"ጌታን እንደ ግል አዳኟ" የተቀበለችው ኖርዌ ለምን ረከሰች?
*****

ወደ 5.5 ሚሊዬን ህዝብ የያዘችው በሰሜን አውሮፓ የምትገኝ ከኖርዲክ ሀገራት መሃከል አንዷ የሆነችውን ኖርዌን ታውቃታለህ?ካወክ እሰዬው

በ18ኛ መቶ ክፍለዘመን ላይ አጅሬዎቹ እንደሚሉት በኖርዌ ውስጥ << የወንጌል እሳት ተቀጣጥሎ ነበር >> አሉ....አሉ ነው

ልክ እንደ አሁናዊ የእኛ ሀገር ሁኔታ በየመንገዱ፣በየገበያው ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የሚቀበል ነፍስ ፍለጋ

<<ኢየሱስ ጌታ ነው ፣ኢየሱስ ያድናል>>

እያሉ የሚኳትኑ ሰዎች ይርመሰመሱባት ነበር።

ቀስ በቀስ የእኝ ቡድኖች ዘመቻቸው ተሳካ። የኖርዌ ሉትርያን ቸርች በ1960 ዓ.ም ኖርዌን ተቆጣጠረች። የኖርዌ 96℅ ህዝቧ ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ መቀበል ቻለ።

ከእዛች ዘመን በኃላ ይህቺ ሀገር ከእግዚአብሔር ጋር ያላት መስተጋብር ገደል መግባት ጀመረ።

በ60 ዓመታት ውስጥ በእዚህች ሀገር ውስጥ ሃይማኖት የለሽ ትውልድ እየተበራከተ መጣ።

ጌታን የተቀበለውም ህዝብ ከ96 ወደ 68℅ በፍጥነት አሽቆለቆለ።

በኖርዌ ሉተርያን ቸርች በማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ አላመጣችም ያለው የኖርዌ መንግስት 632 አብያተክርስቲታናትን በሀራጅ ሸጦ ለደኃ እንዳከፋፈል በእዚህች ሀገር ታሪክ ውስጥ ውሳኔ ሲያስተላልፍ የቤተክርስቲያኒቷ ተከታዮች ሳይቀሩ ውሳኔውን አሜን ብለው ደግፈውት ነበር።

አሁን ላይ ከ68% ጌታን ከተቀበለው ህዝቧ መሃል 52.9%

<<እግዚአብሔር ብሎ ነገር የለም>>

በሚል እምነት ውስጥ ያለ በድን ስጋውን ብቻ አዳራሽ ውስጥ አስቀምጦ ይንቀሳቀሳል።

ከአጠቃላይ ህዝቧ 22℅ ብቻ በእግዚአብሔር የሚያምን ሲሆን ቀሪው አንድ ኃይል አለ በሚል አስተሳሰብ ውስጥ የተዘፈቀ ነው።
ጌታን እንደ ግል አዳኟ አድርጋ የተቀበለችው የኖርዌ ቤተክርስቲያን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ላሳየችው ለዘብተኛ አቋም ይቅርታ ጭምር በመጠየቅ ግብረሰዶማዊነት ኃጢያት እንዳልሆነ ካወጀች ዓመታት አስቆጥራለች

ፀሎት ተደግሞላቸው፣ወንጌል ተሰብኮላቸው ፣ቅልጥ ካለ መዝሙር ጋር የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻነትን ይህቺ ቤተክርስቲያን ታስፈጽማለች።

እንደ Oslo pride የመሳሰሉ የግብረ ሰዶማዊነትን ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎችን የሚደረጉት በእዚህች ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርገው በተቀበለችው ሀገር ውስጥ ነው።

ባሻዬ... እኛን ቅድስት ቤተክርስቲያን ከስርዓት ጥምቀት በኃላ ስመ ክርስትና(ወልደ ገብርሔል፣ሐና ማርያም) እንደምትሰጠን ሁሉ የኖርዌ ቸርች ፆታቸው ለሚቀይሩ አባሏ መንፈስቅዱስ አቀብሎኛል ብላ በስርዓተ ጸሎት ስም ትሰጣለች።

የእዚህች ሀገር ዜጋዋ ከሚሞትበት 4 ገዳይ በሽታዎች መሃከል አንዱ የአእምሮ መታወክ(Mental illness ) እንደሆነ ብነግርህስ..

መጠጥን ላይ ያለውን የእዚህች ሀገርን አቋም ጠይቀኛ።
በዓለም 3ኛ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሴት አልኮል ጠጪ ዜጎችን የያዘችው ይህቺው ሀገር ናት ብልህስ?

በነገርህ ላይ የእዚህች ሀገር እና የእዚህች ቤተክርስትያን የእጅ ሥራ የሆነው (Norewagian Church Aid ) የተባለ ድርጅት አፍሪካ ውስጥ ያለውን የፕሮቴ*ት የወንጌል አገልግሎት ይደግፋል።

ወደ ኢትዮጽያችን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ተቸንክሮ ኖሯል።

መጽሐፍ ቅዱስ

"“ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።ማቴ 7፥20" አይደል ያለን ።እንግዲህ ፍሬያቸው ይህን ይመስላል ።

ሐሳዊውን ወንጌል ዘርተህ አማናዊ የሆኑ የክርስቶስ ደቀመዝሙራትን ማፍራት አይቻልም። ኩርንችት በለስን ታፈራ ዘንድ አይቻላትም።
ለ500 ዓመታት ፕሮቴስታንት ቤት የስብከት ርዕስ ያልሆኑ ጥቅሶች
***

የአዳራሽ ውስጥ ነብያት፣ በሐሰት ላይ የተሾሙ ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጡ መመልከት የማይፈልጉት ጥቅሶች አሉ።

እነኝን ጥቅሶች ርእስ አድርገው ቢሰብኩ ቤታቸውን ከሥሩ የሚንዱ ቃላትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዟልና።

እስኪ ጥቂት ቆንጥረን እንመልከት
***

<<መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ .. ማቴ 3፥1-2"

ይህ ጥቅስ ርዕስ ሆኖ ለምን እዛ ቤት አይሰበክም ብለህ አትጠይቅኝም ውይይ?

ምክንያት ካልከኝ....ይህ ቃል ልብን በሚያሞቅ አጉል ተስፋ

<<ድነሃል፣ኃጢያት ብትሰራም ኢየሱስ ስለ አንተ እያማለደ ያነጸኃል፣ ጠበቃህ ክርስቶስ ስላለ ኃጢያት ብትሰራም ፍርድ አያገኝህም >>

ተብለው ገነት በር ላይ በምናብ ሄደው ለመግባት ወረፋ የሚጠባበቁ ምስኪን ተከታዮችን ያሳምጽባቸዋል።

ስለዚህ ገነትን ወርሰኃል እንጅ ንሰኃ ግባ የሚል ስብከት በእዚህ ቤት አይነኬ ነው።ካካ ነው።

***
“ ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።”
— ያዕቆብ 2፥17 //

ኦ ኦ ...ይህ ጥቅስማ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተቀዶ ቢወጣ ሁሉ ደስ ይላችዋል።(የፕሮቴስታንት ዲኖሚኔሽን የያዕቆብ መልዕክትን በመብቷ በመቀነስ ከ 66 ወደ 65 ወርዳለች ጥቂት ቸርቾች ግን ለምን አይሆንም እያሉ ነው። ) የሆነው ሆኖ ግን ምክንያት ከተባለ

ከፕሮቴስታን << የ5ቱ ብቻ>> የእምነት መሰረት ከሆኑ አስተምሮዎች መሐል አንዱ የሆነውን <<የእምነት ብቻ>> ጽንሰ ሐሳብ ከታች ገንድሶ ይጥለዋል።

"ምንም ሥራ ሳልሰራ በእምነት ብቻ እድናለው" ብሎ የተቀመጠውን ህዝብ ከአዳራሽ ውስጥ ያስፈልሳል እና የያዕቆብ መልክት ተከድኖ ይቀመጥ ተብሎ የተፈረደበት የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ነው።
**

“ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል ... ሐዋር14፥21-22" "

'ጹሙ' ሲባል 'ኢየሱስ ፆሞልናል' ፣'በጎ ነገር ሥሩ' ሲባል 'ሰው በሥራ መንግስቱን አይወርስም' እያሉ ላለመታዘዛቸው ስንፍና ምክንያት በሚደረድር ህዝብ መሃል ይህ ጥቅስ ይዘህ ማስተማር ማለት እንደ አጥፍቶ ጠፊ ወንጌል ተደርጎ ይቆጠራል።

"ዘንጨ፣ ቂቅ ብዬ፣ ፏ ፈሽ እያልኩ በአንድ ቀን የአዳራሽ እጅ ማንሳት መንግስቱን እወርሳለው " ብሎ ለተቀመጠ ትውልድ" መከራ" የሚባል ርዕስ ያለው ስብከት ብትሰብክ ለብልፅግናውና ሜራክል መኒው እንቅፋት ነህና በድንጋይ ተወግረህ ከአዳራሽ ልተወጣ ትችል ይሆናል።
***

“በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ዮሐንስ 16፥26"

እዚህ ጥቅስ ላይ ሲደረስማ ሁሉም አይነስውር ይሆናል።

በእዛ ቤት ስብከት ውስጥ " ኢየሱስ አይለምንም" ብሎ ማንሳት በራስ ላይ ታንክ እንደመንዳት ይቆጠራል።በእነሱ ዘንድ አማላጄ የሚል ተለዋጭ ስም የተሰጠውን ክርስቶስን ስለእኛ አይለምንም ማለት ህዝቡን ከማደንዘዣ እንደማንቃት ይቆጠራል።

በስተመጨረሻም ...ግን ፕሮቴስታንትን ወንድም እህቶች ግድ የላችሁም ጠይቁ! ለምን እንዴት የሚሉ ነገሮች ከአፋችሁ ማውጣት ልመዱ

ክፍል 2 ፣3 እያልን እንቀጥላለን!
በቀጥታ ለአቶ እንዳልክ ዘነበ

ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ በላይ የአማልክትን አምላክ ኢየሱስን ማን አከበረ ?
=============================================================

‹‹ ‹ቅል እንኳን ማንጠልጠያ አለው› የሚል የገረጀፈ ጸረ-ኢየሱስ የሆነ የመንደር ትርክት የምትነግሩኝ የዚህ መንደር የእሁድ ክርስትያች›› በማለት ዲያቆን ነበርኩ የሚል፣ምናልባትም ዲያቆን ሆኖ ‹‹እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ›› የሚለውን ብሎ የማያወቅ ሰው ነው ይሄን ያለን፡፡አሁን አሁን ፕሮቴስታንትነት ስለበዛ በእነሱ መንገድ የተሳብን እንጂ ስሙን እንዲህ ነበር የምንጠራው ‹‹ጌታችን አምላክችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ››፡፡ይሄን አጠራር ነው እንዳልክ የተባለው ሰው መንጠልጠያ እያለ አክብሩት የሚለንን የእየሱስን ስም አጠራር የሚያጣጥለው፡፡‹‹ ማንጣልጠያ የሚፈልገው ብቻውን ሙሉ ሆኖ መቆም ለማይችል ስም ነው›› ይለናል፡፡ ጨምሮም ‹‹ኢየሱስ የሚለው ስም ውስጥ መድሃኒት፣ጌትነት፣ስልጣን አለቅነት ገዢነትና ሀይል አለ›› በማለት የብራራል፡፡ በሌላ ጽሁፉ ደግሞ ‹‹በቀን ውስጥ ሳልጠራው የማልውለው ስም ኢየሱስ›› ይላል፡፡ እንዲሁም ፕሮቴስታንቶች በሚያዘዋውሩት አንድ ቪዲዮ ላይ ‹‹ከማንም የሀይማት ተቋም ውስጥ መወሸቅ እልፈልግም ›› ይለናል፡፡ እንግዲያው እኛ ኦርቶዶክስ ውስጥ ያለነው እውነት ስሆነ እንጂ ለመወሸቅ ፈልገን አይለም፡፡፣መጽሃፍ ቅዱስ ይዳኘን፡፡

የእንዳልክን መንጠልጠያ ስላቅ እንፈትሽ፡፡ በቲቶ 2፡13 ላይ ‹‹የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ›› ይላል፣ 2ኛ ቆሮ 1፡2 ላይ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ››፣ ፊልሞና1፡25 ላይ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ›› ይላል፡፡እንዳልክ ግን እየሱስ ብቻ በሉ ይለናል፡፡ማንጠልጣያ ተጨማሪ አያስፈልገውም ይለናል፡፡ማንን እንከተል እንዳልክን ወይስ መጽሃፍ ቅዱስን? ምርጫው የእናንተ ነው፣ኦርቶዶክስ ግን መጽሃፍ ቅዱስን ነው የምትከተለው፡፡የእንዳልክ አይነቱ ለስሙ ዲያቆን ነበርኩ የሚል ማንጣልጣያውን ተው እያለ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መድሃኒትንት ጌትንት በሥም አጠራሩ እንዳንመሰከር ይቃወመናል፡፡እኛ ግን መጽሃፍ ቅዱስን ሃዋሪያትን እንከተላለን፡፡የተወሸቅነው መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጉያ ውስጥ ነው፡፡ተቃዋሚዎቹ ጌታ አምላክ ክርስቶስን በዚህ መልኩ ስላከበርነው ይከፋቸዋል፡፡

በእርግጥ በፖለቲካ ላይ በሚያነሳው ትችቶች በመንግስት አይን ውስጥ የገባው እንዳልክ፣ከኦርቶዶክስ ጠሉ መንግስት እና ስርዓት ጋር ለመታረቅ ኦርቶዶክስን ማብጠልጠሉ አይገርምም፡፡ ግናስ ለጥቂት ቀናት ሲታሰር ባር ባር ያለው እንዳልክ በኢየሱስ ስም ሞት እንኳን ቢመጣ ማለቱ ቀድሞውኑ ኦርቶዶክስን የሚዘልፍ መች ሞት ይመጣበትና በሚል ስርዓቱ ኦርቶዶክስ ጠል ስለሆነ ተማማኖ ነው፡፡አይገርመንም፡፡ብዙ አባቶቻችን ስለ ክርስቶስ ብለው መስዋዕት ተቀብለዋል፣በኦርተዶክስ ለክርስቶስ ብሎ መከራን መቀበል አዲስ አይደለም፡፡

እንዳልክ ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው ስትባሉ በቀጥታ አሜን ማለት ሲገባችሁ›› እያለ ኦርቶዶክሳዊያንን ይዘልፋል፡፡የትኛውን ኢየሱስ እንደሚያመልኩ አትጠይቁ ዝም ብለችሁ አሜን በሉ ይለናል፡፡መጽሃፍ ቅዱስ 1ኛ ዮሐ 4፡1 ላይ ግን እንዲህ የለናል ‹‹ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።›› ይለናል፡፡ እንዳልክ ግን መንፈስን ሁሉ እመኑ ይለናል፡፡ማቴ 24፡24 ላይ ሀሰተኛ ክርስቶሶች እንደሚነሱ ይነግረናል፡፡ሰዎች በአዕምሯቸው ሀሰተኛ ክርስቶስ ቢያስነሱ እንኳን አሜን በሉ ይለናል ዲያቆን ነኝ የሚለው እንደልክ፡፡2ኛ ቆሮ 11፡13-14 ላይ ‹‹እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና።ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።›› ሀሳዊያን የክርስቶስን ሃዋሪያ የሚመስሉት እነዚህ ሰዎች የሚሰብኩትም ክርስቶስ ሀሳዊ ነው፣ባይሆንማ ሀሳዊያን አይባሉም፡፡የእነሱን ሀሳዊ ክርስቶስ ስም ሲነሳ እንኳን አሜን በሉ ሳትጠይቁ ይለናል እንዳልካቸው ዘነበ፡፡

እየሱስ ጌታ ነው እያልኩ እኖራለሁ ይላል እንዳልክ፣መጽሃፍ ቅዱስ ደግሞ ‹‹ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።›› ይላል ትዕዛዛቱን የሚፈጽም እና ህይወቱን ከሚኖር ውጪ፡፡

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/887366125580438](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/887366125580438)

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/870399150610469](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/870399150610469)

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/478538026463252](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/478538026463252)

[https://www.facebook.com/photo/?fbid=5121802881258024&set=a.104410396330656](https://www.facebook.com/photo/?fbid=5121802881258024&set=a.104410396330656)

[https://www.facebook.com/watch/?v=2979223162222134](https://www.facebook.com/watch/?v=2979223162222134)
ከላይ ያሉትን ሊንኮች እየከፈታችሁ መመልከት ትችላላችሁ
ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የዋልድባ አባቶች መልእክት

"…የዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና  በቅዱስ ሲኖዶስ የወጣውን መመሪያና ትእዛዝ ተከትሎ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ/ም ማኅበረ መነኮሳቱ በአብረንታንት ቤተ እግዚአብሔር ተስብስበው የቅዱስ ስኖዶስ ውሳኔ በገዳማችን እንዲተገብር በማለት ማኅበረ መነኮሳቱ ወስነዋል።

"…በተጨማሪም ማኅበረ መነኮሳቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለቅዱስ አባታችንም፣ እንዲሁም ልህዝበ ክርስቲያኑ የማጽናኛና የማበረታቻ አይዟችህ የሚል ገዳሙ ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤም እንዲጻፍ ሲሉ ማህበረ መነኮሶቱ ወስነዋል። በተጨማሪም በቋርፍ ቤትና በሞፈር ቤቶች ከቀድሞው (ዘወትር ከምናደርገው) በተለዬ መልኩ ጸሎተ ምህላው ተጠናክሮ ይቀጥል።
"…በገዳሙ የሚኖር ማንኛውም መነኩሴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ 150 መዝሙረ ዳዊት በቀን እንዲደግም። ከደገመ በኋላም መጸሐፉን መሬት ላይ ደፍቶ ያስቀምጥ። መቁጠሪያውንና መቋሚያውን ጸሎት ከጨረሰ በኋላ መሬት ላይ ይጣል። ምግብን በተመለከተ በቋርፍ ቤትም ሆነ ብእህል ቤቶችና  በአትክልት ቦታዎች ጨው፣ በርበሬ፣ ያለበት ምግብ ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀን እንዳይመገብ። በማንኛውም ቦታ የገዳማችን መነኮሳት ባእት እሳት እንዳይነድ። ከቤተ እግዚእብሔር የሚሰጠውን ብቻ እንዲመገብ። የተመገበበትን ፋጋ ከጨረሰ በኋላ ባፉደፍቶ እንዲያሳድር። ከምሽቱ 12 ሰዓት ውጭ የመቁንን ደውል እንዳይደውል። ውኃ ከአንድ ብርጭቆ በላይ እንዳይጠጣ። ሻይ እንዳይፈላ። ጭልቃ እንዳይጨለቅ ወስኗል። 

"…ይህ ትእዛዝ በሁሉም የቋርፍ ቤት፣ የአትክልት ቦታ፣ የሞፈር ቤቶች፣ በየዋሻው እና በየፍርኩታው ላሉ ባህታውያን አባቶች መልክቱ ይተላለፍ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን የመጣው አደጋ ቀላል አይደለም በሚል ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ከትናንት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።

"…በአባቶች በኩል ነገሩ በጥብቅ ተይዟል። ነገሩን ያከበዱት ይመስለኛል።
እስኪ ኦርቶዶክሳዊያን በትህትና በጥሞና አንብቧት
ክፍል አንድ

✥✥✥ በዐለ ደብረዘይት ✥✥✥

ትርጉሙ፦ ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ይሆናል።

- ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቤተ ፋጌ እና ቢታንያ በኮረብታው ጫፍ እና በምስራቅ ዳገታ ላይ ይገኛሉ።

- ይህ ተራራ በመፅሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ብዙ ድርጊቶች የተደረጉበት ቦታ ነው። ጌታችን ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ፣ ስለ ዓለም ፍጻሜና ስለ ዳግም ምጽአት በዚህ ተራራ ላይ በትንቢት መልክ ተናገረ (ማቴ.24፥3)። በዚሁ ተራራ ላይ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ.24፥50)። በዚሁ ተራራ ላይ ቀን በከታማና በገጠር ሲያስተምር ውሎ ሌሊት የሚያድርበት የኤሌዎን ዋሻ ይገኛል።በኋለኛው ምጽአቱ በዚሁ ቦታ እንደሚገለጥ ትንቢትተነግሯል።(ዘካ. 14፥3-5)።

- ስያሜው፦ የዓቢይ ጾም እኩሌታ ላይ ያለው ሰንበት በዚህ ተራራ ተጠርቷል። ይህንን ዕለት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዳግም ምጽአት አድርጎ መዝሙሩን ጽፏል። በዚህ ተራራ ላይ «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3)። ተብሎ እንደተጻፈው ለደቀ መዛሙርቱ የዳግም ምጻቱን፣ የዓለምን ፈጻሜ፣ የትንሣኤ ሙታንን፣ ትምህርት በሰፊው ስላስተማረ በዓሉ በተራራው ስም ተሰይሟል።

አመጣጡስ እንዴት ነው?

- ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበበ ትስብዕቱ(ከድንግል ማርያም በነሳው ቅዱስ ሥጋው) ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርኃ መጋቢት ዕለተ እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ምነው ‹‹ የሚያውቀው የለም ይል የለምን ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን ብዙ የመጋቢት ወር ብዙ የእሑድ ዕለት የበዙ ሌሊቶች አሉና ለይቶ የሚያውቅ የለም ለማለት ነው፡፡

-> ሞት ለማንም አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ 3፡19 በዕለተ ምጽኣትም ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፍን ነቅለው ድንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ነጋሪቱን ይመታል ፩ኛመቃብ ፱፥፰ ነጋሪት የተባለው በቁሙ ነጋሪት የሚመታ ሆኖ ሳይሆን አዋጁን የምትክ ንቃ የሚል አዋጅ የሚናገር ይታወጃልና ነጋሪት ይመታል አለ

. ስለዚህ ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባህር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡
. በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም እንደ ዕለት በድን ይሆናሉ፡፡
. ሦስተኛው ነጋሪቱን መትቶ /ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት / ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደግነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡

- ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ 13፡43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያብሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ብሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለክፋ ሥራቸው /ከእኔ ሂዱ/ ብሎ ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡
ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ ዋይ ዋይ እያሉ ደረት ይደቃሉ እንባቸውን ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ልቅሶ ይሆናል የማይረባ ኃዘን ነው ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን 0ይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡

- በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡🤲

-> መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘ ይነብር እግዚእነ ወስተ ደብረ ዘይት ይባላል

-> ምንባብ ዘቅዳሴ
- 1ተሰሎ 4÷13-ፍም::
- 2ጴጥ 3÷7-15::
- ግሐዋ 24÷1-22

-> ምስባክ
" እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመፅእ፣ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ" መዝ 49÷2

-> ወንጌል፦ ማቴ፡ 24÷1-36

-> ቅዳሴው ቅዳሴ አትናቴዎስ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ
ኃይላችን፣ መመኪያችን (መጠጊያችን)፣ የመድኃኒት መገኛ ለሆነ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባል

† መስቀለ ኢየሱስ †
መጋቢት 10 የጌታችን መስቀል በቁፋሮ የተገኘበት

ሰላም እብል ዕፀ አድኅኖ ልምሉመ
እንተ ተሰቅየ ወረወየ እምገቦ መለኮት ደመ
በዛቲ ዕለት እንበለ ይዕዱ ጌሰመ
መስቀል ተረክበ እም ዘተኀብአ ወገብረ መድምመ
በኢየሩሳሌም ቅድመ ወበፋርስ ዳግመ።
(ዐርኬ ዘመጋቢት መስቀል)

የዛሬዋ ዕለት መጋቢት 10 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከኖረበት ቦታ የወጣባት ቀን ናት። መስከረም 16 ቀን ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት ደመራ ደምራ በደመራው ጢስ አማካኝነት የተቀበረበትን ቦታ አገኘች። መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀመረች። ከ 300 ዘመናት በላይ ቆሻሻ እየተጣለበት ታላቅ ተራራ አህሎ ነበርና እነሆ ቁፋሮ ስድስት ወራት ፈጀባቸው መጋቢት 10 በዛሬዋ ቀንም መስቀሉ ወጣ። ሦስት መስቀሎች ናቸው። ሁለቱ መስቀሎች ሽፍታዎቹ የተሰቀሉባቸው ሲሆኑ አንዱ የጌታችን ነው፤ ታዲያ እንዴት ለየችው ቢሉ የጌታችን መስቀል ታላላቅ ታአምራትን አድርጓል ድውይ ፈውሷል ዓይነ ስውር አብርቷል። ይህንን ቀን ቅድስት ቤተክርስቲያን "መስቀለ ኢየሱስ" ስትል ታከብረዋለች፤ በዛሬዋ ቀን ዝማሬው፤ ምስጋናው፤ ትምህርቱ፤ ቅዳሴው ፤ ንባቡ ሁሉም መስቀልን የሚመለከቱ ናቸው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መስቀል የሚጣፍጥ ነገር ተናገረ እንዲህ ሲል “ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” ገላትያ 6፤14።

የመስቀል በዓል የሚከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት የከበረ የእንጨት መስቀል በአይሁድ ክፋት ከተቀበረበት የቆሻሻ ክምር በቅዱሳን ጸሎት፣ በምዕመናን ጥረት፣ በእግዚአብሔር ተዓምር የተገኘበትን ዕለት ለማሰብ፣ ከበዓሉም በረከትን ለመሳተፍ ነው፡፡ ጌታችን እኛን ለማዳን ሰው ሆኖ፣ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለመስጠት በአይሁድ ዘንድ የተረገመ ተብሎ ይታወቅ በነበረው የመስቀል ስቅላት ሞትን በፈቃዱ ተቀብሎ የሞት ምልክት የነበረ መስቀልን የሕይወት መገኛ ወደመሆን ለውጦታልና ነው፡፡

ወወሀብኮሙ ተእምርተ ለእለ ይፈርሑከ
ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት ወይድኅኑ ፍቁራኒከ
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው ወዳጆችህ እንዲድኑ . .
( መዝ . 59 ፥ 4 -5 )

ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ተባለች፡፡ ንግሥት እሌኒም በተፈጠረላት አመቺ ሁኔታ በመጠቀም የጌታችን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡
ንግሥት ዕሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነጽ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ.ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት ዕሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች ከእርሷም ጋር ብዙ ሠራዊት ነበር፡፡ እንደደረሰችም ስለ ከብረ መስቀል መረመረች ጠየቀች፡፡ ቦታውን የሚያስረዳት አላገኘችም፡፡ የአይሁድ ወገን እንቢ ቢሉም በኋላ ግን ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመለከታት አስቆፍሪው ብሎ ነገራት ኪራኮስም ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ እውነተኛው ተራራ ይህ ነው ብሎ ማሳየት ባለመቻሉ ከሦስቱ ተራሮች አንዱ ነው ስላላት አይሁድ ተራሮቹን ይቆፍሩ ዘንድ አዘዘቻቸው፡፡ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ከጌታ ሞት እያመነ በተቸገሩ ግዜ ማንም እንዳያገኘው የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሁሉ የእቤቱን ቆሻሻ የከበረ መስቀል ባለበት ቦታ እንዲጥል አይሁድ አዝዘው ስለነበር ከሁለት መቶ ዓመት በላይ ጥራጊ ስለጣሉበት ታላቅ ተራራ ሆነ፡፡

ዕሌኒ ተራሮቹን ለማስቆፈር ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ከኢየሩሳሌም ወጣ ብለው ያሉትን ኮረብቶች አሳያት፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም "ሰገደ ጢስ" ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡ ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡
ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡፡ የሞተ ሰው አምጥተው በሁለቱ መስቀሎች ላይ በተራ ቢያስቀምጡት አልተነሣም፡፡ በመጨረሻ በአንዱ መስቀል ላይ ቢያስቀምጡት ያን ጊዜ የሞተው ሰው ተነሣ፡፡ በዚህም የጌታን መስቀል ለዩት ፡፡ ዕሌኒም የጌታ መስቀል እንደሆነ አወቃ ሰገደችለት፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ግዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ታላቅ የድኅነት ምልክት የሆነው መስቀል የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ደመራ በመደመር በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብረዋለች፡፡

መስቀሉን ለማግኘት ሰባት ወራት ያህል እንደፈጀ ቢነገርም በአንዳንድ ሊቃውንት ህሳቤ ደግሞ መስቀሉ የተገኘው መስከረም 17 ነው ሲሉ በአጽንዖት ይናገራሉ። ይሁንና አብዛኛው የቤተክርስቲያኗ ሊቃውንት ግን “መስቀሉ የተገኘው መጋቢት 10 ነው፣ ይህ ወር ግን የዐቢይ ጾም ወር በመሆኑ በዓሉ በመስከረም 17 እንዲሆን ሊቃውንቱ ተስማምተው አቆይተውናል” ሲሉ የላይኛውን ሃሳብ ያፈርሳሉ።

ንግሥት ዕሌኒ መስከረም 16 ቀን 320 ዓ.ም በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተመቅደስ ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው ይህ መስቀልም ከዚያ ዕለት ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ተአምራት እየሰራ ሙት እያነሳ ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡ ይህንንም ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው፡፡ በዚህ ጊዜ የአየሩሳሌም ምዕመናን የድሉን ዜና ሰምተው ስለነበር የአንድ ቀን መንገድ ያህል ሄደው በመቀበል ካህናቱ በዝማሬና በቸብቸቦ ወንዱ በሆታ ሴቱ በእልልታ ሆ! እያሉና ችቦ አብርተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም ለመስቀል ችቦ እያበሩ በዓሉን በሆታ በእልልታ በስብሐተ እግዚአብሔር የምታከብረው ይህንን ታሪካዊ ትውፊት በመከተል ነው፡፡ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶች እንደሚሉት ንጉሡ ሕርቃል ይህንን ታላቅ ድል ለማግኘትና የጌታን ቅዱስ መስቀል ከአሕዛብ /ከፋርሶች/ እጅ ለማስመለስ የቻለው በዚያን ጊዜ አብያተ ክርስቲያንናት ሁሉ ለአንድ ሳምንት /አንድ ሱባዔ/ ባደረጉት ጾም ጸሎት ነው፡፡ ይህንንም ለማስታወስና ጌታን ለማመስገን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የዐቢይ ጾም /የጌታ ጾም/ ከመጀመሩ አስቀድሞ "ጾመ ሕርቃል" ብለው አንድ ሳምንት ይጾማሉ፡፡
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ ኢየሱስ የተሰቀለበት ቀኝ ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ስለዚህ መስቀል መምጣት የቤተክርስቲያኗ ጸሐፍት በተለያዩ ሠነዶቻቸው የተረኩ ሲሆን፣ ንጉሡ አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን አስመጥተው በኢትዮጵያ አድባራት ሁሉ በመዞር፣ ሊያሳርፉበት ያልሞከሩበት ቦታ አልነበረም፤ ነገር ግን መሬቱ እየተንቀጠቀጠ አስቸጋረ። በመጨረሻ ግን “መስቀሌን በመስቀልያ ሥፍራ አስቀምጠው” የሚል መለኮታዊ ምሪት ስለደረሳቸው፣ አሁን በአምባሰል ተራሮች ይህም ሥፍራ መስቀልያ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ ባለው በግሼን አምባ ተቀምጧል።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን !
2024/05/03 12:51:16
Back to Top
HTML Embed Code: