Telegram Web Link
ልደቱ በልብወለድ እየመጣ ነው።

ፖለቲከኞች ልብ ወለድ ሲፅፉ ፥ ስራቸው ምን ይመስላል? ይህ ያጓጓል።
በሐገራችን ልብወለድ የመፃፍ አቅም የነበራቸው ጥቂት ፖለቲከኞች ነበሩ። (ምናልባት ብዙ ሊኖሩ ይችላሉ፥ ልብወለድ እንደሚፅፉ የሚታወቁቱ ጥቅት ናቸው)

መለስ ዜና በብዕር ስም ሁለት የልብወለድ ስራዎችን አሳትሟል። ሁለቱን ልብ ወለድ ሲፅፍ የሚታወቅበትን ስም አልተጠቀመም። ይልቅ ተስፋዬ የኋላሸት በሚል የብዕር ስም ነበር ልብወለዶቹን የፃፈው።

አንዳርጋቸው ፅጌም ግጥም ይፅፍ ነበር። አንዳርጋቸው "ትውልድ አይደገናገር፥ እኛም እንናገር" በሚለው መፅሐፉ እንደተረከው ከሆነ መጀመሪያ የእንግሊዘኛ ግጥሙን የፃፈው ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ ነው። ግጥሙ ስለ አዲስ አበባ ነው።

በረከት ስምዖን ገጣሚ ጭምር እንደሆነ ብዙ ሰው የሚያውቅ ይመስለኛል።

የበረከትን ዝነኛ ግጥም 👇

እንደተፋቀርን ላንተያይ፥ ሳንተያይም ልንፋቀር
እንደመናን ካለም፥ ከስተሙራ ስንባረር
በታጋይ ህግ ተገድበን፥ በአጉል ስርአት ስንጠፈር
መቸስ ምን እንላለን፥ በተስፋ ከመሞት በቀር?
(ገጣሚ በረከት ስምዖን)

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ገናና ስም ከሆኑት መካከል አንዱ ብርሃነ መስቀል ረዳ ነው። አብዮተኛው ብርሃነ አብዮታዊ የመድረክ ድራማ ፅፎ እንደነበር ስንት ሰው ያውቃል? ብርሃነ መስቀል "መሬት ለአራሹ" የሚለውን ወቅታዊ ጥያቄ ያቀጣጠለ ድራማ ፅፎ ነበር። ድራማው ለእይታ ከቀረበ በኋላ ተማሪዎች ወደ ፓርላማ አቅንተው የጃንሆይን መንግስት ተቃቀሙ። "መሬት ለአራሹ ፥ ተዋጉት አትሽሹ" አሉ።

ልደቱ አያሌው በልብወለድ መፅሐፍ እየመጣ ነው። ከላይ እንደጠቀስኩት ልብወለድ የሚፅፉ ፖለቲከኞች ነበሩን።

ልደቱ ልብወለድ እንደሚፅፍ የተገነዘብኩት "የአረም እርሻ" ወይም "ቴአትረ ፖለቲካ" በሚለው መፅሐፉ ይመስለኛል።ከሁለቱ መፃህፍት በአንዱ ስለ ልብወለድ ፀሐፊነቱ አንስቷል።

ስጦታ ከእስር ቤት የተሰኘው የልደቱ መፅሐፍ አማራጭ ሕገመንግሥት ነው። ስጦታ ከእስር ቤትን ያነበባችሁ ሰዎች ልደቱ ልብወለድ የመፃፍ ሃሳቡን እንዳልተወው ትገነዘባላችሁ። በመፅሐፉ የመጀመሪያ ገፆች አከባቢ "እስር ቤት ስገባ፥ ከዚህ የጀመርኩትን የልብወለድ ስራ ፅፌ መጨረስ አስቤ ነበር" ይላል። ነገር ግን ከፖለቲካችን አንገብጋቢነት የተነሳ አማራጭ ሕገመንግሥት ወደመፃፉ አዘነበለ።

አሁን ጊዜው ሆኖ ልደቱ አያሌው በልብወለድ መፅሐፍ ሊመጣ ነው


@Tfanos
6
👍3
መስጂዱ በታጣቂ ተከበበ። የምሽት 2 ሰአት ፀሎት ከመሩ በኋላ መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው የነበሩት ኢማም ጦር መሳሪያ ተደቀነባቸው።
"ሰዎቹ የት ሄዱ?"
"አልናገርም"
ታጣቂዎች ኢማሙን እያዳፉ ከወሰዱ በኋላ እጅና እግሩን አስሩት፥ ቀጥሎ እሳት ለቀቁበት። ኢማሙ በእሳት ጋይቶ ሞ ተ።

ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው። በሴራሊዮን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት አከባቢያቸው በታጣቂ ሲከበብ ሰዎች ከሰፈራቸው ሸሹ። ይሄኔ ታጣቂዎች ወደ መስጅድ በማቅናት "ሰዎች የሸሹበት አድራሻ ንገረን" በማለት ኢማሙን ጠየቁ። ኢማሙ የሸሹ ሰዎችን አሳልፌ አልሰጥም አሉ። ሰዎችን ለሞት አሳልፎ ባለመስጠታቸው በእሳት ተቃጥለው ሞቱ።

እስማኤል የ 12 አመት ታዳጊ ነበር። ኢማም በእሳት ሲ ቃ ጠ ሉ ፥ መንደሩ ሲ ጋ ይ ፥ ሰዎች በመደዳ ሲ ረ ሸ ኑ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈ ረ ጠ ጠ። እግሩ ወደመራበት አከባቢ ሸሸ።
ሽሽቱ ብዙ ሰ ቆ ቃ ያለው ነበር። እ ባ ብ ባለበት ጫካ ውስጥ ብቻውን ለማደር ተገዷል። ምግብ ሳይቀምስ ለቀናት ተንከራቷል። አብሮት እየሸሸ ያለ ታዳጊ ሲሞት በአይኑ ተመልክቷል። ማብቂያ የለሽ ሽሽት...

አንድ ቀን እየሸሸ ሳለ ራሳቸውን ነፃ አውጭ የሚሉ አ ማ ፅ ያ ን ያሉበት ሰፈር ደረሰ። እሱ ላይ እና የሚሸሹ ሰዎች ላይ ጥያት አዘነቡባቸው። ታጣቂ ቡድኑ ዜጎችን መያዣ ያደርጋቸዋል። እንደጋሻ ይጠቀማቸዋል።

እስማኤል በ 12 አመቱ ሰዎች አንገታቸው እየተቀነጠሰ ሲገደሉ ፥ ጭንቃታቸው በጥይት ሲ ፈ ነ ዳ ተመልክቷል። ይህ ሁሉ ግን የትራጄዲው መጀመሪያ ነው።

ለአንድ አመት ያህል ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር ጫካ እያደረ ፥ ያገኘው ቦታ እየተሸሸገ ከቆየ በኋላ የመንግስት ወታደሮች ካምፕ ደረሰ። በካምፑ ጥቂት ከቆየ በኋላ ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ወታደር ለመሆን ተገደደ። ከካምፑ ወጥቶ ታጣቂ እጅ መውደቅ ወይም ወታደር መሆን ብቻ ነበር አማራጩ። እየቀፈፈው ወታደር ሆነ። ለመጀመሪያ ጦ ር ነ ት ሲሰማራ እየፈራ ነበር። የመጀመሪያውን ጥ ይ ት ተኩሶ እስኪገድል ድረስ ፍርሃቱ አልለቀቀውም ነበር። አንድ ጥ ይ ት ተኩሶ የባለጋራውን ጭንቅላት ካፈረሰ በኋላ ጨ ካ ኝ ሆነ። ደጋግሞ ተኮሰ፥ ብዙ ሰው ገ ደ ለ።

ገና በ13 አመቱ በመግደል መርካት ጀመረ። "እኒህ ቤተሰቦቼን የ ገ ደ ሉ ጠ ላ ቶ ቼ ናቸው" እያለ ይገድላል። ሲገድል ይረካል።

የ13 አመቱ እስማኤል አኗኗሩ ተቀየረ። ጊዜውን የሚያሳልፈው ሰው በመግደል እና ማ ሪ ዋ ና በመጠቀም ሆነ። ሁለት ሱስ ያዘው። ማ ሪ ዋ ና እና ደ ም ማፍሰስ ሱስ ሆኑበት።

አንድ ቀን አምስት ሰዎች በእነ እስማኤል ፊት ተንበረከኩ። ሰዎች የፍጥኝ ታስረዋል። እነ እስማኤል ለውርርድ ተሰለፉ። ውርርዱ ሰዎች በፍጥነት የ ማ ረ ድ ነው። በፍጥነት አ ር ዶ የገደለ ጀግና ይባላል።
ሰይፋቸውን መዘዙ ፥ ጀምሩ ሲባል ሰውን ያህል ፍጡር እንደ ዶሮ አ ረ ዱ። አንገት ቀንጥሰው ጣሉ። የ13 አመቱ እስማኤል ከሁሉም ቀድሞ አንገት ቀንጥሶ በመጣሉ ጀግና ተባለ።

ታዳጊው ጦረኛ ፀፀት የሚባል ነገር አይሰማውም። እ ፅ እና ደም አስክረውታል። ቤተሰቦቹ በአማፂ ቡድን ስለተገደሉበት የበቀል ረሃብ አለበት። በገደለ ቁጥር ሃሴት ያደርጋል። ጭካኔው እና እድሜው አይመጣጠንም።

ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሰዎችን በቁም ቀ ብ ሮ ያውቃል።
ከአማፂው ወገን የተሰለፉ ለጋ ልጆችን ያዟቸው። ልጆቹ በእድሜያቸው ለጋ ናቸው። እነ እስማኤል በእጃቸው የገቡትን ታዳጊዎች ጉድጓድ እንዲቆፎሩ አዘዙ። የታዘዙትን አደረጉ።
ጉድጓድ ቆፎረው ሲጨርሱ አንድ በአንድ ወደ ጉድጓዱ ጣሏቸው። በመቀጠል አፈር ይመልሱባቸው ጀመረ። በህይወት ያሉ ታዳጊዎች ላይ አፈር ጨመሩ። በነብስ ያለ ሰው ቀበሩ።

እስማኤል ተማሪ ነበር። እንዲህ ጭካኔ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ተማሪ ነበር። ከእድሜው የማይመጣጠን ክፋትን መፈፀም ከጀመሩ በፊት ንፁህ ልብ ያለው ታዳጊ ነበር።

በሴራሊዮን የተጀመረው የእርስ በእርስ ጦርነት የህይወት አቅጣጫውን ቀየረበት። መንደሩ በእሳት ጋየ። ቤተሰቦቹ በጭካኔ ተገደሉ። ጓደኞቹ የጦርነት እሳት በላቸው። መሸሸጊያ ፍለጋ ላይ እታች ስል ከሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል በአንዱ እጅ ወደቀ። ያኔ በግዳጅ መሳሪያ ያዘ። ተገዶ ተኮሰ። ሰው ገደለ። ከዚህ በኋላ ሌላ ሰው ሆነ።

እስማኤል እና ጥቂት ጓደኞቹ ወደ ተሃድሶ ተቋም ሄዱ። ያኔ እስማኤል እድሜው 15 ደርሶ ነበር። ጦርነቱ መደበኛ ህይወቱ ሆኗል። አው ሬያ ዊ ባህሪ ተላብሷል።የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ወደ ማገገሚያ የገቡ ወጣቶች የመጀመሪያ ቀን ፀብ ገጠሙ። ሁለት ወገን ሆነው ሲፋለሙ የስድስት ሰው ህይወት አለፈ።

እስማኤል ዛሬ ህይወቱ ተቀይሮ ሌላ ሰው ሆኗል። የጦርነትን አስከፊ ገፅታ ይመስክራል። ጦርነትን ይቃወማል። ከመቀየሩ በፊት ግን ሊረዱት በፈለጉት ላይ ጭምር የሚጨክን አ ረ መ ኔ ሆኖ ነበር።

እስማኤልንና ጓደኞቹን ትረዳ የነበረች የስነልቦና ባለሞያ "ይህ የናንተ ጥፋት አይደለም" ትላቸው ነበር።

እነ እስማኤል ልጅነታቸውን ተቀምተዋል። ገና በታዳጊነቻቸው ጨካኝ ሆነዋል። የሰውን አንገት እየበጠሱ የሚጥሉ ሆነው ነበር። ይህ ሁሉ ግን የነሱ ጥፋት ብቻ አልነበረም። የእርስ በእርስ ጦርነቱ የህይወታቸውን አቅጣጫ ቀየረው። ከሰውነት ወደ ጨ ካ ኝ አው ሬ ነ ት ተለወጡ።

"ታዳጊው ጦ ረ ኛ" የትርጉም መፅሐፍ ነው። የእስማኤል ህይወትን ይተርካል።

በታዳጊው ጦረኛ መፅሐፍ የሴራሊዮኑ የእርስ በእርስ ጦ ር ነ ት ህይወታቸውን በመጥፎ መንገድ የቀየረባቸውን ታዳጊዎች እንመለከታል። በነርሱ በኩል ደግሞ ሐገራችንን እናያለን።


Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
4
ዳሰሳ በይታያል አስናቀ
* * *

የዙፋን ልፊያን ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ አንብቤ ጨረስኩት ። ደረሲው ፦ በልጅነት አዕምሮው ካደገበት አካባቢ የቃረመውን ፤ በንባብ ያወቀውንና አሁን እየሆነ ያለውን እውነት ደስ በሚል አተራረክ ለመረዳት ቀላል በሆነ ቋንቋ ፅፎልናል። ለዙፋን በሚደረግ እሽቅድድም ውስጥ ማን ምን እንደሚያተርፍ ማን ምን እንደሚያጣ ልብ ያለው ልብ ይበል ይለናል።

ስሜት ያናወዛቸው ጎረምሶች ነፍጥ ሲጨብጡ፥ የእናትነት ክብር ረብ የለሽ እንደሚሆን፣ የፈጣሪ ህልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ አይተናል።

በመፅሐፉ ገፅ 2 -3 ቀጣዩ ሰፍሯል
... እድሜያቸው ምህረት አላስገኘላቸውም ፣ እናትነታቸው ከጭካኔ አላዳናቸውም ፣ ልመናቸው ከጎረምሳ ጥፊ አልታደጋቸውም ። በጠንካራ መዳፉ በጥፊ ሲመታቸው በጀርባቸው ወደቁ።
" ልጄ እናትህ ነኝ ። ፈጣሪን አታሳዝነው "
በእንባ የራሰ ፊታቸው ሌላ ጥፊ ተቀበለ ።
እያለ ይቀጥልና አድርግ የተባለውን የሚያደርግ ፣ ለምን ብሎ የማይጠይቅ መንጋ ስልጣን ሲቆጣጠር ፣ የክብር መለዮ ሲለብስ ሀገር ለውርደት ህዝብ ለስቃይ እንዲሚዳረግ ይነግረናል ።

ገፅ 41 ..." በሕግ አምላክ" እያለች መደፈሯ እንደ እግር እሳት ለበለባት ፣ "መለዮ አክብር " የተባለ ወታደር የጀመረውን ክፋት ሁሉ እርግፍ አድርጎ እንደሚተው እየሰማች አድጋ ተቃራኒው ቢገጥማት ሃዘን ሰረሰራት ።
ከራሷ ተጣልታ ፣ የገዛ እሷነቷን ተፀይፋ መኖር ጀመረች።

" ሁለት ባለስልጣናት ለመንበር ሲሉ በመጣላታቸው የተነሳ የእኔ ማሕጸን ጦር ሜዳ ሆነ " ትላለች ሆድ እየባሳት።

እርስበርስ ጦርነት ሲጀመር ሀብት ማካበት ፣ የንጉስ ዘር መሆን ፣ የተመረጥኩ ነኝ ብሎ መመፃደቅ ከምንም አለመሆን ከሳቱ እንደማያተርፍ የዙፋን ልፊያ ይነግረናል።

ገፅ 134 ... ሁለቱም ተፋላሚዎች ንፁሀንን ማጥቃት ሲፈልጉ " አሲራችሁብናል " የሚል ፈሊጥ እንደሚያመጡ ያውቃሉ። የጀነራሉ ጦር ድል ሲከዳው የመብራት ነዋሪዎችን " ለጠላት መረጃ አቀብላችኋል " ብለው ይረሽናሉ። የፕሬዘዳንቱ ሰራዊት ሽንፈት ሲጎበኛቸው " ከጠላት ተባብራችኋል " ብለው መብራታውያንን ይገድላሉ። ይለናል።

እየተጓዝንበት ያለው መንገድ አደጋ አለው የሚል ሰሚ ያጣበት የእብደት ዘመን ሲሆን ታሪክ አዋቂ አባቶች ዝም እንደሚሉ ከፊል ታሪክ አዋቂ ሆድ አደሮችም ለመኖር የሚጠቅማቸውን እመረጡ ከሁለቱ ተፋላሚዎች ጎራ እንደሚሰለፉ በ ገፅ 172 ላይ በጥሩ መንገድ ተነግሯል። "ከሁለቱም ወገን የተሰለፉ ታሪክ አዋቂዎች ከፊል እውነት ቢኖራቸውም እውነታቸው የተሟላ አይደለም። ረጅም በሆነው የሐገሪቱ ታሪክ እርስ በእርስ የመነካከስ ዘመን ነበር ። ነገር ግን የተነካከሱት ተሳስመው ያውቃሉ። መገፋፋት የገነነበት ዘመን የመኖሩን ያህል የመተቃቀፍም ዘመን ነበር ። በታሪክ አጋጣሚ ለጥፋት የተፈላለጉቱ የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም አብረው ተሰልፈውም ያውቃሉ።
የተሟላ እውነት ምን እንደሆነ የታሪክ ባለሙያዎቹ የሚያውቁ ቢሆኑም ሐቅ ላይ ምራቃቸውን ለመትፋት አላመነቱም ። ከትላንት ገፅ ላይ ለእኩይ አላማቸው የሚበጃቸውን ብቻ መዘዙ..." ይለናል

ይሄ ምናብ የወለደው ፈጠራ ብቻ አይደለም ። በገፀባህሪያት ተዋቅሮ በመቼት ተወክሎ የቀረበ የትላንት እና የዛሬ ታሪካችንን ፣ የነገ ስጋታችንን እና የተደቀነብንን አደጋ ገልፆ የሚያስጠነቀቅ ሰነድ እንጂ።

የጎረቤቶቻችኝ የሴራሊዮን የእርስበርስ ጦርነት እና ዮጋንዳ ሁቱ ቱትሲ እልቂት ፣ በየቀኑ እየሰማነው ያለነው የሱዳናውያን እብደት እንዳይደርሰን ቆም ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል። በርግጥ በከፊል ጀምረነዋል። ባለፉት ጥቂት አመታት ያየናቸው መጠፋፋቶች ውጤታቸው በዜሮ እንደሚባዛ ።

የሆነው ሁሉ ሆኗል ። የምንፈራው እንዳይሆን ከልባችን ስራ እንጀምር ።
ከቁርበትዎ ይምከሩ እንዳለው አለማየሁ ገላጋይ በመለያየት ሞት ነው መፅሀፉ

👉 ስለ - ሀገር ፣ ህዝብና መንግስቱ ሲል ከ ቁርበቱ የሚመክር መሪ እንዲኖረን ።
👉 የለበሰውን መለዮ እና የገባውን ቃልኪዳን የሚያከብር የሀገር ዘብ ወታደር እንዲኖረን
👉 እውቀታቸውን እና ታሪካቸውን በሆዳቸው የማይለውጡ ምሁናንና አዋቂዎች እንዲበዙ
👉 ለምን የሚል ጠያቂ ፣ የሀገሩ መፃኢ እድል የሚገደው ትውልድ እንዲፈጠር በጣም ብዙ ብዙ መስራት እንዳለብን የተገነዘብኩበት መፅሀፍ ።

#የዙፋን_ልፊያ 👌👌👌
ሻሎም

@Tfanos
1
ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ "ጠርዝ ላይ" የሚል መፅሐፍ አለው። ዶክተሩ ካሳተማቸው ስራዎች ሁሉ "ጠርዝ ላይ"ን እና "የማይፃፍ ገድል"ን እወዳለሁ።

ጠርዝ ላይ ጥሩ ስራ ነው። 4 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። ከጉዳዮቹ መካከል አንዱ ቋንቋ ነው።

እንደሚታወቀው ዶክተር በድሉ የቋንቋ ባለሞያ ነው። ይህን ተከትሎ ስለ ቋንቋ ፖሊሲ ሞያዊ ማብራሪያ አስፍሯል።

ጠርዝ ላይን ያነበበ የቋንቋን ጉዳይ በእውቀት መዳኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ይረዳል። ነገረ ቋንቋን ስሜት ይጫነዋል። ሰዎች ከቋንቋ ጋር የተገናኘ ሙግትን በእውቀትና ምክኒያት ከማድረግ ይልቅ ስሜታዊነት ይጫናቸዋል። ጦ ር መማዘዝ ይቃጣቸዋል።

ይህ የብዙ አከባቢዎች ችግር ነው። ዶክተር በድሉ በማስረጃ ጭምር እንደጠቀሰው በብዙ ሐገራት ሰዎች ስለ ቋንቋ ሲወያዩ ስሜታዊ ይሆናሉ። ፀብ ፀብ ይላቸዋል። እነሱ ከሚያምኑት ውጭ የሆነውን መቀበል ይተናነቃቸዋል።

ዶክተር በድሉ "ግእዝ ሞቷል" እንዳለ ሰምተናል። ይህ ብዙ ሰዎችን አናዷል። አጠቃላይ ስለ ቋንቋው የሰጠው አስተያየት ያስቆጣቸው ብዙ ናቸው። ይህ ይጠበቃል። እንግዲህ ራሱ በድሉ ጠርዝ ላይ በሚለው መፅሐፉ እንደጠቀሰው ሰዎች ስለ ቋንቋ ሲነሳ ስሜታዊ ይሆናሉ።

ግን ደግሞ ስሜትን መግራት ያስፈልጋል። ዶክተሩ ላይ ውርጅብኝ ማውረድ አይረባም። ጠቃሚው ነገር ያነሳቸው ነጥቦችን መሞገት ነው።

ግእዝ ሞቷል ወይስ አልሞተም?
ግእዝን ለልጆች ማስተማር ጊዜ ማባከን ወይስ ጠቃሚ?
ግእዝን ለጥናት አላማ ፥ ለምርምር ወዘተ የሚፈልጉ ሰዎች በፈቃደኝነት ይማሩ ወይስ ከታች ይጀመር?
ግእዝን ማወቅ መሰረታዊ ፋይዳው ምንድነው? ጠቃሚው ጉዳይ እኒህ ነጥቦች ላይ መወያየትና መሟገት ነው።

ስሜት ይቀነስ

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
4👍4👎2
ቋንቋ እንዴት ይለመዳል?
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ስለ ቋንቋ ለመዳ እናውራ፥

ቋንቋ ከሰው ልጅ ስነልቦናዊ ስሪት ጋር ባለው ተዛምዶ መነሻ ለስሜት ቅርብ ነው። ከታሪክ እና ማህበራዊ ፍልስፍና ጋር መነካካት ስላለው ኮርኳሪነቱ ያይላል።

የቋንቋ ጉዳይ እጅግ ለስሜት የቀረበ ነው። ማንነት እና ባህልን ገላጭ መሆኑ የጉልበቱ ምንጭ ሊሆን ይችላል።
በተለይ ቋንቋ እና ፖለቲካ ያለ አግባብ ሲጋቡ የደም መፍሰስ ሰበብ ሊሆን ይችላል።

እኛ ሐገር የተለያዩ ብሔሮችን ቋንቋ ባለመቻላቸው የተነሳ የሚወቀሱ በልባቸው ጥላቻ እንዳደረ ተፈርጀው የሚከሰሱ አሉ።
"በኛ ክልል ተወልደው አድገው ቋንቋችንን የማያውቁ ሰዎች ምክኒያታቸው ጥላቻ ነው" እየተባለ ይነገራል።

ወቀሳውን በቅንነት መረዳት በጎ ሆኖ ሳለ ከግንዛቤ ሊገባ የሚገባ እውነታ አለ።

አንድ ሰው በይርጋዓለም በመወለዱ ብቻ ሲዳምኛ እንዲችል መጠበቅ ስህተት ነው። በሻሸመኔ ተወልዶ ያደገ ሁሉ ኦሮምኛ እንዲችል ማሰብ የዋህነት ነው። በወልቂጤ የኖረ ሁሉ ጉራግኛ እንዲናገር ማሰብ ጥፋት ነው።
ጂኦግራፊ ቋንቋን ማወቂያ ሰበብ አይሆንም። የቋንቋ ለመዳ ነገር ብርቱ የሆነ ገፊ ምክኒያት ከጀርባው አለ።

ሰሞኑን ግእዝ መነጋገሪያ ሆኗል። ተማሪዎች ግእዝን መማር አለባቸው ወይስ የለባቸውም በሚል ርዕስ ውዝግብ ተፈጥሯል። ውዝግቡ ሲጨመቅ ጥቂት ግን አንኳር ነጥቦች አሉት። እነርሱም ሴኩላሪዝም ፥ የግእዝ ፋይዳ ፥ የቋንቋው ህልውና (ሞቷል ወይስ አልሞተም) ፥ መማር የሚጀመርበት ወቅት (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎች ለጥናት አላማ ይማሩት ወይስ ከታች ይጀመር) የሚል ነወ። ለውዝግቡ መፍትሄው በእውቀት መሟገት ነው።

አጀንዳዬ ቋንቋ እንዴት ይለመዳል የሚል ነው። የግእዝንም ጉዳይ በዛው መዳኘቱን ለናንተ ልተወው።

የቋንቋ ለመዳን በግርድፉ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል።

ሀ፥ ተግባቦታዊ ምክኒያት

ሰዎች ከሰዎች ጋር ለመግባባት ፥ አዲስ ባህል ለመልመድ፥ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ፥ ጉብኝት እና መሰል ሰበቦችን መነሻ በማድረግ ቋንቋን ሊማሩ ይችላሉ። በዚህ ምክኒያት የሚደረግ የቋንቋ ለመዳ 'ተግባቦታዊ' ተብሎ የሚፈረጅ ነው።
ትልቁ ቁምነገር፥ በዚህ አይነት መንገድ ቋንቋን ማስፋፋት ዳገት መሆኑ ነው። ውጤታማ አይደለም። ተግባቦትን ብቻ ከግምት በማስገባት ቋንቋ ለመማር የሚጥር ሰው የሆነ ሰአት ላይ ቸል ይላል። አንዳች ተጨባጭ ፋይዳ ስለማያገኝበት ይሰለቸዋል።

ለ፥ ኢንስትሩመንታል ወይም ኢኮኖሚያዊ ምክኒያት

ቋንቋን ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወይም ለአንዳች ፋይዳ መማር በዚህ መደብ ይመደባል።
አንድ ግለሰብ አንድን ቋንቋ ተቀጥሮ ሊሰራበት ፥ ሰነድ ሊተረጉምበት ፥ ሃይማኖት ሊያስፋፋበት፥ ፖለቲካ ሊያስፈፅምበት፥ ኪነጥበብ ሊከይንበት ከተማረ "ኢኮኖሚያዊ ወይም ኢንስትሩመንታል ምክኒያት" ይባላል።

ይህ ውጤታማ ነው። በሁለተኛው ሰበብ ቋንቋ በቀላሉ ይስፋፋል። ብዙ ተናጋሪ ይኖረዋል። እንግሊዘኛ ወይም አረብኛ አሊያም ፈረንሳይኛ ከሐገራችን ደግሞ አማርኛ የተስፋፋው በዚህ ምክኒያት ነው። አረብ ሐገር ለስራ የሚሄዱ ሴቶች በአጭር ጊዜ አረብኛ የሚለምዱት በዚህ ሰበብ ነው።

ሁለቱን ነጥቦች የሚገልፅ ቀላል ምሳሌ፥
ለአመታት በኢትዮጵያ ስትኖር አፍ ከፈታችበት ቋንቋ ውጭ ሌላ ቋንቋ የማታውቅ ፥ በሐገሩ ሲኖር ከአካባቢው ውጭ ሌላ ሐገርኛ ቋንቋ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ብዙ ነው። በሐገራቸው ተጨማሪ ቋንቋ ለመልመድ መነሳሳት ያጡት ለምንድነው? መልሱ ግልፅ ነው። የቋንቋ ለመዳ ምክኒያቱ ተግባቦታዊ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ከሐገር ሲወጣ ሌላ ቋንቋ ፈጥኖ ይማራል። አረብኛ ወይም ቻይንኛ አሊያም ሌላ ቋንቋ ፈጥኖ ይለምዳል። ለምን? ምክኒያቱም በአዲሱ ቋንቋ እንጀራ ይጋግርበታል።

በአጭሩ ፥ እንጀራ የሚጋገርበትን ቋንቋ ሰዎች ለመማር ይነሳሳሉ ፥ ያለመገደድ ፈጥነው ይለምዳሉ። ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቋንቋውን ያውቁታል።

እንደምድመው፥

የቋንቋን ጉዳይ ከአውድ ውጭ መበየን አግባብ አይደለም። ሚዛን በጠበቀ ሁኔታ ቋንቋን ማሳደጊያው መንገድ ፖሊሲ ነው። ዜጎችን 'ቋንቋዬን ካልለመዳችሁ ነገር አለ ማለት ነው' ማለት አይበጅም። ይልቅ ሳይንሳዊ እና ዘላቂ የሆነ ፣ የጋራ ጥቅምን ከግምት ያስገባ የቋንቋ ፖሊሲ እንዲዘጋጅ መንግስትን መጠየቅ ይበጃል።

ጠቃሚው እውነታ ፥ ቋንቋ እንጀራ ሲጋገርበት ፣ እውቀት ሲሰነድበት ሰዎች ተረባርበው ይማሩታል።


@Tfanos
2👍1
ግእዝ ሞ ቷ ል?

"ቋንቋ ይወለዳል ያድጋል ይ ሞ ታ ል" ይህን የተማርነው ገና የ 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ሳለን ነው። ይህን ማንም ያውቃል። ግእዝ ከዚህ አንፃር እንዴት ይታያል? ሞ ቷል ወይስ አልሞተም?

ለሰሞንኛው ውዝግብ መፍትሄው ጠቃሚ ጥያቄዎችን መጠየቅ ነው

1፥ አንድ ቋንቋ ሞ ተ የሚባለው በምን አይነት ሳይንሳዊ መመዘኛ ነው?
2፥ ግእዝ በሳይንሳዊ መመዘኛ ሞ ቷል ይባላል ወይ?
3፥ አንድ ቋንቋ ቢሞ ት መቀስቀስ ይቻላል ወይ?
4፥ ግእዝን እነማን ይማሩ? ከታች ጀምሮ ልጆች ይማሩት ወይስ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከጥናትጋ በተያያዘ አላማ በምርጫቸው ይማሩት?
5፥ ግእዝን መማር ያለው ተጨባጭ ፋይዳ ምንድነው?
6፥ ግእዝ ሴኩላር ነው ወይስ ሃይማኖታዊ?
7፥ አንዳንድ ማስተማሪያ ምሳሌዎች ሲዘዋወሩ ሰሞኑን ተመልክተናል። ምሳሌዎቹ ሀይማኖታዊ ናቸው። የሌለ እምነት ተከታይ ልጅ በዚህ መንገድ መማሩ አግባብ ነው?

እርግማንና ቁጣ የትም አያደርስም። እልህ መጋባትና ስሜታዊነት አይጠቅምም። ስለዚህ በስክነት ፥ በእውቀትና በምክኒያት መወያየት ያስፈልጋል። የተለየ ሃሳብ ያራመዱ ሰዎችን መወረፍ አይጠቅምም።

አጠቃላይ ወቅታዊውን የግእዝን ጉዳይ በተመለከተ የተነሱ ሰሞንኛ አጀንዳዎች ከላይ በተነሱ ጥያቄዎች የሚጠቀለሉ ይመስለኛል። ስለዚህ ለጥያቄዎቹ ተጨባጭ መልስ ማፈላለግ ይሻላል።

@Tfanos
👍32
ስለሐገራችን ሙስሊሞች
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

የትላንት ሙስሊሞች፦ ጀጎልን አነፁ፥ አሚሮቹ ሐረርን አቅንተው የከተማ መንግስትን አቆሙ።
የሙስሊሙ ኡማ አሻራ ቀላል አልነበረም። የጊቤ መንግስታት ላይ ባለድርሻ ናቸው፥ የጂማን መልክ አበጃጅተዋል፥ ደግሞም የአዳል ሱልጣኔትና የፈጣጋር ታሪክ የነሱ ነው።

በእውነት ሚዛን ታሪክን ከለካን ፥ሙስሊም አባቶች ኢትዮጵያን ገንብተዋል።
ከአፋር እስከ ሱማሌ፥ ከወሎ እስከ ባሌ፥ ከምስራቅ እስከምራብ ፥ ከሰሜን እስከደቡብ ህያው ማህተም አኑረዋል።

ዛሬ ጥቂት ሙስሊሞች ላይ የምወቅስባቸው ነገር አለ። አባቶቻቸው ባቀኑት ሐገር ባለቤትነት አይሰማቸውም፥ አንዳንዶቹ በማይረባ ነገር ጭምር "እዬዬ" ማለት ቁም ነገር ይመስላቸዋል፥ 'የኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክ' ሲባል የአፄዎቹ ነገር ብቻ ትዝ ይላቸዋል። ደጋግመው "ኹለተኛ ዜጋ አታድርጉን" ይላሉ።

በእርግጥ ትላንት መሰደድ እና ባይተዋርነት ነበር። ለዲናቸው የታመኑቱ በቦሮ ሜዳ እንደ እንስሳ ታርደው ደማቸው ኩሬ ሰርቷል፥ በደልን አስተናግደዋል።

ታሪክ ግን የመገፋቱ ብቻ አይደለም።

የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሙስሊም አባቶች ጉልህ ሚና ነበራቸው። የኢትዮጲያ ትላንት ቢመረመር ፥ አከባቢዎች ቢቃኙ ያለ ሙስሊሙ ታሪክ የሐገሪቱ ታሪክ ሙሉ አይሆንም።

ጀግል የጎደለበት፥ ኢማሙ የሌለበት ፥ አዳል የተረሳበት ፥ ሼህ ጦሏህ የማይዘከርበት ፥ ቢላል የማይታወስበት ታሪክ ሙሉ አይደለም። ያለ ጥርጥር ትላንታችን የሙስሊሙ ማህበረሰብ በጎ አሻራ የታተመበት ነው።

ይህን ሐቅ መረዳትና ማክበር የሁሉም ሃላፊነት ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚና የማይተካ ነው።

ነገር ግን ጥቂት ያልሆኑቱ ለታሪካችው ተገቢውን ክብር የነፈጉ ሰነፎች ሲሆኑ ይታያል።

ምን እያልኩ ነው?

የሙስሊሙ ኡማ 'የኢትዮጵያ ሙስሊሞች' ታሪክን ሲዘክር መገፋትና መከራው ላይ ብቻ ማተኮር ስህተት ነው። ይህ ባይተዋርነትን ሊፈጥር ይቻላል።
ደማቁን እና ያልተነገረውን የሐገር ገንቢነት ታሪክ በኩራት እና በልበ ሙሉነት ማውሳት መዘንጋት የለበትም !

(ድጋሚ የተለጠፈ


@Tfanos
👏43
ፓስተር ፀባኦት እንግዳን አገኘሁት

የዘጠናዎቹ ጴንጤዎች መጋቢ ፀባኦት (ሰብስተን) በደንብ የምታውቁት ይመስለኛል። በስም ባታውቁት እንኳን "ሰማዩ ቢጠራ" የሚለውን መዝሙር በደንብ ታውቁታላችሁ።

"የታመንኩት ጌታ ፥ ተስፋ ያደረግኩት
ቃሎቼን አምኜ ፥ ህይወቴን የሰጠሁት
ሰማዩ ቢጠራ ፥ ለምን እጨነቃለሁ
ይዘንባል ያለኝን ፥ ጌታን አምነዋለሁ
ቃሉን አምነዋለሁ"

ይህን መዝሙር የማይወድ ይኖራል? አይመስለኝም።
የሃዘናችንን ወቅት ያሻገረን ፥ ተስፋ ስንቆርጥ ያነቃን መዝሙር ነው።
ፀባኦት አሁን በሐገረ እስራኤል ይኖራል። ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስለነበር ተገናኝተን ሻይ ጠጣን።

ከላይ ያለውን መዝሙር የፃፈበትን ሁኔታ ጠየቅኩት። በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለ የደረሰው መዝሙር ነው። ከጉሮሮ ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ድንገት ገጠመው። ቀላል የመሰለው ችግር ተወሳሰበ። ማገገም አቃተው። ወደ ሕክምና ተቋም ቢያመራ መታከም አይችልም አሉት። ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ገባ። በዛ ሁኔታ ውስጥ እያለ መዝሙሩን ፃፈው።
በመዝሙሩ ቀጣዮቹ ስንኞች ተካተዋል።
"ድንገት ድምፅ ሰማሁ፥ ከጨለማው መሐል
አይዞህ አትፍራ የሚል ፥ የሚያበረታ ቃል"

መዝሙሩ አፅናኝ ነው። ብዙ ሰዎች ተስፋ በቆረጡበት ወቅት መፅናናት አግኝተዋል። ህይወት ጨልሞባቸው ሳለ በርትተውበታል። በመከራ የሚያልፉ "የታመንኩት ጌታ" ብለው እየዘመሩ ተበረታተዋል።
ደግሞ የመዝሙሩ ዜማ 👌

አንድ ቀን መጋቢ ፀባኦት እና ሌሎች ሁለት አገልጋዮች በመኪና እየተጓዙ ነበር። ሾፌራቸው "የታመንኩት ጌታ" የሚለውን መዝሙር እየደጋገመ ይሰማዋል። ይሄኔ "ዘማሪውን ታውቀዋለህ ወይ?" ብለው እንደዋዛ ጠየቁት። "አላውቀውም ፥መዝሙሩ ብዙ አፄናንቶኛል። ደግሞ ዘማሪው እንደ ሞ ተ ሰምቻለሁኝ" አለ። ፀባኦት በአደጋ እንደ ሞ ተ በሀዘኔታ ለፀባኦት ነገረው። ፀባኦት በእርጋታ ዘማሪው ራሱ እንደሆነ ነገረው። ሾፌሩ አለቀሰ።

ሰሞኑን ከፀባኦት ጋር ሻይ ሰለጠጣን ደስ ብሎኛል። ሻይ እየጠጣን ስለ ተስፋዬ ጫላ አነሳን። ሰፊው ህዝብ እንደሚያውቀው በተስፋዬ መጠን የምወደው ዘማሪ የለም። ከፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ፥ ከገጣሚ በእውቀቱ ስዩም ፥ ከፀሐፊ ሐብታሙ አለባቸው ፥ ከእግርኳሰኛ ሊዮ ሜሲ ፥ ከዘማሪ ተስፋዬ ጫላን እወዳለሁ። የተስፋዬ መዝሙሮች ለኔ ቴራፒዬ ጭምር ነበሩ። ይህን ከዚህ በፊት ፅፌያለሁ። የፃፍኩትን ፀባኦት ለተስፋዬ አጋርቶታል።

ግብዣ ፥ የመጋቢ ፀባኦት (ሰብስተ) እንግዳን የታመንኩት ጌታ (ሰማዩ ቢጠራ) የሚለውን መዝሙር ጋብዣቸኋለሁ።


@Tfanos
4🔥4
ልንመርቅ ነው።

ከዚህ ቀደም ለዙፋን ልፊያ መጻሕፍ የምርቃት ፕሮግራም አስበን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተሰርዞ ነበር። ድግስ መሰረዝ ይጎዳል፥ ቅር ያሰኛል። አሁን የተሰረዘው ዳግመኛ ተሰናድቷል።

የዙፋን ልፊያ መስከረም 14 (የፊታችን ረቡዕ) በ10:30 በወመዘክር ይመረቃል።

ማስታወሻ፥ ከዚህ ቀደም ለንባብ ያበቃሁትን ነገን ፍለጋ የተሰኘ የአጫጭር ልብወለዶች መጻሕፍ ያላገኛችሁ በዙፋን ልፊያ ምርቃት እለት ታገኛላችሁ።

ቀን ፥ መስከረም 14
ቦታ ፥ ወመዘክር
ሰአት ፥ 10፥ 30
🔥52
Tesfaab Teshome pinned «ልንመርቅ ነው። ከዚህ ቀደም ለዙፋን ልፊያ መጻሕፍ የምርቃት ፕሮግራም አስበን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተሰርዞ ነበር። ድግስ መሰረዝ ይጎዳል፥ ቅር ያሰኛል። አሁን የተሰረዘው ዳግመኛ ተሰናድቷል። የዙፋን ልፊያ መስከረም 14 (የፊታችን ረቡዕ) በ10:30 በወመዘክር ይመረቃል። ማስታወሻ፥ ከዚህ ቀደም ለንባብ ያበቃሁትን ነገን ፍለጋ የተሰኘ የአጫጭር ልብወለዶች መጻሕፍ ያላገኛችሁ በዙፋን ልፊያ ምርቃት…»
ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው?

የዙፋን ልፊያ መስከረም 14 ይመረቃል። (መፃሕፍ ፆታው ወንድ ነው ወይስ ሴት?🤔)

በምርቃቱ በርካታ እንግዶች ይገኛሉ።

ምህረት ታሪኩ ፥ ቤተማሪያም ተሾመ ፥ ሀብታሙ ሀደራ ፥ ታዲዮስ አዲሱ ፥ አንዱ ጌታቸው ግጥም ያቀርባሉ።

ረድኤት ዳዲ የስነልቦና ባለሞያ ስትሆን የዙፋን ልፊያን በሞያዋ መነፅር ትዳስሰዋለች።
ምግባር ሲራጅ ዳሰሳ ያቀርባል።
ዋሲሁን በላይ ከመጻህፉ ይተርካል።

ዶክተር ኤርሲዶ ፥ ተስፋዬ ማሞ እና ቤጃይ ኔርሽ የክብር እንግዶች ናቸው።

መድረኩን ጋዜጠኛ ብስራት መለሰ ያጋፍረዋል።

ዝግጁ?

በእለቱ የተወሰኑ የነገን ፍለጋ ኮፒዎችን ታገኛላችሁ።

እለት ፥ መስከረም 14 (ረቡዕ)
ሰአት ፥ 1ዐ : 30
ቦታ ፥ ወመዘክር
1👍1
ነገ ንጥቀት እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሰሞኑን ፈረንጆችን ጨምሮ አንዳንድ አማኒያን ነገ ንጥቀት እንደሆነ እየተናገሩ ነው።

የሚያወሩት እውነት ከሆነ የተወሰኑ አማኞች ነገ ይነጠቃሉ። ሌሎቻችን ታላቁን መከራ እንቀበላለን። (ያድርግላቸው)

እንደ ሐሳብ ግን ፥ ከነገ ወዲያ የመጽሐፍ ምርቃት ስላለኝ ንጠቀቱ ሐሙስ ቢሆን ጥሩ ነው። ካልሆነ ግን ምን ይደረጋል?

ነገ ፃድቃን ከተነጠቁ በኋላ በምድር የምትቀሩ ሰዎች ሐሙስ በመጽሐፍ ምርቃት ፕሮግራሜ ተገኙልኝ
😁102
በዙፋን ልፊያ መጻሕፍ ምርቃት እነማን ይገኛሉ?

ረድኤት ዳዲ

ረድኤት የስነልቦና ባለሞያ እና አሰልጣኝ ናት። በሃሴት የማማከር አግልግሎት የምክክር አገልግሎት ትሰጣለች። በዙፋን ልፊያ መጻሕፍ ምርቃት ላይ ከሚገኙ እንግዶች መካከል አንዷ ረድኤት ዳዲ ስትሆን መጻሕፉን ከሞያዋ አንፃር ትመለከታለች።

ምግባር ሲራጅ

ምግባር ሦስት መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል። ዘንባባ ፥ መንደሪን መንደሪን እና እየዳነ ኼደ ለንባብ ያበቃቸው ስራዎቹ ናቸው። ምግባር የዙፋን ልፊያ ላይ ዳሰሳ ያቀርባል።

ዋሲሁን በላይ

ገጣሚ ተዋናይ እና ደራሲ ነው። በቅርቡ ለንባብ ያበቃው የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው አልንበረከክም መጻሕፍ በአጭር ጊዜ ሁለተኛ እትም ደርሷል። ዋሲሁን ሲተረክ የተለየ ሰው ነው። የሱን ትረካ አለመውደድ አይቻልም። ዋሲሁን ከዙፋን ልፊያ አንድ ክፍል ይተርክልናል።

ተስፋዬ ማሞ

ጋሽ ተስፋዬን ማስተዋወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። ዘርፈ ብዙ ባለሞያ ነው ብዬ ብናገር ለ ቀ ባ ሪ ማርዳት ይሆንብኛል። በሸገር ኤፍ ኤም የሚያዘጋጀው የጥበብ መንገድ የሬዲዮ ፕሮግራም ሰቃይ ፕሮግራም ነው። ነጎድጓዳማ ድምፁ እና የንባብ ዝግጅቱ የፕሮግራሙ ድምቀት ናቸው። ከማዕበል ማዶ በቅርቡ ለንባብ ያበቃው የግለ ታሪክ መጻሕፍ ነው። ተስፋዬ ማሞ የክብር እንግዳ ነው።

ዶክተር ኤርሲዶ ለንዴቦ

የአራዳ እና የአዋቂ ቅልቅል ከፈለጋችሁ ዶክ እውነተኛ ማሳያ ነው። ኤርሲዶን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኹት ኑሮ ማፕ በሚለው መጻሕፍ ነው።
ኤርሲዶ አንደበቱ ርቱዕ ነው። ተራማጅ ነው። ሃሳቡን አደራጅቶ መግለፅ ያውቅበታል። ሞጋች ነው። የልጆቻችን ኢትዮጵያ የተሸኘው ተወዲጅ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ነው። (የአያን ራንድም ወዳጅ ነው😀) ኤርሲዶ የክብር እንግዳችን ነው።

ደግሞ በፕሮግራማችን የተዋጣላቸው ገጣሚያን አሉ።

አንዱ ጌታቸው በጣም የተለየ አፃፃፍ የሚከተል ገጣሚ ነው። አነባበቡም እንደአፃፃፉ ነው። የሚፅፍበት መንገድ ደስ ይላል።

ቤተማሪያም ተሾመ ገጣሚ ብቻ ሳይሆን የግጥም ተርጓሚም ጭምር ነው። በአንድ ወቅት እንዳለጌታ ከበደ "በአገራችን ካሉ ሦስት ምርጥ የግጥም ተርጓሚዎች መካከል ቤተማሪያም ይገኝበታል" ብሎናል።

ሀብታሙ ሀደራ ፥ ሰዎች በስምምነት በጅምላ የሚወዱት ገጣሚ ነው። ግጥሞቹን አያወሳስብም። ሁሉም ሰው እንዲረዳውና ለንባብ እንዲመች አድርጎ መፃፍ ያውቅበታል።

ታዲዮስ አዲሱን እንደማደንቀው ለብዙ ሰው ተናግሬ አውቃለሁ። ግጥሞቹ ብቻ ሳይሆን የሚያነብበትም መንገድ ይለያል። ረጃጅም ግጥሞቹ እንኳ ከጥፍጥናቸው ብዛት አጭር ይመስላሉ።

ምህረት ታሪኩ ጎበዝ ገጣሚ እንደሆነች መቶ ሰባ ሚሊዮን ጊዜ ነግሬያት አላመነችኝም። እናንተ ትነግሯታላችሁ።

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ግጥሞቻቸውን ያቀርባሉ።

መድረክ አጋፋሪው ጋዜጠኛ ብስራት መለሰ ነው። ብስራት በተለያዩ ሚዲያዎች ይታወቃል። በተለይ በፋና ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንዲሁም በሐገሬ ቴሌቪዥን እናውቀዋለን። (በሐገሬ አመራርም ነበር)
አለም አቀፍ የፖለቲካ ትንታኔዎቹ ይወደዱለታል።

ኢንጂነር ቤጃይ ኔርሽ...

ቤጃይን አላስተዋውቅም 😎

እኒህ ሁሉ እንግዶች የናንተን መገኘት ይጠብቃሉ።

ኑ፥ የዙፋን ልፊያን እንመርቅ

ቦታ ፥ ወመዘክር
ቀን ፥ መስከረም 14 (የፊታችን ረቡዕ)
ሰአት ፥ 10:30

ይህን ለሌሎች አጋሩ
4
ነገ

በታ ወመዘክር
ሰአት ፥ 10 : 30

#የዙፋን_ልፊያ
4
ዳሰሳ በቶፊቅ ተማም
* * *
የዙፋን ልፍያን እንዳነበብኩት
የመፅሀፉ ርእስ ፡- የዙፋን ልፍያ
የህትመት አመት ፡- ነሀሴ 2017
የታተመበት ማተሚያ ቤት ፡- ሀይማኖት ማተሚያ ቤት
የገፅ ብዛት ፡- 179
ደራሲ ፡- ተስፋአብ ተሾመ
በቶፊቅ ተማም

በማህበራዊ ሚዲያ ደርዝ ባላቸውና በተመጠኑ ፅሁፎችና በተለይ ግላዊ እይታዎችን በማጋራት ይታወቃል። ከዚህ በፊት በክልል የሬድየ ጣቢያዎች በጋዜጠኝነት ሰርቷል ክራራዊ ህይወት እንዲሁም የአጭር ልቦለዶች ስብስብ የሆነውን ነገን ፍለጋ የተሰኘ መፅሀፍ የሰጠን ተስፋአብ ተሾመ አሁን ደግሞ አቅሙን አጠናክሮ እና በንባብ ዳብሮ የዙፋን ልፍያ የተሰኘ ሶስተኛ እና ወጥ የሆነ ልብ ወለድ ስራ ለአንባብያን ያቀረበ ሲሆን እኔም መፅሀፉን አንብቤ የተሰማኝን ከዚህ በመቀጠል አሰፍራለሁ ፡፡

የተናቀው ሽበት

የመፅኀፉ ዋና ኣላማ በተለይ የጦርነት መነሻ እና ከጦርነት በኋላ የአንድን ሀገር ብሎም ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ቁሳዊ ኪሳራ ማሳየት ከዚህ ባለፈም የሚታየውን የሞራል የባህል ኪሳራም ያሳያል። በዚህ ርእስ ላይ የጦርነትን ዳፋ በተለይ ለሴቶችና አረጋውያን እጅግ የባሰ መሆኑን አሳይቶናል "እባክህ ልጄ" በደፈሰ አይኑ ሲያፈጥባቸው የሚናገሩት ቸገራቸው ልባቸው ራደ እድሜአቸው ምህረት አላስገኘላቸውም›› በማለት በመቁረብያ እድሜ ስለተደፈሩት እናት ያወሳናል ይህ ፀሀፊው ያሰፈረው ሀሳብ በእውኑ ከአመት በፊት እድሜአቸው ወደ ሰማንያ በላይ የሆኑ አዛውንት ላይ እዚሁ ሀገራችን የተከሰተ ድርጊት መሆኑ ይታወሳል።

‹‹ ይህን ዘመን ላለማየት ከታላቁ መከራ በፊት ግደለኝ ብለው ቢፀልዩም ምላሽ አላገኙም ›› በማለት በጦርነቱ ሳቢያ የተደፈሩት የመብራት ኣዛውንት መጨረሻ በዚህ መልኩ መገባደዱን አየነገረን ጎን ለጎንም ጦርነት የሀገሪቱ ትውፊት የነበረውን እርስ በእርስ የመከባባር ስርአት ጦርነት እንደሚንደው አሳይቶናል ፡፡

ልፍያና ፍልሚያ

‹‹ ባለስልጣናቱ በአንደበታቸው ቃል ይዋጋሉ ወታደሮች በጠመንጃ ይጠዛጠዛሉ የሀብታሞችን ጦርነት ድሆች ይዋጋሉ የሹማምንት ልፍያ የተርታ ዜጎች ፍልሚያ ነው ››ገፅ 11 በማለት የጦርነት ደርዙ አንድም ልፍያ አሊያም ሲብስና የሻቱትን ማግኘት ግድ ሲል ፍልሚያ መሆኑን የሚነግረን ተስፋአብ፥ ካለይ እንደተገለፀው አሁንም የሴቶች መደፈር ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን በሚያስንቅ ክፋት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ሞት እና እንግልት ለማሳየት ሞክሯል ።

"አስገድዶ መድፈር ውስጣቸው ያለውን አውሬ ማርካት ያልቻሉ በደፈሯቸው ሴቶች ላይ ጥይት አርከፈከፉ" በማለት የተደፈሩ ሴቶች በአውሬዎች መበላታቸውን ይግልፃል። ከዚህ ባለፈ ጦርነቱ የወጣቶችን ተስፋን የሚያጠፋ መሆኑን እንዲህ አስቀምጦታል ፡፡
"ተስፋ ነበራቸው ፥ ብዙ የመኖር፥ ወላጆቻቸውን የመጦር ፥ የመርዳት ታላላቆቻቸውን የማርካት ተስፋ ነበራቸው ፖለቲካው በላው " ገጽ 12

ጦርነት በተለይ ቀጣይ ሀገር ተረካቢ የሆኑ የወጣቶች ታዳጊዎች ህይወት እንደሚያጨልም ለማሳየት ሞክሯል። ጦርነት ከመጣ ሁልም ነገር የቅርብ ሩቅ መሆኑን እንዲህ በሚል ይገልፃል ፡፡ ‹‹የጦርነት እሳት ሲለኮስ ባለፀጎቹ ገንዘባቸው አላዳናቸውም። ምግብ እያለ ለተራቡ ፥ ገንዘብ እያላቸው ተቸገሩ፥ የአልጋ ቁራኛ ሲሆኑ መድሀኒት ማግኘት አልተቻላቸውም ›› ገፅ 23

የሰላም እጥረት የሚያደርሰውን ኪሳራ ለማሳየት ሞክሯል። ሌላው በመፅሀፉ ያነሳው ሀሳብ ኦሜርታ የተባለውን አቋም የሚያንፀባርቁትን አላየንም አልሰማንም አንናገርም በማለት በብዛት የሚታወቁትን ምሁራን ስለ ሀገር ሰላም እንዲሰሩ የጠቆመበት ነው ፡፡‹‹ መ ሀ ይ ም የሚያቦካው ፖለቲካ ›› በማለት ከገዛ ሀገራቸው ጉዳይ ራሳቸውን ገለል ቢያዳርጉም ከገፈቱ አላመጡም። አላዋቂዎች ያሏቸው በህይወታቸው ላይ ወሰኑ ከጎናቸው ያልተሰለፉት ለሞት እና ለመከራ ዳረጓቸው ›› ገፅ 23
ምሁራንም የገፈቱ ቀማሽ መሆናቸውን ለመጥቀስ ሲሞክር፥ ምሁራን በተለይ ሀገር ወደ ጦርነት እንዳትገባ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ለመጠቆም ሞክሯል ፡፡

በህግ አምላክ

ከጦርነት አንዱ ዳፋ የትዳር ባላጋራን ብሎም ቤተሰብን ማጣት እንዳለ ሆኖ ተደፍሮ ህይወት መበላሸትም የሚያጋጥም መሆኑን በዚህ ክፍል አሳይቶናል
‹‹ በህግ አምላክ እያለች ብትማፀንም ከመደፈር አልዳነችም። መለዮህን እክብር ብትልም አልሆነም። መደፈሯንም ተክትሎ በመጣው ፅንስ ሳቢያ ማስወረድን ብትፈልግም ማስወረድ ለጤና አደጋ በመሆኑ ሳቢያ ያልፈለገቸውን ልጅ ወልዳ ለማሳደግ ያልተረፈችው ህመሟን የምታስታግስበት የወለደችውን የአብራኳን ክፋይ በመስደብ ነው ›› ሰይጣን ዘረ ሰይጣን ዲ ላ በማለት።

ጦርነት ዳፋው ከገዛ ማህፀን የወጣ ልጅ ያሰድባል። በጦርነት ሳቢያ ተደፍረው ስንቶች አባት የሌለው ልጅ ወለዱ? ጦርነት ውብ የሆነውን እናትነት ይፈትናል። ይህ ታሪክ የብዙ ኢትዮጲያውያን ታሪክ ነው። በመደፈር ሳቢያ የሚከሰተውን ጽንስ የሚረግሙ ፥ላም እሳት ወለደች እንዲሉ... ወልደው በፍቅር ለማሳደግ ወደው ፈቅደው አልፀነሱ፥ የፀነሱትን ፅንስ ማውረድ ነፍስ ማጥፋት እየሆነባቸው...

ምነው አምና በሞትኩ
1
ምነው አምና በሞትኩ በሚለው ርእስ ስር ጦርነት ከሚያደርሰው አካላዊ ጉዳት፥ የንብረት ጉዳት፥ የስነ ልቦና ጉዳት ባለፈ ለተለያየ የአእምሮ ህመሞች እንደሚዳርግ ለማሳየት ሞክረዋል ፡፡የአእምሮ ጤና ማለት ምንም አይነት የእምሮ ህመም አለመኖር ብቻ አይደለም። የአእምሮ ጤና ችሎታችንን የምንገዘነብበት እና የመደበኛ ህይወት ጭንቀቶችን የምንሸከመበት መንገድ ነው። በአስተሳሰባችን ፥ በስሜታችን ፥ በድርጊታችን እና በህይወታችን ውሳኔዎች ላይ ተፅእኖ ያሳድራል ፡፡የአእምሮ ጤና ከአለም አቀፍ የበሽታዎች ሸክም 14 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ ህመም የሚይዘው በመሆኑ የአእምሮ ጤና አስፈላጊና የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን የጤና ባለሙዎች ይናገራሉ ፡፡

ጉልበትና ጉድለት

በዚህ ክፍል በተለይ በጦርነት ሳቢያ የአካል ጉዳተኛ የሚሆኑ ዜጎችን በተመለከተ ያሣየበት ነው ለዚህም ‹‹ እባካችሁ ወገኖች ግራ እጁ ከክርኑ በታች ተቆሯል ቀኝ እግሩ ከጉልበቱ በታች ያለው ቀኝ አይኑ ፈሷል ጆሮ የመስማት አቅም ተዳክሟል ›› ገፅ 83

ይህ በጦርነቱ ጉዳት ያጋጠመው ወታደር ታሪክ በማድረግ ሲሆን ወታደሩ ለእለት ጉርስ እያለ ቢለምንም ቸር የነበረው የመብራት ህዝብ በጦርነተ ሳቢያ በድህነት እጅ ከወርች በመያዙ የእለት ጉርሱ ፈተና ሲሆንበት ያሳየናል ከዚህ ባለፈ በጦርነት ሰመጣ የማይነካው ቤተሰብ አለመኖሩንም እንዲህ ብሎ ያስቀምጠዋል
‹‹ የጦርነት እሳት ያልጎነኘው ቤተሰብ ለማግኘት ከሞመከር ይልቅ ፀሀይ በምእራብ በኩል ወጥታ በምስራቅ በኩል እንድትጠልቅ መመኘቱ የተሻለ ውጤት አለው
ወልዶ ለጦርነት
ኖር ለጦርነት
ሰርቶ ለጦርነት›› ገፅ 89

ጦርነት በተንሰራፋበት ልጅ ቢወለድ ለጦርነት፥ ሰርቶ ጥሪት ቢያዝ ለጦር መሳርያ መግዣ ነው ይላል ደራሲው። ይህ በፊት ባለጉልበት እና መሳርያ ታጣቂ ወታደር በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ጉልበቱ አጉድልታል። በዚህም ጦርነት ሰለማዊ ዜጋን ብቻ ሳይሆን ተፈላሚ ሀይሎችንም ድል ፊታቸውን ስታዞር ዳፋው ለነሱም መሆኑን ለማሳየት ሞክሯል ፡፡


የሁለት ህይወቶች ወግ

‹‹ በምድር የቆየችበት እድሜ ሶስት አስርተ የሚሞላ ባሆንም የእድሜዋን እጥፍ የኖረች ይመስል ተጎሳቁላለች ቀይ መልኳ ወደ ጥቁረት ጉዞ ጀምሯል ከፊቷ ማዲያት ያልጎበኘውን ስፍራ ማግኘት አይቻልም ›› ገፅ 115

ይህን የሚላት ህይወት ስለምትባል እና በጦርነቱ ከሴተነቷ ጋር ተዳምሮ ስለፈተናት እንስት ነው

‹‹የእርሰ በእርስ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የሀገሪቱ ህግ ህገ ወጥነት እንዳይሆን አስቀርቷታል የሐይማኖት አባቶች ጆሮ ሲነፈጉ የእምነት ተቋማት አቅም ሰያጡ የመብራት ከተማ አባቶች መደመጥ፤የማይችሉ ሲሆኑ ሸንጎ መዘባበቻ ሲደረግ ስነምግባር ለጉልበት ሲገብር ህግ ለአመፅ ሲሰግድ አየን ››ገፅ 117
ጦርነት የቅርቡን ሩቅ ያደርጋል። ያለ ሰላም ዘርቶ መቃም ወልዶ መሳም ነግዶ ማትረፍ ፤መገበያየት አስቸጋሪ መሆኑን እያሳየ የጦርነትን አበሳ በዚህች ህይወት ብቻ ማሳየት ያልበቃው ተስፋ አብ ሌላዋን ህይወት ያስቃኘናል ፡፡

‹‹ ህይወት እባላለሁ ኣባቴ›› መላ አካልዋን በመገረም ቃኙት ‹‹ ህይወት ነሽ›› መገረም ፊታቸው ላይ ተጋድሞ አዎን አባቴ ›› ገፅ 122

በማለት ራሷን ያስተዋወቀችው ህይወት ያመጣትን ጉዳይ እንዲህ ትገልፃለች ‹‹ ውጊያው ሁልንም ሰዎች ስላደሀየ ሰዎች ችግራቸውን ለመርታት የተለየ መፍትሄ መፈለግ ጀመሩ ታማኝ ሰዎች ማጭበርበር ሲጀምሩ አየሁ ስርቆትን የሚጠየፉ ለሌብነት ተሽቀዳደሙ ሴትነታቸውን ያከብሩ የነበሩ ገላቸውን ለመሸጥ ፈቀዱ ›› ገጽ 124

ጦርነት የሰርክ ኖሮን ያመሰቃቅላል። ይህን ምስቅልቅል ይህንን ክፍተት ለመጠቀም የወሰነቸው ህይወት፥ ጦርነቱ ባመጣው እድል ተጠቃሚ ሆነች። ኑሮ የከበዳቸውን ቀንና ሌሊቱ አንድ የሆነባቸውን ሴቶች ገላቸውን እንዲሸጡ በማድረግ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ብታገኝም የልጇ ከስነ ምግባር ማፈንገጥ እና በአጉል ሱስ መጠመድ መፍትሄ ፍለጋ የመብራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት አባት ጋር መፍትሄ ፍላጋ አምርታለች።
ጦርነት በተለይ በታዳጊ ወጣቶች የስነ ምግባር ዝቅጠት የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው በሁለተኛዋ ህይወት ልጅ አማካኝነት ሊየሳየን ሞክሯል ፡፡

መፍረስና መፍረስ

በዘህ ርእሰ ስር ንፁህ ስለተባለች ገጸ ባህሪ በተለይ የጦሩ አለቃ ባለቤት ስለሆነችው ንፁህ እየነገረን በዛውም ጦርነት ሲመጣ የሹማምንት ቤተሰቦች የተሻለ መኖርያ እና ማረፍያ እንደሚዘጋጅላቸው በአንፃሩ መደዴው ህብረተሰብ ለከፋ ችግር እንደሚተው ያሳየናል ፡፡

ከዚህ ባለፈም የንፁህን የትዳር ፍለጋ ስንክሳር እያዋዛ የተረከበት መንገድ ግሩም ነው

እንደ መውጫ

ከላይ እንደተገለፀው መፅሀፉ ልብ ወለድ ይሁን እንጂ ፥ባለፉት አመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንደ ነበረ ሀገር የጦርነትን አስከፊነት በቀላሉ እንድንገነዘብ ለማድረግ፥ አጠር ባለ መልኩ ያስቀመጠበት ሂደት መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህ ባለፈ በመፅሀፉ መቻል ስለተባው ገፀ ባህሪ ያሰፈረው እንዲሁም ስለ ምናባዊ ከተማዋ መብራት ገለፃ በማድረግ የጦርነቱን ምድር በአግባቡ እንድናውቅ ሲያስችል፥ ለጦርነቱ መነሻ ስለሆኑት ፕሬዘዳንት እና ጄነራል የመፅሀፉ ርአስ ስለሆነቸው ዙፋን የተለያዩ የስነ ፅሁፍ ቴከኒኮችን በመጠቀም... አሰቃቂውን የጦርነት ሁኔታ በሌሎች የህወይት ቅመሞች እያዋዛ አሳይቶናል።

መፅሀፉ እንከን የለሽ ነው ማለት አይደለም። ሌሎች የስነ ፅሁፍ ባለሙያዎች የሚሰጡት ሂስ እንደተጠበቀ ሆኖ ፥ የቃላት ግድፈቶች ታርመው ለቀጣይ ህትመት ቢዘጋጅ እያልኩ በዚህ ላብቃ ፡፡

ማስታወሻ፥

የዙፋን ልፊያ ነገ 11 ሰአት በወመዘክር ይመረቃል
1
2025/10/21 17:55:41
Back to Top
HTML Embed Code: