Telegram Web Link
በኢትዮጵያ ኢኖሚያዊ ምክንያት የሌለው ዋጋ ለምን ይፈጠራል?

መንግስት ዋጋን ፍትሃዊ የማድረግ አቅም አለው?

ዜጎች እንዴት መንግስት ከግል ሴክተር ገበያ ፍትሃዊ ዋጋ እንዲፈጠር እንዲያደርግ ይጠብቃሉ?

ትንታኔውን እንመልከት....https://youtu.be/V41xBdFOCeE
በንግድ ጦርነቱ ከማን ጎን መቆም ያዋጣል? ለኢትዮጵያ ከአሜሪካ እና ከቻይና የተሻለ አጋር ማን ይሆናል?

በቅርቡ በአሜሪካ እየተጣለ ያለውን ታሪፍ ተከትሎ ሀገራት የንግድ አጋር ፍለጋ ላይ ናቸው!

ቻይና አልጨበጥ ባለው የአሜሪካ ውሳኔ ምክንያት ወደ ሌሎች የንግድ አጋር ወደሚሆኑ ሀገራት እየዞረች ነው!

ኢትዮጵያ የንግድ ጦርነቱ እየጦዘ ከቀጠለ ከማን ጎን መቆም ያዋጣታል!

በንግድ ጦርነት እንደ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት የሁለቱም ወዳጅ መሆን ከባድ ነው!

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/k_y2IKUymCo
የኢኮኖሚ እንቆቅልሽ! ! ለጤና አደጋ ሆነው በመንግስት የሚመረቱ!

የብዙ ሀገራት መንግስታት ለህይወት አደጋ የሆኑ ምርቶችን በሀገራቸው እንዳይመረትም ሆነ ዜጎቻቸው እንዳይጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ አያግዱም! ለምን ይመስላችኋል!

በመንግስት ለጤና አደጋ የሆኑ ምርቶች የሚፈጥሩትን ህመምን ለማከም ከፍተኛ የህክምና በጀት ይመደባል!

ለጤና እንደሚጎዳ እየታወቀ በመንግስት ፍቃድ ስለሚመረቱ ምርቶች የሚጠቀሱ ምክያቶችን በምሳሌ እንመልከት!https://youtu.be/UOxmX2rS6RI
#ለመረጃ፡ IMF ይህ ዓመት ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ GDP 117 ቢሊየን ዶላር ሲሆን የኬንያ GDP 132 ቢሊየን ዶላር ይሆናል ሲል ትንበያ አውጥቷል! ይህ ማለት በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ የነበራት የኢኮኖሚ መጠን መሪነት ወደ ኬንያ ይሸጋገራል ማለት ነው!

በኢትዮጲያ የምንዛሬ ሁኔታ በገበያ እንዲወሰን ከተደረገ ጀምሮ የብር የመግዛት አቅም መዳከሙ ጠቅላላ ሀገራዊ የምርት መጠኑን ቀንሶታል!

#በቀላሉ_ለማስረዳት

በዚህ ወቅት፡ አንድ የአሜሪካ ዶላር የ129 የኬንያ ሽልንግ ዋጋ አለው! እንዲሁም  የ131 የኢትዮጵያ ብር ዋጋ አለው (የብሄራዊ ባንክ የዶላር የጨረታ አማካይ ዋጋ ቢወሰድ)!

ከምንዛሬ ፖሊሲ ለውጡ በፊት (የዛሬ 10 ወር)  አንድ የአሜሪካ ዶላር የ57 የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ነበረው (የባንኮች Official የሚጠቀስ ተመን ሲወሰድ)!

ኢትዮጵያ የምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ ከማድረጓ በፊት (2024) አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ የ134 የኬንያ ሽልንግ ዋጋ ነበረው!

ልዩነቱን የሚፈጥረው የኢትዮጵያ ብር በ10 ወር ውስጥ ከ57 ብር ወደ 131 ብር ሲወርድ የኬንያ ሽልንግ ከ134 ወደ 129 የኬንያ ሽልንግ ከፍ ነው ያለው!
#ለመረጃ፡ ከ31 ባንኮች መካከል 28ቱ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገልጿል! በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው!

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የATM ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

#መረጃው፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርትን ጠቅሶ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሞሽን ነው ይፋ ያደረገው፡፡
#ወሳኝ_መረጃ

ኢትዮ ቴሌኮም በጥቅምት ወር 10 በመቶ ድርሻውን ማለትም እያንዳንዳቸው 300 ብር ዋጋ ያላቸውን 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለህዝብ በሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል።

የአክስዮን ሽያጩ ለ121 ቀናት ቆይቷል። አጠቃላይ 47,377 ኢትዮጵያውያን ኢንቨስተሮች ሼሮችን ገዝተዋል፤ በአጠቃላይ 10.7 ሚሊየን ሼሮችን ሽያጭ ተከናውኗል በገንዘብ ሲተመን 3.2 ቢሊዮን ብር ይይዛል።

አሁን ላይ በአክስዮን ሽያጩ የተገኘው 3.2 ቢሊየን ብር ገንዘብ እስካሁን ለምንም አይነት ጥቅም ሳይውል በዝግ አካውንት ተቀምጦ እንደሚገኝ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

መረጃው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው!
#ለመረጃ፡ የዚህ ዓመት የአፍሪካ ሀገራት የGDP እድገት ምጣኔ ትንበያ በቅደም ተከተል (IMF)!

ሴኔጋል: 8.4%
ሩዋንዳ: 7.1%
ጊኒ፡ 7.1%
ኢትዮጵያ: 6.6%
ቤኒን: 6.5%
ደቡብ ሱዳን፡ -4.3%

የደቡብ ሱዳን ህዝብ የIMF ትንበያን ተመልክቶ የሚጓጓውን ፖለቲከኞቹ በዜሮ ያጣፉበታል!

ዓምና ከ25% በላይ ታድግ ይሆናል የተባለላት ደቡብ ሱዳን ወደ ግጭት ገብታ ከዜሮ በታች 27% አድጋ ነው አዲሱ ዓመት የጀመረው!

IMF ደቡብ ሱዳን ዘንድሮ ከዜሮ በታች በ4.3% ታድግና በቀጣይ ዓመት ሰላም ሆና ከበረታች በ64.5% ታድጋለች እያለ ነው!

የ10ሩ የአፍሪካ ሃገራት የGDP መጠን ደረጃ!

1)- South Africa 🇿🇦- $410.34B

2)- Egypt 🇪🇬- $347.34B

3)- Algeria 🇩🇿-$268.89B

4)- Nigeria 🇳🇬-$188.27B

5)- Morocco 🇲🇦-$165.84B

6)- Kenya 🇰🇪-$ 131.67B

7)- Ethiopia 🇪🇹-$ 117.46B

8)- Angola🇦🇴-$113.34B

9)- Ivory Coast🇨🇮- $94.48B

10)- Ghana 🇬🇭-$88.33B
ያልተሳካው የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ሽያጭ! 10% አፈፃፀም! ምክንያቶቹ፡ ውጤቱ እና ስጋቱ!

አትራፊ የሚባለው ዋናው የመንግስት የልማት ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ቀርቦ 50ሺ በማይሞሉ ፈላጊዎች ከተገዛ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንመልከት!

መንግስት ተስፋ የጣለበት የሃብት ክፍፍል 10% ስኬት ከሆነ ያስመዘገበው ወደ ፊት ለሌሎች ድርጅቶች ህልውናው ምንድን ነው?

ከኢኮኖሚ ሪፎርሙ በፊት ኢትዮ ቴሌኮም ድርሻውን ለገበያ አውጥቶ ቢሆን ከአሁን ሽያጩ በላይ የመሸጥ አይችልም ነበር?

ካፒታል ገበያውን ያነቃቃል የተባለው የመጀመሪያ የመንግስት የልማት ድርጅት ሽያጭ ውጤት መዳከም ስላለው ሁኔታ በዝርዝር እንመልከተው! https://youtu.be/uqUGCUlnl1I
ኢትዮጵያ ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ካመለከተች በኋላ ራሽያ እና ቻይናን ጨምሮ 37 ሀገራት የድርጅቱ ሙሉ አባላት ሲሆኑ የኢትዮጵያ ድርድር ለምን አልተጠናቀቀም?

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት/World Trade Organization አባል ለመሆን ካመለከተች 22 ዓመት ሞልቷል! አባል ለመሆን ፈለገች ለምን ጊዜ ወሰደባት?

ኢትዮጵያ አባል ለመሆን 22 ዓመታት የታገሰችው ምን አይነት እድል እና ስጋት ቢኖር ነው?

አሁን ላይ የዓለማችን 98% የንግድ ልውውጥ እየተከናወነ ያለው በአባል ሀገራት መካከል
ነው!

በዓለም ላይ የWTO አባል ያልሆኑ ሀገራት ብዛት ኢትዮጵያን ጨምሮ 39 ሃገራት ብቻ ናቸው! አብዛኞቹ ትንንሽ ደሴቶች እና የፈረሱ ሀገራት ናቸው!

በዝርዝር እንመልከተው!https://youtu.be/lMjBAk5z318
IMF በሚደግፈው ኢኮኖሚ ላይ መንግስት 100% ወሳኝ አይደለም!

የህዝብ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ፍላጎት እና የመንግስታት ዋና የኢኮኖሚ ትኩረት እና በጀት  የት እና የት?

ህዝብ በመንግስታት ላይ እምነት እንዲያጣ ያደረጉ 4 ምክያቶችን በዝርዝር እና በምሳሌ እንመልከት!https://youtu.be/QxeEswEmxOg
#ለመረጃ፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ኢትዮጵያ በ9 ወር ውስጥ ከወጪ ንግድ 5.3 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ያለ ሲሆን ገቢዎች ሚኒስትር በ9 ወር ውስጥ 653.2 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስቢያለሁ ብሏል!
#ለመረጃ፡ ለአምስተኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 60 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ ማቅረቡን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል! ጨረታው ነገ (እሮብ) እስከ 6 ሰዓት ይከናወናል!
#ለመረጃ፡ በአምስተኛው ዙር ብሄራዊ ባንክ ያቀረበውን 60 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ 16 ባንኮች በአማካይ ዋጋ 132.96 ብር ተከፋፍለዋል።
በ15 ቀን ውስጥ የዶላር ጨረታ አማካይ ዋጋ በ1.50 ብር ጨምሯል!

በ15 ቀን ውስጥ ዶላር በጨረታ የተከፋፈሉ ባንኮች ቁጥር ከ26 ወደ 16 ቀንሷል!

የበዓል ወቅት ላይ መቀነስ የነበረበት የዶላር ፍላጎት እንዴት አደገ?

ምክንያቶች.....https://youtu.be/Lhg6xCZBXOU
#ለመረጃ፦ ከሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ተለውጧል! ቤንዚን ከ112.67 ወደ 122.53 ብር አድጓል!
የሰኔ ወር የነዳጅ ዋጋ ስንት ሊሆን ይችላል? መስከረም 2018 የመጨረሻው የድጎማ ወር ከሆነስ....

ነዳጅ በገበያ ዋጋ ሲወሰን የሊትር ስንት ይሆናል የነዳጅ ዋጋ በተለወጠ ቁጥር ለምን ያስገርማል?

ምክንያቱም ወደ ገበያ ስርዓት ለሚገባ እና ከነዳጅ ድጎማ ለመላቀቅ እያለማመደ ባለ ኢኮኖሚ ተገማች አይደለም?

ነገር ግን የቀጣይ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ከተለመደው የወጣ የመሆን እድል ሊኖረው ይችላል!

የመንግስት እቅድ፤ ልምምድ እና የዓለም አቀፉን ዋጋ ከግምት ከተን ትንበያ እንስራ! ሰኔ/2017 እና መስከረም 2018.....

ትንተናውን እንመልከት....https://youtu.be/7B056_qs4Qk
ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነት እያጠፋቸው ያሉ ስራዎች....

ታክሲ ሾፌር ወጪ ለመቀነስ ብሎ ያለረዳት ከሰራ ያስቀጣል!

ወጪ የመቀነስ ምርጫ የሌላቸው ስራዎች እና ሰዎች ህልውናቸው ስራውን ማቋረጥ ነው!

ለኑሮ ውድነት መቋቋም የሚመከረው The Marginal Effect የኢኮኖሚክስ አስተምሮት ህልውናው በሃገራችን እየጠፋ ነው! 

የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ሲባል ብዙ ኢ-መደበኛ ስራዎች ባህሪያቸውን እየቀየሩ ነው!

በዝርዝር በምሳል እንመልከታቸውhttps://youtu.be/RV-ATa5rcdA
#ለመረጃ፦ አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ145% ታሪፍ ወደ 30% ያወረደች ሲሆን ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ125% ታሪፍ ወደ 10% ቀንሳለች።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቂ ደሞዝ መክፈል ይችላል?

ኢኮኖሚው ስራ እና ደሞዝን በተመለከተ የሰራቸው ነባር ስህተቶች፤ የመርህ ጥያቄዎች፤ አማራጮች.....

የቀኝ እና የግራ ክርክሮችን በምሳሌ እንመልከት....https://youtu.be/bpQFjC4OOFY
#ለመረጃ፡ ቱሪዝም ሚኒስትር "በ9 ወር ውስጥ ኢትዮጵያን ከጎበኙ የውጭ ቱሪስቶች 3.5 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል" ብሏል!.....?
2025/07/09 02:04:26
Back to Top
HTML Embed Code: