስ እርግጫ በተረፈን ጊዜ ለወርቁ እናዝናለን። በዳዮችን እንረግማለን። የተወሰደበት እንዲመለስለት እንመኛለን...

አዝንለታለሁ። በጣም እንዳዝንለት የሚያደርገኝ ምክኒያት እናቴ ስለምትወደውና ስለምታዝንለት ነው።
ቤታችን መጥቶ ከአባቴጋ ፖለቲካ ሲያወሩ እሰማቸዋለሁ። ባይገባኝም እሰማቸዋለሁ። ቅንጅትን ሲደግፍ ለሱ ብዬ ቅንጅትን ደገፍኹ። ቅንጅቶች ካሸነፉ ካሳ የሚሰጡት ይመስለኝ ነበር...

አንድ ቀን ፊቱን አርዝሞ "ኢህአዴግ ምርጫ አጭበረበረ" ብሎ ለአባቴ ነገረው።
"ኢህአዲጎች አጭበርብረው አሸነፉ" ተባባሉ።

አዘንኹ። ቅንጂቶች በመሸነፋቸው አዘንኹ።

ይክሱታል ብዬ አስቤ ነበር። ቅንጅቶች ካሸነፉ የተወሰደበትን ያስመልሱለታል ብዬ አስቤ ነበር...

ቅንጅቶች ተሸነፉ።

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
3👍1
😁5
ስለ ለምፅ ምን ያህል ታውቃላችሁ?

ሊያ ያዕቆብ ለምፅ የጀማመራት ገና በለጋነቷ ነበር። ለምፁን ተከትሎ ድብርት መጣ። ራሷን መጥላት ጀመረች። "መስታወት ማየት አልፈልግም" ትል ነበር። ምክኒያቷ የገዛ መልኳን ማየት አለመፈለጓ ነበር።

አንዳንድ ሰዎች ስነልቦናዊ ጉዳት የሚያደርስ ነገሮችን አድርገውባት ያውቃሉ። ለምፅ ስላለባት ብቻ ከታክሲ አስወርደዋት ያውቃሉ።

ሊያ ድብርት አንገላቷታል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ችግሮች ተደራርበውባታል።

ገና በለጋነቷ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ለማድረግ ተገዳለች።

ለምፅ ፥ ድብርት ፥ መገለል ፥ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ያለፈችበት መንገድ ነው።

አሁን ችግሮቿን ተጋፍጣ መርታት ጀምራለች።

የዛሬው ደርዘን ጥያቄ እንግዳዬ ሊያ ያዕቆብ ናት። ተከታተሉ ፥ ለሌሎች አጋሩ ፥ አስተያየት አስፍሩ።

ሊንክ 👇

https://youtu.be/Tii72h4iwTc
👍4
ማነው ባለአደራ
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ብርሃነ መስቀል ረዳ የቀኝ ጌታ ልጅ ነው። በደሴ ከተማ በድሎት እና ምቾት ነበር ያደገው። የጎደለው የለም። ተንቀባሮ ኖሯል፥ ተንቀባሮ ተምሯል። የፊውዳል ስርኣት ቢቀጥል የሚያጣው ነገር የለም። ምናልባትም ባለስልጣን የመሆን ተስፋ ነበረው። ምናልባትም እጅግ ባለጠጋ ሆኖ መኖር ይችል ነበር። ነገር ግን በስርኣቱ ላይ አመፀ። "መሬት ለአራሹ" አለ።

ብርሃነ መስቀል መሬት ለጭሰኛው እንዲሰጥ ሲጠይቅ የገዛ ሃብቱ ላይ እያመፀ ነበር። ከቀኝ ጌታ ረዳ ላይ ሊወርስ የሚችለው ሰፊ ጋሻ መሬት ተስፋ ነበረው። "የኔ የሃብት ተስፋ ይቅርብኝ" ብሎ አመፀ። "መሬት ለአራሹ፥ ተዋጉለት አትሽሹ" አለ። ለተበዳይ ወግኖ ሊፋለም ወሰነ።

"መሬት ለአራሹ" የሚለው ጉዳይ ላይ መሰረታዊ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ይገባኛል። የደርግ የመሬት ፖሊሲ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን የሚናገሩ አሉ። ያ ትውልድ ላይ ቅሬታ ያላቸው ብዙ ናቸው። ተማሪዎች ንጉሡን መገርሰሳቸው አግባብነቱን የሚጠራጠሩ አሉ። ኢህአፓ ፥ መኢሶን ፥ ደርግ... ወዘተ የዛሬ ችግራችን ሰበቦች እንደሆኑ የሚያምኑ ጥቂት አይደለም።የኔ ነጥብ ሌላ ነው።

ነጥቤን ላስረዳ...

በያ ትውልድ ዘመን መደብ የሸጡ የሚባሉ ሰዎች ነበሩ። ከደህና ወገን ሆነው ሳለ ለሌሎች መብት የጠየቁ ሰዎች ናቸው። የባላባት ልጆች ሆነው ሳለ ለጭሰኛው መብት ታገለዋል። እነሱ ባይጨቆኑም ለተጨቋኝ መብት ሲሉ በረሃ ወርደዋል። እኚህ ሰዎች መደብ የሸጡ ይባላሉ።

ብርሃነ-መስቀል ረዳ ትልቅ ማሳያ ነው። የገዛ ምቾቱ ላይ አምፆ ለተበዳይ ድምፅ አሰማ። ድምፅ ማሰማት ብቻ አይደለም ፥ ታገለ። የብርሃነ መንገድ በመጨረሻም የገዛ ህይወቱን አስከፈለው።

ለጊዜው የርዕየተ አለም ጉዳይን እንዘንጋ። ሶሻሊዚም ፥ አሊያም ካፒታሊዝም ወይም ፊውዳሊዝም የሚለውን እንርሳው። የነብርሃነ መነሻ ነጥብ ላይ እናተኩር። መነሻ ነጥባቸው ለተበዳይ ማዘን ፥ ሀገርን መውደድ ፥ ለውጥን መፈለግ ነው። ከግል ጥቅም ይልቅ የወገንን ክብር ማስቀደም ነው መደብ መሸጥ....

ዛሬ የተወሳሰበ ችግር ባለባት ሐገር ውስጥ እንንራለን። ሚሊዮን ወጣቶች ስራ አጥ ናቸው። ባለ ስራዎቹ ደሞዛቸው አያኖራቸውም። ዜጎች ከባርነ**ት የሚስተካከል ኑሮን ይገፋሉ። ለኒህ ወገኖች ድምፅ የሚሆን ማነው?

አባይነህ ሸለሞ "ማነው ባለ አደራ" የሚል መዝሙር አለው።

"ትውልድ ወድቆ በመከራ
ወገን ሲያለቅስ በየስፍራ
አይቶ የሚመለስ ፥ ሰምቶ የሚራራ
ማነው ባላደራ ፥ የሚቆም ከተጎዱት ጋራ
" ይላል።

ማነው ባለ አደራ? እርግጥ ሁሉም ሰው ለራሱ መብት መቆም አለበት። ይህ ብቻ ግን አይበቃም። እንደነ ብርሃነ መስቀል መደቡን የሚሸጥ ያስፈልጋል።

የገንዘብ ችግር የሌለበት ፥ ነገር ግን ለድሆች የሚራራ
የሚባለውን ያላጣ ሆኖ ሳለ ለተራቡት የሚያስብ
ባለ ስልጣን ሆኖ ለተርታ ዜጎች የሚጨነቅ...

ብርሃነ መስቀል የባላባት ልጅ ሆኖ ሳለ ለጭሰኛው ራርቷል። የዘመናችን ብርሃነመስቀል ማን ይሆን?
ማነው ባለ አደራ?

"ትውልድ ወድቆ በመከራ
ወገን ሲያለቅስ በየስፍራ
አይቶ የሚመለስ ፥ ሰምቶ የሚራራ
ማነው ባላደራ ፥ የሚቆም ከተጎዱት ጋራ"

ይሄ ነገር ረዘመ መሰለኝ


@Tfanos
👍42
በቅርቡ አንድ ሰውን ዋሸሁኝ። የታቀደበት አይነት ውሸት ነበር የዋሸሁት።

ከቀናት በኋላ ራሴን ታዘብኹት። ውስጤ የተሸሸገውን ክፉውን እኔነቴን ተዋወቅኹት።

ለመዋሸቴ ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ ሌላ ማብራሪያ መፍጠር ቃጣኝ። "ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የዋሸሁት። ያ ሰው ሊረዳኝ ይገባል" አልኹ።

ሌላ ሰው እኔን የመረዳት ግዴታው ምን ድረስ ነው? ለጥፋቴ ቀላሉ መፍትሔ ይቅርታ መጠየቅ አይደል? "እንዲህና እንዲያ አይነት ምክኒያት ስላለኝ" የሚል ምክኒያት ምን የሚሉት ነገር ነው?

የትኛውም ሰው ከቀላል እስከ ትልቅ ጥፋት ከፈፀመ በኋላ "ለምን?" ተብሎ ቢጠየቅ ማቅረብ የሚችለው ሰበብ ይኖረዋል። ገፊ ምክኒያቱን ያብራራል። ነብሰ ያጠፋ እንኳን "ተረዱኝ" ብሎ የሚናገረው የራሱ "እውነት" ይኖረዋል።

ሰበብ ውጤቱን ይቀይረዋል?

እልፍ ምክኒያቶች የጥፋት ማካካሻ አይሁንም። ሰዎችን ያሳዘነ ፥ ሌላውን የበደለ፥ የዋሸ፥ ያጠፋ ሰው... ሰበብ መደርደር አይኖርበትም። "እንዲህና እንዲያ ስለሆነ ተረዱኝ" የሚል ተማፅኖ ማስቀደም አይጠበቅበትም። የሚቀድመው አሻሚ ባልሆነ መንገድ ይቅርታ መጠየቅ ነው። ቀጥሎ ካሳ ካስፈለገ መካስ ፥ መቀጣት ካለም ቅጣቱን በፀጋ መቀበል ነው።

በእርግጥ የልብ ዝንባሌን ማስረዳት ፥ ገፊ ምክኒያትን ማሳወቅ ፥ እንዲረዱን መጠየቅ አግባብ ነው። ግን ደግሞ ከዛ የሚቀድመው ጥፋትን ማመን ነው።

አውቃለሁ ፥ ይህ ፅሁፍ ከእናንተ ህይወት ጋር አይገናኝም።

የታዘብኩት ራሴን ነው። የሚገስፀውም ራሴን ነው። የሚወቅሰው ራሴኑ ነው። ተስፋአብን እወቅሰዋለሁ!

ጥፋቴን በማመን ፋንታ "ያጠፋኹት በዚህና በዚያ ምክንያት ነው" የሚል ማስተባበሪያ ለመፍጠር ስታገል ራሴን አገኘሁት። ሌሎችን በሚወቅሱበት ጥፋት መመላለስ አያስደነግጥም? አያናድም? እንዲያ ነው የሆነው።

ይህ ፅሁፍ ከእናንተ ህይወት ጋር እንደማይገናኝ አውቃለሁ ...


@Tfanos
1
"ኢትዮጵያ ደሃ ስለሆነች ደሞዛችሁ ይበቃችኋል"
* * *

የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ።

"ኢትዮጵያ ደሃ ናት። ከሐገራችን ኢኮኖሚ አንፃር ለሐገራቸው መስዋዕትነት ይክፈሉ" የሚሉ ሰዎች አሉ።

ጥሩ።

የጤና ባለሞያዎች የሐገሪቱ ብቸኛ ባለቤት አይደሉም። በልዩነት መስዋዕትነት እንዲከፍሉ አይገደዱም።

ከሁሉ በፊት፥

የመንግስት ሹማምንት መስዋዕትነት ከፍለው አረዓያ ይሁኑ። በዝቅተኛ ደሞዝ ሕዝብን ያገልግሉ። ጥቅማቅሞችን ይተው። የሚያሽከረክሩትን ቅንጡ መኪና ያቁሙ። ሐገራችን ደሃ ስለሆነች በዝቅተኛ ደሞዝ ያገልግሉ!

(መሪ ለተመሪው አርዓያ ሲሆን ጥሩ ነው)

የዲጂታል ሚሊሻው ነገር አጃዒብ ነው

አዲስ ሳይንሳዊ ግኝት ያስተዋወቁ ይመስል "ሐገራችን ደሃ ናት" ይላሉ ዲጂታል ሚሊሻዎች። የማናውቀውን ስላሳወቁን እናመስግናቸው። እነርሱ ባይነግሩን ኖሮ ሐገራች ሐብታም ትመስለን ነበር።

እንግዲያውስ ካድሬዎች ለሌላው የመከሩትን እነሱው ይተግብሩት። ለአጨብጫቢነቸው ከመንግሥት ካዝና የሚፈስላቸውን የሕዝብ ገንዘብ መቀበል ያቁሙ።

ዜጎች ኑሮ ሲወደድባቸው "ሐገራችን ደሃ ስለሆነች በጥቂት ገንዘብ አገልግሉ" የሚሉ ግብዞች እነርሱም ተመሳሳዩን ያድርጉ። ሐገራችን ደሃ ስለሆነች በጥቂት ደሞዝ ብቻ ያገልግሉ፥ ጥቅማጥቅም አይቀበሉ። ቅንጡ ኑሯቸውን ይተውት! (መሰረታዊ ኑሮን በማያሟላ ገቢ ህይወታቸውን ደጉመው ያሳዩ)

በተረፈ "እኔ በድሎት እየኖርኩ አንተ ግን በችጋር አለንጋ ተገረፍ" ማለት ሚዛናዊ አለመሆን ብቻ አይደለም። ስር የሰደደ ክፋት ጭምር እንጂ!


@Tfanos
7👍7
አንዳንድ ነገሮች....

ልደቱ በትላንትናው እለት ለBbc በሰጠው ቃለ መጠይቅ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች እየተዘዋወሩ ነው። አንዳንዱ ወቀሳ በጣም ያስቃል። ቀላል ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ቃለ መጠይቁን ሳያነቡት ነው ትችት እያወረዱ ያሉት።

ልደቱን አትውደደው ፥ በሃሳቡ አትስማማ ፥ መንገዱ ስህተት ነው ብለህ እመን። መብትህ ነው። ግን ደግሞ ለራስህ ክብር ይኑርህ!

ራሱን የሚያከብር ሰው ለትችት ወደ አደባባይ ከመውጣቱ በፊት የተፃፈውን ያነባል።

ልደቱ በ97ቱ ምርጫ "ህዝቡን ክጃለሁ" ብሎ እንደተናገረ አስመስለው የሚፅፉ ሰዎች አሉ። እንዲህ አይነት ፅሁፍ የፃፉ ሰዎች በአጭሩ ቃለ መጠይቁን አላነበቡም። (አለማንበብ መብት ነው። ግን ደግሞ ባላነበቡት ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት ራስን ትዝብት ላይ ይጥላል)

ልደቱ ያለው ነገር ግልፅ ነው። በ97 ምርጫ እንደ ፓርቲ ህዝቡን ክደናል ነው ያለው። "ህዝቡ መርጦን ሳለ ፓርላማ አንገባም በማለት ካድነው" ነው ያለው። ይህን ደግሞ ድንገት ዛሬ የተናገረው አይደለም። ደጋግሞ ተናግሮታል። አዲስ ጉዳይ አይደለም። "ፓርላማ አለመግባት የመረጠንን ህዝብ ድምፅ አለማክበር ነው" ብሎ ሲያምን ፥ ያመነውንም ሲናገር ኖሯል።
በ5 ደቂቃ ተነቦ የሚያልቅ ቃለመጠይቅ ሳያነቡ ለወቀሳ አደባባይ መውጣት ምን ይባላል?

ልደቱ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ የተናገረው ያስቆጣቸውም አሉ።

ከእውነት ጋር መደባደብ ካልፈለግን ፥ በተረት ራሳችንን መሸንገል ካልወደድን በቀር የተናገረው ሐቅ ነው።

እንደ ህዝብ ለራሳችን የተጋነነ ግምት አለን። ፃድቃን እንደሆንን ማመን ይቃጣናል። እግዚአብሔር ከሌላው በተለየ በሚያደላላት ሐገር እንደሚኖሩ የሚያምኑ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው ቀላል አይሉም። ግን ደግሞ እውነታው ሌላ ነው።

መራራውን እውነት መቀበል ይኖርብናል። በሽታውን የካደ አይድንም። ከእውነት እየተጣሉ ለውጥ አይመጣም። በብዙ ኋላቀር አስተሳሰብ የተተበተብን ነን። እንደ ህዝብ ብዙ ጎዶሎዎች አሉብን። በዚህ ወቅት ከተረት ይልቅ የሚጠቅመን መራሩን እውነት መጋፈጥ ብቻ ነው።
የሸሸነው እውነት ፥ ልንቀበለው ያልወደድነው ጥፋታችን ያደቀናል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ምናብ ወለድ መመፃደቃችን ወቅት እየጠበቀ ይቀጣናል።

ሐገር መውደድ ምንድነው?

ሐገር መውደድ ማለት ከእውነት ጋር ፀብ መግጠም ማለት አይደለም። እንደ ሐገር ያለብንን ሕፀፅ መካድ ፥ እንደ ህዝብ ያለብንን ደካማ ጎን አለመቀበል ሐገር መውደድ አይደለም። ይህ ተራ አድርባይነት ወይም ደግሞ አጓጉል ቅዠታምነት ነው!

የህዝብን ስህተት እየነቀሰ የሚተች ሰው ህዝብን የሚንቅ አሊያም ከማንም እበልጣለሁ ባይ አይደለም።

"ህዝብ አይወቀስም" የሚል ደፋር ሰው ዛሬም ይኖር ይሆናል። ግን ደግሞ ህዝብ በደንብ ይወቀሳል። "ህዝብ አይሳሳትም" የሚለው አባባል ለጆሮ ደስ ይል ይሆናል። ግን ደግሞ ፈርጠም ያለ ስህተት ነው። ህዝብ በደንብ ይሳሳታል። ሲሳሳት ደግሞ ይወቀሳል።

ለማንኛውም ልደቱ አያሌው 5 መፅሐፎች እና ከ30 በላይ መጣጥፎችን ፅፏል። የፖሊሲ አማራጭ ፥ የሕገመንግስት ማሻሻያ ፥ወዘተ ፅፏል። ስለሆነም ፖለቲካዊ ሃሳቦቹን አንብቦ መተቸት ለሐገር ፖለቲካ ጭምር ጥቅም ስላለው እሱ ላይ ማተኮሩ ይሻላል።


@Tfanos
👍4
የጤና ባለሞያዎችን መደገፍ ለምን....
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ዜጎች የሃኪሞችን ጥያቄ መደገፍ የውዴታ ግዴታችን ነው።

ላስረዳ

ምክኒያት አንድ፥

እውቀት ሊከበር ይገባል። ታታሪነት ተገቢውን እውቅና ማግኘት ይኖርበታል። ታታሪዎች ሲገፋ፥ አዋቂዎች ሲዋረዱ መጥፎ መልእክት ይተላለፋል።

አንድ ዶክተር የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ በብዙ መትጋት ግዴታው ነው። ደግሞም ጎበዝ ተማሪ መሆን ይጠበቅበታል። እኩዮቹ በሸነና ሲሉ አንገቱን ቀብሮ ለማንበብ ይገደዳል። ከዚህ ሁሉ በኋላ መሰረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ሲሆን ሌሎች እውቀትን እንዲንቁ ይገደዳሉ።

"ጠንክሬ ብማር ፥ ታታሪ ብሆን ፥ ሰቃይ ተማሪ ሆኜ ብገኝ ምን ጥቅም?" የሚል ትውልድ ይበዛል። ትምህርትን የማያከብር ዜጋ በበዛ ቁጥር የሀገር ነገ ፥ የማህበረሰብ እጣ ፋንታ ይኮላሻል።

የሃኪሞችን ጥያቄ መደገፍ ለእውቀት እና ታታሪነት ተገቢውን ክብር መስጠት ነው

ምክኒያት ሁለት

"የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመፅ በሮች ይከፈታሉ" ይባላል። እንዳለመታደል የሐገራችን ፖለቲካ ከአመፅ የተጋባ ነው። የመብት ጥያቄዎች በአመፅ ይታጀባሉ። መንግስት ሃይል ካልተጠቀመ ሐገር ያስተዳደረ አይመስለውም። ይህ ዋጋ ሲያስከፍለን ኖሯል።

የጤና ባለሞያዎች የመብት ጥያቄ አንስተዋል። ጥያቄያቸው እጅግ ተገቢ ነው። ተገቢ ብቻ ሳይሆን እስከአሁን አለመመለሱ እንደ ሐገር ያሳፍራል። ሐኪሞች ተገቢ ጥያቄ በማንሳት ብቻ አልተገደቡም። ጥያቄያቸውን ያቀረቡበት መንገድ ስልጡን ነው። ይህ ብዙ ያስተምራል።

ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ፥ በብዙ የሚያስፈልገን ባህል ነው። ሃኪሞች የተከተሉት መንገድ አረዓያነት ያለው በመሆኑ የተነሳ ከጎናቸው መቆም ይኖርብናል።

ምክኒያት ሦስት፥

ከአጀንዳ ፖለቲካ ጋር ፀበኞች ነን። እንደ ህዝብ መሰረታዊ የሆኑ አጀንዳዎች ቢኖሩንም ትኩረታችን ሌላ ነው። በብሔር እና በሃይማኖት ተከፋፍለናል። ከጋራ ጉዳያችን ይልቅ ከፋፋይ ነገሮች ይስቡናል።

በቡድን መከፋፈላችን ሐገራዊ አንድነትን ጭምር ለአደጋ የሚዳርግ ሆኗል።

ዶክተሮች ድጋሚ አርዓያ ሆነውናል።

ብሔር ዘለል መተባበር ፥ ሃይማኖት ተሻጋሪ ግኑኝነት ማድረግ እንደሚቻል አሳይተውናል። የጋራ አጀንዳን በሃይማኖት አሊያም በብሔር ሳይከፋፈሉ ማቅረብ እንደሚቻል አስተምረውናል።

ፖለቲካችን አጀንዳ ተኮር እንዲሆን ፥ የመብት ጥያቄዎቻችንም በመተባበር መከወን እንደሚችል ላሳዩት አረዓነት ሲባል ሊደገፉ ይገባል።

ምክኒያት አራት፥

"ትውልዱ ሐገሩን አይወድም" የሚል ወቀሳ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ይሰነዘራል። ሐገር መውደድ የፖሊሲ ውጤት ጭምር ነው።

ዜጋ ሐገሩን እንዲጠላ ከሚያደርጉት የተለያዩ ምክኒያቶች መካከል አንዱ በሐገር የመገፋት ስሜት ነው። "ያገለገልኳት ሐገር ገፍታኛለች" ብሎ የሚያስብ ሰው በልቡ ጥላቻ ሊወለድበት ይችላል። በእርግጥ አንዳንድ ሰው ሐገር እና መንግስትን ለዩ የሚል ክርክር እንደሚገጥም ይገባኛል። ነገር ግን ይህ ንግግር መሬት ላይ ያለውን እውነታ አይቀይረውም።

ሰዎች በአገዛዝ ሲበደሉ ፥ ሐገር አገልግለው ሲያበቁ ተገቢውን ክብር ሳያገኙ ሲቀሩ ለሐገራቸው ያላቸው ፍቅር ይሸረሸራል። ይባስ ብሎ ለሌላው መጥፎ ምሳሌ ይሆናል። ሌሎች ሰዎች ጭምር "ሐገራችንን ብናገለግል አንመሰገንም" የሚል አደገኛ ስሜት ይፈጥርባቸዋል። ይህ ስሜት ሲጎለብት የገዛ ሐገራቸውን የሚመዘብሩ ፥ ለወገናቸው ርህራሄ የሌላቸው ሰዎች ይበዛሉ። ይህ ምን እንደሚያስከትል ማብራራት አይጠበቅብኝም።

ለሃኪሞች ጥያቄ ተገቢውን ድጋፍ ለመስጠት ከምንገደድበት ምክኒያቶች መካከል አንዱ ብሔራዊ ስሜትን መጠበቅ ነው። ሃኪሞች ለህዝብ ላደረጉት አገልግሎት የሚመጥን ክፍያ ይሰጣቸው ማለት ዜጎች የሐገር ፍቅር ስሜታቸው እንዳይሸረሸር መታገል ጭምር ነው።

ምክኒያት አምስት፥

የነገ መብታችን በዛሬው የሃኪሞች ጥያቄ ውስጥ ተሸሽጓል። ዛሬ የጤና ባለሞያዎች ያቀረቡትን ተገቢ ጥያቄ መንግስት በሃይል ሊደፈጥጠው ይችላል። "ዶክተሮች እንደጀመሩት እነሱው ይወጡት" ብለን ዝም ብንል እና ጥያቄው በመንግሥት ቢደፈጠጥ የነገ እጣፈንታችን ለከፋ አደጋ ይጋለጣል።

ነገም በተራችን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ብናነሳ የድፍጠጣ ትምህርት ይሆናል። "ትላንት ዶክተሮችን እንደደፈጠጥኩት ዛሬም ሌላውን እደፈጥጣለሁ" የሚል መንግስታዊ ትምክህት ይፈጠራል።

ይህ ነገረ ረዘመ፥ እዚህጋ እናብቃ።

ከጤና ባለሞያች ጥያቄ ጋር መተባበር የውዴታ ግዴታችን ነው!


@Tfanos
19
2025/10/24 03:30:00
Back to Top
HTML Embed Code: