Telegram Web Link
#ለመረጃ፡ IMF "መንግስት #በውርስ እና #በስጦታ የሚገኝ ሃብት ላይ ግብር የመጣል ሃሳብ እንዳለው አውቂያለሁ" ብሏል!
IMF እንደሚለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለልተኛ ቢሆን ምን ይለወጣል?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አወቃቀር ገለልተኛ ተቋምነት ባህሪ የለውም!

IMF ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ብሔራዊ ባንክ ገዢ እና ምክትል ገዢው ገለልተኛ ቢደረጉ....

ካልተቻለ ቢያንስ ከ6 ቱ የቦርድ አባላት 2ቱ ገለልተኛ ቢሆኑ የሚል ምክረ ሃሳብ ሲያቀርብ ነበር!

IMF ተቋሙን ገለልተኛ አድርጉት የሚለውን ጥያቄ አቅርቦ ነበር!

የኢትዮጵያ መንግስት በምላሹ ባንኩን ገለልተኛ ተቋም ማድረግ ህገመንግስታዊ አይደለም ብሏል!

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እንደተቋም እና በአስተዳደር ደረጃ ገለልተኛ ቢሆን ምን ይፈጠር ነበር....

ከሌሎች ሃገራት ልምድ ጋር በምሳሌ እንመልከተው! https://youtu.be/3KO_1SfW55Y
#ለመረጃ፡ በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር እና ከዓመታዊ የንግድ ሥራ ትርፍ ግብር ምጣኔ ስሌት! ከግብር #ተቀናሽ መጠን!
የፀደቀው_የገቢ_ግብር_አዋጅ_ቁጥር_1395_2017_1.pdf
8.9 MB
የፀደቀውን አዲሱን የገቢ ግብር አዋጅ ሰነድ ለምትፈልጉ! ዛሬ ሙሉ ሰነዱ ወጥቷል!
በIMF የተማረሩ ሀገራት! በመጨረሻ IMF ኢትዮጲያ ደርሷል!

በ IMF ድጋፍ ዙሪያ ክርክር አለ! ለሀገራት ይጠቅማል እና ይጎዳል!

ከ IMF ድጋፍ ተከትለው ስለሚመጡ የጉዳት ማስረጃዎች ከጥቅሙ ይበዛሉ!

ከ IMF ጋር ሪፎርም በማድረግ ከፍተኛ መማረር ውስጥ ስለገቡ ሀገራት እና ምክንያት በምሳሌ እመለከታለን!

ኢትዮጲያ ከIMF ጋር የቅርብ ሪፎርም አካል ነች! የአንድ ዓመቱን ምልክት ከሌሎች ሀገራት ጋር እያነጻጸርን እመለከታለን!https://youtu.be/T631z06d49g
ከIMF መበደር እና ከIMF ጋር በጋራ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረግ ይለያያል!

በዓለም ላይ ብዙ ሀገራት ከIMF የመበደር ልምድ አላቸው! ነገር ግን ከIMF ጋር በጋራ የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማድረግ አይደፍሩም!

ሃገራት ከIMF ብድር ከመውሰድ ለምን ወደ ጠቅላላ የኢኮኖሚ ሪፎርም እንደሚዞሩ እንመልከት!

የኢትዮጵያ ታሪክ የተለየ አይደለም!

በዝርዝር እና በምሳሌ እንመልከተው!https://youtu.be/GMRDoImqjhg
ባንኮች በግዳጅ ሊዋሃዱ ነው!

በኢትዮጵያ ከ10 በላይ የንግድ ባንኮች አይኖሩም!

በቀጣይ ዓመት 5 ቢሊየን ብር ካፒታል የማያሟሉ ባንኮችን በግዳጅ እንደሚያዋህድ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል!

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ30 የግል ባንኮች መካከል 5 ቢሊየን ብር ላይ የደረሱት በጣም ጥቂት ናቸው!

ስለዚህ ውህደት ለምን አስገዳጅ ሆነ?

ባንኮች በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ምን አይነት እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ?

የሌሎች ሃገራት ልምድ ምን ይመስላል?

በዝርዝር እንመልከተው....https://youtu.be/zE7nUloSDKY?si=dxePYOnK4TdL3d9r
የባንክ ወለድን በ300% ቀንስ ቢባል እምቢ አለ! የአሜሪካ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የትራምፕን ትዕዛዝ አልቀበልም ብሏል!

የአሜሪካ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ጀሮም ፓውል በትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስን አልተማረም!

ነገር ግን በአሜሪካ ውጤታማ እና የሚከበር ብሄራዊ ባንክ ገዢ ነው!

ለመጀመሪያ ጌዜ በ2017 በትራምፕ ቢመረጥም ከተመረጠ ጀምሮ እስካሁን እየተተቸ ነው!

አሁን ላይ ወደ ጦፈ ጸብ ገብተዋል!

ትራምፕ "ለአሜሪካ ከቻይና በላይ ስጋቷ በዚህ ሰው የሚመራው ብሔራዊ ባንኳ ነው" እስከማለት ደርሷል!

የብሔራዊ ባንክ ገዢውን ጥንካሬ፤ ድክመት፤ ከትራምፕ ጋር የተጣሉበት ምክንያት በዝርዝር እንመልክት!

የእኛ ሃገር መሪዎች እና የብሄራዊ ባንክ ገዢዎች እንዲሁም ስርዓቱ ሊማር የሚችለውን ነጥብ በዝርዝር እንመለክት!https://youtu.be/7UuipxyVElA
ብሔራዊ ባንክ የማክሮ ማሻሻያ የዓመት ሂደት ሪፖርት አውጥቷል! ነገር ግን በሪፎርሙ የመጣው #ጫና ተረስቷል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከIMF ጋር የመጨረሻ ሪፎርም ካደረገ ዓመት ሞላው!

ባንኩ የአንድ ዓመት ሂደቱን ሪፖርት አውጥቷል!

የጋዜጣዊ መግለጫው ርዕስ "በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተወሰዱ የማክሮ ማሻሻያ የአንድ ዓመት ጉዞ ውጤቶች በአጭሩ" ይላል!

"የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በማክሮ ሪፎርሙ የአንድ ዓመት ጉዞ ሂደት የተገኙ ዐበይት ስኬቶችንና ቀሪ ሥራዎችን በተመለከተ አጭር ዘገባ" በሚል ሰፊ ሃሳቦች እና ቁጥሮችን አቅርቧል!

መሰረታዊው ጥያቄ በሪፎርሙ ምክንያት ያጋጠሙ ጫናዎች በሪፖርቱ አልተጠቀሱም!

በዝርዝር እንመልከታቸው!

https://youtu.be/IO7cIsgLNHk?si=7e186muIwGjNItBL
#ለመረጃ፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተወሰዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የአንድ ዓመት ጉዞ ወጤቶች በሚል የወጣውን መግለጫ ለማንበብ ለምትፈልጉ!
የምንዛሬ ልዩነት እየሰፋ ነው! የጥቁር ገበያው ለምን ጨመረ?

ዶላር በመደበኛ ባንክ በሳምንት ውስጥ አንድ ብር ሳይጨምር በጥቁር ምንዛሬ ግን በጣም ጨምሯል!

ጥቁር ገበያው ከመደበኛው ምንዛሬ 25 በመቶ ብልጫ አለው!

Exchange Rate Unification እየተሳካ አይደለም!

የምንዛሬ ልዩነቱ መስፋት ከIMF ሪፖርት ጋር ይገናኛል?

በዝርዝር እንመልከታቸው….https://youtu.be/bzHINRB-Ku4
#ለመረጃ፡ "ከአሜሪካ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመናድ እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት እየሰሩ ነው" ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ!

1. Shgey Money Transfer - Silver Spring, MD, and Falls Church, VA, USA!

2. Adulis Money Transfer - Falls Church, VA, and Silver Spring, MD, USA!

3. Ramada Pay (Kaah) - Falls Church, VA, USA!

4. TAAJ Money Transfer - Minneapolis, MN, USA!
#ለመረጃ፡ "በሕገ ወጥ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማት በኩል የሚላክ ገንዘብ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ድርጊት ጋር በተያያዘ ሊወረስ ይችላል" ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ! ህጋዊ የሆኑ አስተላላፊ ተቋማትን በድረገጹ አሳውቋል! https://nbe.gov.et/mta/
ውድ ባይሆንም ተፈላጊው ዶላር ነው!

ይሮ እና ፓውንድ ውድ ሆነው ዶላር ይዞ መገኘት ግን ያዋጣል! ለምን?

ኢትዮጵያ ውስጥ ውዱ ገንዘብ የኩዌት ዲናር፤ ፓውንድ፤ ይሮ ቢሆንም በጣም ተፈላጊው ዶላር ነው! ለምን?

ዶላር ይዞ መገኘት ከይሮ እና ከፓውንድ በላይ ለምን ያዋጣል?

መንግስት፤ ባለሃብት፤ ነጋዴ፤ መደበኛው ሰው የሚፈልገው እና የሚተማመንበት ምንዛሬ የትኛው ነው? ለምን?

በዝርዝር እና በምሳሌ እንመልከተው....https://youtu.be/lqCDbNAtHMk
#ለመረጃ፡ ብሔራዊ ባንክ ዘጠነኛውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያካሂድ ነው! የ150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ማክሰኞ ሃምሌ 29 እንደሚካሄድ ገልጿል።
2025/10/24 11:29:58
Back to Top
HTML Embed Code: