Telegram Web Link
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የኢንቨስትመንት ባንኮች ተከፍተዋል ማለትም...

1. CBE (ሲቢኢ) ካፒታል አ.ማ የኢንቨስትመንት ባንክ (ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

2. ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ (ከወጋገን ባንክ)

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ አዲስ ምዕራፍ ነው!

በኢንቨስትመንት እና በንግድ ባንክ መካከል ፍጹም የተለያየ ባህሪ፤ ዓላማ እና ተግባር ምን እንደሆነ እንመልከት....https://youtu.be/bOSz9LHNsHY
የዘንድሮ ያህል #ዋጋ_ንረት አወዛግቦ አያውቅም!

በፓርላማ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ ዋጋ ንረት ሲመልሱ የሚከተሉትን ሃሳቦች ማንሳታቸው አነጋጋሪ ሆነዋል...

1. የዋጋ ንረት ሲቀንስ የፍጆታ ሸቀጦች ዋጋ በዛው ልክ ይቀንሳል ማለት አይደለም!

2. የዋጋ ንረት መቀነስ እና የኑሮ ውድነት አንድ እና ያው አይደለም!

3. የዋጋ ንረት ቀነሰ ማለት የእድገት ምጣኔው ቀነሰ ማለት ነው! Increasing at decreasing rate

4. Inflationንን ዜሮ ማድረግ እድገትን ዜሮ ማድረግ ነው! እድገት ባለበት ቦታ Inflation አይቀርም!

እስቲ ከኢኮኖሚክስ አስተምሮ አንፃር መልሶቹን እንፈትሻቸው! እስከመጨረሻው ተመልከቱት!https://youtu.be/3ct7z8l2xqU
የአፍሪካ ኢኮኖሚስቶች መቼ ነው የሚነቁት?

የ2025 የአፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች 57ኛ ስብሰባ!

አፍሪካ በየዓመቱ የ170 ቢሊየን ዶላር የመሰረተ ልማት ክፍተት ያለባት አህጉር ነች!

የአፍሪካ ኢኮኖሚስቶች ስለ እድገት የሚያስቡት መለወጥ አለበት!

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ኢኮኖሚስት ግብጿዊቷ ዶ/ር ሃናን ሃሳብ....https://youtu.be/cQbhExlhzug
#ለመረጃ፦ ቤንዚን 112.67 ብር ገብቷል!

ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሰረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት ተወስኗል።

በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ:-

ቤንዚን 112.67
ኬሮሲን 107.93
ነጭ ናፍጣ 107.93
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109.22
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106.75 ብር በሊትር የሚሸጥ ይሆናል።
የሰኔ ወር የነዳጅ ዋጋ ስንት ሊሆን ይችላል? መስከረም 2018 የመጨረሻው የድጎማ ወር ከሆነስ....

ነዳጅ በገበያ ዋጋ ሲወሰን የሊትር ስንት ይሆናል የነዳጅ ዋጋ በተለወጠ ቁጥር ለምን ያስገርማል?

ምክንያቱም ወደ ገበያ ስርዓት ለሚገባ እና ከነዳጅ ድጎማ ለመላቀቅ እያለማመደ ባለ ኢኮኖሚ ተገማች አይደለም?

ነገር ግን የቀጣይ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ከተለመደው የወጣ የመሆን እድል ሊኖረው ይችላል!

የመንግስት እቅድ፤ ልምምድ እና የዓለም አቀፉን ዋጋ ከግምት ከተን ትንበያ እንስራ! ሰኔ/2017 እና መስከረም 2018.....

ትንተናውን እንመልከት....https://youtu.be/7B056_qs4Qk
በኢትዮጵያ የገንዘብ አቅርቦት ጥብቅ ሆኖ ይቀጥላል! 2ኛ ዙር የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ውሳኔ!

የብድር ጣሪያ 18% ሆኖ ይቀጥላል! የፖሊሲ የብድር ወለድ በ15% ይቀጥላል!

መጋቢት 16/2017 የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ 2ኛ ዙር ስብሰባ በማድረግ 3 ጥብቅ ውሳኔዎች አሳልፏል....https://youtu.be/4AywalrK6mQ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ ቁጥር -2
ጋዜጣዊ መግለጫ
ኢትዮጲያ የቢሊየን ዶላሮች የውጪ እዳ ሽግሽግ አግኝታለች!

የውጪ እዳ የማራዘም ድርድር ቅድመ ሁኔታ ምንድን ነው?

የሚሸጋሸገው እዳ ከዓመታዊ የውጪ ንግድ ገቢ መጠን ይበልጣል!

የኢትዮጲያን የውጪ እዳ ያከማቹት ምክንያቶች.....

ከእዳ የመክፍያ ጊዜ መራዘም ኢኮኖሚው ምን ያተርፋል!

ዘርዘር አድርገን እንመልከተው.....https://youtu.be/ZXpm9btybwk
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ልምምድ!

የደሞዝተኛውና የቢዝነስ ክፍሉ ገንዘብ በመንግስት እየተፈለገ ነው!

ሸማች ለአምራቹ እና ለአገልግሎት ሰጪው ዋስትና ቢሆንም መንግስት በተለያየ ዘዴ የሸማቹን እና የቢዝነስ ክፍሉን ገንዘብ በሸማቹ በራሱ ከሚወጣ እኔ ልጠቀምበት እያለ ነው!

ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት.....https://youtu.be/K27tCxQtxuU
#ለመረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ መጋቢት 23/2017 ዓም ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በጨረታው 12 ባንኮች መሳተፋቸውን ባንኩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስፍሯል፡፡

በዚህም አማካኝ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 131 ነጥብ 7095 ብር ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል።
#ለመረጃ፡ ከዚህ በፊት ከፍራንኮ ቫሉታ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች በሙሉ በብሔራዊ ባንክ አዋጅ 1359/2017 መሠረት የተሻሩ በመሆናቸውን  ያለውጭ ምንዛሪ ፈቃድ መስተንግዶ እንደሌለ ዛሬ የጉምሩክ ኮሚሽን የገለፀበት ደብዳቤ!
ባንኮች ለዶላር ያላቸው ፍላጎት ለምን ቀነሰ?

ከዚህ በፊት በተደረጉ 2 የብሔራዊ ባንክ የዶላር ጨረታ ላይ ዶላር ያገኙ ባንኮች ቁጥር ዝቅተኛ ነው!

ነገር ግን በ3ኛ ጨረታ የካቲት 18 ከነበረው የዶላር ጨረታ አንድ ዶላር አማካይ ዋጋ ከ135 ብር ወደ 131 ብር ቀንሷል!

የዚህ ጨረታ የጨረታ አማካይ የቀነሰበትን ምክንያት እንመልከት....

የጨረታ አማካይ ዋጋ ከገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ መሆኑ በምንዛሬ ገበያ ላይ ሊያሳይ የሚችለው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል እንመልከት....

የቀጣዩ ጨረታ ዋጋ በመጨመር ወይስ በመቀነስ ይጠበቅ?

የጥቁር ገበያው ቀጣይ እርምጃ ምን ሊሆን ይችላል?

ለመረጃው https://youtu.be/4oPDI6ejbzI
ቦንድ ገዝቶ ከቀናት በኋላ ትርፍ ማግኘት ቀላል ኢንቨስትመንት ነው!

ሌሎች ኢንቨስትመንቶች የሚጠይቁት ያህል ካፒታል፤ ሂደት፤ ጊዜ አይፈልግም!

የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ እንዴት መግዛት ይቻላል! የምን ያህል ቀን፤ በምን ያህል ብር……

የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ (Treasury Bills) ለማህበረሰቡ በሽያጭ መቅረቡ በብዙ መለኪያ ለገዢም ለሻጭም አዋጪ ነው!

ነገር ግን የገንዘብ ፖሊሲ ስለሆነ ስጋት አያጣውም….

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/XnXcIMaguvs
Licensing_&_Renewal_of_Banking_Business_Draft_Directive.pdf
640.9 KB
የባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 እና የብሔራዊ ባንክ  አዋጅ ቁ 1359/2017 መሠረት ብሔራዊ ባንክ የባንኮች ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕድሳት ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል።

መመሪያው ስለ ውጪ ባንኮች...

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው፤

ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ፤

የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም እንደሚገደዱ ፤

ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል እንዳለባቸው ፤

በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን፡ የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ ይከፍላቸዋል።

ረቂቅ መመሪያው ከዚህ በታች ተያይዟል
ኢትዮጵያ በትራምፕ 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ።

ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ነው፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

ለምሳሌ፡- ቻይና 67% ታሪፍ አሜሪካንን የምታስከፍል ሲሆን ትራምፕ በአዲሱ ታሪፍ 34% ያስከፍላሉ። ካምቦዲያ 97% ታሪፍ አሜሪካንን ታስከፍላለች አሜሪካ አሁን 49% የምታስከፍል ይሆናል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ በርካታ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ታውቋል።
2025/07/10 11:47:48
Back to Top
HTML Embed Code: