Telegram Web Link
👍71🔥1
ባለሥልጣናቱ በአንደበታቸው ቃል ይዋጋሉ። ወታደሮች በጠመንጃ ይጠዛጠዛሉ። የሀብታሞችን ጦርነት ድሆች ይዋጋሉ። የሹማምንት ልፍያ የተርታ ዜጎች ፍልሚያ ነው።

ፀሐይ ወደ ዘወትር ማደሪያዋ ስትከተት የሐገሪቱ ጨለማ ጀመረ። ጨረቃ የጠለቀችውን ፀሐይ ልትተካ አልወደደችም። ሰማዩ ፅልመት ሲለብስ ሰይፍ ከሰገባ ተመዘዘ።

መልዓከ-ሞት ስራ በዛበት።
አንገቶች እየተቀሉ ወደቁ፣ አንጎሎች ተበረቀሱ፣ እልፍ ደረቶች የጥይት ናዳ ወረደባቸው፣ እጆች ተቀነጠሱ፣ እግሮች ተቆርጠው ሜዳ ላይ ወደቁ።

ለወራት ዝናብ ጠምቶት የነበረ ደረቅ መሬት በሰው ደም ራሰ፣በረሃው በደም ጨቀየ።

ጦርነቱ በጀመረ የሰዓታት ውስጥ እድሜ አ ጋ ን ን ት ተፈትተው የተለቀቁ መሰለ፣ ተቆጥሮ የማያልቅ ነውር ተፈፀመ፣ ባልተገራ ሰውነት ውስጥ ተሸሽጎ የከረመ ሰ ይ ጣ ን ተገለጠ።

ከመምሸቱ በፊት እንዲህ አልነበረም።

ፀሐይ ስትጠልቅ የሐገሪቱ ጨለማ ጀመረ። ሰዎች ወደ አ ው ሬ ነ ት ተለወጡ፣ አ ጋ ን ን ት አካል ለብሰው ተንቀሳቀሱ፣ ወሲብን አጣጥመው የማያውቁ ወጣቶች ከእናቶቻቸው በእድሜ የሚበልጡ ሴቶችን በማስገደድ ተገናኙ፣ ወንዶች በወንዶች ተደፈሩ፣ ወጣት ሴቶች ወደ ማሕጸቸው ብረት ገባ።

አስገድዶ በመድፈር ብቻ በውስጣቸው ያለውን አውሬ ማርካት ያልቻሉ፣ በደፈሯቸው ሴቶች ብልት ላይ ጥይት አርከፈከፉ።

ሐገሪቱ እንዲህ አልነበረችም።

ፀሐይ ከመጥለቋ የሐገሪቱ ጨለማ ጀመረ።

አብሮ በኖረ፣ ክፉና ደጉን በጋራ ባሳለፈ፣ ከዘመድ ይልቅ ቅርብ በተባለ ጎረቤት መዘረፍ የማያስደነግጥ ሆነ። ብዙ ዜጎች በአንዲት ምሽት ገሀነም ምን እንደሚመስል አወቁ።
‹‹አንድ ጥይት ይበቃኛል፣ በአንዲት ጥይት ብቻ ገላግሉኝ›› ይላሉ ሞት የራባቸው ወጣቶች።
ተስፋ ነበራቸው። ብዙ የመኖር፣ ወላጆቻቸውን የመጦር፣ ልጆቻቸውን ለወግ ማዕረግ የማብቃት ፣ ታናናሾቻቸውን የመርዳት ፣ ታላላቆቻቸውን የማኩራት... ተስፋ ነበራቸው። ተስፋቸውን ፖለቲካ በላው።

ጥይት ያጎደለው አካላቸው ስቃይ ፈጥሮባቸዋል። የውሃ ጥማቱን፣ የቁስሉን ጥዝጣዜ መቋቋም ሲያቅታቸው ሕይወታቸውን ንቀው ሞትን ናፈቁ።

በየአቅጣጫው የተበተነውን ጦረኛ ‹ግ ደ ሉን › ይላሉ። ሞትን ይለምናሉ።

‹‹ጠብታ ውሃ ይበቃናል››
‹‹በአንዲት ጥይት አሰናብቱኝ››
‹‹እማዬ ነደድኩልሽ››
‹‹ልጄ ናፈቀኝ››
‹‹ሚስቴን ሳልሰናበት››
የሰቆቃ ድምፆች በየአቅጣጫው ይሰማሉ።
ከመምሸቱ በፊት ቀኑ ከሌላው ቀን የሚለይ አይመስልም ነበር።


#የዙፋን_ልፊያ ገፅ 11

@Tfanos
3
የምስር ወጥ እንቁጣጣሽ...

ቂጣ በጎመን አልወድም። ከምግቦች ሁሉ በቁጥር አንድ የምጠላው ሳይሆን አይቀርም። (በእርግጥ ቁጥር አንድ የሚለው ግነት ነው😀)

"97 አመተ ምህረት ሲባል ከምርጫ 97 ቀድሞ ቂጣ በጎመን ትዝ ይለኛል" ብዬ ብናገር ጥቂት ግነት ያለው ሐቅ ነው። ያኔ ብዙውን ጊዜ ቂጣ በጎመን ነበር የምንበላው። ቁርስ ቂጣ በጎመን ፥ ምሳ ቂጣ በጎመን ፥ ራት ቂጣ በጎመን።
በእርግጥ አልፎ አልፎ ለውጥ አለ። ፎቼ ፥ ድንች ፥ ቦሎቄ ፥ ሩዝ ...
ከድንች በቀር የያኔው ምግባችን ያስጠላኛል።

97 አ.ም የ 3ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ። ትምህርት ቤት ሆኜ ስለምሳ አስቤ እበሳጫለሁ። ቤት ውስጥ እንጀራ እንደማይኖር እርግጠኛ ስለምሆን እናደዳለሁ። ቂጣ ወይ ቦሎቄ አሊያም ሩዝ እንደምበላ ሳስብ እበሽቅ ነበር።

አመቱ አልቆ አዲስ አመት መጣ። 98 አ.ም ሆነ። "የጎመን ድስት ውጣ ፥ የገንፎ ድስት ግባ" ተባለ። ለአንድ ቀን የጎመን ድስት ወጣልንና የምስር ወጥ ድስት ገባልን።

98 አ.ም እንቁጣጣሽን በምስር ወጥ አከበርን። በጣም ደስ አለኝ።

ፀልዬ ነበር። "ጌታ ሆይ ለአመት በአሉ አስበን" ብዬ ፀልዬ ነበር። ለቁርስ ምስር ወጥ ሲቀርብ "ፀሎቴ ተመለሰ" አልኩ። ፀሎቴን ለእናቴ ነገርኳት። ስስ ቅሬታ አየሁባት።

አውዳመትን በምስር ወጥ ያከበርንባቸው ሌሎች አጋጣሚዎች አሉ። በስጋም ፥ በዶሮም አክብረን እናውቃለን። ግን የ98 አ.ም እንቁጣጣሽ አይረሳኝም። ምስር ወጥ ስለበላሁ ደስ የተሰኘሁበት እንቁጣጣሽ ነበር።

ለአውዳመት ስሜቴ ምውት ነው። አያጓጓኝም ፥ አያስደስተኝም ፥ አያስከፋኝም። አንዳንዴ ግን ለአውዳመት ምስር ወጥ ብርቅ የሚሆንባቸውን ማሰብ ያምረኛል።

የዛሬ 20 አመቱን የቤታችንን እንቁጣጣሽ አስታውሼ ፈገግ ባልኩበት አፍታ ፥ በአሉን በረሃብ የሚያሳልፉ ኢትዮጵያን ትውስ ይሉኛል


@Tfanos
6
አሮጌ እንቁጣጣሽ
* * *

መሶቡ ታጥሮበት ፥ የአገር ልጅ ተርቦ
ዘመን ላይሰረይ ፥ ህይወት ጭዳ ቀርቦ
ለቆሸሸ መንፈስ
ለአሮጌ እንቁጣጣሽ ፥ ቄጤማ ጎዝጉዘን
እንዳምና ካቻምነው ፥ ሬ ሳ ላይ ቆመን
በአረጀ እንቁጣጣሽ...
ግፍ የታተመበት ፥ የማያልፍ ዘመን
አለፈ እንላለን ፥ ህይወት እያሳለፍን

(በድሉ ዋቅጅራ ፥ የወይራ ስር ፀሎት ገፅ 80)


@Tfanos
4
ዳሰሳ በፍልስፍና መምህር ዮናስ ታደሰ

የተስፋአብ ተሾመ ተስፋኣብ ተሾመ <<የዙፋን ልፊያ>> መፅሐፍን አነበብኩት። ወደድኩትም።

ዋና ገፀ ባህሪውን ሰው ሳይሆን "መብራት" የምትባል በአንዲት "ምናባዊት አገር"😁 ውስጥ የምትገኝ ምናባዊት ከተማ ያደረገ ልብ ወለድ መፅሐፍ ነው። መፅሐፉን ስናነብ በዋናነት የሰው ገፀ ባህሪ የውጣ ውረድ ሰንሰለትን እየተከተልን ሳይሆን ግኡዝ በሆነ የከተማ ዋና ገፀባህሪነት ውስጥ ባሉ የተለያዩ ገፀ ባህርያት (በዋናነት መብራታውያን) ውጣ ውረዶች ሰንሰለት ተከትለን ነው። ምናልባት አንባቢ ይሄ እስኪገለጥለት ድረስ፤ የተለያየ አይነት እርስ በርሱ የሚገናኝ የማይመስል የገፀ ባህርያት ግለ ታሪክ ሲያነብብ፣ "ይሄ ነገር የአጫጭር ልብ ወለዶች ጥርቅም ሊሆን ነው እንዴ?" ብሎ ግር ሊሰኝ ይችላል። ግዴለም ንባቦትን ይቀጥሉ ይገለጥሎታል። ደራሲው በመጀመሪያው የረዥም ልብ ወለድ ድርስት ስራው እንዲህ አይነቱን ነገር መሞከሩ በራሱ የሚደነቅ ነው።

በእርግጥ የልብ ወለዱ ዘውግ ነገሮችን በአሪስቶትል ቋንቋ፣ ሊሆኑ ይችሉ በነበሩበት (as it might be) ወይም ሊሆኑ በሚገባቸው (as it ought to be) ሳይሆን፤ በስብሐት ገብረ እግዚአብሔር አገላለፅ ታሪኩ የልብ ወለድ ድርሰት ቅርፅ ለማስያዝ እንዲረዳ ብቻ የታሪኩ ፍሰትን በተወሰነ ምናባዊ ቅርፅ አስተካክሎ ነገሮችን በሆኑበት ልክ (as it is) ሊተርክ የሚሞክር የ naturalist school አፃፃፍ የተከተለ ነው። በግሌ የዚህ ዓይነቱ መንገድ አድናቂ ባልሆንም በጭብጣቸው (theme) ምክንያት ልክ እንደ የስብሐት "ትኩሳት" እና "ሌቱም አይነጋልኝ"፣ እንደ የበአሉ ግርማ "ኦሮማይ" አይነቶች አንብቤ የምወዳቸው አሉ—የተስፋአብ የዙፋን ልፊያም ይዞት ከተነሳው ጭብጥ አንፃር ወድጄዋለሁ።

በእንደዚህ አይነት የድርሰት ዘውግ ውስጥ በብዙ የአማርኛ ድርሰቶች ላይ የማስተውለውን ምንም አስፈላጊነት በሌለው ቦታ ላይ፣ "መፃፍ እችላለሁኮ" ለማለት የሚመስል ግን ታኝከው የተተፉ፣ "ሰማዩ ጠቁሮ ነበር"፣ "ጭጋጉ እንዲህ መስሎ ነበር"፣ "አውሎ ነፋሱ እንዲያ ሲሆን ነበር"... በሚል የሚጀምሩ አሰልቺ ማጀቢያ ገለፃዎችን ሳይጠቀም፤ አሁን አሁን ደግሞ እድሜ ለድህረ-ዘመናዊነት ንቃተ-ህሊና ያመጣልህን፣ ትርጉም ይስጥ አይስጥ ሳትጨነቅ፣ የአንባቢ አእምሮ ሰብስቦ ለመያዝ የሚቸገርባቸው የቃላት ሰላጣ መአት የማፍሰስ እና የመፍሰስ አባዜ ሳይጠናወተው፤ ደራሲው ነገሮችን በተመጠኑ እና በተዋቡ ቃላት፣ የነገሮችን ሁኔታ በማያሻማ መልኩ ጥርት ባለ ቋንቋ ከሽኖ የሚገልፅበት ድርሰት ሆኖ አጊኝቼዋለሁ—የዙፋን ልፊያ።

አንዳንድ ሰዎች፣ "የዙፋን ልፊያ የእርስ በርስ ጦርነት ያለውን አስከፊ ገፅታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ድርሰት ነው" ብለው ሲገልፁት ተመልክቼአለሁ። ትክክል ነው፣እውነት አላቸው። ከዚያም ባሻገር ግን በስፋት ባይሄድበትም የእርስ በርስ ጦርነት አስከፊ ገፅታ ምንጭን የሚጠቁምበት—ማህበረሰባዊ የስነ-ምግባር ልሽቀትና ከዚህ የተነሳም የምሑራዊ ሐቀኝነት መጥፋት—ሐሳብም ቋጥሮአል። ለምሳሌ ንፁህ የምትባል ገፀ ባህሪ የታዘበችውን እንመልከት:-

<<ጦርነት አስጀማሪ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ የሰውን ክፋት ልክ አየች። የሀገሪቱ ዜጎች እርስ በርስ ሲጠላሉ ኖረው ለመጠፋፋት አጋጣሚ እየጠበቁ እንደቆዩ አመነች። ጦርነቱ በጀመረ ማግስት ያደፈጠ ክፋት ተገለጠ፣ የተሰወረ ነውር ለአደባባይ ዋለ። "ክፉዎች ነበርን" ትላለች የሆነው ሁሉ እየደነቃት። "ክፉዎች ነበርን። የክፋታችንን ጥልቀት ጦርነት ገለጠው። የእርስ በርሱ ጦርነት ገመናችንን አደባባይ ላይ አዋለው" ትላለች ለራሷ።>> (ገፅ 142-143 አፅንኦት የራሴ)

በሌላ በኩል ደግሞ፣ "ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ" የሚለው የተለመደ ብሂል የሚያዋጣ አይደለም ብሎ ሊገዳደር የሚሞክርም ነው:-

<<ምሁራን እውቀታቸው አላዳናቸውም። ፖለቲካ ምን እንደሆነ የማያውቁት በፖለቲካ እሳት አለመቃጠል አልሆነላቸውም።...>> (ገፅ 15 አፅንኦት የራሴ)

በዙፋን ልፊያ ከወደድኳቸው ነገሮች ውስጥ ከመፅሐፉ ርእስ ጀምሮ አርእስት አመራረጥና የገፀ ባህርያቱ (የአብዛኞቹ) ስሞች ከታሪክ ፍሰቱ ጋር የተሰናሰሉ መሆናቸውን ነው። ምናልባት መፅሐፉ ገና እየተነበበ ስለሆነ spoiler እንዳይሆንብኝ እንጂ፤ ለምሳሌ፣ <<የዙፋን ልፊያ>> የሚለው የመፅሐፉ አርእስት ራሱ ምን ለማለት እንደተፈለገ እንዲሁ በቀላሉ የሚጠቁመን ገላጭ አርእስት ቢመስለንም ቅሉ፤ ከገፀ ባህሪ ስምና ባህርያት ጋር ተሰናስሎ የተሸከመውን ያልጠበቅነውን ቅኔአዊ ትርጓሜ መጨረሻ ላይ ሲገለጥልን ደሞ፣ "አሃ!" ብለን መገረማችንና ደራሲውን ማድነቃችን አይቀርም። "ጉልበትና ጉድለት"፣ "መፍረስና መፍረስ" የሚሉ አርእስቶች፤ "ህይወትና ህይወት"—ሁለቱ ህይወቶች፣ "ንፁህ"፣ "ዙፋን" የሚሉ የገፀ ባህርያት ስሞች ምፀት እና ቅኔ ያዘሉ ሐሳቦችን ያረገዙ ሆነው ስናገኛቸው ደግሞ ሌላ አድናቆት ያጭርብናል።

በመጨረሻም በ"የዙፋን ልፊያ" ላይ ያለኝ ቅሬታ የነገሮችን ሁኔታ በቃላት ትረካ (ወደ መስበክ የሚያጋድል) ለመግለፅ ከሚሞክረው naturalist የአፃፃፍ ስታይል ይልቅ፤ የነገሮችን ሁኔታ በተግባራት የመንስኤና ውጤት ሰንሰለት ሴራ (a plot having a series of events with a causal chain of actions) ለመግለፅ በሚያስችለው የromanticism የአፃፃፍ ስታይል ቢፃፍ ኖሮ እንደ "ፍቅር እስከ መቃብር" ዘመን የሚሻገር ድርሰት ይሆን ነበር እላለሁ። በቀጣዩ መፅሐፍ (ተከታይ እንደሚኖር ወፊቱ ሹክ ብላኛለች😁) ደግሞ ይሄኛውን የ romantic school መንገድ እንዲሞክረው እመኛለሁ።

አንዳንድ ከመፅሐፉ የቀነጫጨብኳቸውና የወደድኳቸውን አባባሎች/አገላለፆች ላስቀምጥና ላብቃ:-

— "ለሰው ወለድ ችግር መለኮታዊ መፍትሔ መሻት መፈረካከስን ሊያዋልድ ሆነ።... ፈጣሪ ይጠብቀናል ከማለት በላይ አይጠብቀንም ብሎ ማመኑ መልካም ነው።"😁

— "ከፖለቲካ ራሳችንን ባገለልን ቁጥር ከእኛ በስነ-ምግባር እና በእውቀት ባነሱ ሰዎች ለመመራት እንገደዳለን።" ይሄኛው ከፕሌቶ የተዋሰው ፍልስፍናዊ ሐሳብ መሆኑን ወድጄዋለሁ።

— "ምልጃ ፋይዳ የለውም። መከራውን ማክሸፊያ የሰው አእምሮ ብቻ ነው..."

— " 'ውሸት ነው' ማለታቸው የለየለት ቅጥፈት እንደሆነ እያወቁ ራሳቸውን ሸነገሉ።"

— " 'አልዋሽህም...' አለች ለውሸት እየተዘጋጀች።"

— "አንድ ገንዘብ የሚጠቀም በሁለት መንግስታት የሚተዳደር ህዝብ ተፈጠረ።"

—"መከራን እንደ መልመድ ያለ መከራ ከወዴት ይገኛል?"

— "ትላንት ዛሬ ላይ እንዲያዝዝ ተፈቀደ፣ ነገ ለትላንት እንዲገብር ተወሰነ።"👌

— "ዙፋን ይህን ሁሉ ታውቃለች"😁

እና ሌሎች ብዙ ኮርኳሪ አገላለፆች...

እስቲ እናንተ ደግሞ አንብቡና የተሰማችሁን አካፍሉ።

እያነበብን እንጂ ጎበዝ!!
* * *

ዳሰሳ አቅራቢያችን ዮናስ ታደሰ በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ትምህርት ቤት የፍልስና መምህር ነው።


@Tfanos
1👍1
ልደቱ በልብወለድ እየመጣ ነው።

ፖለቲከኞች ልብ ወለድ ሲፅፉ ፥ ስራቸው ምን ይመስላል? ይህ ያጓጓል።
በሐገራችን ልብወለድ የመፃፍ አቅም የነበራቸው ጥቂት ፖለቲከኞች ነበሩ። (ምናልባት ብዙ ሊኖሩ ይችላሉ፥ ልብወለድ እንደሚፅፉ የሚታወቁቱ ጥቅት ናቸው)

መለስ ዜና በብዕር ስም ሁለት የልብወለድ ስራዎችን አሳትሟል። ሁለቱን ልብ ወለድ ሲፅፍ የሚታወቅበትን ስም አልተጠቀመም። ይልቅ ተስፋዬ የኋላሸት በሚል የብዕር ስም ነበር ልብወለዶቹን የፃፈው።

አንዳርጋቸው ፅጌም ግጥም ይፅፍ ነበር። አንዳርጋቸው "ትውልድ አይደገናገር፥ እኛም እንናገር" በሚለው መፅሐፉ እንደተረከው ከሆነ መጀመሪያ የእንግሊዘኛ ግጥሙን የፃፈው ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ ነው። ግጥሙ ስለ አዲስ አበባ ነው።

በረከት ስምዖን ገጣሚ ጭምር እንደሆነ ብዙ ሰው የሚያውቅ ይመስለኛል።

የበረከትን ዝነኛ ግጥም 👇

እንደተፋቀርን ላንተያይ፥ ሳንተያይም ልንፋቀር
እንደመናን ካለም፥ ከስተሙራ ስንባረር
በታጋይ ህግ ተገድበን፥ በአጉል ስርአት ስንጠፈር
መቸስ ምን እንላለን፥ በተስፋ ከመሞት በቀር?
(ገጣሚ በረከት ስምዖን)

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ገናና ስም ከሆኑት መካከል አንዱ ብርሃነ መስቀል ረዳ ነው። አብዮተኛው ብርሃነ አብዮታዊ የመድረክ ድራማ ፅፎ እንደነበር ስንት ሰው ያውቃል? ብርሃነ መስቀል "መሬት ለአራሹ" የሚለውን ወቅታዊ ጥያቄ ያቀጣጠለ ድራማ ፅፎ ነበር። ድራማው ለእይታ ከቀረበ በኋላ ተማሪዎች ወደ ፓርላማ አቅንተው የጃንሆይን መንግስት ተቃቀሙ። "መሬት ለአራሹ ፥ ተዋጉት አትሽሹ" አሉ።

ልደቱ አያሌው በልብወለድ መፅሐፍ እየመጣ ነው። ከላይ እንደጠቀስኩት ልብወለድ የሚፅፉ ፖለቲከኞች ነበሩን።

ልደቱ ልብወለድ እንደሚፅፍ የተገነዘብኩት "የአረም እርሻ" ወይም "ቴአትረ ፖለቲካ" በሚለው መፅሐፉ ይመስለኛል።ከሁለቱ መፃህፍት በአንዱ ስለ ልብወለድ ፀሐፊነቱ አንስቷል።

ስጦታ ከእስር ቤት የተሰኘው የልደቱ መፅሐፍ አማራጭ ሕገመንግሥት ነው። ስጦታ ከእስር ቤትን ያነበባችሁ ሰዎች ልደቱ ልብወለድ የመፃፍ ሃሳቡን እንዳልተወው ትገነዘባላችሁ። በመፅሐፉ የመጀመሪያ ገፆች አከባቢ "እስር ቤት ስገባ፥ ከዚህ የጀመርኩትን የልብወለድ ስራ ፅፌ መጨረስ አስቤ ነበር" ይላል። ነገር ግን ከፖለቲካችን አንገብጋቢነት የተነሳ አማራጭ ሕገመንግሥት ወደመፃፉ አዘነበለ።

አሁን ጊዜው ሆኖ ልደቱ አያሌው በልብወለድ መፅሐፍ ሊመጣ ነው


@Tfanos
6
👍3
መስጂዱ በታጣቂ ተከበበ። የምሽት 2 ሰአት ፀሎት ከመሩ በኋላ መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው የነበሩት ኢማም ጦር መሳሪያ ተደቀነባቸው።
"ሰዎቹ የት ሄዱ?"
"አልናገርም"
ታጣቂዎች ኢማሙን እያዳፉ ከወሰዱ በኋላ እጅና እግሩን አስሩት፥ ቀጥሎ እሳት ለቀቁበት። ኢማሙ በእሳት ጋይቶ ሞ ተ።

ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው። በሴራሊዮን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት አከባቢያቸው በታጣቂ ሲከበብ ሰዎች ከሰፈራቸው ሸሹ። ይሄኔ ታጣቂዎች ወደ መስጅድ በማቅናት "ሰዎች የሸሹበት አድራሻ ንገረን" በማለት ኢማሙን ጠየቁ። ኢማሙ የሸሹ ሰዎችን አሳልፌ አልሰጥም አሉ። ሰዎችን ለሞት አሳልፎ ባለመስጠታቸው በእሳት ተቃጥለው ሞቱ።

እስማኤል የ 12 አመት ታዳጊ ነበር። ኢማም በእሳት ሲ ቃ ጠ ሉ ፥ መንደሩ ሲ ጋ ይ ፥ ሰዎች በመደዳ ሲ ረ ሸ ኑ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈ ረ ጠ ጠ። እግሩ ወደመራበት አከባቢ ሸሸ።
ሽሽቱ ብዙ ሰ ቆ ቃ ያለው ነበር። እ ባ ብ ባለበት ጫካ ውስጥ ብቻውን ለማደር ተገዷል። ምግብ ሳይቀምስ ለቀናት ተንከራቷል። አብሮት እየሸሸ ያለ ታዳጊ ሲሞት በአይኑ ተመልክቷል። ማብቂያ የለሽ ሽሽት...

አንድ ቀን እየሸሸ ሳለ ራሳቸውን ነፃ አውጭ የሚሉ አ ማ ፅ ያ ን ያሉበት ሰፈር ደረሰ። እሱ ላይ እና የሚሸሹ ሰዎች ላይ ጥያት አዘነቡባቸው። ታጣቂ ቡድኑ ዜጎችን መያዣ ያደርጋቸዋል። እንደጋሻ ይጠቀማቸዋል።

እስማኤል በ 12 አመቱ ሰዎች አንገታቸው እየተቀነጠሰ ሲገደሉ ፥ ጭንቃታቸው በጥይት ሲ ፈ ነ ዳ ተመልክቷል። ይህ ሁሉ ግን የትራጄዲው መጀመሪያ ነው።

ለአንድ አመት ያህል ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር ጫካ እያደረ ፥ ያገኘው ቦታ እየተሸሸገ ከቆየ በኋላ የመንግስት ወታደሮች ካምፕ ደረሰ። በካምፑ ጥቂት ከቆየ በኋላ ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ወታደር ለመሆን ተገደደ። ከካምፑ ወጥቶ ታጣቂ እጅ መውደቅ ወይም ወታደር መሆን ብቻ ነበር አማራጩ። እየቀፈፈው ወታደር ሆነ። ለመጀመሪያ ጦ ር ነ ት ሲሰማራ እየፈራ ነበር። የመጀመሪያውን ጥ ይ ት ተኩሶ እስኪገድል ድረስ ፍርሃቱ አልለቀቀውም ነበር። አንድ ጥ ይ ት ተኩሶ የባለጋራውን ጭንቅላት ካፈረሰ በኋላ ጨ ካ ኝ ሆነ። ደጋግሞ ተኮሰ፥ ብዙ ሰው ገ ደ ለ።

ገና በ13 አመቱ በመግደል መርካት ጀመረ። "እኒህ ቤተሰቦቼን የ ገ ደ ሉ ጠ ላ ቶ ቼ ናቸው" እያለ ይገድላል። ሲገድል ይረካል።

የ13 አመቱ እስማኤል አኗኗሩ ተቀየረ። ጊዜውን የሚያሳልፈው ሰው በመግደል እና ማ ሪ ዋ ና በመጠቀም ሆነ። ሁለት ሱስ ያዘው። ማ ሪ ዋ ና እና ደ ም ማፍሰስ ሱስ ሆኑበት።

አንድ ቀን አምስት ሰዎች በእነ እስማኤል ፊት ተንበረከኩ። ሰዎች የፍጥኝ ታስረዋል። እነ እስማኤል ለውርርድ ተሰለፉ። ውርርዱ ሰዎች በፍጥነት የ ማ ረ ድ ነው። በፍጥነት አ ር ዶ የገደለ ጀግና ይባላል።
ሰይፋቸውን መዘዙ ፥ ጀምሩ ሲባል ሰውን ያህል ፍጡር እንደ ዶሮ አ ረ ዱ። አንገት ቀንጥሰው ጣሉ። የ13 አመቱ እስማኤል ከሁሉም ቀድሞ አንገት ቀንጥሶ በመጣሉ ጀግና ተባለ።

ታዳጊው ጦረኛ ፀፀት የሚባል ነገር አይሰማውም። እ ፅ እና ደም አስክረውታል። ቤተሰቦቹ በአማፂ ቡድን ስለተገደሉበት የበቀል ረሃብ አለበት። በገደለ ቁጥር ሃሴት ያደርጋል። ጭካኔው እና እድሜው አይመጣጠንም።

ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሰዎችን በቁም ቀ ብ ሮ ያውቃል።
ከአማፂው ወገን የተሰለፉ ለጋ ልጆችን ያዟቸው። ልጆቹ በእድሜያቸው ለጋ ናቸው። እነ እስማኤል በእጃቸው የገቡትን ታዳጊዎች ጉድጓድ እንዲቆፎሩ አዘዙ። የታዘዙትን አደረጉ።
ጉድጓድ ቆፎረው ሲጨርሱ አንድ በአንድ ወደ ጉድጓዱ ጣሏቸው። በመቀጠል አፈር ይመልሱባቸው ጀመረ። በህይወት ያሉ ታዳጊዎች ላይ አፈር ጨመሩ። በነብስ ያለ ሰው ቀበሩ።

እስማኤል ተማሪ ነበር። እንዲህ ጭካኔ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ተማሪ ነበር። ከእድሜው የማይመጣጠን ክፋትን መፈፀም ከጀመሩ በፊት ንፁህ ልብ ያለው ታዳጊ ነበር።

በሴራሊዮን የተጀመረው የእርስ በእርስ ጦርነት የህይወት አቅጣጫውን ቀየረበት። መንደሩ በእሳት ጋየ። ቤተሰቦቹ በጭካኔ ተገደሉ። ጓደኞቹ የጦርነት እሳት በላቸው። መሸሸጊያ ፍለጋ ላይ እታች ስል ከሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል በአንዱ እጅ ወደቀ። ያኔ በግዳጅ መሳሪያ ያዘ። ተገዶ ተኮሰ። ሰው ገደለ። ከዚህ በኋላ ሌላ ሰው ሆነ።

እስማኤል እና ጥቂት ጓደኞቹ ወደ ተሃድሶ ተቋም ሄዱ። ያኔ እስማኤል እድሜው 15 ደርሶ ነበር። ጦርነቱ መደበኛ ህይወቱ ሆኗል። አው ሬያ ዊ ባህሪ ተላብሷል።የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ወደ ማገገሚያ የገቡ ወጣቶች የመጀመሪያ ቀን ፀብ ገጠሙ። ሁለት ወገን ሆነው ሲፋለሙ የስድስት ሰው ህይወት አለፈ።

እስማኤል ዛሬ ህይወቱ ተቀይሮ ሌላ ሰው ሆኗል። የጦርነትን አስከፊ ገፅታ ይመስክራል። ጦርነትን ይቃወማል። ከመቀየሩ በፊት ግን ሊረዱት በፈለጉት ላይ ጭምር የሚጨክን አ ረ መ ኔ ሆኖ ነበር።

እስማኤልንና ጓደኞቹን ትረዳ የነበረች የስነልቦና ባለሞያ "ይህ የናንተ ጥፋት አይደለም" ትላቸው ነበር።

እነ እስማኤል ልጅነታቸውን ተቀምተዋል። ገና በታዳጊነቻቸው ጨካኝ ሆነዋል። የሰውን አንገት እየበጠሱ የሚጥሉ ሆነው ነበር። ይህ ሁሉ ግን የነሱ ጥፋት ብቻ አልነበረም። የእርስ በእርስ ጦርነቱ የህይወታቸውን አቅጣጫ ቀየረው። ከሰውነት ወደ ጨ ካ ኝ አው ሬ ነ ት ተለወጡ።

"ታዳጊው ጦ ረ ኛ" የትርጉም መፅሐፍ ነው። የእስማኤል ህይወትን ይተርካል።

በታዳጊው ጦረኛ መፅሐፍ የሴራሊዮኑ የእርስ በእርስ ጦ ር ነ ት ህይወታቸውን በመጥፎ መንገድ የቀየረባቸውን ታዳጊዎች እንመለከታል። በነርሱ በኩል ደግሞ ሐገራችንን እናያለን።


Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
4
ዳሰሳ በይታያል አስናቀ
* * *

የዙፋን ልፊያን ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ አንብቤ ጨረስኩት ። ደረሲው ፦ በልጅነት አዕምሮው ካደገበት አካባቢ የቃረመውን ፤ በንባብ ያወቀውንና አሁን እየሆነ ያለውን እውነት ደስ በሚል አተራረክ ለመረዳት ቀላል በሆነ ቋንቋ ፅፎልናል። ለዙፋን በሚደረግ እሽቅድድም ውስጥ ማን ምን እንደሚያተርፍ ማን ምን እንደሚያጣ ልብ ያለው ልብ ይበል ይለናል።

ስሜት ያናወዛቸው ጎረምሶች ነፍጥ ሲጨብጡ፥ የእናትነት ክብር ረብ የለሽ እንደሚሆን፣ የፈጣሪ ህልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ አይተናል።

በመፅሐፉ ገፅ 2 -3 ቀጣዩ ሰፍሯል
... እድሜያቸው ምህረት አላስገኘላቸውም ፣ እናትነታቸው ከጭካኔ አላዳናቸውም ፣ ልመናቸው ከጎረምሳ ጥፊ አልታደጋቸውም ። በጠንካራ መዳፉ በጥፊ ሲመታቸው በጀርባቸው ወደቁ።
" ልጄ እናትህ ነኝ ። ፈጣሪን አታሳዝነው "
በእንባ የራሰ ፊታቸው ሌላ ጥፊ ተቀበለ ።
እያለ ይቀጥልና አድርግ የተባለውን የሚያደርግ ፣ ለምን ብሎ የማይጠይቅ መንጋ ስልጣን ሲቆጣጠር ፣ የክብር መለዮ ሲለብስ ሀገር ለውርደት ህዝብ ለስቃይ እንዲሚዳረግ ይነግረናል ።

ገፅ 41 ..." በሕግ አምላክ" እያለች መደፈሯ እንደ እግር እሳት ለበለባት ፣ "መለዮ አክብር " የተባለ ወታደር የጀመረውን ክፋት ሁሉ እርግፍ አድርጎ እንደሚተው እየሰማች አድጋ ተቃራኒው ቢገጥማት ሃዘን ሰረሰራት ።
ከራሷ ተጣልታ ፣ የገዛ እሷነቷን ተፀይፋ መኖር ጀመረች።

" ሁለት ባለስልጣናት ለመንበር ሲሉ በመጣላታቸው የተነሳ የእኔ ማሕጸን ጦር ሜዳ ሆነ " ትላለች ሆድ እየባሳት።

እርስበርስ ጦርነት ሲጀመር ሀብት ማካበት ፣ የንጉስ ዘር መሆን ፣ የተመረጥኩ ነኝ ብሎ መመፃደቅ ከምንም አለመሆን ከሳቱ እንደማያተርፍ የዙፋን ልፊያ ይነግረናል።

ገፅ 134 ... ሁለቱም ተፋላሚዎች ንፁሀንን ማጥቃት ሲፈልጉ " አሲራችሁብናል " የሚል ፈሊጥ እንደሚያመጡ ያውቃሉ። የጀነራሉ ጦር ድል ሲከዳው የመብራት ነዋሪዎችን " ለጠላት መረጃ አቀብላችኋል " ብለው ይረሽናሉ። የፕሬዘዳንቱ ሰራዊት ሽንፈት ሲጎበኛቸው " ከጠላት ተባብራችኋል " ብለው መብራታውያንን ይገድላሉ። ይለናል።

እየተጓዝንበት ያለው መንገድ አደጋ አለው የሚል ሰሚ ያጣበት የእብደት ዘመን ሲሆን ታሪክ አዋቂ አባቶች ዝም እንደሚሉ ከፊል ታሪክ አዋቂ ሆድ አደሮችም ለመኖር የሚጠቅማቸውን እመረጡ ከሁለቱ ተፋላሚዎች ጎራ እንደሚሰለፉ በ ገፅ 172 ላይ በጥሩ መንገድ ተነግሯል። "ከሁለቱም ወገን የተሰለፉ ታሪክ አዋቂዎች ከፊል እውነት ቢኖራቸውም እውነታቸው የተሟላ አይደለም። ረጅም በሆነው የሐገሪቱ ታሪክ እርስ በእርስ የመነካከስ ዘመን ነበር ። ነገር ግን የተነካከሱት ተሳስመው ያውቃሉ። መገፋፋት የገነነበት ዘመን የመኖሩን ያህል የመተቃቀፍም ዘመን ነበር ። በታሪክ አጋጣሚ ለጥፋት የተፈላለጉቱ የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም አብረው ተሰልፈውም ያውቃሉ።
የተሟላ እውነት ምን እንደሆነ የታሪክ ባለሙያዎቹ የሚያውቁ ቢሆኑም ሐቅ ላይ ምራቃቸውን ለመትፋት አላመነቱም ። ከትላንት ገፅ ላይ ለእኩይ አላማቸው የሚበጃቸውን ብቻ መዘዙ..." ይለናል

ይሄ ምናብ የወለደው ፈጠራ ብቻ አይደለም ። በገፀባህሪያት ተዋቅሮ በመቼት ተወክሎ የቀረበ የትላንት እና የዛሬ ታሪካችንን ፣ የነገ ስጋታችንን እና የተደቀነብንን አደጋ ገልፆ የሚያስጠነቀቅ ሰነድ እንጂ።

የጎረቤቶቻችኝ የሴራሊዮን የእርስበርስ ጦርነት እና ዮጋንዳ ሁቱ ቱትሲ እልቂት ፣ በየቀኑ እየሰማነው ያለነው የሱዳናውያን እብደት እንዳይደርሰን ቆም ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል። በርግጥ በከፊል ጀምረነዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት ያየናቸው መጠፋፋቶች ውጤታቸው በዜሮ እንደሚባዛ ።

የሆነው ሁሉ ሆኗል ። የምንፈራው እንዳይሆን ከልባችን ስራ እንጀምር ።
ከቁርበትዎ ይምከሩ እንዳለው አለማየሁ ገላጋይ በመለያየት ሞት ነው መፅሀፉ

👉 ስለ - ሀገር ፣ ህዝብና መንግስቱ ሲል ከ ቁርበቱ የሚመክር መሪ እንዲኖረን ።
👉 የለበሰውን መለዮ እና የገባውን ቃልኪዳን የሚያከብር የሀገር ዘብ ወታደር እንዲኖረን
👉 እውቀታቸውን እና ታሪካቸውን በሆዳቸው የማይለውጡ ምሁናንና አዋቂዎች እንዲበዙ
👉 ለምን የሚል ጠያቂ ፣ የሀገሩ መፃኢ እድል የሚገደው ትውልድ እንዲፈጠር በጣም ብዙ ብዙ መስራት እንዳለብን የተገነዘብኩበት መፅሀፍ ።

#የዙፋን_ልፊያ 👌👌👌
ሻሎም

@Tfanos
1
ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ "ጠርዝ ላይ" የሚል መፅሐፍ አለው። ዶክተሩ ካሳተማቸው ስራዎች ሁሉ "ጠርዝ ላይ"ን እና "የማይፃፍ ገድል"ን እወዳለሁ።

ጠርዝ ላይ ጥሩ ስራ ነው። 4 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። ከጉዳዮቹ መካከል አንዱ ቋንቋ ነው።

እንደሚታወቀው ዶክተር በድሉ የቋንቋ ባለሞያ ነው። ይህን ተከትሎ ስለ ቋንቋ ፖሊሲ ሞያዊ ማብራሪያ አስፍሯል።

ጠርዝ ላይን ያነበበ የቋንቋን ጉዳይ በእውቀት መዳኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ይረዳል። ነገረ ቋንቋን ስሜት ይጫነዋል። ሰዎች ከቋንቋ ጋር የተገናኘ ሙግትን በእውቀትና ምክኒያት ከማድረግ ይልቅ ስሜታዊነት ይጫናቸዋል። ጦ ር መማዘዝ ይቃጣቸዋል።

ይህ የብዙ አከባቢዎች ችግር ነው። ዶክተር በድሉ በማስረጃ ጭምር እንደጠቀሰው በብዙ ሐገራት ሰዎች ስለ ቋንቋ ሲወያዩ ስሜታዊ ይሆናሉ። ፀብ ፀብ ይላቸዋል። እነሱ ከሚያምኑት ውጭ የሆነውን መቀበል ይተናነቃቸዋል።

ዶክተር በድሉ "ግእዝ ሞቷል" እንዳለ ሰምተናል። ይህ ብዙ ሰዎችን አናዷል። አጠቃላይ ስለ ቋንቋው የሰጠው አስተያየት ያስቆጣቸው ብዙ ናቸው። ይህ ይጠበቃል። እንግዲህ ራሱ በድሉ ጠርዝ ላይ በሚለው መፅሐፉ እንደጠቀሰው ሰዎች ስለ ቋንቋ ሲነሳ ስሜታዊ ይሆናሉ።

ግን ደግሞ ስሜትን መግራት ያስፈልጋል። ዶክተሩ ላይ ውርጅብኝ ማውረድ አይረባም። ጠቃሚው ነገር ያነሳቸው ነጥቦችን መሞገት ነው።

ግእዝ ሞቷል ወይስ አልሞተም?
ግእዝን ለልጆች ማስተማር ጊዜ ማባከን ወይስ ጠቃሚ?
ግእዝን ለጥናት አላማ ፥ ለምርምር ወዘተ የሚፈልጉ ሰዎች በፈቃደኝነት ይማሩ ወይስ ከታች ይጀመር?
ግእዝን ማወቅ መሰረታዊ ፋይዳው ምንድነው? ጠቃሚው ጉዳይ እኒህ ነጥቦች ላይ መወያየትና መሟገት ነው።

ስሜት ይቀነስ

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
4👍4👎2
ቋንቋ እንዴት ይለመዳል?
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ስለ ቋንቋ ለመዳ እናውራ፥

ቋንቋ ከሰው ልጅ ስነልቦናዊ ስሪት ጋር ባለው ተዛምዶ መነሻ ለስሜት ቅርብ ነው። ከታሪክ እና ማህበራዊ ፍልስፍና ጋር መነካካት ስላለው ኮርኳሪነቱ ያይላል።

የቋንቋ ጉዳይ እጅግ ለስሜት የቀረበ ነው። ማንነት እና ባህልን ገላጭ መሆኑ የጉልበቱ ምንጭ ሊሆን ይችላል።
በተለይ ቋንቋ እና ፖለቲካ ያለ አግባብ ሲጋቡ የደም መፍሰስ ሰበብ ሊሆን ይችላል።

እኛ ሐገር የተለያዩ ብሔሮችን ቋንቋ ባለመቻላቸው የተነሳ የሚወቀሱ በልባቸው ጥላቻ እንዳደረ ተፈርጀው የሚከሰሱ አሉ።
"በኛ ክልል ተወልደው አድገው ቋንቋችንን የማያውቁ ሰዎች ምክኒያታቸው ጥላቻ ነው" እየተባለ ይነገራል።

ወቀሳውን በቅንነት መረዳት በጎ ሆኖ ሳለ ከግንዛቤ ሊገባ የሚገባ እውነታ አለ።

አንድ ሰው በይርጋዓለም በመወለዱ ብቻ ሲዳምኛ እንዲችል መጠበቅ ስህተት ነው። በሻሸመኔ ተወልዶ ያደገ ሁሉ ኦሮምኛ እንዲችል ማሰብ የዋህነት ነው። በወልቂጤ የኖረ ሁሉ ጉራግኛ እንዲናገር ማሰብ ጥፋት ነው።
ጂኦግራፊ ቋንቋን ማወቂያ ሰበብ አይሆንም። የቋንቋ ለመዳ ነገር ብርቱ የሆነ ገፊ ምክኒያት ከጀርባው አለ።

ሰሞኑን ግእዝ መነጋገሪያ ሆኗል። ተማሪዎች ግእዝን መማር አለባቸው ወይስ የለባቸውም በሚል ርዕስ ውዝግብ ተፈጥሯል። ውዝግቡ ሲጨመቅ ጥቂት ግን አንኳር ነጥቦች አሉት። እነርሱም ሴኩላሪዝም ፥ የግእዝ ፋይዳ ፥ የቋንቋው ህልውና (ሞቷል ወይስ አልሞተም) ፥ መማር የሚጀመርበት ወቅት (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎች ለጥናት አላማ ይማሩት ወይስ ከታች ይጀመር) የሚል ነወ። ለውዝግቡ መፍትሄው በእውቀት መሟገት ነው።

አጀንዳዬ ቋንቋ እንዴት ይለመዳል የሚል ነው። የግእዝንም ጉዳይ በዛው መዳኘቱን ለናንተ ልተወው።

የቋንቋ ለመዳን በግርድፉ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል።

ሀ፥ ተግባቦታዊ ምክኒያት

ሰዎች ከሰዎች ጋር ለመግባባት ፥ አዲስ ባህል ለመልመድ፥ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ፥ ጉብኝት እና መሰል ሰበቦችን መነሻ በማድረግ ቋንቋን ሊማሩ ይችላሉ። በዚህ ምክኒያት የሚደረግ የቋንቋ ለመዳ 'ተግባቦታዊ' ተብሎ የሚፈረጅ ነው።
ትልቁ ቁምነገር፥ በዚህ አይነት መንገድ ቋንቋን ማስፋፋት ዳገት መሆኑ ነው። ውጤታማ አይደለም። ተግባቦትን ብቻ ከግምት በማስገባት ቋንቋ ለመማር የሚጥር ሰው የሆነ ሰአት ላይ ቸል ይላል። አንዳች ተጨባጭ ፋይዳ ስለማያገኝበት ይሰለቸዋል።

ለ፥ ኢንስትሩመንታል ወይም ኢኮኖሚያዊ ምክኒያት

ቋንቋን ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወይም ለአንዳች ፋይዳ መማር በዚህ መደብ ይመደባል።
አንድ ግለሰብ አንድን ቋንቋ ተቀጥሮ ሊሰራበት ፥ ሰነድ ሊተረጉምበት ፥ ሃይማኖት ሊያስፋፋበት፥ ፖለቲካ ሊያስፈፅምበት፥ ኪነጥበብ ሊከይንበት ከተማረ "ኢኮኖሚያዊ ወይም ኢንስትሩመንታል ምክኒያት" ይባላል።

ይህ ውጤታማ ነው። በሁለተኛው ሰበብ ቋንቋ በቀላሉ ይስፋፋል። ብዙ ተናጋሪ ይኖረዋል። እንግሊዘኛ ወይም አረብኛ አሊያም ፈረንሳይኛ ከሐገራችን ደግሞ አማርኛ የተስፋፋው በዚህ ምክኒያት ነው። አረብ ሐገር ለስራ የሚሄዱ ሴቶች በአጭር ጊዜ አረብኛ የሚለምዱት በዚህ ሰበብ ነው።

ሁለቱን ነጥቦች የሚገልፅ ቀላል ምሳሌ፥
ለአመታት በኢትዮጵያ ስትኖር አፍ ከፈታችበት ቋንቋ ውጭ ሌላ ቋንቋ የማታውቅ ፥ በሐገሩ ሲኖር ከአካባቢው ውጭ ሌላ ሐገርኛ ቋንቋ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ብዙ ነው። በሐገራቸው ተጨማሪ ቋንቋ ለመልመድ መነሳሳት ያጡት ለምንድነው? መልሱ ግልፅ ነው። የቋንቋ ለመዳ ምክኒያቱ ተግባቦታዊ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ከሐገር ሲወጣ ሌላ ቋንቋ ፈጥኖ ይማራል። አረብኛ ወይም ቻይንኛ አሊያም ሌላ ቋንቋ ፈጥኖ ይለምዳል። ለምን? ምክኒያቱም በአዲሱ ቋንቋ እንጀራ ይጋግርበታል።

በአጭሩ ፥ እንጀራ የሚጋገርበትን ቋንቋ ሰዎች ለመማር ይነሳሳሉ ፥ ያለመገደድ ፈጥነው ይለምዳሉ። ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቋንቋውን ያውቁታል።

እንደምድመው፥

የቋንቋን ጉዳይ ከአውድ ውጭ መበየን አግባብ አይደለም። ሚዛን በጠበቀ ሁኔታ ቋንቋን ማሳደጊያው መንገድ ፖሊሲ ነው። ዜጎችን 'ቋንቋዬን ካልለመዳችሁ ነገር አለ ማለት ነው' ማለት አይበጅም። ይልቅ ሳይንሳዊ እና ዘላቂ የሆነ ፣ የጋራ ጥቅምን ከግምት ያስገባ የቋንቋ ፖሊሲ እንዲዘጋጅ መንግስትን መጠየቅ ይበጃል።

ጠቃሚው እውነታ ፥ ቋንቋ እንጀራ ሲጋገርበት ፣ እውቀት ሲሰነድበት ሰዎች ተረባርበው ይማሩታል።


@Tfanos
2👍1
ግእዝ ሞ ቷ ል?

"ቋንቋ ይወለዳል ያድጋል ይ ሞ ታ ል" ይህን የተማርነው ገና የ 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ሳለን ነው። ይህን ማንም ያውቃል። ግእዝ ከዚህ አንፃር እንዴት ይታያል? ሞ ቷል ወይስ አልሞተም?

ለሰሞንኛው ውዝግብ መፍትሄው ጠቃሚ ጥያቄዎችን መጠየቅ ነው

1፥ አንድ ቋንቋ ሞ ተ የሚባለው በምን አይነት ሳይንሳዊ መመዘኛ ነው?
2፥ ግእዝ በሳይንሳዊ መመዘኛ ሞ ቷል ይባላል ወይ?
3፥ አንድ ቋንቋ ቢሞ ት መቀስቀስ ይቻላል ወይ?
4፥ ግእዝን እነማን ይማሩ? ከታች ጀምሮ ልጆች ይማሩት ወይስ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከጥናትጋ በተያያዘ አላማ በምርጫቸው ይማሩት?
5፥ ግእዝን መማር ያለው ተጨባጭ ፋይዳ ምንድነው?
6፥ ግእዝ ሴኩላር ነው ወይስ ሃይማኖታዊ?
7፥ አንዳንድ ማስተማሪያ ምሳሌዎች ሲዘዋወሩ ሰሞኑን ተመልክተናል። ምሳሌዎቹ ሀይማኖታዊ ናቸው። የሌለ እምነት ተከታይ ልጅ በዚህ መንገድ መማሩ አግባብ ነው?

እርግማንና ቁጣ የትም አያደርስም። እልህ መጋባትና ስሜታዊነት አይጠቅምም። ስለዚህ በስክነት ፥ በእውቀትና በምክኒያት መወያየት ያስፈልጋል። የተለየ ሃሳብ ያራመዱ ሰዎችን መወረፍ አይጠቅምም።

አጠቃላይ ወቅታዊውን የግእዝን ጉዳይ በተመለከተ የተነሱ ሰሞንኛ አጀንዳዎች ከላይ በተነሱ ጥያቄዎች የሚጠቀለሉ ይመስለኛል። ስለዚህ ለጥያቄዎቹ ተጨባጭ መልስ ማፈላለግ ይሻላል።

@Tfanos
👍32
ስለሐገራችን ሙስሊሞች
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

የትላንት ሙስሊሞች፦ ጀጎልን አነፁ፥ አሚሮቹ ሐረርን አቅንተው የከተማ መንግስትን አቆሙ።
የሙስሊሙ ኡማ አሻራ ቀላል አልነበረም። የጊቤ መንግስታት ላይ ባለድርሻ ናቸው፥ የጂማን መልክ አበጃጅተዋል፥ ደግሞም የአዳል ሱልጣኔትና የፈጣጋር ታሪክ የነሱ ነው።

በእውነት ሚዛን ታሪክን ከለካን ፥ሙስሊም አባቶች ኢትዮጵያን ገንብተዋል።
ከአፋር እስከ ሱማሌ፥ ከወሎ እስከ ባሌ፥ ከምስራቅ እስከምራብ ፥ ከሰሜን እስከደቡብ ህያው ማህተም አኑረዋል።

ዛሬ ጥቂት ሙስሊሞች ላይ የምወቅስባቸው ነገር አለ። አባቶቻቸው ባቀኑት ሐገር ባለቤትነት አይሰማቸውም፥ አንዳንዶቹ በማይረባ ነገር ጭምር "እዬዬ" ማለት ቁም ነገር ይመስላቸዋል፥ 'የኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክ' ሲባል የአፄዎቹ ነገር ብቻ ትዝ ይላቸዋል። ደጋግመው "ኹለተኛ ዜጋ አታድርጉን" ይላሉ።

በእርግጥ ትላንት መሰደድ እና ባይተዋርነት ነበር። ለዲናቸው የታመኑቱ በቦሮ ሜዳ እንደ እንስሳ ታርደው ደማቸው ኩሬ ሰርቷል፥ በደልን አስተናግደዋል።

ታሪክ ግን የመገፋቱ ብቻ አይደለም።

የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሙስሊም አባቶች ጉልህ ሚና ነበራቸው። የኢትዮጲያ ትላንት ቢመረመር ፥ አከባቢዎች ቢቃኙ ያለ ሙስሊሙ ታሪክ የሐገሪቱ ታሪክ ሙሉ አይሆንም።

ጀግል የጎደለበት፥ ኢማሙ የሌለበት ፥ አዳል የተረሳበት ፥ ሼህ ጦሏህ የማይዘከርበት ፥ ቢላል የማይታወስበት ታሪክ ሙሉ አይደለም። ያለ ጥርጥር ትላንታችን የሙስሊሙ ማህበረሰብ በጎ አሻራ የታተመበት ነው።

ይህን ሐቅ መረዳትና ማክበር የሁሉም ሃላፊነት ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚና የማይተካ ነው።

ነገር ግን ጥቂት ያልሆኑቱ ለታሪካችው ተገቢውን ክብር የነፈጉ ሰነፎች ሲሆኑ ይታያል።

ምን እያልኩ ነው?

የሙስሊሙ ኡማ 'የኢትዮጵያ ሙስሊሞች' ታሪክን ሲዘክር መገፋትና መከራው ላይ ብቻ ማተኮር ስህተት ነው። ይህ ባይተዋርነትን ሊፈጥር ይቻላል።
ደማቁን እና ያልተነገረውን የሐገር ገንቢነት ታሪክ በኩራት እና በልበ ሙሉነት ማውሳት መዘንጋት የለበትም !

(ድጋሚ የተለጠፈ


@Tfanos
👏43
ፓስተር ፀባኦት እንግዳን አገኘሁት

የዘጠናዎቹ ጴንጤዎች መጋቢ ፀባኦት (ሰብስተን) በደንብ የምታውቁት ይመስለኛል። በስም ባታውቁት እንኳን "ሰማዩ ቢጠራ" የሚለውን መዝሙር በደንብ ታውቁታላችሁ።

"የታመንኩት ጌታ ፥ ተስፋ ያደረግኩት
ቃሎቼን አምኜ ፥ ህይወቴን የሰጠሁት
ሰማዩ ቢጠራ ፥ ለምን እጨነቃለሁ
ይዘንባል ያለኝን ፥ ጌታን አምነዋለሁ
ቃሉን አምነዋለሁ"

ይህን መዝሙር የማይወድ ይኖራል? አይመስለኝም።
የሃዘናችንን ወቅት ያሻገረን ፥ ተስፋ ስንቆርጥ ያነቃን መዝሙር ነው።
ፀባኦት አሁን በሐገረ እስራኤል ይኖራል። ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስለነበር ተገናኝተን ሻይ ጠጣን።

ከላይ ያለውን መዝሙር የፃፈበትን ሁኔታ ጠየቅኩት። በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለ የደረሰው መዝሙር ነው። ከጉሮሮ ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ድንገት ገጠመው። ቀላል የመሰለው ችግር ተወሳሰበ። ማገገም አቃተው። ወደ ሕክምና ተቋም ቢያመራ መታከም አይችልም አሉት። ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ገባ። በዛ ሁኔታ ውስጥ እያለ መዝሙሩን ፃፈው።
በመዝሙሩ ቀጣዮቹ ስንኞች ተካተዋል።
"ድንገት ድምፅ ሰማሁ፥ ከጨለማው መሐል
አይዞህ አትፍራ የሚል ፥ የሚያበረታ ቃል"

መዝሙሩ አፅናኝ ነው። ብዙ ሰዎች ተስፋ በቆረጡበት ወቅት መፅናናት አግኝተዋል። ህይወት ጨልሞባቸው ሳለ በርትተውበታል። በመከራ የሚያልፉ "የታመንኩት ጌታ" ብለው እየዘመሩ ተበረታተዋል።
ደግሞ የመዝሙሩ ዜማ 👌

አንድ ቀን መጋቢ ፀባኦት እና ሌሎች ሁለት አገልጋዮች በመኪና እየተጓዙ ነበር። ሾፌራቸው "የታመንኩት ጌታ" የሚለውን መዝሙር እየደጋገመ ይሰማዋል። ይሄኔ "ዘማሪውን ታውቀዋለህ ወይ?" ብለው እንደዋዛ ጠየቁት። "አላውቀውም ፥መዝሙሩ ብዙ አፄናንቶኛል። ደግሞ ዘማሪው እንደ ሞ ተ ሰምቻለሁኝ" አለ። ፀባኦት በአደጋ እንደ ሞ ተ በሀዘኔታ ለፀባኦት ነገረው። ፀባኦት በእርጋታ ዘማሪው ራሱ እንደሆነ ነገረው። ሾፌሩ አለቀሰ።

ሰሞኑን ከፀባኦት ጋር ሻይ ሰለጠጣን ደስ ብሎኛል። ሻይ እየጠጣን ስለ ተስፋዬ ጫላ አነሳን። ሰፊው ህዝብ እንደሚያውቀው በተስፋዬ መጠን የምወደው ዘማሪ የለም። ከፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ፥ ከገጣሚ በእውቀቱ ስዩም ፥ ከፀሐፊ ሐብታሙ አለባቸው ፥ ከእግርኳሰኛ ሊዮ ሜሲ ፥ ከዘማሪ ተስፋዬ ጫላን እወዳለሁ። የተስፋዬ መዝሙሮች ለኔ ቴራፒዬ ጭምር ነበሩ። ይህን ከዚህ በፊት ፅፌያለሁ። የፃፍኩትን ፀባኦት ለተስፋዬ አጋርቶታል።

ግብዣ ፥ የመጋቢ ፀባኦት (ሰብስተ) እንግዳን የታመንኩት ጌታ (ሰማዩ ቢጠራ) የሚለውን መዝሙር ጋብዣቸኋለሁ።


@Tfanos
4🔥4
2025/10/28 13:20:54
Back to Top
HTML Embed Code: