Telegram Web Link
ቴራፒስት ተስፋዬ ጫላ...
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
መሞት ተመኝታችሁ ታውቃላችሁ? ራሳችሁን ሳታጠፉ መሞት...
ሁሉም ነገር ጨልሞብኝ ያውቃል። ራሴን ለማጥፋት ከመመኘት ውጭ ያሉ ሁሉም አሉታዊ ስሜቶች ተፈራርቀውብኛል። በሀይለኛ ድብርት ውስጥ ሆኜ "ምናለ በሞትኩ" ብዬ አስብ ነበር።

ራስን ማጥፋት ያስፈራል። ስለዚህ ራሴን ሳላጠፋ ብሞት እመኝ ነበር።

አንድ ሰሞን ልቋቋማው የማልችለው ድብርት ውስጥ ገባሁ። ከዛም ለወራት ሰውነቴን አልታጠብኩም። ሶስት ወር ሰውነቴን ሳልታጠብ ቆየሁ። ካልሲና የውስጥ ሱሪ እንኳን አልቀይርም ነበር። ሰውነቴ በቅማል ተወረረ። ፀጉሬን አከክ ባደርግ በጥፍሬ ስር ቅማል ይሰነቀራል። በየለቱ ከሰውነቴ እየለቀምኩ የምገድለው ቅማል ብዙ ነው። የተንጨባረረ ፀጉሬ ቅጫምና ቅማል ተዳብለውባታል። ያደገ የብብቴ ፀጉር ይከረፋ ነበር። የሰውነቴን ግማት እያወቅኹ መታጠብ አስጠላኝ።

"ተስፋአብ ለምንድነው የሚኖረው?" መልስ አልነበረኝም። ራሴን ማጥፋት አልፈልግም። ነገር ግን መሞት እመኛለሁ። በሆነ መንገድ በሞትኩ እላለሁ።

ሰው ሁሉ የሚጠላኝ ይመስለኝ ነበር። እንደሚወዱኝ የማውቃቸውን ሰዎች ጭምር ጠላኋቸው። ለኔ ያልነገሩኝ ድብቅ ጥላቻ ያላቸው ይመስለኛል። "ይጠሉኛል" የሚለውን የገዛ ሃሳቤን አምኜ ተቀበልኩ። በራሴ ምናብ በፈጠርኩት መጥፎ ስሜት የተነሳ ልቤ ተንኮታኮተ።

ለምንድነው የማልሞተው እላለሁ። ከተኛሁበት መነሳት ያስጠላኛል። ምግብ በትግል ነው የምበላው። ስለስሜቴ ለማንም አላወራም። ምን እየተሰማኝ እንደሆነ ማንም አያውቅም። ዝም ማለቴ ብቻ ነበር የሚታወቀው።

የሚገርመው ወደከፋ ድብርት ውስጥ የከተተኝ የረባ ምክኒያት አለመኖሩ ነው። ድንገት ድብርት ጓዙን ጠቅልሎ ሰፈረብኝ። ምናልባት ያለፉ ነገሮች ተደራርበው ሊያስደብሩኝ ወቅት እየጠቁ ይሆናል።

ደስ የማይሉ የህይወት ገጠመኞች አሉኝ። 2001 አከባቢ ከቤት ወጥቼ ለተወሰነ በረንዳ አድሬ አውቃለሁ። (አጭር የጎዳና ተዳዳሪነት ህይወቴ ብዙ ነገር አሳይተውኛል።) ያኔ የሚያስደነግጡ ነገሮች ገጥመውኝ ነበር።

የወደድኳቸው ጠልተውኝ ፥ ያከበርኳቸው አዋርደውኝ ፥ ያመንኳቸው ክደውኝም ያውቃሉ። ርቦኝ ያውቃል።
ምናልባት የግመሉን ወገብ የሰበረው ስንጥር ታሪክ ተደግሞብኝ ይሆናል።
በጀርባው ብዙ ሸክም የተጫነበት ግመል ነበር። አንዲት ስንጥር ሲጨመርበት ወገቡ ተሰበረ። የግመሉን ወገብ የሰበረው ስንጥሩ አይደለም። የቀደመው ሸክም እንጂ... እኔም እንዲያ ሆኜ ይሆናል።

በድብርት ውስጥ ሳለሁ ቴራፒስት የሆነኝ ተስፋዬ ጫላ ነው። በመጥፎ ስሜት ውስጥ ሳለሁ ፥ ምናለ በሞትኩ ብዬ በምመኝበት ወቅት መዝሙሮቹ አፅናኑኝ።
ተስፋዬም ከጥንትም እወደዋለሁ። በዛን መጥፎ ስሜት ውስጥ ሳለሁ ግን ሁለት መዝሙሮቹ ፈውስ ሆኑኝ።

መዝሙሮቹ "ቀን አለ" እና "ሚስጥር" ይላሉ።

የሆነ ቀን ሁለቱን መዝሙሮች ደጋግሜ ሰማሁ። ያኔ ሸክም ከላዬ ተነሳ። ተፈወስኩ።

አንዱ መዝሙር
"ያሰቡት ሳይሰምር ፥ ሲቀር ሆኖ እንደህልም
በእኩለ ቀን ላይ ፥ በጊዜ ሲጨልም
በእድሜ ያከማቹት ፥ በዋዛ ሲበተን
በመከራ እሳት ፥ ማንነት ሲፈተን
ሁኔታውን ሳይሆን ፥ ቃልህን አምናለሁ
ታድናለህ ብዬ ፥ ፀንቼ እዘምራለሁ
ወጀቡ ሲበዛ ፥ ባንተ ተስፋ አልቆርጥም
ይዘንባል እላለሁ ፥ ደመናን ባላይም
ቀን አለ
ፀሐይ ትወጣለች ፥ ይሄ ለሊት ያልፋል
የታመኑት ጌታ ፥ በክብር ይመጣል
ፀጋ ልኮልኛል ፥ እሸጋገራሁ
ባስጨነቀኝ ራስ ላይ ፥ ቆሜ እዘምራለሁ"

ሌላ መዝሙር

"ሚስጥር አለ ውስጤ ፥ ለሰው ያልነገርኩት
አብረውን ለበሉ ፥ ያላጨዋወትኩት
ዙሪያዬ ፀጥ ሲል ፥ በሮቼን ዘግቼ
ልንገረው በእንባዬ ፥ የውስጤን አውጥቼ"


@Tfanos
9🔥2
የዙፋን ልፊያ በቅርቡ ለንባብ የሚቀርብ ስራዬ ነው። ልብወለድ ነው።

ስነ-ፅሑፍ ለፖለቲካ ጉዳይ ተገቢውን ትኩረት መስጠት መቻል አለበት ብዬ አምናለሁ። ስነ-ፅሁፍ ከሰው ለሰው በሰው ነው። ሰው ይፅፋል ፥ በሰው በኩል ለሰው ይቀርባል። በአንድም በሌላም ትኩረቱ ስለ ሰው ነው።
ፖለቲካ ደግሞ በእያንዳንዱ ሰው ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳደራል። ብንወድም ባንወድም በፖለቲካ ተፅዕኖ ስር ነን።

"ፖለቲካ በሩቁ" ባዮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ መሆን አይችሉም። ሰው ፖለቲካን ይሸሽ ይሆናል። ፖለቲካ ግን ሰውን አይሸሽም። ስለዚህ ለፖለቲካ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።

የዙፋን ልፊያ ሁነኛ ትከረቱ ቀጣይ ነጥቦች ናቸው

ፖለቲካ በተርታ ሰው ህይወት ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድነው?
ጦርነት እና የግለሰብ ህይወት ምን አገናኘው?
የፖለቲከኞች ግላዊ ባህሪ እና የዜጎች የእለት ተዕለት ህይወት እንዴት ይገናኛል?
ከላይ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች "የዙፋን ልፊያ" መፅሐፌ ትኩረት ናቸው።

በተቻለኝ መጠን ከቀደመው ስራዬ የተሻለ ስራ ለማምጣት የሞከርኩ ይመስለኛል።

የዙፋን ልፊያ መፅሐፍ መቶ ኮፒ ብቻ በቅደመ-ክፍያ ቀርቧል። ለራሳችሁ ወይንም ለሌሎች ሰዎች በቅድመ ክፊያ መግዛት ይቻላል።

በተለይ የምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በአካል መገኘት ለሚችሉ ጥሩ ማስረከቢያ መንገድ ይኖራል።

የአንዱ ዋጋ 450 ብር ነው። ከዛሬ ጀምሮ በቅድመ ክፍያ ይግዙ። መቶ ኮፒ ብቻ ከተሸጠ በኋላ ቅድመ ክፍያው ይቆማል።

1000242160537 ተስፋአብ ተሾመ

ይህን ለሌሎች ማጋራት ይበረታታል

@jtesfaab መገኛዬ ነው
8👍1🔥1
የትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ሰላማዊ ኑሮ የምትኖር እመቤት ነበረች። የጦርነት እሳት ሲለኮስ ቤቷ ፈረሰ። ባሏን አጣችው። ዘመዶቿ ወደ ሞት ተነዱ።
የምታደርገው ግራ ቢገባት ልጆቿን ይዛ ወደ አዲስ አበባ ስደት ጀመረች። ከቀዬዋ ተፈናቅላ ኮበለለች።

ደሴ አከባቢ ስትደርስ በለቅሶ ተሳፋሪውን አወከኝ። "ልጄን" እያለች መጮህ ጀመረች። በእቅፏ የነበረው ልጅ ሞቷል። የታቀፈችው የገዛ ልጇን በድን ነበር። ረሃብ ልጇን ገድሎታል።
ማንም ምንም ማድረግ አልቻለም። በአከባቢው ባለ አንድ ቤተክርስቲያን የአብራኳን ክፋይ ቀበሩት። እናት በረሃብ የሞተ ልጇን ቀብራ ሌሎችን ይዛ አዲስ አበባ ገባች። አዲስ አበባ ላይ ጎዳና ተዳዳሪ ሆናለች።የተረፉ ልጆቿን ታቅፋ ትለምናለች ፥ ሲመሽ ጎዳና ታድራለች።

ከውሾች ተሻምታ ትበላለች። ወንዶች እንዳያጠቋት ትማፀናለች። ህይወቷ ሙሉ ለሙሉ ጨለማ ነው። ከጦርነቱ በፊት እንዲህ አልነበረም...

ከላይ ያለውን ታሪክ ሌፍተናንት ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀል በመፅሐፉ አስፍሮታል። ታሪኩ እውነተኛ ነው። ባለታሪኳ ለዮሐንስ ነግራው ፥ "አዙሪት" በሚለው መፅሐፉ አስፍሮታል።

ጦርነት እየናጠን ነው። ሐገሪቱ በጦርነት እየታመሰች ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ ከኦሮሞ ነፃነት ጦር ጋር የሚደረገው ጦርነት ብዙሃንን ቀጥፏል። በአማራ ክልል የሚደረገው ጦርነት ለበርካታ ንፁሃን መቀጠፍ ሰበብ ሆኗል።

ዜጎች በወጡበት ይቀራሉ፥ አዛውንቶች በስተርጅና እድሜያቸው የውርደት ሞትን ይቀበላሉ፥ በብሔር ማንነት የሚገደሉ ተቆጥረው አያልቁም ፥ ጦርነት ወለድ ረሃብ የቀጠፋቸው ብዙ ናቸው ፥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለማኝ ሆነዋል።
በደህናው ቀን ለራሳቸው የማያንሱ ሰዎች ዛሬ በየጎዳናው ቁራሽ እንጀራ ይለምናሉ።

ከዚህ አዙሪት የሚያወጣን ምንድነው?

በአማራ ክልል በሚደረገው ጦርነት ከብቶች ጭምር እየተነዱ ይወሰዳሉ ፥ ሰብል ላይ እሳት ይለቀቃል ፥ ህፃናት የድሮን ሲሳይ ይሆናሉ ፥ የታመሙ ሰዎች ህክምና ማግኘት አይችሉም።

ምን አይነት መረገም ነው?

የኦሮሚያው ጦርነት ጆሮ ተነፍጎታል። የተረሳ ጦርነት ነው። ወላጋን በመሰለ ለምለም አከባቢ ረሃብ ገብቶ አልተደቅንም።

ምንድነው ተስፋችን?

በቃን ማለት ያስፈልጋል። በአማራ ህዝብ ላይ የታወጀው ጦርነት መቆም አለበት። የትግራይ ህዝብ ከቁስሉ ሳያገግም ሌላ ጦርነት ተደግሶለታል። ይህ ሊቆም ይገባል። የተረሳው የምዕራብ ኦሮሚያው ጦርነት መቆም አለበት።

ጦርነት ይብቃ። የድሃ ልጅ ህይወት አይቀጠፍ። ክቡሩ የሰው ልጅ ደም በዋዛ አይፍሰስ!

ለሹማምንትን ዙፋን ሲባል፥ ወጣቶች በመቃብር መከተት የለባቸውም።

ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
16😢3
ካላጡ ካልተቸገሩ ፥ መኖር ማን ይጠላል በአገሩ
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ጨዋማው ህንድ ውቅያኖስ እሳት የሚተፋ ይመስል ከባድ ወበቅ አለ፡፡ በውቂያኖሱ ከመርከብ ያነሰች ፥ ከጀልባ የምትሻል ታንኳ መሳይ በእርጋታ ታዘግማለች። ጥም የጎዳቸው ፥ ረሃብ ያደቀቃቸው፥ ሰቀቀን የተጫናቸው ኢትዮጵያውያን፥ ኤርትራውያን እና ሶማሊያዊያን ችግር ሽሽት በትንሿ ጀልባ ታጭቀው የስደት ጉዞን እያደረጉ ነበር፡፡

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ነው። ህንድ ውቂያኖስን አቋርጦ ወደ አረብ አገራት በመግባት ህይወታቸውን ለመለወጥ ተስፋ ያደረጉ ሰዎች መከራውን ችለው እየተጓዙ ሳለ ድንጋጤ የሚፈጥር የጭካኔ ተግባር ተከሰተ።

3 አዘዋዋሪዎች አንድን ወጣት ይዘውት ቆሙ። አዘዋዋሪዎቹ ፈላጭ ቆራጭ ናቸው። መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ከሌለ በቀር የወደዱትን ያደርጋሉ። ማንም ሊያስቆማቸው አይችልም!
የተሰዳጁ ትኩረት በአዘዋዋሪዎቹ ላይ ቢያርፍም የስደተኛው ስሜት ግድ ሳይሰጣቸው ያሰቡትን ተገበሩ። ተጋግዘው ወጣቱን ወደ ውቂያኖሱ ወረወሩት፡፡ አዎ ወጣቱ ወደ ህንድ ውቂያኖስ ጣሉት!

ይሄን ዘግናኝ ድርጊት ከተመለከቱት መኻከል ጥቂቶቹ በድንጋጤ ጮኹ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ በድንጋጤ መጮኽ እንደ ወንጀል ተቆጠረ። የጮኹት በሙሉ ተመርጠው ተቀጡ። ቅጣቱ የቀደመውን ድርጊት የመሰለ ነው። ወደ ውቅያኖሱ ተወረወሩ!

"መጀመሪያ ላይ ወደ ውቅያኖስ የተወረረው ወጣት ጥፋት ምንድነው?" የሚል ጠያቂ ይኖራል። የወጣቱ ጥፋት 'አይነግቡነቱ' ነው። አዘዋዋሪዎች ከተጓዦቹ መካከል መልከ ቀና የሆነውን ወጣት መረጡ። ቀጥሎ ልብሱን ገፈፉት! ከዚህ በኋላ የተፈጥሮ ሕግ ተጣሰች። ፆታዊ ጥቃት ተፈፀመበት። በጉልበተኛ ወንዶች ተገዶ ተደፈረ። ከዚህ በኋላም እንደማይጠቅም ቆሻሻ እቃ ወደ ውቅያኖስ ከነ ህይወቱ ተወረወረ፡፡

ካላጡ ካልተቸገሩ
መኖር ማን ይጠላል በአገሩ

ሌላ ሰቆቃ፥
በየመን እድል የከዳቻቸው ኢትዮጵያውያን በታጣቂዎች ታገቱ፡፡ ከእግቱ በኋላ የተፈፀሙ ዘግናኝ ድርጊቶች ቅዠት እንጂ እውን አይመስሉም፡፡
በአንድ እለት ከታገቾቹ መካከል ውብ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ተመረጠች። ቀጥሎ በተመልካች ፊት ሌላ አመትዮጲያዊ ጋር ወሲብ እንድትፈፅም ትዕዛዝ ተላለፈ። ነገሩ አጣብቂኝ ነው። አማራጩ በሰዎች ፊት መዋሰብ አሊያም መሞት ነው።

የሐገሩን ልጅ እንዲያስነውር የታዘዘው ወጣት 'አሻፈረኝ' አለ፡፡ 'እንዲህ ያለ ድርጊት ለመፈፀም አካሌ አይታዘዝም' የሚለው ምላሹ ያስቆጣቸው ወታደሮች የልጁን ብልት ቆረጡበት፡፡ በመቀጠልም ልጅቷን ከተፈራረቁባት በኋላ ገደሏት፡፡

ካላጡ ካልተቸገሩ
መኖር ማን ይጠላል በአገሩ

በስደት ዘመኗ ሴተኛ አዳሪነት ላይ የተሰማራች አንዲት ኢትዮጵያዊት አለች።
ይች ሴት የወሲብ አገልግሎት የምትሰጠው በተለመደው መንገድ አይደለም፡፡ ወሲብን የሚፈልጉትን በአፏ ታስተናግዳለች። ወሲብ ፈልገው የሚመጡ ወንዶች በእርካታ አፏ ላይ ፈሳሻቸውን እስኪያፈሱ ድረስ ብልታቸውን ትጠባለች።
"እንዴት ያለችው ነውረኛ ሴት ናት?" የሚል ሰው ሊኖር ይቻል ይሆናል፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡

ይህች ሴት ህይወቷን ለመለወጥ በተሰደደችበት ምድር ጀምበር ጠለቀባት። ቀን ጠሞባት ለአስገድዶ መደፈር ተዳረገች። መደፈሯ ሳያንስ ፅንሰት ተፈጠረ። በዚህ መንገድ የተረገዘ ልጅ ወልዶ ለማሳደግ ዝግጁነት ስላልነበራት ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ ጽንሱን አስወገደችውና ለፌስቱላ ተጋለጠች፡፡

ይህች ሴት እጅግ ሰቅጣጭ የህይወት ገጠመኝ አላት፡፡

የአፍ ወሲብ ከመጀመሯ በፊት ከአንድ ወሲብ ፈላጊ ጋር በገንዘብ ተደራድራ ተስማማች። ወሲብ ከመጀመርዋ ሰገራዋ አመለጣት፡፡ አዎ ሰገራዋ አመለጣት! (ፌስቱላ እጅግ አስቃያሚ በሽታ ነው) በዚህ አይነት ወቅት ምን ይሰማታል የሚለውን ለናንተ አእምሮ ተውኩት፡፡

ከዚህ አሳዛኝ ገጠመኝ በኋላ ይህች ሴት የገንዘብ ጎዶሎዋን ለመሙላት የወሲብ ንግድ ውስጥ ብትገባም ፥ ወሲብን በተፈጥሯዊ መንገድ አትፈፅምም፡፡ ወሲብ የሚፈልጉትን በአፏ ታስተናግዳለች፡፡

ካላጡ ካልተቸገሩ
መኖር ማን ይጠላል በአገሩ

ከላይ የተጠቀሱት ታሪኮች እውነተኛ ናቸው። ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት "የሞት ጉዞ" በሚለው መፅሐፉ ከላይ ያሉትን ጨምሮ ሌሎች ዘግናኝ መከራዎችን አትቷል።

ዛሬ ሌላ የስደት አለም መጥፎ ዜና ሰምተናል። በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ባህር ሰጥመው ህይወታቸው ተቀጥፏል።

ሰው ለምን ይሰደዳል?

'ይህ ሁሉ ጉድ እያለ ሰው ለምን ይሰደዳል?' የሚል ጠያቂ ካለ ምላሹ "ጎዶሎን ለመሙላት፥ ሽንቁርን ለመሸፈን ሰዎች ይሰደዳሉ" የሚል ነው፡፡

"ማብቅያ የሌለው ሽሽት" የሚል መፅሐፍ አንብቤ ነበር። የስደት ታሪክን የሚያትት መፅሐፍ ነው። ባለታሪኩ በመጀመሪያው ሕገወጥ ስደት ለብዙ መከራ ተዳርጎ ነበር። አብረውት የነበሩ ሰዎች ህይወታቸው ሲቀጠፍ አይቷል። ነገር ግን ድጋሚ ለሕገወጥ ስደት ተዳረገ። ሞት እያለው እያወቀ ሞትን ደፍሮ ተጋፈጠ።

"ካላጡ ካልተቸገሩ
መኖር ማን ይጠላል በአገሩ?"

ነፃነት አልባ ሕዝብ ነፃነት ፍለጋ ይሰደዳል። ድሃ ህዝብ ዳቦ ፍለጋ ይሰደዳል።


@Tfanos
😢103
"ሰውን አልነካውም። ከነካኝ ግን አልለቀውም..."
(ተስፋኣብ ተሾመ)

ታክሲ ውስጥ ነን። አንድ ተሳፋሪ ከረዳቱጋ በማይረባ ጉዳይ ተጋጨና በፀያፍ ቃል ተሳደበ። ከስድብ አልፎ ለድብድብ ተጋበዘ። ገሰፅነው። አጠገቤ ነበር። ተው አልኩት። "እኔን ስለማታውቀኝ ነው፥ ሰው ካልነካኝ አልነካም። ሰላማዊ ነኝ። የነካኝን ግን አልፋታውም" አለኝ። ሳቄን በግድ መለስኩ።

ብዙ ሰዎች እንዲህ ሲሉ እንሰማለን። "ሰው ካልነካኝ አልነካም" ይላሉ። ለጨዋነታቸው ማስረጃ የሚያደርጉት ሳያነኩ አልመንካታቸውን ነው። በእርግጥ ይህ ትክክለኛ መመዘኛ ነው?

ስትነካ ምላሽህ እንዴት ነው? ስትነኪ በምን መንገድ ትመልሻለሽ?

"ካልነኩኝ ማንንም አልነካም" ማለት ትክክለኛ መመዘኛ አይደለም። ሳይነኩ መነካካትማ ጤና ማጣት ነው። ይህን የ7 አመት ህፃን ያውቀዋል። የስብዕና እውነተኛ መለኪያ የተነካን ሲመስለን የምንሰጠው ምላሽ ነው።

ብዙ አጥፊዎች የሚደረድሩት ሰበብ አላቸው። አመፀኞች ለአመፃቸው ምክኒያት ማቅረብ ይችላሉ። ሌላው ላይ ጉዳት ያደረሱ ሰዎች ለምን እንዲያ እንዳደረጉ ማስረዳት አያቅታቸውም። ዋናው ጥያቄ እዚህጋ ነው። ሰበብ ሲኖር የሚጣስ ሰላማዊነት እውነት ሰለማዊነት ነው?

ስንነካ ምላሻችን ምንድነው? ሰዎች ጆሮ ሲነሱን ምን እንዳደርጋለን? ስንቆጣ ምን አይነት ሰዎች ነን? ንዴታችን እንዴት ይገለጣል? ዋናው ነጥብ ይህ ነው።

"ወራጅ አለ" ብለነው የማይሰማ ረዳት ያናዳል። ከፌርማታ አሳልፎ የሚያወርድ ታክሲ ያስቆጣል። አለመቆጣት አይቻልም። ቁም ነገሩ ቁጣው እንዴት ይገለጣል የሚል ነው። አንዳንዱ ለገላጋይ የሚያስቸግር ፀብ ይገጥማል። ካልGe *ደልኩት ይላል። የአንዳንድ ሰው ቁጣና የተፈፀመበት ጥፋት አይመጣጠንም።

በመንገድ ሲያልፍ በስህተት የገፋውን ሰው ለመ*ግደDeል የሚጋበዝ አለ። እንዴት ይቅርታ አልጠየቀኝም ብሎ ኮብልስቶን ያነሳል። ታክሲ ውስጥ ፈቅ ያላለለትን ሰው በፀያፍ ስድብ የሚሳደብ አለ። ወላጆቹን ሲያናድዱት ካልደበደብኳቸው ባይ ብዙ ነው። ታላቁ ላይ ቡጢ መሰንዘር የማያስደነግጠው ጥቂት አይደለም። "ሚስቴ ራት አላቀረበችልኝም" ብሎ ዱላ የሚያነሳም አለ።...

ሁሉም ሰው ለጥፋቱ ምክኒያት አለው። ራሱን እንደሰላማዊ ሰው ይቆጥራል። "ካልተነካው በቀር ማንንም አልነካም" ይላል። ዋናው ነጥብ ሌላ ነው። ሳትነካ ሰለማዊ ልትሆን ትችላለህ። ስትነካ ግን ምን አይነት ሰው ነህ? ሰው እስኪነካሽ ሰላማዊ ልትሆኚ ትችያለሽ። ሰው ሲነካሽስ?

መብትን በማስከበር አምናለሁ። ሽራፊ መብትን አሳልፎ መስጠት አግባብ አይደለም። ድንበር የሚጥስን ፥ ክብርን የሚጋፋን ፥ መብትን የማያከብርን ሰው ማስቆም ያስፈልጋል። ጉዳዩ ያለው ስለምላሻችን አይነት ነው። ከተፈፀመው ጥፋት የማይመጣጠን ምላሽ እየሰጡ ፥ በቸልታ ሊታለፍ ለሚችል ጉዳይ የፀብ ካርድ እየመዘዙ መኖር አግባብ አይደለም። በረሮን ለማጥፋት ዲማሚት ጥቅም ላይ አይውልም። አንዳንድ ሰዎች ድርጊታቸው እንዲያ ነው። ለበረሮ ዲማሚትን ይጠቀሙና "ሰው ካልነካኝ አልነካም" ይላሉ። ዋናው ጥያቄ ስትነካ እንዴት ነህ የሚል ነው።

እንደ ቁጣ ያሉ ተፈጥሯዊ ስሜቶችን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ እንደማይቻል አውቃለሁ። ነገር ግን ቁጣን ማስተዳደር ይቻላል። የምትቆጣበት ጉዳይ ምንነት ፥ የቁጣህ መጠን እና ቁጣህ የተገለፀበት መንገድ አንተነትህን ይገልፀዋል።

ከ2 ደቂቃ መሻገር የሌለበት ቁጣ አንተጋ ሳምንታት ከፈጀ ራስህን መርምር። ቢያናድሽም ግን ዋጥ አድርገሽ ልታልፊ የሚገባን ጉዳይ ወደ ከፋ ፀብ ካሳደግሽው ራስሽን መርምሪ።

ሰው ካልነካህ ሰው አትነካም አይደል? ጥሩ ነው። ዋናው ጥያቄ ስትነካ እንዴት ነህ የሚል ነው። ያልነካሽን ሰው አትነኪም? መልካም ነው። ዋናው ጥያቄ የተነካሽ ቀን እንዴት አይነት ሰው ነሽ የሚል ነው።


@Tfanos
8
ስለ ጆርዲ በዛብህና ተያያዥ ጉዳይ...
(ተስፋኣብ ተሾመ)

ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ወንጀል ነው። በሕግ የተከለከለ ነው። በሕግ የተከለከለን ነገር ማድረግ ወንጀል ነው። ያስጠይቃል። ማህበረሰብ ሁልጊዜም እንዲህ ካሉ ድርጊች በተቃራኒ መቆም አለበት።

ጆርዲ ተጋልጣለች። እንኳን ተጋለጠች። በተለይ ለታናናሾቻችን የምናስብ ከሆነ ፥ ለእሴቶቻችን ዋጋ የምንሰጥ ከሆነ እንዲህ ካሉ ነውሮች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተቃራኒ መሆን አለብን። የጆርዲ ድርጊት ነውርም ወንጀልም ነው።

ደግሞ የሳንቲሙን ግልባጭ ማሰብ ያስፈልጋል።

አንድን አጀንዳ ከፊት ሆኖ የሚመሩ ሰዎች ቴክኒካሊ የአጀንዳው ተወካይ ናቸው። ጥፋታቸው አጀንዳውን ይጎዳል። ይህን በጥንቃቄ ማሰብ ያስፈልጋል።

እዚህ ሐገር ኑሮ ለሴቶች ሲ ዖ ል መሰል ነው። በጦርነት ቀጠናቸዎች የሴቶች ማህፀን ጦር ሜዳ ይሆናል። በመደዳ ይደ ፈ ራ ሉ። የአገራችን 80 በመቶ አከባቢ ገጠር ነው። በገጠሪቱ ያሉ ሴቶች ኑሯቸው የጭንቅ ነው።

ያለ እድሜ ጋብቻ ፥ ጠለፋ ፥ መ ደ ፈ ር ፥ የቤት ውስጥ ጥቃት ፥ የኢኮኖሚ ድቀት ወዘተ ዛሬም የሴቶች ችግር ነው። ሞዴስ እንኳን የማያገኙ ሴቶች ብዙ ናቸው። መማር ተራራ ላይ የመሮጥ ያህል የቸገራቸው ሴቶች አሉ። በባሎቻቸው የሚደበደቡ ሴቶች አሉ። ይህን ሁሉ በልባችን መመዘገብ አለብን።

የሳንቲሙን ግልባጭ ማየት አለብን።

የሴቶች ጥቃት ሊቀለበስ የማይገባ አጀንዳ ነው። አጀንዳው የሁላችን አጀንዳ መሆን አለበት። እንደ ጆርዲ ባሉ ሴቶች የተነሳ የመብት ጥያቄ እንዳይደፈጠጥ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በሷ ጥፋት የተነሳ ስለሴቶች የሚያወሩ ሰዎችን ማሸማቀቅ አያስፈልግም። አጀንዳ እና ግለሰብ ይለያይ።

ለሴት መብት መከበር አዋጩ መንገድ ምንድነው? ውይይት ይፈልጋል። ፌሚኒዝም አሊያም ሊብራሊዝም ፥ ካፒታሊዝም ወይም ሌላ አማራጭ ሆኖ መቅረብ ይችላል። ዋናው ነጥብ ግን የሴቶች ጥ ቃ ት መቆም አለበት። ይህ ሊቀለበስ የማይገባ አጀንዳ ነው። ይህን ሁሌም በልብ ማኖር ያስፈልጋል

ስለ ሴቶች የምትሰሩ ሰዎች አሁን ወሳኝ ወቅት ላይ ናችሁ። ራሳችሁን አጥሩ። ቡድናችሁን ለዩ። ከማይወክላችሁ አስተሳሰብ ተነጠሉ። ያለ ቅድመ ሁኔታ ነውርን አውግዙ። የማውገዙ ጥቅም ለናንተው ነው። የቆማችሁለት የመብት አጀንዳ እንዳይጎዳ ካሰባችሁ ፥ ስለ ሴቶች የእውነት ግድ ከሰጣችሁ የማይወክሏችሁን አውግዙ።

ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ወንጀል ነው። የአገራችን ሕግ ይህን ይከለክላል። ስለዚህ ወንጀለኞች ይቀጡ። ደግሞም የሳንቲሙ ሁለተኛ ገፅ እንዳይዘነጋ፥ በነጆርዲ የተነሳ የሴቶች እውነተኛ ጥቃት እንዳይድበሰበስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።


@Tfanos
14🥰1
አፈንጋጭ ነበርኩ
(ተስፋኣብ ተሾመ)

አፈንጋጭ ነበርኩ። ሆነ ብዬ ከሰው እነጠላለሁ። ልዩ ሆኖ መታየት ያስደስተኛል። በተለይ ሀይስኩል እያለሁ በደንብ አፈነግጥ ነበር።

አምስት ጓደኛሞች ነበርን። መፅሐፍ እንዋዋሳለን። ከሁሉም ፈጣኑ አንባቢ እኔ ስለ ነበርኩ እና ባነበብኩት መፅሐፍ ቁጥር አንፃራዊ ብልጫ ስለነበረኝ እመፃደቅ ነበር። የእውቀት የበላይነት ያለኝ መስሎ ይሰማኛል። በሃሳብ ጥራት የላቅሁ እንደሆንሁ ይሰማኛል። አፈነግጥ ነበር።

ከመሬት ተነስቼ ባህል አንቋሽሽ ነበር ፥ ሃይማኖት ላይ እሳለቃለሁ ፥ ለሰዎች ሃሳብ ክብር አልሰጥም ፥ ያለ ማገነን ሰው እንቃለሁ። አሳፋሪ ሰው ነበርኩ።

ያለምክንያት አፈነግጣለሁ።

አንድ ቀን አንድ አባባል ሰማሁ። "እንደ አለም አስብ ፥ እንደ አከባቢህ ኑር" የሚል አባባል ሰማሁ። አባባሉ በልቤ ታተመ።

ቀስ እያለ ትዕቢቴ ይለቀኝ ጀመር። ሰው አለማክበሬ ያሳፍረኝ ጀመር። እሴት ላይ መሳለቄ ያሸማቅሸኝ ጀመር።

ልጅነት ነበረብኝ። የእውቀት ልጅነት ነበረብኝ። የእድሜ ልጅነት ነበረብኝ። የብስለት ልጅነት ነበረብኝ።
ጥቂት ልብወለድ መፅሐፍት ብቻ አንብቤ ከሁሉም ሰው የተሻልኩ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ስህተት ነበር።

ማፈንገጥ ጥሩ ነው። ማፈንገጥ ብቻውን ግን ጋ ጠ ወ ጥ ነ ት ነው። ማፈንገጥ ጥሩ የሚሆነው በምክኒያት መሰረት ላይ ሲታነፅ ፥ በእውቀት ምሶሶ ሲደገፍ ነው

ዛሬ ላይ ከሰው ከመለየቴ በፊት ሁለቴ አስባለሁ። ራሴን እጠይቃለሁ። "ለምንድነው የማፈነግጠው? በቂ ምክኒያት አለኝ? በእውቀት የተደገፈ መከራከሪያ ይኖረኛል?" እላለሁ።

ድሮ አፈንጋጭ ነበርኩ። እውቀትም ፥ ብስለትም ስለሚያንሰኝ አፈነግጥ ነበር


@Tfanos
🥰94👍4
የቀበሩትን መ ና ፈ ቅ
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *

የአባት ገ ዳ ይ ነው። አባቱን በገዛ እጁ ገድሎ ወሂኒ ወረደ። ለጥፋቱ እስር ተበየነበት።
ከእለታት በአንዱ በሲቃ ሲያለቅስ የወሂኒው ጠባቂ ሰማ።

"ምን ሆነህ ነው የምታለቅስ?" አለው ጠባቂው
"አባቴ ናፍቆኝ" ብሎ መለሰ እስረኛው።

እስረኛው የሚያለቅሰው በናፍቆት ነው። የሚያነፋርቀው የአባቱ ናፍቆት ነው። ልብ አድርጉ ፥ የታሰረው የገዛ አባቱን ገድሎ ነው። በእጁ የገደለውን አባት ይናፍቃል። አባቱ ያለበት እንዲመጣ ይመኛል።

ከላይ ያለውን ታሪክ ያነበብኩት ከፊልፕ ያንሲ መፅሐፍት መካከል በአንዱ ላይ ነው። የትኛው መፅሓፉ ላይ እንዳነበብኩ አላስታውስም። ነገር ግን የፊልፕ ያንሲ መሆኑን አውቃለሁ።

ባለታሪኩ ብዙ ሰው የሚወክል ይመስለኛል። አንዳንድ ሰው ገድሎ የቀበረውን ይናፍቃል።
ማን ነው የሚናፍቅህ ፥ ማነው የሚናፍቅሽ?
ናፈቅሽኝ የሚልሽ ሰው አለ አይደል? ናፈቅሽኝ ከማለቱ በፊት በቁምሽ ገድሎሻል። ናፈቅኸኝ ትልሃለች። ከዛ ቀድሞ ግን በቁምህ ቀብረሃለች።

ከሚናፍቁን ሰዎች መካከል ፥ በገዛ እጃችን የገደልናቸው አሉ። ከሚናፍቁን ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ በገዛ እጃችን ያጠፋናቸው ናቸው። ያከሰምነው ደርሶ ይናፍቀናል።

"የትላንቱ ፍቅር ናፈቀኝ" እንላለን። የትላንቱን ፍቅር የቀበርነው ግን እኛው ነን። የልጅነት መንፈሳዊነታችን ይናፍቀናል። ነገር ግን የልጅነት መንፈሳዊነታችን ገዳዮች እኛው ነን። የቀደመው ደስታችን በሚናፍቀን አፍታ የቀደመው ደስታችን ቀዳዮች መሆናችንን እንዘነጋለን።

ንስሃ መግባት ይኖርብን ይሆናል። ላከሰምነው ተስፋ ፥ ላኮላሸነው ፍቅር ፥ ላጠፋነው ፋኖስ ፥ ለገደልነው ደስታ ፥ ለቀበርነው ጓደኝነት... ንስሃ መግባት ይኖርብናል።

ብዙ ነገር ይናፍቀን ይሆናል። ናፍቆት እያነፋረቀን ይሆናል። መራራውን እውነት መቀበል ይኖርብናል። የሚናፍቀን ነገር በገዛ እጃችን የገደልነው ነገር ይሆናል። ይህን መራራ ሐቅ ተቀብሎ ንስሃ መግባት ያስፈልጋል።

የቀደመውን ጥፋት የሚገነዘብ ፥ ለቀደመው ስህተት ሃላፊነት የሚወስድ ሰው ለነገው ይታረማል። ትላንት ገድለን የቀበርነውን ማወቅ ፥ በእጃችን ያለውን እንዳንገድል ይጠቅመናል።


@Tfanos
9
ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ስሜታዊ የሚያደርግ አጀንዳ መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን በቁጣ ሰበብ ሰዎችን ለጉዳት መዳረግ አስፈላጊ አይደለም።

ሰሞንኛ አጀንዳን ተከትሎ "እገሊትም እንዲያ ናት" የሚል ወሬ ማናፈስ የጀመራችሁ ሰዎች እረፉ። ይህ አደገኛ ነገር ነው።

ሰዎች እንደ ንፁህ የመታየት መብት አላቸው። ተጨባጭ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ሰዎችን መወንጀል ሰዎችን ለአደጋ ይዳርጋል። ጣጣው ብዙ ነው። ህይወት ይናጋል።

እንደ ንፁህ የመቆጠርን መብት መግፈፍ አስፈላጊ አይደለም። አንድ ሰው ያለ ጥፋቱ መጥፎ ስም ከሚሰጠው ጥፋተኛው ነፃ ቢባል ይሻላል። አንድ ሰው ያለ ወንጀሉ ከሚቀጣ 99 ወንጀለኛ ነፃ ቢሆን ይሻላል የሚለውን ዝነኛ መርህ እናክብር።

በአንድ ወቅት በጀርመን አንድ ወንጀል ተፈፀመ። ወንጀሉን የፈፀመው ሰው መንታ ወንድም አለው። ከሁለቱ መንትዮች ወንጀለኛው የቱ እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም። ሁለቱ መንትዮች እውነተኛውን ወንጀለኛ እንዲያጋልጡ ሲጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። ሦስት መፍትሄ ብቻ ነው ያለው። ሁለቱንም ነፃ መልቀቅ ወይም ሁለቱንም ማሰር አሊያም ከሁለት አንዱን በግምት ማሰር። ፍርድ ቤት ሁለቱንም ለቀቀ።
ሁለቱን ወይም በግምት ከሁለት አንዱን ማሰር ይቻል ይሆናል። ነገር ግን በዚህ አካሄድ ያለ ወንጀል የሚታሰር ሰው ስለሚፈጠር ወንጀለኛን ነፃ ማድረግ ተመረጠ።

ነፃ ሰውን ወንጀለኛ ከማድረግ ወንጀለኛውን ነፃ ማድረግ ይሻላል።

በግምት ፥ በጥርጣሬ ወዘተ ተነሳሳታችሁ ሰዎችን አትወንጅሉ። የሰው ህይወት ይዛባል።

ሰዎች እንደ ንፁህ የመቆጠር መብት አላቸው። ያንን መብት አክብሩ


@Tfanos
17👎1
"ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ን እያስተዋወቃችሁት ነው"
(ተስፋኣብ ተሾመ)

ሬዲዮ ጣቢያ እሰራ ነበር። ከእለታት በአንዱ ጠንከር ያለ ፕሮግራም ሰራሁ። ፕሮግራሙ ስለ ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ነው። በዝግጅቱ የራሴን ምልከታ አላካተትኩም። የባለሞያ አስተያየት ብቻ ግብአት እንዲሆነኝ ተጠቀምኩ። የስነ ልቦና ባለሞያ እና የማህበረሰብ ጥናት ባለሞያ አናገርኩ። ጉዳዩ ከስነልቦና አንፃር እና ከማህበረሰብ አንፃር ምን ጉዳት እንዳለው ማብራሪያ ጠየቅኩ። በባለሞያ አይን የነገሩኝን ለአድማጭ በሚመች መንገድ አጠናቀርኩ።

በሚያሳዝን ሁኔታ የሰራሁት ዝግጅት ታገደ። አየር ላይ እንዳይውል ተደረገ። "ምነው" ብል "አትንቀልቀል" ተባልኩ። ነገሩ ስለከነከነኝ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠየቅኩ።

የኔ እቅድ ሰ ዶ ማ ዊነ ት ን በተመለከተ 3 ፕሮግራሞች መስራት ነበር። የ ሰ ዶ ማ ዊ ነ ት ጉዳት በባለሞያ እንዲብራራ ማድረግ የመጀመሪያው ክፍል ነው። ሁለተኛው ክፍል የችግሩ ሰለባ ሰዎች እንዴት ከችግሩ ሊወጡ ይችላሉ ለሚለው ጥያቄ ከባለሞያዎች መፍትሔ ማፈላለግ ሲሆን፥ የመጨረሻው ክፍል ታዳጊ ልጆች ወደዚህ ዝንባሌ እንዳይገቡ ምን ይደረግ የሚል ነበር።

ፕሮግራሙን ለመስራት ከማቀዴ በፊት አሳሳቢ መፅሐፍትን አንብቤ ነበር።
"ውስጥ አዋቂ"
"የአዲሳባ ጉዶች"
"የአማፃ መንገድ"
"የ ሰ ዶ ም ነፍሳት" የሚሉ መፅሐፍት አንብቤ ስጋት ውስጥ ገብቼ ነበር።
"ባህላችን አይደለም" በሚል መንገድ ብቻ ችግሩን ማቆም እንደማይቻል እንዳስብ ሆኛለሁ። "ምንድነው መፍትሄው?" ብዬ ባስብ... ግንዛቤ ማስጨበጥ ፥ ሞያዊ ትንታኔ ማቅረብ መላ መስሎ ተሰማኝ። በዚህ መሰረት ፕሮግራም ሰራሁ፤ አይተላለፍም ተባለ።

መጨረሻ ላይ የተሰጠኝ መልስ ፈገግ የሚያሰኝ ነበር። "ስለ ጉዳቱም ቢሆን ማውራት ማስታወቂያ መስራት ነው። ስለዚህ ምንም አይወራ" ተባለ

በእውነት?
እንደዛ ነው?

ጉዳቱን ማውራት ማስተዋወቅ ነው ማለት የሰውን ንቃተ ህሊና መሳደብ ነው። የመፍትሔ መንገድ እንፈልግ የሚልን ሰው እንደ አስተዋዋቂ መቁጠር የሰውን የማሰብ አቅም መሳደብ ነው።

ዛሬ ላይ በግልፅ መወያየት እና ሳይንሳዊ መፍትሔ መፈለግ ግዴታ ነው። ማስተዋወቅ ይሆናል በሚል ስም ስለ ጉዳዩ አለማውራት የገዛ እግርን በጥይት እንደመምታት ነው።

በዚህ ዘመን ኢንተርኔት አለ። መረጃ መታፈን አይችልም። ፊልሙ ለዝንባሌው ቀስቃሽ ግብአት ነው። አደንዛዥ እፅም የራሱ ሚና አለው።
ለችግሩ መባባስ ብዙ አስቻይ ሁኔታ ባለበት ዘመን ላይ "ማስተዋወቅ ስለሚሆን ዝም እንበል" አይባልም።

ይልቅ ከስሜት መውጣት ያስፈልጋል።

አንዳንድ ሰዎች ስሜት የተጫነው ዘመቻ ከፍተዋል። ስሜት ብዙ ጉዳት ያስከትላል። ማስተዋል ያስፈልጋል።

ባህልም ቢሆን ስታንዳርድ አይደለም። "ባህል አይፈቅድም" ማለት ብቻውን ውጤት አያመጣም። አእምሮን መጠቀም ያስፈልጋል። ሳይንሳዊ መፍትሔ መሻት አለብን።

ከስነልቦና ፥ ከፍልስፍና ፥ ከሶሾሎጂ እንዲሁም ከአእምሮ ጤና አንፃር መፍትሄ መፈለግ አለብን።


@Tfanos
13👍1
"የሴት ልጅህን ብልት ተልትለሃል" አሉት።

"ወላሂ አላደርኩትም" ቢልም አልታመነም። ምስክሮች ቢደረድርም ተቀባይነት አላገኘም። "ስለት ተጠቅመህ የገዛ ልጅህን ብልት የተለተልክ አ ረ መ ኔ ነህ" አሉት።

ካሊድ ይባላል። ኢትዮጵያዊ ነው። ውልደት እና እድገቱ መርካቶ ነበር። በትምህርቱ ሰቃይ፥ በባህሪው ምስጉን ሆኖ አደገ። ካደገ በኋላ ለብዙ ሰዎች "የተስፋይቱ ምድር" ወደ ሆነችው አሜሪካ አቀና። በአሜሪካ ኑሮውን ቀጠለ።

በአሜሪካ ሳለ ከደቡብ አፍሪካ ከሆነች ሴት ጋር ተዋውቆ ትዳር መሰረተ። በፍቅር የተሟሟቀ የትዳር ቆይታ ነበራቸው። በትዳራቸው ሴት ልጅ አፍርተዋል።

ከእለታት በአንዱ ጎጇቸው ዘመመ። ትዳራቸው ተነቃነቀ። ፍቅራቸው ደፈረሰ።
የደፈሰው አልጠራም። የዘመመው አልተቀናም። ትዳራቸው ፈረሰ።

ከትዳራቸው መፍረስ በኋላ "ክፉኛ እጎዳሃለሁ" ብላ የቀድሞ ሚስት ዛተች።..
አንድ እለት ለካሊድ መጥሪያ ደረሰው። በቀድሞ ባለቤቱ ክስ እንደተመሰረበት ተነገረው። ክሱ "ሴት ልጅህን ገርዘሃታል" የሚል ነበር። ካሊድ የተባለው አስገርዘሃታል አይደለም። ገርዘሃታል ነው።ክሱ በገዛ እጅህ ሴት ልጅህን ገርዘሃታል የሚል ነው።

ካሊድ ክሱን ሊያስተባብል ፍርድ ቤት ቀረበ። "አላደረግኩትም" አለ። "በሃይማኖቴም በባህሌም የሴት ልጄን መራቢያ መመልከት ፥ መነካካት አይፈቀድልኝም። እንዴት አድርጌ እገርዛታለሁ?" አለ። ሰሚ አላገኘም። "አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ፥ ሐገርህ ኋላቀር ናት። ጎጂ ልማዶች ካሉባት ሐገር መምጣትህ ብቻውን ያስጠረጥርሃል" አሉት።

ማስረጃዎችን ደረደረ።

ልጅቷ ተገረዘች በተባለችበት ወቅት ካሊድ ስራ ላይ ነበር። ስራ ገበታው ላይ ለመሆኑ ማስረጃ አቅርቧል። ከሳሽ "ከስራው ቀርቶ ነው የገረዛት" ነበር ያለችው። በተባለበት ወቅት በስራ ገበታው ላይ ለመገኘቱ ማስረጃ አቀረበ።

የውሸት ፈተና በሚፈትን ማሽን ፊት ተቀምጦ ያለምንም ችግር አልፏል። ማሽኑ "እየዋሸ አይደለም" ብሎ መስክሮለታል። በተቃራኒው ከሳሽ በማሽኑ ፊት ቀርባ ለመፈተን ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርድ ቤት ከሳሽን በውሸት መፈተኛው እንዳትፈተን ፈቀደላት። ይህ ግራ አጋቢ ውሳኔ ነበር።

ከሳሽ ካሊድ ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ ታደርስበት ነበር። "ልጅህን ለዘላለም እንዳታገኛት አድርግሃለሁ" ብለዋለች። መኪናው ላይ ጉዳት አድርሳለች። እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ካሊድ ለፍርድ ቤት አቀረበ። "ሆነ ብላ እየጎዳችኝ ለመሆኑ ማስረጃ ይሆነኛል" ቢልም ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገበት።

ካሊድ ሴት ልጁን በገዛ እጁ እንደገረዛት ነበር የተነገረው። በኢትዮጵያ ግርዛትን ማንኛውም ሰው እንደማይፈፅም ፥ ለመግረዝ ልምድ እንደሚያስፈለግ ለፍርድ ቤት ቢያስረዳም ማብራሪያው ውድቅ ተደረገበት።

"የተገረዘች ሴት ቁስለት ስለሚኖርባት መገረዟ ወዲያው ይታወቃል። ልጄ ላይ ደግሞ ይህ አልታየም" አለ። ይህም ውድቅ ተደረገበት።

የህፃናት ስነልቦና ባለሞያዎች ተገረዘች የተባለችውን ልጅ አጥንተዋት ነበር። "ልጅቷ እየተናገረች ያለችው ትልቅ ሰው ያሰለጠናትን ነው" አሉ። የባለሞያዎችም ሃሳብ ውድቅ ተደረገ።

ካሊድ ማለ። "ወላሂ አላደርግኩትም" አለ። ተሰሚ አልሆነም።
ፍርድ ቤት ካሊድን በአስራአምስት አመት እስራት ቀጣው። አስራ አመስት አመታት ሊታሰር ወደወህኒ ወረ።
ካሊድ የተፈረደበት ቀን የካሊድ ጠበቃ አለቀሰ። "ካሊድ ሐቀኛ ነው። ማስረጃዎች ነበሩት" ብሎ አለቀሰ። ጠበቃው ነፃ ሊያወጣው ስላልቻለ አነባ።

ካሊድ ወሂኒ ሆኖ ይግባኝ አለ። ታዋቂ ጠበቆች ይግባኝ ጠየቁለት ፥ ነገር ግን ፍትህ ተነፈገ። ይግባኙን ፍርድ ቤት ጣለበት።

ካሊድ እስር ቤት ዘጠኝ አመት ከቆየ በኋላ አመክሮ ተፈቀደለት። ስነስርዓት ያለው ታራሚ ስለሆነ በአምክሮ ይለቀቅ ተባለ። ከዛስ... ሳይለቀቅ ቀረ።

ካሊድ "ፍትህ ያጣ እንባ" በሚል ርዕስ ህይወት ታሪኩን ፅፎታል። እርሱ ፍትህ የተነፈገ ሰው ነው። ለምን ፍትህ ተነፈገ? አጭሩ መልስ በሚዲያ የተነሳ ነው።

ካሊድ እንደተከሰሰ ሚዲያ አጀንዳውን አጮኸው። "በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የገረዘ ሰው ለፍትህ ሊቀርብ ነው" የሚል ዜና ተቀባበሉ። ጋዜጠኞች ካሊድን ተቀባበሉት። "የመጀመሪያው የሴት ገራዥ ሊቀጣ ነው" አሉ።

ካሊድ በመፅሐፉ ላይ "የሚዲያ ተፅዕኖ ፍትህ እንዳጣ አድርጎኛል" ይላል።

በእርግጥ የህዝብ ጩኸት ፍትህ ያዛባል።

የህዝብ ጩኸት እውነታቸውን የቀበረባቸው ፥ የሚዲያ ዘመቻ ፍትህን የቀማባቸው ብዙ ናቸው።

ይህ ምን ያስተምረን ይሆን?

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
😢22👏2
ሁለቱ መምህራን
* * *
አንዳንድ ሰው ስራው ገናና ነው። ታሪኩ በብዙ የሚተረክ ፥ ተግባሩ የሚወደስ ፥ ገናናነቱ የሚዘከር ነው። ልክ እንደ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር

ስለ ዶክተር ተወልደ ምን እንላለን? በእርግጥ ብዙ ማለት እንችላለን። ደግሞም በጥቂት ቃላት መገለፅም እንችላለን። "የምድራችን ጀግና" በሚል የከበረ ስምም ልንጠራውም እንችላለን።

ስለ የምድራችን ጀግና ማብራራት አይደለም ሃሳቤ። የምድራችንን ጀግና ዶክተር ተወልደን ያስተማሩ ሁለት መምህራንን ላስታውሳችሁ

1፥ ዶክተር ተወልደ አንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ወቅት ከአንድ መምህሩጋ መግባባት አቃተው። (ባልሳሳት የ5ኛ ክፍል ተማሪ ነበር) ቀለሜው ተማሪ ከአስተማሪው መግባባት አለመቻሉ በአጭር አልተቋጨም። ለቤተሰብ ስሞታ ቀረበ።

"ተወልደ ብርሃንን ተው በሉት" ተባለ።
"ምንድነው ጥፋቱ?" አሉ አክስቱ።
"ይፈጥናል፥ ይንቀለቀላል"
"እኮ እንዴት?"
"በዚህ አመሉ ከቀጠለ ያ ብ ዳ ል"
"እንዴት ሆኖ?"
"መጠየቅ ያበዛል፥ ጥያቄዎቹ ለሱ እድሜ የሚሆኑ አይደሉም። የአስራሁለተኛ ክፍሎችን ጥያቄ ይጠይቃል"

(ውይይቱ ቃል በቃል እንዲህ አይደለም። ሃሳቡ ግን የተፃፈው ነው)

ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር በልጅነቱ አእምሮው ፈጣን ነበር። ለመምህሩ ፈታኝ ጥያቄ ያቀርባል። በሚያሳስዝን ሁኔታ መምህሩ የአእምሮውን ፍጥነት ጠላ። አስተማሪውን ጠጣር ጥያቄ መጠየቁ እንደ ጥፋት ቆጥሮ ስሞታ አቀረበ።

2

ሁለተኛው መምህር ልዩ ሰው ነው። ጌታቸው ቦሎዲያ ይባላል። አዎን ታላቁ ጌታቸው ቦሎዲያ!
ተወልደ ብርሃን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለ ጌታቸው የነ ተወልደ መምህር ነበር። ከእለታት በአንዱ ጌታቸው ለተማሪዎች ማብራሪያ አቀረበ። የመምህሩ ማብራሪያ ከተማሪዎች መካከል ለአንዱ አልተዋጠም። ተወልደብርሃን ቅር ተሰኘ።

"መምህር የተሳሳቱ ይመስለኛል" አለ ተወልደ
"የቱጋ?"
ተወልደ አብራራ።
ጌታቸው ቦሎዲያ የላቀ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ምላሽ ለተወልደ መለሰ። "ልክ ልትሆን ትችላለህ፥ ስለዚህ እኔም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ነገር ላጥና። መፅሓፍ ላገላብጥ። አንተም ተጨማሪ ነገር አንብብ። ከሁለታችን የማናችን ልክ እንደሆነ እናመሳክራለን" አለ። (ቃል በቃል አይደለም)

ጌታቸው እንዴት ያለ ታላቅ መምህር ነው? በተማሪዎች ፊት ተሳስቼ ይሆናል ለማለት የሚያስደፍር የሞራል ልዕልና ነበረው። ከተማሪዎቹ መካከል በአንዱ "ሳይሳሳቱ አይቀርም" ሲባል ለማድመጥ ፈቃደኛ ሆነ።

ብዙ መምህራን በሁለቱ የተወልደ መምህራን የሚወከሉ ይመስለኛል

ስለ ዶክተር ተወልደ ሌላ ጊዜ በሰፊው እንጨዋወታለን

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
7
"እ ብ ድ ነኝ" ፥ የአንዳርጋቸው ፅጌ ድራማ
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
በዘመነ ደርግ ለእድገት በህብረት ዘመቻ ከተመረጡ ወጣቶች መካከል አንዱ አንዳርጋቸው ፅጌ ነበር። አንዳርጋቸው በዘመቻው ደስታ አጣ፥ ከዘመቻው ለማምለጥ ወጠነ።

በወቅቱ ወጣት የነበረው አንዳርጋቸው ያኔ የኢህአፓ አባል ብቻ ሳይሆን ዋና አመራሮችን ከቦታ ቦታ የሚውስድ ሹፌራቸው ጭምር ነበር። እናም 'ከዘመቻው አምልጬ የኢህአፓን ስራ ልከውን' ብሎ ወጠነ፥ ውጥኑም እንዲሰምር ድራማን ፈጠረ።

ከእለታት በአንዱ እንዲህ ሆነ። ለሊት ነው፥ አብዛኛው ሰው እንቅልፍ ላይ ሳለ ያልተኙቱ ተተራመሱ። በኡኡታ እንቅልፍ ላይ ያሉትን አነቁ፥ ጠባቂዎች ተጣድፈው ወደ ስፍራው ደረሱ።

የመተራመሱ ሰበብ አንዳርጋቸው ነበር። ጨርቅ ቀዶ ራሱን ሰቆሎ ሊ ገ ድ ል ሲል ደረሱበትና አተረፉት። ግራ መጋባትና ውክቢያ በቤቱ ተፈጠረ።
'ምን ነክቶት ሊሞት አሰበ' ተብሎ ሲጠየቅ ከወዳጆቹ "አልፎ አልፎ የሚነሳ የአእምሮ ህመም አለበት፥ ይህን ያደረገው እብደቱ ተቀስቅሶ ነው" የሚል መልስ ተሰጠ።
የነገሩን ልክነት ለማጥራት ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰደ። በምርመራ ቦታ አንዳርጋቸው ግድግዳው ላይ እያፈጠጠ መዛበረቅ ጀመረ። ለሚቀርብለት ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ ሁሉ አራምባና ቆቦ ሆነ። ይሄኔ መርማሪዎች 'ይህ ወጣት የአእምሮ መታወክ አለበት' ብለው ደመደሙ። አብሯቸው ቢቆይ ድንገት ህይወቱን በገዛ እጁ ሊያጠፋ እንደሚችል ጠረጠሩ። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ እሱን ማሰናበት ሆነ።

አንዳርጋቸው ፅጌ ያኔ እንደ እብድ ሆኖ የታየው ድራማ ሲሰራ ነበር። ከዘመቻው የማምለጫ እቅድ ማዘጋጀት ሲጀምር አልፎ አልፎ የሚነሳ 'የአእምሮ መታወክ' እንዳለበት ውስጥ ውስጡን አስወራ። ቀጥሎ ገመድ ይዞ ራሱን ሊ ገ ድ ል እንዳሰበ አስመስሎ ተወነ። ይሃኔ እብደቱን ያመኑቱ በድንጋጤ በገጠር ያለውን ዘመቻ አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ወሰኑ።


@Tfanos
9
'አማራ በትግራዩ ጦርነት'
* * *

በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትግራዩ ጦርነት ዋና አክተሮች የአማራ ኤሊት ይመስላቸዋል፥ ወይንም አስመስለው ያቀርባሉ።
የትግራዩ ጦርነት ተዋናዮችን ማንነት በብሔር መመደብ ፥ በነገድ ኮታ መስጠቱ አስፈላጊ ባይሆንም አማራን ለሚወቅሱቱ አግባባዊ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።

ከልደቱ አያሌው እስከ ኢንጂነር ይልቃል ፥ ከቴዎድሮስ አስፋ ወሰን እስከ ያየሰው ሽመልስ ጦርነቱን ተቃውመዋል፤ የኤርትራን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል፣ ለህዝቡ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። እውነት ለመናገር የትግራዩን ጦርነት ያወገዙ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ብዙ ነው። ምናልባት ከጦርነቱ አውጋዦች መሓከል ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው።
ይሄን እውነት ቸል ብሎ አማራን መኮነን ጥፋት ነው።

ምናልባት 'ብዙ አማራዎች ጦርነቱን ደግፈዋል' የሚል ክርክር ይመጣ ይሆናል፤ ይህ ከፊል እውነት ነው። ጦርነቱን የደገፉት ከአማራ የተወለዱት ብቻ አይደሉም። ከሁሉም ብሔር የተውጣጡ ሰዎች ለጦርነቱ ድጋፍ ሰጥተዋል፥ ዘመቻውን መርተዋል። ጦርነቱ ላይ በፕሮፖጋንዳ ፥ በፖለቲካ አመራር ፥ በጦር ተሳትፎ የነበራቸውን የሌላውን ብሔር ተወላጆች በብዛት መቁጠር ይቻላል።

አለማዬ ፥ ጦርነቱን በብሔር ኮታ መከፋፈል አይደለም። ነገር ግን አግባብነት በጎደለው እና ከአውድ በወጣ መንገድ አማራን መውቀስ ህዝብን ለጥቃት የሚያመቻች በትር ማቀበል እንዳይሆን ማሰብ ያስፈልጋል !

@Tfanos
12👏1😁1
የመፅሐፍ ምርቃት

"የዙፋን ልፊያ" ነሐሴ 23 ይመረቃል።

አድራሻ ፥ አራት ኪሎ ዋሊያ መፅሐፍት

10 ሰአት ተኩል።
🔥95
አብይ አህመድን መናቅ ማንን ጠቀመ?
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
"አብይ አህመድ የክፋቱን ያህል እውቀት ቢኖረው...."
ከላይ ያለው አገላለፅ የቴዎድሮስ ፀጋዬ ነው። ቴዲ አብይ አህመድ ክፉ እንደሆነ ደጋግሞ ተናግሯል፥ አስረድቷል። አብይን "ክፉ" ከማለቱ መሳ-ለመሳ አብይ አላዋቂ ስለመሆኑ አብራርቷል። "አብይ አህመድ ደ ደ ብ ነው" ይላል። አብይ በዚህ ክፋቱ እውቀት ቢኖረው ከአሁኑ የከፋ ጥፋት እንደሚፈፅም አስረድቶ ያውቃል።

አብይ ደ ደ ብ ነው?
በእርግጥ አብይ አህመድ ደ ደ ብ ነው? በእውነቱ አብይ ደ ደ ብ ነው?

ብዙ ሰው፥ ጠቅላይ ሚኒስተሩ እውቀት የለሽ፥ ልፍስፍስ ፥ ንክ ፥ ወዘተ እንደሆነ ያምናል። አብይ መራሹ ብልፅግና መንግስትም ፍፁም ደካማ ፥ ለመውደቅም አንድ ሃሙስ የቀረው ይመስለዋል።

በእርግጥ፥ እውነታው እንደዛ ነው?

አብይ እየተናቀ ሰባት አመት ገዝቷል። ቀጣይ ብዙ የስልጣን አመታት ከፊቱ እንዳሉት በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።

አብይንና ብልፅግናን በስልጣን ካቆዩት አስቻይ ሁኔታዎች መካከል አንዱ እንደደካማ መቆጠሩ ይመስለኛል። ብዙ ሰው የአብይን የማድረግ አቅም ዝቅ አድርጎ ይገምታል። ብልፅግና በአንድ ግፊ የሚወድቅ ልፍስፍስ ፓርቲ ይመስለዋል።

አንዳንዴ ዝቅ ተደርጎ መቆጠር ድል ማድረጊያ መሳሪያ ይሆናል። ባለጋራውን ደካማ እና ምንም አቅም የሌለው አድርጎ የሚያስብ ተፋላሚ አያሸንፍም። ተፎካካሪውን በቀላሉ እንደሚረታ ገምቶ ወደ መፋለሚያ ቦታ የሚወርድ ፥ በቂ ዝግጅት አያደርግም። የቤት ስራውን አይሰራም። በተቃራኒው እንደደካማው የሚቆጠረው አቅሙን አሟጦ ይጠቀማል። እስከመጨረሻው ጠብታ ይፋለማል።

"አብይ ደ ደ ብ ነው" ብሎ የሚያስብ ፖለቲከኛ በቂ የእውቀት ትጥቅ ታጥቆ እየተፋለመ ነው? አይመስለኝም።
ብልፅግና ለመውደቅ አንድ ሀሙስ የቀረው ልፍስፍስ እንደሆነ የሚያምኑ የቤት ስራቸውን እየሰሩ ነው? አይደለም።

ተቃዋሚዎች አብይን እያናናቁት ፥ አብይ ሰባት አመት በመንበር ቆይቷል። ተቃዋሚዎች ንቀታቸውን እስኪያቆሙ ድረስ አብይ በመንበር ይቀጥላል።

በግጥም እንዝጋው። (2013 ዓ.ም የፃፍኩት ግጥም ነው። በእርግጥ ግጥሙ መስመር በመስመር አብይን ይወክላል ማለት ላይሆን ይችላል)
የድል መንገድ
* * *
ለተጋጣሚ አይን ፥ አንሶ የቀረበ
ለፍልሚያ አውድማ ፥ አሻግሮ ያሰበ
ትምክህትን የቀጣ፥ ራሱን ያልካበ
አቅመቢስ በመምሰል፥ ጠላት አሰነፈ
ባለጋራ ሲሞኝ፥ እርሱ አሸነፈ

ቂ ሎ ች ለመሸነፍ ፥ጠላትን ሲንቁ
ደካማ በመምሰል፥ ድልን መቀናጀት፥ ጠቢባን አወቁ


@Tfanos
8
የሴቶች ዘመን ከደጅ ነው!
(ተስፋኣብ ተሾመ)
***
ጥንት ጉልበት የብዙ ነገር ምንጭ ነበር። ውትድርናው ጉልበትን ይሻል፥ መብልና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ያለ ጉልበት ማሟላት አይቻልም፥ ለመኖር ጉልበት ወሳኝ ነበር። አያቶቻችን ያድናሉ ፥ ይለቅማሉ። ይፈለማሉ። ይህን ለማድረግ ጉልበት የሌላቸው ይሸነፋሉ። ሲስተሙ ገፍቶ ይጥላቸዋል።

ዘመን ተለወጠ።

ልዩ እና ታላቅ አብዮት ተከስተ። የአንዲስቱሪ አብዮት ፈነዳ። የኢንደለስትሪ መስፋፋት የሰውን አኗኗር ለወጠ።
የኢንዱስትሪ አብዮት ጉልበትን በእውቀት የሚተካ መደላድልን ፈጠረ። ከዘመን ዘመን ሳይንስ ደረጀ፥ ቴክኖሎጂ ፈረጠመ። የጉልበት አቅም ኮስሶ የእውቀት ተመን ይጨምር ዘንድ የግድ ሆነ።

ይህ ለሴቶች ታላቅ የምስራች ነው!

ሁላችንም እንደምናውቀው ሴቶች በጉልበት ከወንድ ያነሱ ናቸው። በዚህ የተነሳ ሃይል የሁሉም ነገር ምንጭ በነበረበት ዘመን ወንዶች ቁንጮ ሊሆኑ ችለዋል። ይህ ግን የሚያበቃበት ዘመን ተቃርቧል።

ውትድርናን ጨምሮ ትልልቅ ጉዳዮች ለሳይንስ የሚገብሩበት ዘመን እየመጣ ነው። ትላንት ግብርና ያለ ጉልበት አይታሰብም። ዛሬ ግን ሳይንስ ምስጋና ይግባውና አእምሮ ጉልበትን እየተካ ነው። ትላንት ውትድርና ያለ ጉልበት አይታሰብም። ነገ ግን ይህ ይቀየራል። ሳይንስና ቴክንሎጂ ውትድርናን ከጉልበት ወደ አእምሮ ይወስደዋል። ከዚህ ቀደም ጉልበት ብዙ ተፅዕኖ ነበሰው። ነገ ግን አእምሮ ዋና ይሆናል። ያኔ መወዳደሪያው ጉልበት ሳይሆን እውቀት ይሆናል።

ትላንት ሃይል ዋና ነገር ሳለ ሴቶች በጉልበት ከወንድ ያንሱ ነበር። ነገ እውቀት ዋና ነገር ሲሆን ግን ሴቶች በአእምሮ ያነሱ አይደሉምና መወዳደሪያው ላይ አቻ ይሆናሉ።

ተራ ነገር ቢመስልም ሴቶች ውበት የሚባል ተጨማሪ ሃይል አላቸው። ይህ ተራ አባባል ይመስል ይሆናል። እውነታው ግን ውበት በሰዎች ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አድራሽ ነው።
ሰዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጥቂት ነገሮች አሉ። አንዱ ውበት ነው። ሌሎቹ ደግሞ ፣ ስልጣን ፥ ሀብት ፥ እውቀት እና ዝና ናቸው።

ሴት ውበት አላት። ይህ ተጨማሪ እድል ነው።

የሴቶች ዘመን በደጅ ነው።

ነገ ሴቶችን "ከናንተ እኩል እንድንወዳደር ውበታችሁን ቀንሱልን" ለማለት እንገደድ ይሆናል።

ሴቶች ፥ ከፊታችሁ ላለው ዘመን በሚገባው ልክ ተዘጋጁና ዘመናችሁን ውረሱት !


@Tfanos
👍4
"ልጅነት የሚያደርሰውን ጉዳት ጠላት አያደርሰውም"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ሰሞኑን የዘሪቱ ከበደን መፅሐፍ ሳነብ ነበር። "ከልጅነት እስከልጁነት" ን ጓግቼ ነው የገዛሁት። ፈጥኜም አነበብሁት።
መፅሐፏን ሳነብ የተለያዩ ስሜቶች ተሰምተውኛል። ቅሬታ ፥ ግርታ ፥ ፈገግታ ፥ መደነቅ ተፈራርቀውብኛል። በተለይ ልጇ ክርስቲያን ላቀው በሆስፒታል ፅኑ ህሙማን ክፍል ሳለ የነበራት ስሜት ሃዘን ውስጥ ከቶኛል። በበገና ስቱዲዮ የነበራቸው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ትኩረቴን ስቦታል።ዘሪቱ እና ጓደኞቿ መፅሐፍ ቅዱስን የተረዱበት መንገድ ፥ ፀጋና ሕግን የበየኑበት አግባብ ፥ ለሃይማኖቶች ያላቸው ምልከታ ብዙ ያወያያል።

ከዘሪቱ መፅሐፍ ትኩረታችሁን የሳበው የቱ ነው?

ከንባባችን በኋላ ወደ ልባችን የሚቀረው ልዩ ልዩ ነው። አንዳችን ልብ ውስጥ የቀረ በሌላው ያልታየ ይሆናል።

"ልጅነት የሚያደርሰው ጉዳት ጠላት ከሚያደርሰው የከፋ ነው" ይህን አባባል ያገኘሁት ከዘሪቱ መፅሐፍ ነው። (አባባሉ ቃል በቃል አይደለም) የዘሪቱ ከበደ እናት ልጅነት ከባለጋራ በላይ ጉዳትን እንደሚያደርስ ትናገር ነበር። የእናቷን አባባል ዘሪቱ የተረዳችው ዘግይታ ነው።

ልጅነት ልዩ ልዩ ነው። በአካል ልጅ መሆን አለ። ደግሞ የአእምሮ ልጅነት አለ። አንዳንዱ በስነልቦና ያልበሰለ ልጅ ነው። አንዳንዱ በመንፈሳዊ ነገር ልጅነት ያጠቃዋል። ከልጅነት እውነተኛ ገፅታዎች መካከል አንዱ አለመብሰል ነው። (ሌላው ደግሞ ንፅህና)

ዘሪቱ በይፋ እንደነገረችን ከሆነ ማመፅ ያስደስታት ነበር። እርሷና ባሏ ትዳርን በሚያስቡበት ወቅት ባህላዊ ሰዎችን እንደ ኋላ ቀር ቆጥረው ይንቁ ነበር። ሰርጋቸው ላይ ጭምር ባህል ላይ ያላቸውን አመፅ አሳይተዋል።

ልጅነት ያሳምፃል። ልጅነት ነገሮችን በእኛ አቅጣጫ ብቻ እንድናይ ይገፋናል። በልጅነት ስሜት ይገናል። የቀደመውን ልማድ እንደ አሮጌ ቆጥረን እንድንንቀው ያደርጋል።

ዘሪቱ "ምናልባት ባህልን እና ትልልቅ ሰዎችን በጭፍን ከማናናቅ ይልቅ፥ የሚናገሩትን ብሰማቸው አንዳንድ ጉዳቶችን ማስቀረት እችል ይሆናል" ትላለች።

ልጅነት ልዩ ልዩ ነው ብለን አይደል?

አንዳንዴ ባለመብሰላችን የተነሳ ያመፅንባቸው ልማዶች አሉ። ልጅነት ገፋፍቶን ከእኛ አንፃር ብቻ የተመለከትናቸው ነገሮች አሉ። ስሜታችንን መከተል ዋና ነገር መስሎን ያውቃል። ታላላቆቻችንን ማድመጥ አስፈላጊነቱ ይጠፋብን ይሆናል። ይህ ሁሉ ልጅነት ነው።

በህይወታችን ትልልቅ ተግዳሮቶች ይገጥሙናል። አንዳንዴ ባለጋራ ከፈጠረብን መከራ በላይ አለመብሰላችን የፈጠረው መከራ ይገዝፋል።

በእርግጥ ልጅነት የሚያመጣው ችግር ፥ ጠላት ከሚያመጠው የከፋ ይሆናል። ከሌላ የሚወረወርን ፍላፃ መመከት ወይም መሸሽ ይቻል ይሆናል። ከራስ አለመብሰል የሚመዘዝን ሰ ይ ፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?

በእርግጥም በስሜት ፥ በእውቀት ፥ በመንፈሳዊ ነገር አለማደግ ታላቅ ፈተና ነው።


@Tfanos
@Tfanos
2
የመፅሐፍ ምርቃቱ ተሰርዟል!

"የዙፋን ልፊያ" የተሰኘች መፅሐፌን የፊታችን አርብ እንደማስመርቅ አስተዋውቄ ነበር። ነገር ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክኒያት የመፅሐፉ ምርቃት ተሰርዟል።

ስለሆነም ፥ "የዙፋን ልፊያ" ያለ ምርቃት ሰሞኑን ለገበያ ትቀርባለች።

ይህን ላልሰሙ አሰሙ።
🤔5👍4
ህዳሴ ግድብ ማለቁ ደስ ይላል። ግን ደስታዬ ከፊል ነው።

ኢትዮጵያ የግድቡ የተረጋገጠ የባለቤትነት ዋስትና የላትም። ነገ ጠዋት ቤንሻንጉል ክልል ልገንጠል ቢል አስቻይ ሁኔታ አለው። ዜጎች መቀነታቸውን ፈተው የገነቡት ግድብ ቋሚ ሀብት ለመሆኑ ሽራፊ ማረጋገጫ የለም።

ክልሎች እጩ ሐገር ናቸው። ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ሉኣላዊ ሐገር እንዲሆኑ ሕገመንግስታዊ ድጋፍ አላቸው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደገፍ እንዲሉ የፖለቲካ ልዩነታችን ከእለት እለት እየሰፋ ይገኛል።
እርስ በእርስ እየተገፋፋን ፥ እየተቃቃርን ፥ እየተዋጋንና እየተቆራረጥን ነው።

ለምሳሌ ግድቡ የሚገኝበት ቤንሻንጉል ክልል ባለፉት አመታት ችግር ውስጥ ነበር። የየብስ ትራንስፖርት ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ግጭትም ነበር። ይህ ወዴት ይወስዳል?

አንድ ዜጋ ለዳር ድንበር ህይወቱን ከከፈለ በኋላ ፥ ያ ቦታ ሊገነጠል ይችላል። ታዲያ ለሐገር ደም ማፍሰስ ለምን?

ትግራይ ፥ ቤንሻንጉል፥ አማራ ፥ ኦሮሚያ ፥ ሶማሌ ወዘተ እጩ ሐገራት ናቸው።

የመገንጠል ስጋት እያለ ፥ የሆነ ክልል ላይ የተገነባ ሐብት ሐገራዊ ሊሆን ይችላል? አይመስለኝም!

@Tfanos
🔥116👍5😢3
2025/10/22 16:50:01
Back to Top
HTML Embed Code: