Telegram Web Link
"የዮናታን ወንጌል"
* * *

ዛሬ የኢየሱስ ስም መነገጃ ሆኗል። መፅሐፍ ቅዱስን እየጠቀሱ ከመፅሐፍ ቅዱሱ ተፃሪ የሚሆኑ እልፍ ናቸው። በኢየሱስ ስም ፀረ ኢየሱስ ድርጊት ይከወናል። ኢየሱስን በቤቱ ባይተዋር ማድረግ የሚፈልጉቱ ቁጥር የሌቸውም።

ዮናታን ድሆችን በአደባባይ ተሳድቧል። ድህነትን ሳይሆን ደሃን ተሳድቧል። ድሆች ጥቁር ጉንዳኖች እንደሆኑ መናገሩ ሳያንስ ለቃ ቃሚ ብሏል።

ዮናታን ጨዋ እንዲሆን አይጠበቅበትም። "የእግዚአብሔርን ቃል እስብካለሁ እያልክ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ለምን ትድባለህ?" ብሎ መጠየቅ ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው።

ዮናታንና ቢጤዎቹ ድሃን ሲንቁ ልክ የላቸውም። ድሃን ለመፀየፍ የሄዱበትን ርቀት የገዛ ነውራቸውን አያዩበትም።
"ድሃ..." እያሉ ሲሳደቡ በጥረታቸው ገንዘብ ያገኙ ፥ በልፋታቸው የሀብት ማማ የወጡ ይመስላል። ዳሩ ግን የስኬታቸው ምንጭ ግልፅ ውንብድና ነው።

ዮናታን አክሊሉ እና መሰሎቹ የህዝብን ስስ ብልት ያውቁታል። የህዝብን ደካማ ጎን በመጠቀም አጭበርብረው ባለጠጋ ሆኑ። ሌላ ተአምር የለውም። ሌላውን አጭበርብሮ ገንዘብ ያከማቸ ሰው ድሃን ሲፀየፍ እንደማየት የሚያሳፍር ምን አለ?

ዶክተር ደረጀ ከበደ "የአምልኮ ነፃነት" የሚል መዝሙር አለው። "የኢየሱስ ስም ለንግድ ጨረታ ወጣበት" የምትል ስንኝ በመዝሙሩ ውስጥ ተካቷል። የዛሬ ነቢያት መንገድ ይኸው ነው። የኢየሱስን ስም መነገጃ አድርገው ገንዘብን አከማቹ። ሌላ ተአምር የለም!

የተማርነው ወንጌል ሌላ ነው። የሰማነው መፅሐፍ ቅዱስ ሌላ ነው። ዛሬ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጭምር እያመፁ በአደባባይ የሚያቀረሹ ነውረኞች ጊዜ ይቀጣቸው ይሆናል። ግን ደግሞ እኒህን ነውረኞች መቃወም በተለይ ከፕሮቴስታንቱ የሚጠበቅ የቤት ስራ ነው።

"እኛ የምናውቀው ወንጌል ይህ አይደለም። ወንጌላችን ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ ገንዘብ አይደለም" ማለት ከፕሮቴስታንቱ ማህበረሰብ ይጠበቃል።

"ንፁህ ወንጌል እንዳንሰብክ መሰናክል አትሁኑ"ማለት ከወንጌላውያን አማኞች ይጠበቃል።

@Tfanos
17👍4😁2
9ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ። በእለቱ የከሰአት ነበር ፈረቃችን። ለትምህርት ቤት እየተዘገጃጀሁ ሬዲዮ እሰማለሁ። ያን እለት እሰማ የነበረው ኤፍ ኤም አዲስን ነበር። የእለቱ እንግዳ ደግሞ ጌታሁን ሄራሞ ይባላል።

ጌታሁን ሄራሞ ስለ ቀለም ሳይንስ ሲተነትን ሰምቼው አጃዒብ አልኹ። እንዴት ያለ ጉደኛ ሰው ነው አልኹ። ስሙን ሲነር ላይን ደብተሬ ላይ ፃፍኩት። "ጌታሁን ሄራሞ" ብዬ ፃፍኩ።

ሲኒር ላይ ማስታሻ ደብተሮች ነበሩኝ። (ለስብሰባ ወቅት የሚሰጠው ደብተር ማለቴ ነው) ሬዲዮ ስሰማ ፥ መፅሔት ሳነብ ፥ ከሰዎችጋ ሳወራ... የሰማሁትን አዲስ ጉዳይ በዛ ማስታወሻ እፅፋለሁ። ያን ቀን የጌታሁንን እውቀት እና ጌታሁንን በማስታወሻዬ ፃፍኩት።

እንደተለመደው ለሰዎች ስለጌታሁን እውቀት አወራኹ። (እስከዛሬ ድረስ የሚከተለኝ አመል አለ። የሆነ ሰውን ከወደድኹት በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች ስለዛ ሰው አወራለሁ)

አንዲት ልጅ "ጌታሁን ሄራሞን የማውቀው ይመስለኛል። አባቴ ይወደዋል። መዝሙር አለው" አለችኝ። ተጠራጠርኳት። በልቤ እውነቷን እንዲሆን ተመኝቼ አለፍኹ።

አንድ ቀን መንፈሳዊ መፅሔት ሳገላብጥ "ጌታሁን ሄራሞ" የሚል ስም አየሁ። ተስገብግቤ አነበብኹት። ከመጀመሪያው በላይ ወደድኹት። "ይህ ሰውዬ በጣም ደስ ይላል" አልኹ።

ሌላ ቀን፥

ኳየር ነበርኹኝ። የቸርች ዘማሪ ነበርኹ። ድምፄ ለመዝሙር ባይሆንም በህብረት እንዘምር ነበር። የመዝሙር ግጥምና ዜማ እፅፍ ነበር። ኳየር መሄዱ ደስ ያሰኘኝ ነበር። የኳዬር ልጆች መንፈሳዊ ያልሆኑ መፅሐፍትን ስለማነብ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ስለሚጠይቁኝ የእውቀት የበላይነት ይሰማኝ ነበር። ለኳዬሬ ልጆች የጌታሁንን እውቀት አጣቅሼ ነገርኳቸው። "እሱ እኮ በጌታ ነው" አሉ። ደስ አላቸው። ደስ አለኝ።

የኳዬራችን ሰብሳቢ ጥበቡ አሰፋ ይባላል። መፅሐፍ አሳየኝ። "የለማኙ ሎጂክ" ይላል ርዕሱ። "የምትወደው ሰውዬ መፅሐፍ ነው" አለኝ። የጌታሁን ሄራሞ መፅሐፍ ነው። መፅሐፉን ሳነብ ከቀደመው ይበልጥ ወደድኹት።

የዛሬ 6 አመት አከባቢ ድንገት ጌታሁን ትዝ አለኝ። "ምናልባት ፌስቡክ ይጠቀም ይሆናል" ብዬ አሰብኹ። ፌስቡክ ላይ ሳገኘው ደስ አለኝ። የጓደኝነት ጥያቄ አቀረብኹ። ተቀበለኝ። ሲቀበለኝ ኩራት ተሰማኝ።

ከእለታት በአንዱ ከቸርች ልጆች ጋር ስለ ፌስቡክ አወራን። "ፌስቡክ ላይ ብዙ ምርጥ ሰዎች አሉ" አልኹኝ። ማስረጃ እንዲሆነኝ ስለ ጌታሁን ሄራሞ አወራሁ።

ፍቅሬ ቡንጤ የሚባል ሰው ከጌታሁን ጋር ተምሬያለሁ አለን። ፍቅሬ ቡንጤ የሻሸመኔ ሸዋበር ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ሰዎች ታውቁታላችሁ አይደል? አዎ እሱ ነው።

ፍቅሬ ከጌታሁን ጋር መማሩን ነገረኝ።
"ምን አይነት ተማሪ ነበር" አልኩት። "ጎበዝ ተማሪ አልነበረም" አለኝ። ግር አለኝ። "ጌታሁን ጎበዝ አልነበረም?" አልኩት።

"ጎበዝ አልነበረም። እሱ ከጎበዞች በላይ ነው። የእሱን ጉብዝና በቃል አይገለጥም። በሁሉም ትምህርት የላቀ ተማሪ ነበር። ማንም የማይሰተካከለው ሰው ነው። እንደሱ አይነት አእምሮ ያለው ሰው አይቼ አላውቅም" አለኝ

"ደግሞ ጉብዝናው በትምህርት ብቻ አይደለም። ኳስ ሲጫወትም ጎበዝ ነው። የእጅ ኳስም ይጫወት ነበር። ደግሞ በጣም ትሁት ነበር" አለን።

መቼስ "ታድሎ" ከማለት ውጭ ምን ይባላል?

እኔ ጌታሁን ካለው አቅም ሩቡ ቢኖረኝ ትሁት አልሆንም። በትዕቢት አገር አተራምስ ነበር።

በኢኮኖሚ ተሳክቶለታል። እውቀቱን ነው ወደ ገንዘብ የመነዘረው። ይህ በጣም ጥቂቶች ብቻ ያሳኩት ነገር ነው።

አዋቂ ነው ሲባል የእውነት አዋቂ ነው። ፍቅሬ ቡንጤ እንደመሰከረለት ከልጅነቱ ጀምሮ ሰቃይ ተማሪ ነበር።

ሰው ሲያከብር ከልቡ ነው። ታናናሾቹን ጭምር ያከብራል። ወደ ታናናሾቹ ዝቅ ማለት ያውቅበታል።

ከልቡ ትሁት ነው።

መንፈሳዊ ነው።

እኔ ጉራ ከምነፋባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ "ከጌታሁን ጋር እተዋወቃለሁ" የሚል ነው። በጣም ለብዙ ሰዎች ከጌታሁን ጋር ምሳ በልተን እንደምናውቅ አውርቻለሁ። ሲቪ በሉት።

ለመጀመሪያ ጊዜ ስሙን በሬዲዮ ከሰማሁበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሳከብረው ኖሬያለሁ።

መከበርም ፥ መወደድም ፥ መደነቅም እኩል የሚገባው ሰው ነው። ሶስቱንም እኩል የምንሰጠው በጣም ለጥቂት ሰዎች ነው። ከነኚያ መካከል አንዱ ጌታሁን ሄራሞ ነው


@Tfanos
👍62
ጊዜን ማስተዳደር
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ነብስ ካወቅንበት ጀምሮ ያለውን ዘመን እናስላው። ጊዜው እንደሸማኔ መወርወሪያ ይሮጣል። በአይን ጥቅሻ ዘመን ይከንፋል። እድሜ ይጣደፋል።

ቅርብ ጊዜ አይደል ልጆች የነበርን?

ጊዜን እንዳይባክን የሚያደርገው ምን ይሆን?

ጊዜ የላቀው ሀብት ነው። አያያዙን ላወቁበት በስኬት የሚመነዘር፥ ላላወቁበት የነገ ውድቀትን የሚያዋልድ ነው።... ጊዜን እንዴት እናስተዳድር?

ርዕሱን የዘነጋሁት ፀሐፊ ራስን ማስተዳደር የሚል መፅሐፍ አለው። ጊዜ አጠቃቀምን በተመለከተ ጠቃሚ ትምህርት አስፍሮ አንብቤ ነበር። (መፅሐፉን 2010 አከባቢ ነው ያነበብኩት)

ጊዜያችንን የሚበለው ድርጊታችን ነው። ድርጊታችንን ደግሞ በአራት መደብ መክፈል እንችላለን።

በወፍ በረር እንያቸው።

ሀ፥ አጣዳፊ ያልሆነ ፥ ደግሞም የማያስፈልግ።
ይህን በተመከተ ማብራሪያ ያስፈልግ ይሆን? አንድ ጉዳይ አስፈላጊም አስቸኳይም ካልሆነ ጉልበታችንን ልናባክንት እንደማይገባ ነጋሪ አያስፈልገንም። ይልቅ ወደ ቀጣዩ..

ለ፥ አጣዳፊ የሚመስል ዳሩ ግን የማያስፈልግ

እንዲህ ያለው ነገር የብዙ ወጣቶችን ጉልበት ይበላል። ጊዜን ያበክናል። ሱስ አይነተኛው ምሳሌ ነው። አስፈላጊነቱ ምንም ነው። ነገር ግን ያጣድፋል፥ ያቻኩላል። "አሁን ካልሆነ" ይላል። ለእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው እድሜን ያበክናል። እርጅናን የምሬት ያደርጋል።

ሐ፥ አጣዳፊ ደግሞም አስፈላጊ

ይህች ጉዳይ ሁሉንም የምትሸውድ ናት። ጊዜን ለማስተዳደር የላቀው መንገድ እንዲህ ባለው ጉዳይ ላይ ማተኮር ይመስላል። አስገራሚው ነገር ግን አጣዳፊ ጉዳዮች ጊዜን አባካኝ መሆናቸው ነው።

አጣዳፊ እና አስቸኳይ ጉዳዮች በእለት ተዕለት ጉዳዮች ቢዚ ያደርጉናል። በጥቃቅን ነገሮች እንድንወጠር ያስገድዱናል። ጊዜያችንን የሩጫ ያደርጉታል። እንደባከንን ዘመናችንን ሊጨርሱት ይችላሉ።

መ፥ አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን የሚያስፈልግ

በዚህ ነጥብ ላይ ማተኮር የሚችሉ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። አስተዋዮች ዋነኛ ትኩረታቸው አጣዳፊ ያልሆኑ ነገር ግን አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ነው። ይህ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል። ደግሞም ስኬታማ ያደርጋቸዋል።

የመጨረሻዎቹን ሁለት ነጥቦች (ሐ እና መ) ግልፅ የሚያደርግ ምሳሌ እናምጣ

በትምህርት መጀመሪያ ለፈተና መዘጋጀት አስፈላጊ ነገር ነው። ነገር ግን አጣዳፊ አይደለም። በአመቱ መጨረሻ ላይ ለሚደረግ ፈተና መስከረም ላይ መዘጋጀት አስቸኳይ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን አስፈላጊ ነው። (አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊ)

በአመቱ መጨረሻ ለፈተና መዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ደግሞም አጣዳፊ ነው። (አስፈላጊና አጣዳፊ)

ከላይ እንዳነሳነው ለስኬት የሚረዳው እና የተሻለ የጊዜ መጠቀሚያ መንገድ አጣዳፊ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊው ላይ ማተኮር ነው።

የላቀው ተማሪ በአመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለፈተና ይዘጋጃል። የፈተናው ወቅት ሲደርስ ለክለሳ የሚሆን የተትረፈረፈ ጊዜ ይኖረዋል። ራሱን ጫና ውስጥ አይከትም። ተረጋግቶ ለፈተና ይቀመጣል።

ፈተና ሲደርስ የሚያጠናውስ? ሩጫ ይበዛበታል። ለክለሳ የሚሆይ ጊዜ አይኖረውም። ውጥረት ውስጥ ስለሚገባ መረጋጋት ሊቸገር ይችላል።

(በእርግጥ ልዩ ሁኔታዎች ከግምት ይገባሉ)

ብዙ ሰው አጣዳፊ እና አስፈላጊ በሆነው ጉዳይ ላይ ሲዳክር ጊዜ ያመልጠዋል። አጣዳፊ እና አስፈላጊ ነገሮች ደግሞ ያደረ የቤት ስራ ውጤት የመሆን እድላቸው ቀላል አይደለም። አስፈላጊ ነገር ግን የማያስቸኩሉ በሆኑበት ወቅት ላይ "ጊዜ አለኝ" በሚል መዘናጋት ሳይሰሩ ይቀራሉ። በመጨረሻም ሩጫ ያስከትላሉ።

ተጨማሪ ምሳሌ፥

ስፖርት መስራት ለጤና አስፈላጊ ነው። ግን ደግሞ አጣዳፊ አይደለም።

አንድ ወጣት ዛሬ ስፖርት ሳይሰራ ቢቀር በማግስቱ ደም ግፊት አይዘውም። ስለዚህ አስቸኳይ አይደለም።

አንድ ወጣት ስፖርት ሳይሰራ ፥ እንቅስቃሴ ሳያደርግ እድሜውን ቢገፋ እና ለአላስፈላጊ ውፍረት ቢዳረግስ? ከዛጋር ተያይዞ የጤና መታወክ ቢከተልስ? ያኔ ስፖርት መስራት አጣዳፊም አስፈላጊም ጭምር ይሆናል ማለት ነው። ብዙ ጫና ተከትሎ ይመጣል። ምናልባትም ኢኮኖሚ ይናጋል።

ወጣቱ ቀድሞ ስፖርት የሚሰራ ቢሆን ቀጥሎ የሚመጣውን ቀድሞ ያግደዋል። ጊዜውም በአግባቡ ተጠቀመ ማለትም አይደል?

የፃፍኩት ግልፅ ነው? ዝም ብዬ ዘበዘብኩ ወይስ ሃሳቤን በትክክል ገለፅሁ?

ማለት የፈለግሁት በአጭሩ ልድገመው።

ጥሩ ጊዜ ማስተዳደሪያው መንገድ አስቸዃይ እና አስፈላጊ የሆነው ላይ ማተኮር አይደለም። የተሻለው መንገድ አስፈላጊ ነገር ግን አስቸኳይ ያልሆነውን በአግባቡ መስራት ነው። ያኔ አስፈላጊ እና አጣዳፊ በሆኑ ነገሮች የመዳከር እድል ይቀንሳል


@Tfanos
👍82
መንጌ፥ ሐገር ወዳዱ...
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም ልደታቸው ተከበረ። "ቆራጡ መሪ" ተብለው ሲወደሱ ከርመው ሐገር ጥለው የሸሹት መንጌ ልደታቸው ተከበረ።

ስለመንግሥቱ ሲወራ "ሐገር ወዳዱ" ይባላል። ሐገር ምንድነው? የመንግስቱን ስርኣት የሚያሳዩ ጥቂት ምሳሌዎች እንምዘዝ። (ሐገር ወዳድ ተብዬው ሰው ሐገር አፍራሽ ስርኣት መገንባቱን በጥቂት ምሳሌ...

1፥ መንግስቱ ወልዴ የተባለ አንድ መፅሐፍ ነጋዴ ነበር። መንግስትን የሚቃወም ፅሁፎች ትበትናለህ ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ። ቀጥሎ አንድ አብዮት ጠባቂ ከላይ እስከታች በጋዜጣ አስጠቅለለው። ከዛም ነዳጅ አርከፍክፎ አቃጠለው፡፡ አዎን ሰው በእሳት ተቃጥሎ ተገደለ። መንግስቱ ሀይለማርያም መራሹን መንግስት የሚቃወም ፅሁፍ ይበትናል ስለተባለ ይህን ቅጣት ተቀበለ

2፥ አብነት ሰፈር አከባቢ አንድ አስር አለቃ እንደልቡ ይፈነጭ ነበር፡፡ አካም ቡልቲ በሚል ቅፅል ስም የሚጠራ ሰውን ገደለው። በመግደል አላበቃም (በወቅቱ ደርግን ይቀወማሉ የሚባሉ ሰዎችን መግደል ተአምር አይደለም)። የሟች አስከሬን ቤተሰቦቹ ደጅ ላይ ተቀበረ። መውጫ መግቢያ በራቸው ላይ የልጃቸው አስከሬን ተቀበረ! ከዚህም የተነሳ የሟች አባት አበደ፡፡ ጨርቁን ጣለ፡፡ የአእምሮ ህመም ገጠመው
(ሁለቱም ታሪኮች ማዕቀብ በሚለው የእንዳለጌታ መፅሐፍ ላይ ተካተዋል-

3፥ ሻለቃ መላኩ ተፈራ ከዝነኛ የደርግ ሹማምንት መካከል አንዱ ነው። የስመጥርነቱ መንስኤ የአመራር ብቃቱ ሳይሆን የጭካኔ ደረጃው ነው።
ጎንደርን ሲያስተዳድር የጭካኔ መዋቅር ዘረጋ። ልዩ እስር ቤት አቋቋመ፥ ተጠርጣሪዎች የሚሰቃዩበት የምርመራ ክፍል አደራጀ፡፡
ደግሞ ከእርሱ ትዕዛዝን የሚቀበል መቺ ኃይል መሰረተ፡፡

'ፀረ-አብዮት' ተብለው የሚፈረጁ ሰዎች ቅጣታቸው ግልፅ ነው። ይገደላሉ! በቂ የወንጀል ማስረጃ እንደሌለባቸው እየታወቀ እንኳ ያለ ርህራሄ ይገደላሉ።

የገጠር ነዋሪዎች ወደ ከተማ ያለ ልዩ ፈቃድ ወደ ከተማ እንዳይገቡ እገዳ የጣለ ሰው ነው።

'ደርግን ተቃውመዋል' የተባሉ ዜጎችን ሲለው 'በእስራት ይቀጡ' ይላል። ካሻው የጅራፍ ግርፋትን ይወስናል። ሲፈልግ ደግሞ በስቅላት ያስገድላል። ስቅላት ሲሰለቸው በጥይት ያስደበድባል።

ሻለቃው ጭካኔው ድንበር የለሽ ቢሆንም የደርግ መንግስት "ቆራጥ፥ ታጋይ ፥ አብዮተኛ ወዘተ " በማለት በ1980 አ.ም ሸልሞታል። ሽልማቱን የቸረው ደግሞ መንግስቱ ሃይለማርያም ነበር። (ሽልማቱ ለጭካኔህ አመሰግናለሁ ማለት መሆኑ ነው)

4፥ በዘመነ-ደርግ ሕዳር 14 ቀን 1967 አ.ም በተለምዶ 60ዎቹ የሚባሉት እና በአንድ ጀንበር የተገደሉ ሰዎች አሉ።

ደርግ ያለ በቂ ምክኒያት ሰዎችን ከመረሸኑ በፊት ስለ-ሰዎቹ እጣ ፈንታ ስሜት የተጫነው ውይይት ያደረገ ሲሆን መገደላቸውን ብርሃኑ ባየህ ብቻ መቃወሙን ፍቅረስላሴ ወግደረስ ፅፏል። ብርሃኑ ባየህ "ግድ የላችሁም ሕጋዊ መንገድ እንጓዝ፥ ፍርድ ቤት ይወስን፥ ሕግ ነፃ ካደረገ ነፃ ይሆኑ፥ ከቀጣቸው ይቀጡ። እኛ ግን ስልጣናችንን ተጠቅመን መወሰን የለብንም" ብሎ የነበረ ቢሆንም ሰሚ አላገኘም። ሰዎቹ ተረሸኑ።

ጎህ መፅሔት ቆየት ባለ እትሙ ያልተለመደ ጉዳይ ስለሟቾቹ አስነብቦ ነበር። አስር አለቃ ደሳለኝ 'ሰዎቹን የገደልኩት እኔ ነኝ' ካለ በኋላ ዝርዝሩን አብራርቷል።
ጓድ መንግስቱ "ልዩ ተልእኮ አለ፥ ይህን በአግባቡ ከፈፀማችሁ ሽልማት አላችሁ ካለን በኋላ እኔና ጓደኛዬ ለተልእኮ ተሰማራን" ብሏል። መንግስቱ ሰዎቹ በቀጥታ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲገደሉ አስደረገ።

"ሐገር ወዳዱ" የሚባለው መንግስቱ በስልጣን ዘመኑ አንድ ትውልድ ፈጅቷል። ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣቶችን ፥ የሐገር ባለ ውለታ አባቶችን ፥ ባለ ተስፋ ተማሪዎችን በመደዳ ያስገደለ ሰው ነው።

ሐገር መውደድ ምንድነው?

አንባገነኖችን የማወደስ ባህል እስካለ ድረስ እስመጨረሻው ከጭቆና ነፃ አንወጣም!


@Tfanos
@Tfanos
👍111👎1
የዛሬ ስምንት ዓመት አከባቢ ሻሸመኔ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተሰጠ። ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ነው የስልጠናው አዘጋጅ። ጣምራ "ዘመነ-ሃሊዮ" በተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራሙ ለሚሳተፉ ልጆች ፥ በኪነጥበብ ውስጥ ተሳትፎ ላላቸው ፥ የጋዜጠኝነት አቅሙ ላላቸው ወጣቶች ነበር ስልጠናውን ያዘጋጀው። (ስለጣምራ በተለይም ስለ ስራ አስኪያጁ ብሩክ ሌላ ጊዜ እፅፋለሁ)

አሰልጣኛችን ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ነበር። አዳነ ጥያቄ ጠየቀ። "የምትወዱት ጋዜጠኛ ማን ነው?" አለ። ሁሉም የሚወደውን ስም ጠቀሰ። የመአዛ ብሩ፥ የመንሱር አብዱልቀኒ እና የደረጀ ሀይሌ ስም በደንብ ተጠቀሰ። የኔ ተራ ደረሰ። አልዓዛር አስግዶም አልኩ። ለአዳነ አረጋ ቃል በቃል "ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጋዜጠኛ የሚባለው አልዓዛር ነው " አልኩት።

አዳነ ስለ አልዓዛር ነገረን። "በጣም ትሁት ሰው ነው። ስራውን ይወዳል። ያነባል። ጠቅላላ እውቀቱ የሚገርም ነው። ስለየትኛውም ጉዳይ በእኩል አቅም ያስረዳል" አለ። የአልዓዛርን ስልክ ሰጠኝ። በስንተኛው ቀን ለአሊዝ ደውዬለት ጥቂት አወራን። (ጥቂት ሲባል ሰላሳ ደቂቃ ገደማ ነው😀)
የደወልኩለት ቀን ስፖርት 365 ላይ ከአዩ ወልደሚካኤል ጋር በቬንገር ጉዳይ ተጨቃጭቀው ነበር። አሊዝ በጣም ስሜታዊ ሲሆን ያስታውቅበት ነበር። ለቬንገር ተገቢው ክብር አለመሰጠቱ አበሳጭቶት ነበር።

ከአእምሮዬ የማይጠፉ የአልዓዛር ስራዎች አሉ።

"ፋና ዳሰሳ" ከምወዳቸው የሬዲዮ ፕሮግራሞች መካከል ነው። በተለይ ተስፋዬ አለነ የሚሰራቸው ዳሰሳዎች ደስ ይሉኝ ነበር።አርብ በደረሰ ቁጥር በጉጉት የፋናን ዳሰሳ እሰማለሁ። ማጀቢያው ጭምር ደስ ይለኛል። አንድ ቀን አልዓዛር ዳሰሳ ሰራ። ከዛ በፊት በዳሰሳ ሰምቼው አላውቅም። የሰራው ስለ ፊፋ ቅሌት ነበር። ገረመኝ። የርዕሰ ጉዳይ ምርጫው አስገረመኝ። አለም አቀፍ ፖለቲካ በሚተነተንበት ፕሮግራም የእግርኳስን ፖለቲካ በውብ አቀራረብ ተነተነው። እግር ኳስ ከእግርኳስም በላይ እንደሆነ አሳየ። ከዛን ጊዜ በኋላ የአሊዝን ዳሰሳ በጉጉት የማደምጥ ሆንኹ።

ባርሳ ከ ፒ ኤስጂ ጋር ተጫውቶ ውጤት የቀለበሰበትን ቀን የትኛውም የእግር ኳስ ተመልካች አይዘነጋውም። ከጨዋታው እኩል የማይዘነጋ ፕሮግራም አልዓዛር ሰርቷል።

የፕሮግራሙ መግቢያ.. 👇

"ሰው እሱ ማንም ቢሆን 22 ተጫዋቾች ቅሪላ የሚላፉበት ዋዘኛ ጨዋታ ነው ቢላችሁ አትስሙ፥ ስራ ፈቶች ዝርጉን አረንጓዴ ንጣፍ በሺ ስፍር በከንቱ ይከቡታል ቢሉ እሱም እውነት አይደለም። ቢሊየን ሰዎች በሁሉም የኑሮ መደብ ያሉ እግርኳስን አቅልን በመሳት ወሰን ሆነው ቢወዱ፥ በሃሴት እና በስብራት ጊዜ ለምን የእንባ ዶፍ እንደሚያዘንቡ ግራ ቢገባቸው የትላንቱን የጨዋታ ምስል ስጧቸው።.... እኔ እግርኳስን ስለትላንቱ ምሽት እወዳለሁ" ብሎ ይጀምራል ዘገባው። ይህ ዘገባ ከተሰራ ሰባት ወይ ስምንት አመት ቢሆነውም አይረሴ የአሊዝ ስራዎች መካከል ነው።

ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን ሲመጣ (የዛሬ 9 አመት) አልዓዛር በፋና መፅሔት ዳሰሳ ሰርቷል። ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ አልዓዛር በ90 ደቂቃ እና በ120 ደቂቃ ዝግጅቶች እንጂ በምሳ ሰአት ዜና ሰምቼው አላውቅም ነበር። ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠበት ቀን ልዩ ክስተት ነበር። በዛ ልዩ ክስተት አልዓዛር የምሳ ሰአት ትንታኔ ሰራ። (ምናልባት ለልዩ ቀን ልዩ ሰው ተመርጦ ይሆናል)

በፋና ኤፍ ኤም ስፖርት 365 ን ረጅም ጊዜ እከታተል ነበር። ሁሴን አብዱልቀኒ ፥ አዩ ወልደሚካኤል ፥ ዳዊት ንጉሴ በጋራ ፕሮግራሙን ያደምቁታል።... በሂደት ግን ሁለቱ አዘጋጆች ከሐገር ወጡ። ሁሴን እና ዳዊት ከፕሮግራሙ ጎደሉ። ያኔ ሁለቱን የሚተካ አንድ ሰው ተከሰተ... አልዓዛር አስግዶም!

አልዓዛር በቀለም ከሁለቱም የተለየ ሆኖ ሳለ ሁለቱ የፈጠሩትን ጉድለት አስረሳ። ወዲያው ደምቆ ታየ።

ስፖርት 365 ላይ የተገኘ የመጀመሪያ ቀን የነበረው አስተያየት በሙሉ ስለ አልዓዛር ነበር። ሁሉም አድማጮች ለአልዓዛር ያላቸውን አድናቆት እና ፍቅር ይገልፁ ነበር። "ደጋግመን ልናገኝህ እንፈልጋለን ፥ እንወድሃለን ፥ የራስህ አየር ሰዓት ይኑርህ...." ወዘተ። የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ አዩ ወልደሚካኤል ከአድማጭ የተላኩ በርካታ የአድናቆት መልክቶችን ለአዓዘር ሲያቀርብ አሊዝ በትህትና "አመሰግናለሁ" ይል ነበር።

አልዓዛር አስግዶም የእርግር ኳስ ተጫዋች ቢሆን እንደ አንድሬስ ኢኒየስታ የሚሆን ይመስለኛል።

ረጋ ብሎ የሚጫወት ፥ ኳስን የሚያሾር ፥ አከባቢውን በደንብ የሚቀኝ ፥ አርቲስት ፥ ራስ ወዳድ ያልሆነ ፥ ኳስ በነካ ቁጥር ውበት የሚጨምር....

አሊዝ የጋዜጠኞች ኢኒዬስታ ነው።


@Tfanos
4
በፈረንጆች 2014 ብራዚል በጀርመን ሰባት ለአንድ ተሸነፈች። በማግስቱ ዮናስ አዘዘ በሬዲዮ ውጤቱን ሲገልፅ "ብራዚል ሰባት ለአንድ ተሸነፈች። አድማጮች እናቴ ትሙት ከልቤ ነው" አለ።

ጨዋታውን ያላየ ሰው ብራዚል ሰባት ገባባት ሲባል አያምንምና መሓላ ያስፈልጋል።

የዛሬውን ጨዋታ ላላየ ሰው "የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ አምስት ለምንም ተጠናቀቀ። እናቴ ትሙት በፍፃሜ ጨዋታ ፥ ያውም በሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ አምስት ጎል ገባ" ተብሎ ይነገራቸዋል።

ሊዊስ ኤኔሪኬ እንኳን ደስ ያለው
👍61
የብልፅግና ካድሬዎች ጀዋር መሐመድ እንዳበቃለት ይነግሩናል። "ከዚህ በኋላ ተፅዕኖ አይፈጥርም፥ ምንም አያመጣም" ይላሉ።

ደግሞ ጀዋርን ሲረግሙት ፥ ሲሳለቁበት ፥ ሲያብጠለጥሉት ፥ በኮሜንት ሲዘልፉት ይውላሉ።

ምንም አያመጣም ካሉ ለምን ንቀው አይተውትም?

የማይፈሩት ከሆነ እየደጋገሙ አንፈራህም ማለት ለምን አስፈለጋቸው?

@Tfanos
👍13🔥1
መንግስት "ጠመንጃ አስቀምጣችሁ በሃሳብ ሞግቱኝ" ይላል። የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ደግሞ ያስራቸዋል።

የመንግስት አካሄድ "በሃሳብ አትሞግቱኝ ፥ ጠመንጃም አታንሱብኝ የሚል ነው"


@Tfanos
👍9😁72
"ሰው ማለት"

ቀን ብርሃን ሳለ
አብሮህ እየዋለ
አብረህ የምትውለው
ሰው ማለት ጥላ ነው።

አዎ - ጥላ
አጅቦህ የሚውል ከፊትና ኋላ
ኋላም ላይ 'ሚሰወር ፈፅሞ የሚሸሽ
ዙሪያህ ሲጨላልም ቀኑ ደግሞ ሲመሽ

ደግሞህ ከሸሸበት መልሶ 'ሚመጣ
ጨለማው ሲገፈፍ ፀሐይ ስትወጣ

ሰው ማለት ጥላ ነው
አዎ........ ጥላ

(ዘሪሁን ገብረጊዮርጊስ "ሳቅ ያፈናቸው ስንኞች" ገፅ 54)


@Tfanos
14🥰1
ቴዲ ፀጋዬ ልደቱ ነው። እንኳን ተወለደ። እኔ ከEbs ጀምሮ ተከታታዩ ነበርኩ። የማይረሱ ብዙ ፕሮግራሞችን ሰርቷል። (ለወደፊት ስለሱ እፅፋለሁ

አማርኛን የሚያዝበት መንገድ ደስ ይላል። በሐገራችን በጣም ጥቂት ምርጥ ገጣሚያንን ከጠራን አንዱ ቴዎድርስ ፀጋዬ ነው። ምርጥ የግጥም መድብል ከጠራን የቴዲ ፀጋዬን መድብል መዝለል አንችልም።

ቴዲ የተለዩ እና አይረሴ አገላለፆች አሉት።

ጥቂቶቹን እናስታውስ...

"ዶክተር ደብረፂዮን ማለት የችግር አንቴና ነው"

"ህወሃት ማለት ከድል ማህፀን ሽንፈት የሚያዋልድ ፓርቲ ነው"

"ህወሃት ሀይማኖት ነው። መሪዎቹ የሀይማኖቱ መሪዎች ናቸው። መለስ ዜናዊ ደግሞ የሀይማኖቱ አምላክ ነው። ህወሃት አሁን አምላኩ የሞተበት ሀይማኖት ነው"

"የዶክተር አብይን ድምፅ መስማት የስነልቦና ጥቃት ማስተናገድ ነው"

"ለኢያስፒድ ተስፋዬ ስራ ካገኘልኝ ሲቪዬን እልክለታለሁ። ስራው ግን የጀዋር መሀመድ ጫት ቀንጣሽነት መሆን የለበትም"

"ተመልካቾች ከዚህ ቀጥሎ አስፈሪ ነገር ልናሳያችሁ ስለሆነ ይቅርታ። መጥፎ ነገር ማየት የማትፈልጉ አሳልፉት።... የአብይ አህመድን ንግግር ልናሰማችሁ ስለሆነ ይቅርታ"

....
😎


@Tfanos
😁124🔥2
የድሬዳዋ ከንቲባ የትግራይን ህዝብ "ከሰይጣን የባሱ ናቸው" ብሎ ነበር። ያውም በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርቦ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጃኒን እንደከሰሳት ሁሉ የድሬዳዋው ከንቲባም መከሰስ ነበረበት። ነገር ግን እስከአሁን ምንም አልተባልም። በስልጣኑም ቀጥሏል።

ምን ማለት ነው?

1፥ ባለሥላናት ያሻቸውን ማድረግ ፥ የፈለጉትን ህዝብ መስደብ መብታቸው ነው። ወገኔ የሚሉት ሲነካ ግን የመክሰስ ሰልጣን አላቸው።

2፥ መንግስት ትኩረት የሚሰጠው መርጦ ነው። አንዱ ወገን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ሲሰደብ ዝም ይላል። ሌላው ሲሆን ደግሞ በቲክቶክ ለተሳደበው ይጠየቃል።

3፥ ሕግ የሚሰራው ቲክቶከር ላይ እንጂ በቴሌቪዥን አይተገበርም።

4፥ ሁሉም መልስ ነው


@Tfanos
👍145👎4
ጆርዲ እና ተድላ ሰሞኑን ክርክር ለማለት የሚከብድ ክርክር አድርገው ነበር።

በሙግታቸው ካነሱት ውስጥ ትኩረቴን የሳበው በትዳር ውስጥ ያለ መደፈር ነው። በትዳር ውስጥ "መደፈር" የሚለው አገላለፅ ብዙ ሰዎች ምቾት አይሰጣቸውም። ምክኒያታቸውን እረዳዋለሁ።

መደፈር የሚለውን ቃል ሚስት ሳትፈልግ የሚደረግ ወሲብ ብለን እንያዘውና አንድ ታሪክ እናንሳ። እውነተኛ ታሪክ ነው።

አንዲት ባለትዳር ሴት አለች። ከሆነ ጊዜ በኋላ ከባሏጋ ወሲብ ለመፈፀም መቸገር ጀመረች። ግኑኝነቱን ማሰብ ጭምር ያስጨንቃታል። ገና ወሲቡ ሲጀመር መቀመጫዋ አከባቢ ሀይለኛ ህመም ይሰማታል። ወገቧን ያማታል። ወሲብ በራሱ ስቃይ ይሆንባታል።

ነገሩ ግራ ሲያጋባት ወደ ጤና ተቋማት አመራች። ህመም የለብሽም ተባለች። በተደጋጋሚ ትመረመራለች ህመም የለብሽም ትባላለች።

በመጨረሻም የስነልቦና ባለሞያ ዘንድ ሄደች። ህመሟ ተገኘ። የልጅነት ጠባሳ ነበር።

በልጅነቷ እድሜ አያቷ አስገድዶ ሊደፈራት ይሞክር ነበር። አያቷ በመቀመጫ በኩል ሊገናኛት በተደጋጋሚ ሞክሯል። ያ ተደጋጋሚ ጥቃት የስነልቦና ጠባሳ ፈጠረባት።

አድጋ ቤተሰብ ከመሰረተች በኋላ የተዳፈነው የስነልቦና ችግር ተቀሰቀሰ። ህመሟ አገረሸ። ወሲብ ማለት ህመም ሆነባት።

ሰዎች በተለያየ ምክኒያት የወሲብ ፍላጎታቸውን ያጡታል። አንዱ ምክኒያት የስነልቦና ችግር ነው። አንዳንዶች በወር አበባ ወቅት እና በአካላዊ የጤና ችግር ወቅት ካልሆነ በቀር ሚስት ለወሲብ ፈቃደኛ መሆን አለባት ይላሉ።

እርግጥ የስነልቦና ችግርን እንደ ጤና ችግር አንረዳውም። ብዙ ሰው ህመም የሚመስለው አካላዊ ህመም ብቻ ነው። ሴቷ በህመም ወቅት ልንረዳት ይገባል የሚል ሰው ስነልቦናዊ ጉዳይን ለመረዳት ፈቃደኝነት ሊኖረው ይገባ ነበር።

"በትዳር ውስጥ መደፈር የለም" የሚል መሟጓቻ ያላችሁ ሰዎች ምን እያላችሁ እንደሆነ እረዳለሁ። ነገር ግን በትዳር ውስጥ መደፈር አለ የሚሉ ሰዎች ምን እያሉ እንደሆነ ልትረዱ ይገባል። ባልተወሳሰበ አማርኛ "ሴቷን ተረዱ" እያሉ ነው።

በሰው ህይወት ብዙ ውስብስብ ገጠመኞች ይኖራሉ። ወሰብሳቤ ገጠመኞች ስነልቦናችን ላይ የራሳቸውን አሻራ ያኖራሉ። ያን ለመረዳት መሞከር ጥሩ ነው።

ሴቶች ባል ካገቡ በኋላ ለወሲብ ፍላጎት ቢያጡ መፍትሄው "ወሲብ ግዴታሽ ነው" ማለት አይመስለኝም። ሁኔታዋን ለመረዳት መሞከር እና በጋራ መፍትሔ መፈለግ ነው።

የሴቶች አጀንዳ ወደ አደባባይ መውጣቱ ጥሩ ነው። በብሽሽቅ እና ለመሸናነፍ በመሞከር ነገሩን ማወሳሰብ አይበጅም። ወንዶች ሴቶች ምን እያሉ እንደሆነ ለመረዳት በመሞከር ከፊል ችግሩን ማቅለል እንችላለን

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
@Tfanos
👍168
አብይ አህመድ በዛሬው እለት ከኪነጥበብ ሰዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በነካ እጃቸው ከፖለቲከኞች ጋር ውይይት ቢያደርጉ ጥሩ ነበር...


@Tfanos
😁3
"በእቅፍሽ ልሰወር"
* * *

ስካር ከጠመንጃ
መንበር ከጥላቻ
እየተጣመሩ
እየተባበሩ
እየተዳመሩ
ለሞት አዳይ መልአክ ፥ ሰይፍን ቢያቀብሉ
አሰላሳይ አንጎል ፥ የተሸከሙቱ ፥ አንገቶች ተቀሉ

ተመልከች ሐገሩን

ጎበዝ እንደዘበት ፥ በወጣበት ቀረ
ወላጅ ጧሪ ልጁን ፥ በዋዛ ቀበረ
የሀዘን ስል ካራ ፥ እናትን ገደለ
የመሞትን ተራ ፥ አባት ተከተለ

ተመልከች ሐገሩን

የሞት መልአክ ሰይፉን ፥ ከሰገባ መዟል
ብርቱ ይቀጠፋል
አዛውንት ይወድቃል
ጎበዙ ይረግፋል
አዳጊ ይቀጫል

እባክሽ አለሜ

ፍልሚያ እና መቀጠፍ ፥ በበዛበት ሐገር
መሸሸጊያ ሁኚኝ ፥ በእቅፍሽ ልሰወር

(Repost

@Tfanos
19
ተመስገን ማርቆስ...

ዘማሪ ነው። ሻሸመኔዎች በልዩነት የምንወደው ዘማሪ ነው!

ልጆች ሆነን ዘወትር ማክሰኞ ሻሸመኔ ሸዋበር ቃለህይወት ቤተክርስቲያን መሄድ ያስደስተን ነበር። ብዙ ምክኒያቶች አሉን። እኔ በግሌ ቃለህይወት የመሄጃ ምክኒያቴ ወንጌል አልነበረም። ሐቅ መናገር ይኖርብኛል። ስብከቱን የምሰማበት ብስለት የለኝም። ቸርች የምሄደው ተመስገን ማርቆስን እና ፓስተር ጌቱ ዱሬሳን ለማየት ነው። ስለ ፓስተር ጌቱ ሌላ ጊዜ እፅፋለሁ።

ተመስገን ማርቆስ ሲዘምር ደስ ይላል። ነገረ ስራው ሁሉ በትህትና የተሞላ ነው። ሁላችንም እንወደዋለን። እንደምንወደው ያውቃል። ሰዎች ስለሚወዱት አይኮፈስም።

የመጀመሪያ የመዝሙር አልበሙን 96 አ.ም ክረምት ላይ አወጣ። የአልበሙ ርዕስ ፋሬስ ይላል። የተወሰንን ልጆች ቅፅል ስሙን ፋሬስ አልነው። በሳይክል ወደ ቤት ስሄድ እየተጫጫህን "ተሜ" እንለዋለን። ከሳይክል ወርዶ ያቅፈናል። በቁም ነገር ቆሞ ያናግረናል።

ታላላቆቹን ያከብራል። የሚገርመኝ ለህፃናትም ለአባቶችም እኩል አክብሮት ነበረው። የአስር አመት ልጅ መንገድ ላይ ቢያስቆመው በትህትና ያናግረዋል። ትህትና ሲባል የማስመሰል ትህትና ሳይሆን እውነተኛ ትህትና ነው።
ዱርዬዎችን በወዳጅነት ስሜት ያናግራል። አመፀኞችን አይገፋም።

ሻሸመኔ መንገድ ዳር ድንች በዳጣ ይሸጣል። ወጣቶች ተሜን ድንች እንብላ ሲሉት አብሮ ይበላል።

በጉባኤ መሐከል "ፀጉርህ አደገ" ቢሉት አይቀየምም። ሄዶ ፀጉሩን ይቆረጣል።

ሶስት አልበሞች እስኪሰራ ድረስ ከሻሸመኔ አልወጣም ነበር። "ፋሬስ ፥ ሀይል አለ እና እግዚአብሔር ይበልጣል" የሚሉ ሶስት አልበሞች ሰርቶ ሻሸመኔ ይኖር ነበር።

አድገን መንፈሳዊ የኪነጥበብ ቡድን መሰረትን። ያኔ ተሜ ተባባሪያችን ሆነ።

ከቀናት በአንዱ ኤርገዶ ጫማ ፥ አሮጌ ቲሸረት መናኛ ሱሪ ለብሰን ወደ ቤቱ ሄድን። በር ስናንኳኳ ከፈተልን። በቤቱ ሳሎን አስተናደን። የምንፈልገውን ጠየቀን። ትንሽ ብር እንፈልጋለን አልነው። ከፈለግነው በላይ ሰጠን። እየሳቀ "ሀብታም ስትሆኑ አንድ በአንድ ምሳ ትጋብዙኛላችሁ" አለን። ተስማምተን ተለያየን። ስልክ ቁጥሩን ሰጥቶን "ስትፈልጉኝ ደውሉልኝ። ባስፈልግኳችሁ ጊዜ ብታዙኝ እታዘዛለሁ" አለን።

እሱን ለማዘዝ እኛ ማን ነን?

ከሻሸመኔ ወጥቶ ወደ አሜሪካ የሚያቀናበት ጊዜ ደረሰ። ያን ቀን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የነበረው ሃዘን ጥልቅ ነበር።

ህፃናት በልጆች ትምህርት ጊዜ እየተገኘ ይጎበኛቸዋልና አዘኑ። ወጣቶች በሚፈልጉት ጊዜ ሁሉ ይተባበራቸዋልና አዘኑ። ታላላቆች አክባሪያቸው እና ታዛዣቸው ነውና አዘኑ።

ተመስገን ማርቆስ ትሁት ሰው ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎችን በክፉ አንስቶ አያውቅም። ከትህትና ጎድሎ አያውቅም። ታዛዥ ሰው ነው።

ብዙ ተወዳጅ መዝሙሮች አሉት።

"ገና ነው ገና ገና"
"ደሙ ሀይል ጉልበቴ"
"እግዚአብሔር ይበልጣል"
"ዛሬም ሀይለኛ ነው"
"የኪደን ልጅ"
"ዋጋ ሚጠይቅ ነው ክርስትና"
"በጨነቀኝ ጊዜ ፀሎቴን"
"ነጋ ለሊቱ ነጋ"
ወ ዘ ተ

የሻሸመኔ ሰዎች ተመስገንን በመዝሙሮቹ ብቻ ሳይሆን በማይለወጥ ትህትናው እና ሰው አክባሪነቱ ያውቁታል። ለቤተክርስቲያን ያለው ታዛዥነት ሁሌም የሚታወስ ነው። ለታናናሾቹ አረአያ ነው።

ተመስገን ማርቆስ


@Tfanos
20👍1
የሆነ ጠዋት ከአንቅልፌ ስነቃ "ሰው እንዴት ኤቲስት ይሆናል? ፈጣሪ የለም ማለት እኮ ጅ* ልነት ነው" እላለሁ።

ሌላ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ "ሰው እንዴት አማኝ ይሆናል? አማኝነት እኮ ጅልነት ነው" እላለሁ።

ማመንም መካድም ልክ እየመሰለኝ ተቸግሬያለሁ።

አሁን ግን መፍትሔ አግኝቻለሁ። የኔ ችግር የጤና ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ሄጄ መፍትሄ ላፈላልግ።
👍112👎2
"ማነው የሚያድንሽ"
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *

ለተሰበቀ ጦር ፥ ጋሻሽ መሆን ቻልኹ
እሳት ሲነድብሽ ፥ ዝናብ ሆኜ መጣኹ
ወንዙን ለማሻገር ፥ ድልድይሽ እንድሆን ፥ እኔው ተነጠፍኹ
እንደ መሲህ ሆኜ ፥ ከክፉ ጠበቅኩሽ
እልፍ'ዜ አዳንኩሽ
ወንዙን አሻገርኩሽ
ካፊያ እንዳይነካሽ ፥ መጠለያ ሆንኩሽ

ዳሩ ፥

ከወደረኛ ጦር ፥ ጋሻ እንዳልሆንኩሽ
በቃል ቀስት ወጋሁሽ
ከካፊያ ከልዬ ፥ ለመብረቅ አጨኹሽ
ከእሳት ነጥቄ፥ ለገሃነም ዳርኩሽ

ማነው የሚያድንሽ
ማነው 'ሚጠብቅሽ
ከእኔ 'ሚታደግሽ?

ይህ ልቤ ፥

ከጊንጥ ሊያስመልጥሽ ፥ ከቶ ያልሰነፈ
በመርዛም አንደበት ፥ ደጋግሞሽ ነደፈ
ከቀስት ከፍላፃ ፥ አንቺን የጠበቀ
የቃልን ስል ሰይፍ ፥ አንቺው ላይ ሰበቀ

ማነው የሚያድንሽ
ማነው 'ሚጠብቅሽ
ከእኔ 'ሚታደግሽ?

እኔ፥

ድልድይሽ እየሆንኩ ፥ ወንዙን አሻግሬ
ወደ ገደል ላኩሽ ፥ በቃሌ ገፍትሬ

ማነው የሚያድንሽ
ማነው 'ሚጠብቅሽ
ከእኔ 'ሚታደግሽ?


@Tfanos
5👍1
"ለምን ትታው አትሄድም?"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ተከራይቼ የምኖርበት ግቢ ወጣት ጥንዶች አሉ። አንድ ምሽት ወደ ቤት ስገባ ከቤታቸው የሲቃ ድምፅ ሰማሁ። ጆሮዬን ብቀስር እየጮኸች "በናትህ" ትላለች። እየደበደባት ነው። በእናትህ የሚለው ልመናዋ ጣር ያለበት ነው። "እንዳትገለኝ" እያለችው ነው። "እናትሽ ት በ*" እያለ ይደበድታል። እያለቀሰች በእናትህ ትለዋለች። እንዳትገለኝ ትለዋለች።

በሩን ከውስጥ ቆልፎታል። በሩን መደብደብ ጀመርኩ። የሚከፍትልኝ የለም። ያለኝን ሀይል ተጠቅሜ በሩን መደብደብ ቀጠልኩ። አልከፍት ሲለኝ "አንድ ጉዳት ቢደርስባት እገድ**ልሃለሁ" አልኩት። የተናገርኩት አፌ ላይ እንደመጣ ነው። ምንም ማድረግ እንደማልችል አውቃለሁ።

በሩ ሲከፍት ተንደርድራ እግሬ ስር ተደፋች። ፊቷ በደም ርሷል። በደመነፍስ ፊቱ ስገተር ዘወር አለ።

ያን ቀን ሁለት ግራ አጋቢ ጥያቄዎች ተፈጠሩብኝ። ግቢያችን ብዙ ተከራይ ነበር። ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሊያድኗት አልሞከሩም። በቤታቸው በር ቆመው የስቃይ ጩኸቷን ይሰማሉ። ቲያትር እንደሚያይ ሰው ጥቃቷን ይመለከታሉ።
እንዴት ዝም ይላሉ የሚለው ግር አለኝ።

አንዷ የግቢያችን ተከራይ "ሁሌም ይመታታል" አለችኝ ቀለል አድርጋ። ሁሌም እየደበደባት አብራው መቆየቷ ግራ ገባኝ። "ለምን ትታው አትሄድም" አልኩ። ተናደድኩባት።

ትቶ መሄድ ቀላል እንዳልሆነ እስኪገባኝ ድረስ በጭቆና መካከል የሚቆዩ ሴቶች ነገር ይገርመኝ ነበር። መከራን የሚታገሱበት ሰበብ ግራ ያጋባኝ ነበር። ኋላ ላይ ግን ትቶ መሄድ ከባድ መሆኑን አወቅኹ።

ትቶ መሄድ ከባድ ነው። ጨክኖ ትዳርን ትቶ መውጣት ከባድ ነው።

"ሰው ምን ይለኛል?" የሚል ስጋት አለ። የሰው ምላስ ጦር ነው። ይወጋል። "ፈት፥ ጋለ**ሞታ" ወዘተ የሚለውን ስድብ ፥ የማያባራን ወቀሳ ፥ የማይቋረጥን ሃሜት የሚቋቋሙ ጥቂት ናቸው። እንዲህ ያለ ችግር ላለመጋፈጥ ሲሉ እየተጨቆኑ መቆየትን ይመርጣሉ።

"ነገ ይቀየራል" የሚል የማይጨበጥ ተስፋ ያላቸው አሉ። በእርግጥ ሰው ይቀየራል። ነገር ግን ይቀየራል በሚል ተስፋ በግል ህይወት አይቆመርም። ቤቱን የማያከብር አባወራ ፥ ሚስቱን የሚደበድብ ባል ፥ ትዳሩ ላይ የሚዞሙት አመንዝራ ፥ ልጆቹ ዳቦ ቸግሯቸው ቢራ የሚራጭ ሰነፍ ... ነገ ይቀየር ይሆናል በሚል ተስፋ አደጋ እያደረሰ ይቀጥላል። ሰውዬው ከመቀየሩ በፊት ሚስትቱ....

ጊዜም ሌላው ችግር ነው። አንዳንዱ "ካገባሁ አጭር ጊዜ ነው ፥ እንዴት እፈታለሁ?" ይላል። አንዳንዱ ደግሞ "ይህን ሁሉ ጊዜ የለፋሁበትን እንዴት አፈርሳለሁ" ይላል። በዚህ የተነሳ ትተው የማይሄዱ ብዙ ናቸው።

ከሁሉም የከፋው ግን ስነ-ልቦናዊ ባ ር ነ ት ነው። አጥቂ ወንድ የሴቷን በራስ መተማመን ያኮላሸዋል። ለራሷ ያላትን ዋጋ ይቀማዋል። በደልን በፀጋ እንድትቀበል ያደርጋታል። ተሸናፊ እና ተስፋ ቢስ ትሆናለች። ከዚህ በኋላ ትታ መሄድ አትችልም። እየተደበደበች ሞቷን ትጠብቃለች...


@Tfanos
@Tfanos
12👍2😢2
ቀነኒ እና ኤልዳና
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *
የሀማኖት መብት እየጣሱ ፥ የብሔር መብት ማክበር አይቻልም። የሴቶችን መብት እየጨፈለቁ ፥ የድሃን መብት አከብራለሁ ማለት ዘበት ነው።

ለሰብአዊ መብት እውነተኛ ክብር ያለው ሰው የሚጥሰው መብት አይኖርም።
መብት ሁለንተናዊ ነው። ተናጥላዊ መብት የለም። የተሸራረፈ መብት ሊኖር አይችልም።

ከሁሉም የሚቀድመው የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር ማወቅ እና በእውነተኛ ልብ ማክበር ነው። ሰብአዊ ክብርን በእውነተኛ ልቡ የተቀበለ ሰው የሚቆምበት መሰረት አለው። ሰብአዊ ክበር የገባው የሚገዛለት እሴትና መርህ ይኖረዋል።

ሰብአዊ ክብር እሴቱና መርሁ የሆነ ድርጊቶቹ ከሰብአዊ ክብር ፀብ አይገጥሙም። ከራሱ ጋር አይላተምም። ሰብአዊ ክብር እሴቱ ያልሆነ ሰው ግን ጠዋት መብት ደፍጥጦ ከሰአት የመብት ጥያቄ ያቀርባል።

ተራ ምሳሌ፥

ኤልዳና ሰሞኑን አጣማሪዋን "አባቴ" ስላለችው የሰደቧት ሰዎች በማግስቱ ስለ ቀነኒ እየተሟገቱ ነው። መሟገታቸው ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ የመርህ የለሽ ሰው ባህሪ ነው።

መብት የሚሸራረፍ ነገር አይደለም። አንዲት ሴት ባሏን በምትጠራበት ስም የተነሳ ክብሯ ላይ ምራቁን የሚተፋ ሰው የመብት ሀሁ ያልገባው ሰው ነው።

መብት ሰፊ ነው። በነፃነት ማሰብ ፥ የግል ምርጫ ፥ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ወዘተ መብት ነው። መብት ማለት በህይወት መኖር ብቻ አይደለም። ጭቆና ነውር የሚሆነው ከእኛ ውጭ ያለ ሰው ሲፈፅመው አይደለም። እኛ የሰዎችን መብት እየደፈጠጥን ሌሎች ሰዎችን ስንወቅስ ከራሳችን እየተላተምን ነው።

ስሜትን ብቻ መከተል ጥሩ አይደለም። ወደ አእምሯችን የመጣውን ሁሉ ለመተግበር መፍጠን አለመብሰል ነው።

ሰዎች ላይ ለመሳለቅ ከመሞከራችን በፊት "ድርጊቴ ከመሰረታዊ እሴቴ ጋር ይስማማል? ስለራሴ ከማወራው ጋር አብሮ ይሄዳል?" ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።

ሲያሻን የሰዎችን የግል ፍላጎት እየደፈጠጥን ፥ ሌላ ሰውን በመብት ጥሰት መውቀስ ከራስ መጣላት ብቻ አይደለም። "እኔ መብት የመጣስ ስልጣን አለኝ፥ አንተ ግን የለህም" ማለት ነው።

አውቃለሁ ፥ በቀነኒ እና በኤልዳና ጉዳይ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ይህን ጉዳይ የመረጥኩት ሆነ ብዬ ነው።

ሰብአዊ ክብር ሰፊ ነው። ከሰዎች መብት ላይ የምንሸርፈው ጥቂት ነገር ሊኖር አይገባም። ትልልቅ ጭቆናን መቃወም ጥሩ ነው። ነገር ግን በጣም ጥቂት የምትመስለውን መብት ለመጣስ ስልጣን እንደሌለን ማስታወስም ይኖርብናል።


@Tfanos
@Tfanos
12
2025/10/23 16:09:45
Back to Top
HTML Embed Code: