Telegram Web Link
ፍተሻ በአዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕግ አግባብን የተከተለ ፍተሻና ብርበራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከሶስት ቀን በፊ ባወጣው መግለጫ፣ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሕግ አግባብን የተከተለ ፍተሻና ብርበራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ኅብረተሰቡ ለፀጥታው ሥራ ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፣ የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ሥጋት ላይ የሚጥሉ ወንጀለኞችን አስመልክቶ ለጠቅላይ መምሪያው በደረሱ ጥቆማዎችና በጥናት በለያቸው የሰላምና ፀጥታ ሥጋቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድና ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የሚያስችል የተጠናከረ ቁጥጥርና ፍተሻ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ደረሱኝ ካላቸው ጥቆማዎችና በጥናት እንደለያቸው ከገለጻቸው ከባድ ወንጀሎች መካከል "የጦር መሣሪያ ዝውውር፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ይገኙበታል"ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
በዳነሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ 8,445 ሰዎች “ዳግም” ተፈናቀሉ

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የአካባቢው መንግሥት አስታወቀ።

ጎርፍ የተከሰተው የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ እና የቱርካና ሀይቅ መደበኛ የውኃ ይዞታውን በከፍተኛ ፍጥነት በመልቀቁ ነው። የወረዳው ባለሥልጣናት በአጠቃላይ 8,445 ሰዎች “ዳግም” መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የአካባቢው መንግሥት አስታወቀ። በወረዳው ጎርፍ የተከሰተው “የኦሞ ወንዝ ሞልቶ መደበኛ የመፍሰሻ አቅጣጫውን ለቆ በመውጣቱ እና የቱርካና ሀይቅ መደበኛ የውኃ ይዞታውን በከፍተኛ ፍጥነት በመልቀቁ” እንደሆነ የዳሰነች ወረዳ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጽህፈት ቤት ትላንት አርብ አስታውቋል።

በወረዳው በተከሰተው ጎርፍ ምክንያት በአጠቃላይ 8,445 ሰዎች “ዳግም”

መፈናቀላቸውን የዳሰነች ወረዳ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ሰይድ መናገራቸውን መግለጫው ይጠቁማል።
ከኢትዮጵያ በኬንያ ወደሚገኘው ቱርካና ሐይቅ የሚፈሰው የኦሞ ወንዝ እየሞላ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲያፈናቅል የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።

ከዚህ ቀደም በተከሰተ ተመሣሣይ የጎርፍ አደጋ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም በሦስት ቦታዎች በጊዜያዊነት ተጠልለው እንደሚገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ መናገራቸውን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ቢሮ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጹ ያሰራጨው ጽሁፍ ይጠቁማል። ኃላፊው እንዳሉት በ2016 ክረምት የተከሰተ ተመሳሳይ የውኃ ሙሌት “የ28 የሚሆኑ ቀበሌያትን” አፈናቅሎ ነበር።

የኦሞ ወንዝ ሲሞላ የአካባቢውን ነዋሪዎች ከቀያቸው ከማፈናቀል ባሻገር የዳሰነች እና የኦሞራቴ ከተሞችን አደጋ ውስጥ ሲጥል ቆይቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
በወላይታ ሶዳ ከተማ በግድያ ወንጀል ተፈርዶበት በምህረት የተለቀቀው ተከሳሽ የ8 ዓመቷ ታዳጊ ላይ በፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በእስራት ተቀጣ

በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሶዶ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ ኤፍሬም ጪማ የተባለ ግለሰብ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ 12፡30 አካባቢ የግል ተበዳይ የሆነችውን የ8 ዓመት ታዳጊ ጁስ እና ኮሾሮ ገዝቶ በማታለል የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙ ተገልፆል፡፡

ግለሰቡ ከዚህ በፊት በነፍስ ግድያ ወንጀል ተባባሪ ሆኖ 14 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደበትና የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ በምህረት የወጣ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኤፍሬም ጪማን በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerasssefa
‹‹ሠራተኞች ለመኖር የሚያስችላቸው ደመወዝ ተከፍሏቸው እየኖሩ ነው ማለት አይቻልም››  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ)

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ለመኖር የሚያስችላቸው ደመወዝ እየተከፈላቸው ነው ለማለት እንደማይቻል፣ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ገለጸ፡፡
የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ድሪብሳ ለገሠ፣ አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ሠራተኞች ደመወዝ ተከፍሏቸው በመኖር ላይ ናቸው ብሎ አፍን ሞልቶ ለመናገር የሚከብድ መሆኑን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በተዘጋጀ የአጀንዳ መድረክ ላይ የተገኙት አቶ ድሪብሳ ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የሠራተኞች የደመወዝና ሌሎች ዋና ዋና ጥያቄዎቻቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ስናቀርብ ቆይተናል፤›› ብለው፣ እየታዩ ያሉ ተጨባጭ እውነታዎችን ተቀብሎ በማስተካከል በኩል መዘግየቶች በመኖራቸውና በፍጥነት ካልተፈቱ ወዳልተፈለገ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

Via:- Reporter

@Yenetube @Fikerassefa
መንግሥት፣ በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ መሻሻል ያለባቸው በርካታ አንቀጾች አሉ ብሎ እንደሚያምን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባስገባው ባለ 30 ገጽ መነሻ ሃሳብ ላይ መጠቆሙን ሪፖርተር አስነብቧል።

መንግሥት፣ አንቀጾቹ "በሰፊ ውይይት"፣ "በክርክር" እና "በሙሉ መግባባት" መሻሻል እንዳለባቸው በሰነዱ ላይ መጠቆሙንም ዘገባው ጠቅሷል። ኾኖም ሕገመንግሥቱ "ሕገመንግሥታዊነት" እምብዛም ያልታየበትና እስካኹንም "በተግባር ያልተፈተነ" መኾኑን የጠቀሰው የመንግሥት ሰነድ፣ ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አንዳንድ ችግሮች ሊያስከትል እንደሚችልም ገልጧል ተብሏል።

ከዚህ አንጻር የሕገመንግሥት ማሻሻያ ማድረግ፣ "አዲስ ሕገመንግሥት ማስተዋወቅ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል" በማለት መንግሥት በሰነዱ ላይ ስጋቱን እንዳሠፈረም ዘገባው አመልክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ!

የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ፣ቫግነር በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ከአገሪቱ ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ።ቫግነር በምዕራባዊቷ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ከአውሮፓውያኑ 2021 ጀምሮ ከአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመጣመር ጽንፈኞችን ለመምታት እየሰራ ነበር።

ቫግነር "ከማሊ ሕዝብ ጎን በመሆን ሽብርተኝነትን ተዋግቷል፤ በዚህም ነዋሪዎችን ለዓመታት ሲያሸብሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች እና አዛዦቻቸውን ገድያለሁ" ሲል በቴሌግራም ገጹ አስታውቋል።

ቫግነር ከአገሪቱ እንደሚወጣ ያስታወቀው የማሊ ወታደሮች ከአንድ ሳምንት ባነሰ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የከፋ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በአገሪቱ ማዕከል ከሚገኘው ትልቅ የጦር ሰፈር መውጣታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየወጡ ባለበት ወቅት ነው።ማሊ ለአስርት ዓመታት ከእስላማዊ ታጣቂዎች ጋር ስትታገል ቆይታለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ፀረ ጦርነት ዘመቻ ዛሬ በበይነመረብ ተጀምሮል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተመልካቾች በተከታተሉት ዉይይት ላይ የሃገሪቱ የተለያዩ አቆም ያላቸዉ ፖለቲከኞች እና ትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ሃይሎች ተሳትፈዉበታል ፡፡

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሃይሎችን በመወከል ዘመነ ካሴ ንግግር አድርጎል ፡፡

በኢንተርኔት መቆረጥ ምክንያት ያልተመለከታችሁ
ቀጣዩን ሊንክ በመጠቀም መመልከት ትችላላችሁ👇👇👇
https://youtu.be/gkZic7SDHv8?si=ruIgaSJRBUiBkh7x
በነገው ዕለት በወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በዝግ እንዲካሄድ ተወስኗል።

ጨዋታው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) በቀጥታ ይተላለፋል።

መች ይሆን ህዝቡ እግርኳስ በነፃነት በስቴድየም ማየት የሚጀምረው??
የህክምና ጓንት እና ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት ማቆሙን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት በአገሪቱ ውስጥ ሁለት የጓንት አምራቾች ያሉ ሲሆን፣ ዘንድሮ ሙሉ በሙሉ የህክምና ጓንት በአገር ውስጥ ምርት እየተሸፈነ ነው፡፡

እንደ ጋዜጣ ፕላስ ዘገባ በሙሉ አቅሙ እያመረተ የሚገኝ አንድ ስሪንጅ ፋብሪካ በድሬዳዋ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ፋብሪካው ምርቶቹን ለአገልግሎቱ እያቀረበ በመሆኑ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት አቁመናል ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሲዳማ ቡና ሻምፒዮን ሆነ


በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን  2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።
በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ መስፍን ታፈሰ የሲዳማ ቡናን ግቦች  አስቆጥረዋል።

በዝግ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ ያስገኘ ተጫዋች ሆኗል።

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫን ማንሳቱን ተከትሎ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ  በቀጣይ አመት በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክልም ይሆናል።

ወላይታ ድቻ በ2ኛው አጋማሽ ከተደጋጋሚ ሙከራዎች ባሻገር ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ በሚል ተሽሮበታል።

በ2010 ዓ.ም በተሳተፈበት የኮንፌደሬሽን ዋንጫ በ1ኛው  ዙር ቅድመ ማጣሪያ የግብጹን ጠንካራ ክለብ ዛማሊክ በደርሶ መልስ አሸንፎ የነበረው ወላይታ ድቻ በድጋሜ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፍበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከአራት አመታት መቋረጥ በኋላ በ2016 ዓ.ም መጀመሩም ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
ዜና: "#በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም ሲገባቸው የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት የሚሰሩ ናቸው" - ጠ/ሚኒስትር አብይ

"በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት” የሚሰሩ ናቸው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት በበርካታ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ክፍል በተላለፈው ቃለምልልሳቸው በመጨረሻው ክፍል ላይ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው የሚሰሩት ሲሉ የተቹት ጠ/ሚኒስትሩ "እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሃሰት መረጃዎችን እና የፈጠራ ዜናዎችን በማሰራጨት ሕዝቡን ለማሳሳት ሲሞክሩ ተስተውለዋል” ብለዋል።

በገለጻቸውም "ሚዲያ ልክ እንደ እሳት ነው፤ ያጠፋልም ያለማልም፤ እንደቢላዋ ለጥሩ አሊያም ለመጥፎ ነገር ሊውል የሚችል ነው" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ "በዓለም ላይ ገለልተኛ የሚባል ሚዲያ  የለም" ሲሉ ተደምጠዋል፣ “መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ዘገባ ሊሰሩ ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።

መገናኛ ብዙሃንን ለመልካም አላማ ከተጠቀምናቸው ውጤታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ በተቃራኒው ሚዲያዎች ለጥፋት አላማ የሚውሉ ከሆነ ከፍተኛ አደጋን ያስከትላሉ ሲሉም ገልጸዋል።

በተጨማሪም "የለውጡ መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ነጻነት በኢትዮጵያ በርካታ አዳዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከ60 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች እየተላለፉ ይገኛል" ብለዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ

ኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

በ34ኛ ሳምንት የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባእንደርታ ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ መድን ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በተመለሰ በ2ኛ አመቱ ሊጉ ሊጠናቀቅ 3 ጨዋታ እየቀረው በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሳክቷል፡፡

ከአሁን በፊት ከጅማ አባጅፋር እና መቐለ ሰባእንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የመድን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ሻምፒዮን በመሆንም ታሪክ ሰርቷል፡፡

ኢትዮጵያ መድን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳ 10ኛው ክለብም ሆኗል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ

ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ፈተናው እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት እየተሰጠ ባለው የመውጫ ፈተና 190 ሺህ 787 ቅድመ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 102 ሺህ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የቤት ውስጥ ሰራተኞችን የሚመለከተው ኮንቬንሺን 189 እንዲፀደቅ ጥረት እያደረግን ነው ሲል አንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር አስታወቀ።

የአንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር የህብረቱ ፕረዝደንት ሒሩት አበራ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከፈረመች አመታት ቢቆጠሩም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ የቤት ሰራተቾች በማህበረ ተደራጅተው ስለመብቶቻቸው ያለመጠየቅ፣እንደ ማኒኛውም ሰራተኛ የሰራተኞችን መብት በሚያስጠብቀው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156 ውስጥ እንዲሁም በሌልች የህግ ማእቀፍ ውስጥ ያለመካተታቸውና ያለመጠየቃቸው እስካሁን አዋጁ ሳይፀድቅ ቆይቷል  ብለዋል።

ስለቤት ውስጥ  ሰራተኞች የሚያወሳውን አለም አቀፍ ስምምነት 189 ኮንቬንሺን ለምን አልተፈረመም ብለን ስንጠይቅም ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ነው ይባላል በህግ አውጪው በኩል ሲሉም አስረድተዋል። መመሪያው ፀድቆ በስራ ላይ ቢውል፣ የቤት ሰራተኞችን መሰረታዊ መብቶች የሚያስጠብቅ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚያስተካክልና የስራ ከባቢያቸውንም ምቹ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን፣ መመሪያውና የስራ ቅጥር ውሉ፣ የቤት ሰራተኞች ጉልበታቸው ሲደክም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡በአሁን ወቅት የቤት ሰራተኞች በስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚዋዋሉት ውል ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ሐላፊነትን የማይሰጥና መብትና ግዴታን የማይለይ ነው፡፡

ሆኖም ይህን ችግር ለመፍታት ነው ማህበሩ የተቋቋመው ያሉ ወ/ሮ ህሩት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከአራት አመታት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት፣ በሀገሪቱ ወደ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰራተኞች እንዳሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቷ፣ እነዚህ ዜጎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርሱባቸውም በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ 

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/07 04:31:20
Back to Top
HTML Embed Code: