Telegram Web Link
🛒 BUYING OLD GROUPS 🛒

ድሮ የከፈታችሁት Group Chat ነበር? Owner ከሆናችሁ ፣ History Visible ከሆነ እና Chat Clear ካልተደረገ እንገዛችኋለን!

👥2023 - 🇪🇹 200 ETB

👥2022 - 🇪🇹400 ETB

👥2021 - 🇪🇹450 ETB

👥2020 & 2019 - 🇪🇹500 ETB

👥2018 & 2017 - 🇪🇹600 ETB

Payment Methods:
🇪🇹Telebirr, Bank
Proofs - https://www.tg-me.com/OLDGPPROOF

ሜምበር ለውጥ አያመጣም 1ሺ ሜምበርም ሆነ 10 ዋጋው አንድ ነው.. የተከፈተበት አመት ላይ ብቻ Chat ይኑረው።

ለመሸጥ: @OldGroupBuyer_APX
👍5
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍6
🟢 SAMSUNG M16 5G 🟢 (NEW)

✔️storage 128gb
✔️Ram 6gb
✔️Dual

💵Price 25,000 Birr

🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

😀 0942405669
✈️@Endalk4240

Join channel https://www.tg-me.com/phonestore_22
👍5
ከሴት መስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስ ጋር በተያያዘ በአንድ ወር ውስጥ ከ35 በላይ ሆቴሎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል ተባለ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ሴት የመስተንግዶ ሠራተኞች ሰውነታቸውን የሚያጋልጥ አለባበስ እንዲለብሱ የሚያስገድዱ ከ35 በላይ ሆቴሎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

በሆቴል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሴት የመስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስን የተመለከተ መመሪያ ጸድቆ ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የወጣው መመሪያ፤ ሴት የመስተንግዶ ሠራተኞች ሰውነታቸውን የሚያጋልጥ አለባበስ እንዲለብሱ የሚያስገድዱ አሰሪዎች ላይ ቅጣት የሚጥል ነው። 

ይህም የጸደቀው መመሪያ ተግባር ላይ ከመዋል የዘገየው የትርጉም ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው እንደሆነ፤ በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥ እና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ገነት ይመር ለአሐዱ ተናግረዋል።በአሁን ሰዓት የትርጉም ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የገለጹት ወ/ሮ ገነት፤ ለሆቴል አገልግሎት ሰጪዎቹ ከቅጣት በፊት ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዚህም ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ 35 ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።"ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ መመሪያው በሚያዘው መሠረት የቅጣት እርምጃ መውሰድ እንጀምራለን" ያሉት ኃላፊዋ፤ መረጃዎች ተጠናቅረው ሲቀርቡ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡አክለውም፤ "ከማስጠንቀቂያው ጎን ለጎን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ እና ላይኛው መዋቅር ድረስ እየተሰጠ ይገኛል" ብለዋል።

Via Ahadu
@YeneTube  @FikerAssefa
👍464👎1
አትሌት ትግስት ግርማ ታሰረች!

አትሌት ትግስት ግርማ ከትናንት በስትያ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ሻምፒዮና በ1500ሜ ክለቧን መቻልን በመወከል 2ኛ በመውጣት ውድድራን ያጠናቀቀችው የመቻል ስፖርት ከለብ አትሌት ትዕግስት ግርማ መታሰሯ ተሰምቷል።

አትሌቷ ለቶኪዮ የዓለም አትሌትክስ ሻፒዮና ሚኒማ ለማምጣት ወደ ኳታር ዶሃ ዳይመንድ ሊግ በማቅናት ላይ እያለች ነው በቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ከክለቧ በተላለፈ ደብደቤ መሰረት እንደታሰረች ኢትዮ ራነርስ ገፅ አስነብቧል።

የአትሌቷ እስር ምክንያት ከዚህ በፊት ክለቧን ሳታስፈቅድ ወደ አውሮፓ ለውድድር በመሄዷ እንደሆነ ምንጮች ገልፀውልኛል ያለው ገፁ ሳታስፈቅድ ስለሄደችበት ምክንያት መጠየቁን አንስቷል።

ምንጩ ጥያቄ ሲመልሱም አትሌቷ አሰልጣኟን ጠይቃ በቃል እንደፈቀደላት ከውድድር ከተመለሰችም በኋላ ጉዳዩ እንደታየና እንደተፈታላት የገለፁ ሲሆን ከመፈታቱ በፊት በተላለፈ ደብዳቤ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ለኢትዮራነርስ ገልፀዋል።

ጉዳዩ የሚመለከታችሁ በሙሉ ከክለቧ ጋር በመነጋገርና ችግረሩን በመፍታት ለአትሌቷ መፍትሔ እንዲመጣና ወደ ውድድሯ እንድታቀና አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲደረግላት በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ብለዋል የአትሌቷ የቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች መግለፃቸውን ጠቁሟል።

via ኢትዮ ራነርስ
👍33😁144👀1
🚨 Update


2 ዕጩ ሀኪሞች (Dr.Sador Bereket and Dr.Ifa Adugna) ስለታሰሩ ቅዱስ ጳውሎስ ሙሉ ኢንተርኖች ስራ እንዳቆሙ የደረሠን መረጃ ያሳያል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍78😭18🔥5👎1
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሰጠው የሦስት ወራት የጊዜ ገደብ ዛሬ ይጠናቀቃል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በልዩ ሁኔታ መዝግቦ በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ህወሓት የቦርዱን አሰራር ተከትሎ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ ወስኖ ነበር።

በደብረፂዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን በበኩሉ ህወሓት ዳግም እንደማይመዘገብ ገልፆ፣ የቀድሞ እውቅናው ሊመለስ ይገባል በማለት የራሱን “ጠቅላላ ጉባኤ” ያለውን ጠራ።

ምርጫ ቦርድ የደብረፂዮን ቡድን የጠራው ስብሰባ የቦርዱን አሰራር አልተከተለም በማለት በወቅቱ ውድቅ አድርጎታል።

ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ለህወሓት የተሰጠው የስድስት ወራት የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ ቦርዱ በህወሓት ላይ ጊዜያዊ የእግድ ትዕዛዝ በመጣል በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ጉባኤ እንዲጠራ በማስጠንቀቅ፤ ይህ ካልሆነ ግን እንደሚሰርዝ አሳስቦ ነበር።

ያ የተሰጠው የሦስቱ ወራት ጊዜ ዛሬ ያበቃል።

በደብረፂዮን ገብራሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን በበኩሉ መንግስት የፕሪቶሪያን ስምምነት መሰረዝ እስካልሰረዘ ድረስ ቦርድ ሰረዘን አልሰርዘንም ምንም አይነት ተጽእኖ የለውም ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በበኩላቸው የምርጫ ቦርድ መመሪያ ካልተቀበሉ ወደ ጦርነት እንደሚመለሱ ከዚህ ቀደም ህወሓትን በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።

የደብረፂዮን ቡድን ከኤርትራ እና ከፋኖ ጋር በመተባበር በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደር ያስባል የሚሉት ደግሞ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው።

እነዚህ ቡድኖች እርስበርስ የሚቃረን ግብ ያላቸው መሆናቸውን የሚገልፁት አቶ ጌታቸው፣ እንዴት እና በምን ላይ ልግባቡ ነው ብለው ይጠይቃሉ።

@Yenetube
👍165👎1😭1
Update Wolayita Sodo

እኛ የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የጤና ባለሞያወች ድንገተኛ ክፍል ባስቀመጥነው መረሀ ግብር መሰረት እየሰራን ባለን ሰዓት የሆስፒታላችን የበላይ አካላት
1.ዶ/ር ወክል ወልደ(CED)
2.ዶ/ር ታከለ ተክሉ(CAD)
3.ተስፋሁን ሞላ(Admin) የፈደራል ፖሊስ አባላትን አምጥተው እያስፈራሩን ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ሥራ ልናቆም እየተገደድን ነው።


@Yenetube
👍595🔥31
#BREAKING

ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።
😁38👍27🔥25👎41
#Update

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል።

አዲስ ተመራቂዎች ኑ እና አመልክቱ ከነገ ጀምሮ የሚል ማስታወቂያ አውጥቷል።

ይህ ያስቆመው ይሆን ?

@Yenetube @Fikerassefa
😁131👎58👍25🔥3
መቀሌ

የፌደራል ፖሊስ ወደ ትግራይ እየገባ ነው። በፕርቶሪያው ስምምነት መሰረት የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ በመግባት የፌደራል ተቋማትን ይጠብቃል፣ህግ ያስከብራል።

በዛሬው ዕለት በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት መቀሌ ገብተዋል።

ህወሃት ዛሬ በምርጫ ቦርድ ከፓርቲነት መሰረዙ ይታወቃል።

ፎቶ :- File
@Yenetube @Fikerassefa
👍85😁3112🔥4👎3
2025/07/13 06:14:24
Back to Top
HTML Embed Code: