Telegram Web Link
የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ አሰናድቻለሁ አለ፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተሰናድቷል፡፡በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉን ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ባለሞያዎች የደመወዝ የገቢ ግብር ይሻሻል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በንፅፅር ይናገራሉ፡፡የኢትዮጵያ ብር እና የኬንያ ሽልንግ ከዶላር አንፃር የምንዛሪ ዋጋቸው እኩል ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከ600 ብር ጀምሮ የሚያገኝ ደመወዝተኛ የገቢ ግብር ይቆረጥበታል፤ በኬንያ ደግሞ የገቢ ግብር የሚቆረጠው ከ24,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው፡በኢትዮጵያ ደመወዙ ከ10,900 ብርና ከዚያ በላይ የሆነ ተቀጣሪ 35 በመቶ የገቢ ግብር ሲቆረጥበት፤ በኬንያ ከ800,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው 35 በመቶ የገቢ ግብር የሚቆረጥበት፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
‘’ኢትዮጵያ የካሳ ኮሚሽን የወሰነላትን ገንዘብ ጨምሮ ሌሎች ተሰብሳቢ ገንዘቧን፤ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስመለስ የምታደረገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች’’ ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ ከየትኛው ጎረቤት ሀገር አንደሆነ ግን በስም አልጠቀሱም፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ይህን የተናገሩት ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባል የሆኑት አቶ እሸቱ ገ/ማርያም ‘’የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ይበርር ነበር፣ እሁን ግን እንደተቋረጠ እየሰማን ነው፣ የአየር መንገዱ ሃብትም ጨምር እንደተወሰደ ይነገራል ይሄንን በዲፕሎማሲ እንዲፈታ ምን አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ ቢሰጠን?’’ ሲሉ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ‘’የአለም አቀፍ አቪዬሽን ድርጅት የሚያወጣው ደረጃ አለው፣ በዚህም የተለያዩ የአየር መንገዶችን ሃብት አፍነው ይዘው አላስወጣ ያሉ አገራት እነማን ናቸወ ብሎ በዓመቱ በሚያወጣወ ሪፖርት ውስጥ በቀዳሚነት የሚሰለፉት አንዳንድ ጎረቤቶቻችን ናቸው’’ ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ‘’እንዚህ ጎረቤቶቻችን ብዙ የአውሮፕላን ምልልስ እና እንቅስቃሴ ያለባቸው አይደሉም፣ አዲስ አበባ በቀን የሚኖረው እነሱ ጋር ምናልባት በወር ቢኖር ነው፣ ገንዘብ በመያዝ ግን ቁጥር አንድ ደረጃ ላይ የሚሰለፉ ናቸው’’ ብለው በስም ያለጠቀሱትን አገር ወቅሰዋል፡፡

‘’ይህን ጉዳይ የሚከታተል አለም አቀፍ ድርጅት እና ስምምነት አለ’’ ያሉት ሚኒስትሩ ነገር ግን በስም ያልጠቀሱት እና ጎረቤት ሲሉ የጠቀሱት አገር ያለው መንግስት ጋር ይህን ‘’አክብሮ የመስራት ጉድለት አለበት’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘’እኛ ግን በእነዚህ ተቋማት እና አሰራሮች መሰረት ንበረታችንና ገንዘባችንን ለማስመለስ የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን’’ ብለዋል፡ያለን ሃቅ እና ንብረት ይህ ብቻ አይደለም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ሃሳባችን የአየር መንገዱ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የሚጠቀሱ ተሰብሳቢ ሂሳቦች አሉን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘’እንደሚታወቀው የካሳ ኮሚሽን ነበረ፣ የካሳ ኮሚሽኑ የወሰነልን ገንዘብም አለ’’ ብለዋል፡፡ በሆደ ሰፊነት እስከ ዛሬ ያልተሰበሰበ በገንዘብ የሚገለጹም፣ በገንዘብ የማይገለጹም ሊኖር ይችሉ ይሆናል በሂደት ይታያል’’ ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡እኛ በሰላማዊ በፖለቲካዊ እና ህጋዊ አግባብ ንብረታችንንና ጥቅማችንን ለማስከበር የምናደርገውን እንቅስቃሴ እንቀጥልበታለን ብለዋል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባንም” አሉ!

በኤርትራ በኩል “ትንኮሳ” ቢኖርም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገሪቱ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ። ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ የሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ስታነሳ “ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ያሉት ሚኒስትሩ፤ መንግስት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለው አቋም “አይዛነፍም” ሲሉ ለፓርላማ አባላት ገልጸዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፤ ከፓርላማ አባላት በቃል ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። ጥያቄ ካቀረቡት አንዱ የሆኑት የአብኑ የፓርላማ ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ አንስተዋል።

ኤርትራ እና ኢትዮጵያን “ወደ ጦርነት ጅማሮ” እየወሰዳቸው ያለ “የቃል ጦርነቱ የተጀመረ ይመስለኛል” ያሉት የፓርላማ አባሉ፤ ሁለቱ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ያላቸው “ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት” በምን መልኩ እንደሚገልጽ ጠይቀዋል። ዶ/ር ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር “ወደ ጦርነት መግባት እድል አለ ወይ?” ሲሉም ተጨማሪ ጥያቄ አክለዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ “ከኤርትራ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ አስተባብለዋል። ጉዳዩ የሚያሳስባቸው፣ የሚመለከታቸው ዜጎች፣ የህዝብ ተወካዮች እና የቀድሞ የመንግስት ኃላፊዎች “የራሳቸውን ምልከታ” እንደሚያጋሩ ግን ሚኒስትሩ አልሸሸጉም። እነዚህ አካላት “ጆሮ ሊሰጣቸው ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneYube @FikerAssefa
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
እንኳን ለታላቁ የአረፋ ቀን አደረሳችሁ

ዒድ ሙባረክ !

1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ አርብ (በጁምዓ እለት) ተከብሮ ይውላል።

መልካም በዓል
የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች የተደረገው የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በድምቀት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ያደረጉት የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀትና በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ከኢድ ሶላቱ ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲስ አበባ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክ ሀዋሳ ከተማ  ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ መካነ ኢየሱስ አካባቢ፣ ግሩም ግዛው የተባለ ግለሰብ 150 ሺ ብር ግምት ባለው አይፎን ፕሮማክስ 15 ስልክ እያወራ እያለ  ኮድ-2-1226 A/A  በሆነ ሞተር ላይ የነበረ ግለሰብ ከጆሮው መንትፎ  እንደወሰደበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ ስልኩ እንደተወሰደበት ወዲያው  ለፖሊስ ማመልከቱን ተከትሎ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ባደረገው ክትትል፣ በሀዋሳ ከተማ ስልኩን ገዝታ እየተጠቀመችበት ከምትገኝ ጸጋ ጴጥሮስ ከተባለች ግለሰብ እጅ ስልኩ ሊያዝ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከተሰረቀው ስልክ ጋር በቁጥጥር ስር የዋለችው ጸጋ ጴጥሮስ በበኩሏ፣ ምንተስኖት መቻል ከሚባል ግለሰብ እንደገዛች ለፖሊሰ ተናግራለች፡፡

የመንታፊዎችን ሰንሰለት አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ ፖሊስ በሰራው ስራ፣ ምንተስኖት የተባለውን ግሰለብ ከያዘው በኋላ ሌላ ተጨማሪ አማኑኤል ሻንቆ የተባለ ሰው አብሮት እንደነበር  ባገኘው መረጃ መሰረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ጠቁሟል፡፡

ይህን ተከትሎም ገዢዋን ጸጋ ጴጥሮስን ጨምሮ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክ ሸጠዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለቱን ግለሰቦች ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ አምጥቶ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በሞተር የሞባይል ስልክ ቀምቶ መሰወር ለጊዜው የማይደረስበት ቢመስልም ፖሊስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በእንዲህ መልኩ ወንጀለኞችን አድኖ እንደሚይዝና የግል ተበዳዮችም የትኛውም ዓይነት ወንጀል ሲፈጸምባቸው በአቅራቢያቸው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሊያመለክቱ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ከተማ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በመተከል ዞን፣ በቡለን ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 10 ሰላማዊ ሰዎች እና የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የመተከል ዞን እና የቡለን ወረዳ አስተዳደር በከተማይቱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ባንክ ቤትን ጨምሮ በተቋማት ላይ ዝርፊያ እና ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።

ጥቃቱ በቡለን ከተማ ላይ የተሰነዘረው፤ ዛሬ አርብ ግንቦት 29፤ 2017 ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እንደነበር ነዋሪዎቹ እና የቡለን ወረዳ አስተዳደር ገልጸዋል። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሶስት የቡለን ከተማ ነዋሪዎች ጥቃቱ እስከ ረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ድረስ የቆየ እንደነበር አመልክተዋል።

ታጣቂዎቹ ዛሬ ንጋት ላይ ወደ ከተማ ሲገቡ መመልከታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የዓይን እማኝነታቸውን የሰጡ አንድ ነዋሪ፤ መቶ ገደማ የሚሆኑ ታጣቂዎች በአንድ መስመር ሲጓዙ ማየታቸውን ተናግረዋል። ከታጣቂዎቹ ውስጥ ገሚሶቹ ቡላ ቀለም ያለው የደንብ ልብስ እንደለበሱ እና የተቀሩት ግን የሲቪል ልብስ መልበሳቸውን መመልከታቸውን አክለዋል።

ነዋሪው “ክላሽ እና ብሬል የያዙ ነበሩ” ያሏቸው ታጣቂዎች ጥቃት መሰንዘር ሲጀምሩ በቤታቸው እንደነበሩ ገልጸዋል። በጥቃቱ አስር ሰዎች መገደላቸውን፣ የባንክ እና ፖሊስ ጣቢያ መዘረፉን መስማታቸውንም አስረድተዋል።

🔴 ለዝርዘሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16129/
የ27 ጊዜ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሀፍ ተፃፈለት።

የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችሁ ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት።ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ  የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል። በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መፃፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል።ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች።

መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ስትናገር ሰምተናታል።

ለጊዜው ''Dissecting Haile'በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።መፅሀፉ ለገበያ የሚቀርበው በመጪው ነሀሴ ወር መሆኑንም ሰምተናል።የአትሌት ኃይሌን የህይወት ታሪክ የሚመለከት ሌላ መፃህፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኗንም ልጁ ተናግራለች።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
አሳዛኝ መረጃ

ወጣቱ ምንተስኖት ሰንበቱ ይባላል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ አመት ተማሪ ሲሆን በዛሬው እለት  በከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ በገመድ ተሰቅሎ ሕይወቱ ጠፍቶ ተገኝቷል።

ፖሊስ አስክሬኑ ለምርመራ ወደ ወራቤ ሆስፒታል መላኩ ታውቋል ።


@Yenetube @Fikerassefa
የሩሲያ ሠራዊት የዩክሬን የጦር ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ድርጅቶችና የጦር ሰው አልባ አውሮፕላን መገጣጠሚያዎች ላይ የቡድን ጥቃት መፈፀሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
ሕንድ የዓለም ረጅሙን የባቡር ድልድይ አስመረቀች

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የዓለማችንን ረጅሙን የባቡር ድልድይ መርቀው ከፍተዋል።

359 ሜትር የሚረዝመው እና በችናብ ወንዝ ላይ የተገነባው ይሕ ግዙፍ ድልድይ የካሽሚር ግዛትን ከተቀረው የሕንድ ክፍል በባቡር የሚያገናኝ ነው ተብሎለታል። የድልድዩ ርዝመት ከፈረንሳዩ ኤፍል ታዎር በ35 ሜትር የሚበልጥ እንደሆንም ተገልጿል።

ለግንባታው 5.1 ቢሊየን ዶላር የወጣበት ይሕ ፕሮጀክት አጠቃላይ የባቡር መስመሩ 272 ኪ.ሜ የሚረዝም ነው።

በተራራማው የካሽሚር ግዛቶች ውስጥ ያለው አስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥ ለትራንስፖርት አገልግሎት የማይመች እና አስቸጋሪ ቢሆንም ሕንድ የሰራችው ይሕ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድልድይ እና የባቡር መስመር በአካባቢው ያለውን የትራንስፖርት ችግር የሚፈታ ነው ሲል የዘገበው ኢንዲፔንዳንት ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
2025/07/07 09:05:08
Back to Top
HTML Embed Code: