Telegram Web Link
#ለመረጃ፡ በሁሉም ሀገራት ላይ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ!
ትራምፕ ሁሉንም ሀገራትን የሚያካትት ታሪፍ እየሳቁ ጥለዋል!

አሜሪካ ለሁሉም ሀገራት የየድርሻቸውን ታሪፍ በሰበር ዜና መልክ በዝርዝር አሳውቃለች!

ታሪፉ ከዝቅተኛው 10% እስከ 49% የደረሰ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት የተጣለበትን የ10% ታሪፍ በፀጋ መቀበሉን ገልጿል!

ከተጣለው አዲስ ታሪፍ ኢትዮጵያ ልታተርፍ የምትችልበት እድል አለ?

ታሪፉን በፀጋ የተቀበሉ፤ አዲስ የመልስ ህግ ያወጡ እና የዛቱ ሀገራትን እንመልከት....

የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የወደፊት እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል እንመልከት....https://youtu.be/5-D8Vav4H7w
#ለመረጃ፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 711 ደንበኞቹ ያቀረቡትን የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ በመገምገም ለ698 (98%) ለሚሆኑ ደንበኞቹ በድምሩ የ122.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልጿል።
ትራምፕ በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለጹ ሲሆን! ቻይና በምላሹ ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቃለች!

ማን ዋጋ ይከፍል ይሆናል!
ዝሆኖቹ ወይስ ሳሩ!

በዝርዝር እንመልከተውhttps://youtu.be/lXsjemNSy-4
#ለመረጃ፦ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት 13.6 በመቶ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።

የምግብ ነክ ዕቃዎች የዋጋ ጭማሪ 11.9% ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ የ16.2% የዋጋ ግሽበት ማሳየታቸውን እወቁልኝ ብሏል!
ኢብራሂም ትራውሬ ቡርኪናፋሶን እያሻገረ ነው!

ECOWAS፤ IMF እና World Bank እየዛቱበት ቢሆንም አስደናቂ ለውጥ እያደረገ ነው!

አሁን ደግሞ ሰልባጅ ልብስ አልቀበልም በማለቱ ከትራምፕ ጋር መዛዛት ጀምሯል!

ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት የለወጥ መነሳሳት ምክንያት የሆነው ወጣቱ ወታደራዊ መሪ እያደረገ ያለውን ድንቅ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እርምጃዎች እንመልከት!

ሀገራቸውን በማይወዱ መሪዎች እየተመሩ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦች መቼም ትራውሬን በማየት መቆጨት አለባቸው!

https://youtu.be/zoTfArJTIy4
#ለመረጃ፡ በነዳጅ የሚሠሩ ባለሁለት እግር (ሞተር ሳይክል) እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የነገሮች ሁሉ መነሻ እና መድረሻ፡ Game Theory!

12 የተለያዩ ኢኮኖሚስቶች ኖቤል የወሰዱበት ጥልቅ ሃሳብ! Prison's Dilemma!

የግለሰብ፤ የድርጅት፤ የሃገር ጉዳይ ከዚህ ውጪ አይደለም!https://youtu.be/YKAr7ZMYi4k
#ለመረጃ፡ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችዉን ቀረጥ ወደ 245% አሳድጋለች።

ወደፊት በድርድር ወደታች ለሚያወርዱት በቀልድ የታሪፍ ተመን ጉልበት እየተፈታተሹብን ነው!
ዶላር ፈላጊዎች ትንሽ ተረጋጉ!

ብሔራዊ ባንክ ለነገ 70 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ አውጥቷል!

ብሔራዊ ባንክ በየ15 ቀኑ የዶላር ጨረታ አወጣለሁ ባለው መሰረት ቀኑን ጠብቆ 70 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ አውጥቷል!

የባለፈው 15 ቀን ጨረታ ውጤት ብዙ ለወጥ በገበያው ፈጥሯል! በ3ኛ ጨረታ አማካይ ዋጋ መቀነስ አሳይቷል!

ይህ ጨረታ ገበያው ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ይኖረዋል!

የጨረታው ልምምድ የምንዛሬ ገበያውን እንዴት እንደሚወስነው እንመልከት!https://youtu.be/Y0eO6J-yAhQ
#ለመረጃ፡ በዛሬው የዶላር ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 131.4961 ብር ሆኗል! ለጨረታ የቀረበውን 70 ሚሊየን ዶላር 26 ባንኮች እንደተከፋፈሉት ብሔራዊ ባንክ ገልጿል!

የዛሬ 15 ቀን የነበረው ጨረታ አማካይ የጨረታ ዋጋ 131.7095 ብር ነበር!
2025/07/09 13:27:01
Back to Top
HTML Embed Code: