Telegram Web Link
የአፍሪካ አገር፣ ሚስጥራዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሆና እንደምታውቅ ስንቶቻችን እናውቃለን?

የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከተፈጠረ 100 አመት ያልሞላው ቴክኖሎጂ ሲሆን እንደ ቦምቦቹ ብዛት ከከተሞች እስከሃገራት የሚደርስ ቦታን ማጥፋት የሚችል ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ነው። አለም ላይ እስካሁን አስር ሃገራት የዚህ መሳሪያ ባለቤት መሆን ችለዋል ወይንም ችለው ነበር። እነዚህም ራሺያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ እና በዚህ ቪዲዮ የምንመለከታት አፍሪካዊት ሀገር ናቸው። ይህንን ልዩ ዝግጅት ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉት፤ መሰል ዝግጅቶችን በየጊዜው ለመከታተል ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

https://youtu.be/Va_GpklAY3I
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 3 Sessions


We’re continuing our 14-part expert-led workshop series with four important sessions in Week 3:

🧱 Geotechnical Properties & Structures
🌍 Seismic Design & Earthquake Resistance
🏗 Steel & Composite Structures
🪟 Aluminum & Glass Design


📅 June 17, 19, & 21, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also streaming live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
📩 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

A big thank you to all our partners for making this series possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #Geotech #SeismicDesign #StructuralEngineering #FacadeDesign
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።

አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/leeltbridal

Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
ተጨማሪ ጥቃት

ኢራን በእስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ ከደቂቃዎች በፊት አዲስ የሚሳኤል ጥቃት አድርሳለች።

በጥቃቱ ምክንያት በበርካታ ቦታዎች ጭስ ይታያል። እስራኤል ከኢራን የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን  ማክሸፍ አለመቻሏ የእስራኤል ዜጎች ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ

👉1መኝታ 75ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር
ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር
👉2መኝታ 94ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር
ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር
👉2መኝታ 103ካሬ
10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር
ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር
👉3መኝታ 132ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር
ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር
👉3መኝታ 146ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር
ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር
‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም በጀት 350 ቢሊየን ብር ሆኖ ለምክር ቤት ሊቀርብ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባዉን ሁለት ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡አስተዳደሩ ረቂቅ በጀቱ ለካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ላደረገ የመደበኛ በጀት ደግሞ 100.1 ቢሊዮን ብር የበጀት ጣሪያ ወስኗል፡፡በሌላ በኩል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የመሬት ሊዝ ዋጋ ላይ ማሻሻያ አፅድቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ የተመሰረቱት የቀድሞ የደቡብ ክልሎች የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማድረግ እንደሚኖርባቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ!

የበጀት ንግግራቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ካቀረቡ በኋላ ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስተሩ አቶ አህመድ ሽዴ በቀድሞው የደቡብ ክልል ስር የነበሩ አዳዲስ ክልልሎች ደሞዝ ለመክፈል ጫና አለባቸው ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

በቀመሩ መሰረት በጀት እንደሚደለደል ያስታወሱት ሚኒስትሩ ክልሎች ችግር ሲገጥማቸው በህጉ መሰረት የአጫጭር ጊዜ ብድር እንሰጣቸዋልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡በመልሳቸው በደቡብ የሚገኙት ክልሎች የሲቪል ሰርቪሳቸውን መልሰው ማደራጀት በቀጣይ ሊታሰብ ይገባል ሲሉ ነው ምክረ ሃሳብ ያቀረቡት፡፡

‹‹እንደሚታወቀው እነዚህ ክልልሎች የማይሰራም ጭምር በጣም ሰፊ ሰራተኛ ነው ያላቸው፣›› ያሉት አቶ አህመድ፤ በመሆኑም ሪፎርም ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከብልፅግና ፓርቲ ዋና ፀህፈት ቤት ጋር በመሆን የፕላን እና ልማት ሚኒሰቴር ሰፊ ጥናት ማከናወኑንም ነው የገለጹት፡፡አዳዲስ የወጡት ክልሎች፡- ሲዳማ፣ ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማእከላዊ ኢትዮጵያ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Via KGEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት አዲስ የተሾሙትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ መግደሉን አስታወቀ!

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ እና ከአገዛዙ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑትን አሊ ሻድማኒ መገደሉን አስታውቋል።ዋና አዛዡ የተገደሉት በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ መሆኑም ተዘግቧል።

ጥቃቱ የተፈፀመው የእስራኤል ጦር በደረሰው መረጃ መሰረት፤ በኢራን ወታደራዊ ተዋረድ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ባለስልጣኖች አንዱ የሆኑትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥን ዒላማ በማድረግ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

አሊ ሻድማኒ በዚህ ወር መጀመሪያ እስራኤል የጥቃት ኦፕሬሽን ውስጥ የተገደሉትን የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አላም አሊ ራሺድን ተክተው ሚናውን መረከባቸው ይታወሳል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።ግድያው በኢራን ወታደራዊ እዝ መዋቅር ላይ ወሳኝ ጉዳትን የሚያደርስ ሲሆን፤ የኢራንን የጦር ኃይሎች ከፍተኛ አመራሮችን እስራኤል በተደጋጋሚ ዒላማ አድርጋ እያጠቃች ትገኛለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን ዛሬ ማለዳ በማዕከላዊ እስራኤል 30 ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች፡፡

ኢራን ዛሬ ማለዳ በማዕከላዊ እስራኤል 30 ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን የእስራኤል መከላከያ አስታውቋል።

አምስተኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል እና ኢራን ግጭት አገራቱ የሚሳኤሎች ጥቃታቸውን ቀጥለዋል።

በቴልአቪቭ እና በእየሩሳሌም ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

ጦሩ አብዛኛዎቹ ሚሳኤሎች ከሽፈዋል ብሎ የተወሰኑት ግን ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጿል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከቴልአቪቭ በስተሰሜን በሚገኝ ሄርዝሊያ በተሰኘው ሸለቆ አካባቢ የተቃጠሉ አውቶብሶችን እሳት ሲያጠፉ ታይተዋል።

በሌላ ዜና የእስራኤል ጦር ትናንት ማምሻውን በቴህራን በፈጸመው ጥቃት ባለፈው ሳምንት የተገደሉትን ወታደራዊ አዛዥ የተኩትን አሊ ሻድማኒን መግደሉን አስታወቀ።

ሻድማኒ የኢራን ጥምር ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብረው የአብዮታዊ ዘቡ ካህታም አል አንቢያ የተሰኘው ማዕከላዊ ዋና መስሪያ ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት በቅርቡ ነበር።

ከሳቸው በፊት ተቋሙን ይመሩ የነበሩት ጎላማሊ ራሺድ በእስራኤል ጦር ባለፈው ሳምንት መገደላቸውን ተከትሎ ነበር ወደ ኃላፊነት የመጡት።

የኢራን መገናኛ ብዙኃን ስለ ሻድማኒ ሞት የዘገቡት ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ከስልጣን ተነሱ ፤

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስን፤ ትናንት የብልጽግና መሪዎች በስብሰባ ላይ ተቀምጠው ከስልጣን ተነስቶ በሕግ እንድጠይቅ መወሰኑን በማወቅ ተችሏል።

በቅርቡ የሲዳማ ክልል ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለታሰሩት አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ተጠሪ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ኮሚሽነሩም የአለማየሁ የቅርብ ሰው መሆኑ ተነግሯል።

ተጠማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

@Yenetube @Fikerassefa
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር የማሻሻያ አዋጅ ጸደቀ!

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር የማሻሻያ አዋጅ ጸደቀ።6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 37ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበን የማሻሻያ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ እንደገለጹት፤ ማሻሻያ አዋጁ ሀገሪቱ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ጥረት ላይ ያላትን ድርሻ በአግባቡ እንድትወጣ የሚያስችል ነው፡፡ቀደም ሲል በሥራ ላይ የነበረው አዋጅ ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ በርካታ ድንጋጌዎችን የያዘ እንደነበር ጠቅሰው፤ ነገር ግን ወቅቱን ያገናዘበና በሚፈለገው ደረጃ ሥራውን ውጤታማ አድርጎ ለመምራት በሚያስችል መልኩ አለመደራጀቱን ተናግረዋል፡፡

በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀልና ሽብርተኝነት በገንዘብ መርዳት ድንበር ተሻጋሪና ዓለም አቀፋዊ ችግር መሆኑን በመግለጽ፤ ወቅቱን የጠበቀ፣ ጠንካራ ህግና አሰራር ሥርዓት መዘርጋት የተረጋጋ እና ግልጽነት ያለው ጤናማና ቀልጣፋ የፋይናንስ ሥርዓት የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከፋይናንስ ግብረሀይል ምክረ ሀሳብና ዘርፉን በተመለከተ ሀገሪቱ ፈርማ የተቀበለቻቸው ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ እንዲሆንና ያጋጠሙ ክፍተቶችን ለመሙላት የህግ ማዕቀፉን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡የተለያዩ የፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ያልሆኑ ተቋማት ትክክለኛነትና ተጠቃሚ ባለሀብቶች እነማን እንደሆኑ ለመለየት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ ወንጀልን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ መረጃዎችን ለመያዝ የሚያግዝ አሰራር ያስቀመጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ምክር ቤቱ በተጨማሪም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

[ጋዜጣ ፕላስ]
@YeneTube @FikerAssefa
10 ቢ. ዶላር የሚፈጅ ፈጣን መንገድ ለመገንባት ታቅዷል!

የኢትዮጵያ መንግሥት 2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚያካልል የፈጣን መንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት ማቀዱን ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባሳተመው አዲስ የኢንቨስትመንት “ስምምነት መጽሐፍ” ውስጥ መገለጹን ስፑትኒክ ዘግቧል።

በውጥኑ የተካተቱ የመንገድ መስመሮች፦

- አዲስ አበባ–ኮምቦልቻ–ደሴ፦ 352.2 ኪ.ሜ (2.32 ቢሊየን ዶላር)፣

- አዲስ አበባ–ጂማ፦ 345.5 ኪ.ሜ (2.03 ቢሊየን ዶላር)፣

- አዲስ አበባ–ደብረ ማርቆስ፦ 317.6 ኪ.ሜ (1.64 ቢሊየን ዶላር)።

ፕሮጀክቱን በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ተጫራቾች ለመተግበር መታቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገልጋይ  አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣ ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ 5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የእራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን <<ግብረ ሰዶማውያን ናቸው>> በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን <<የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት >>በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን <<ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው>>ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መግለጫ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን << ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ>> ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።

መምሪያውና የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴው በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዘርሮችን በመግለጽም ጉዳዩ  ለሚመለከተው አካል ቀርቦ  ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል።በተያያዘም መምሪያውና የሕግ ባሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴው ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ክትትል በማድረግ ለፍጻሜ እንደሚያበቁት ገልጸዋል።

Via:- ዳጉ_ጆርናል
@YeneTube @Fikerassefa
ትራምፕ ኢራን "ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ" ጠየቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኔይ የት እንደሚገኙ በትክክል እንደሚያውቁም ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ እርሳቸውን "ለጊዜውም ቢሆን" ለማጥፋት ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።

ትራምፕ የኢራን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ ቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።

ትራምፕ የኢራን መሪን ለአሁኑ 'የመግደል እቅድ' የለንም ብለዋል ።

ዶናልድ ትራምፕ "እኛ" የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኔን አንገድልም - "ቢያንስ ለጊዜውም ቢሆን" ብለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አያቶላህ የት እንዳሉ በትክክል እናውቃለን "ቀላል ኢላማ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ነገር ግን "ትዕግሥታችን በጣም ጠባብ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል ያለው ቢቢሲ ነው።

እስራኤል ኢራንን ማጥቃት ከጀመረች ከአምስት ቀናት በኋላ ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ መታኮሳቸውን ቀጥለዋል ።

ኢራን ማምሻውን በቴል አቪቭ እና ሃይፋ ያሉ ሰዎችን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።

ብዙ ኢራናውያን ቴህራንን ለመሸሽ እየሞከሩ መሆኑ ተዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 3 Sessions


We’re continuing our 14-part expert-led workshop series with four important sessions in Week 3:

🧱 Geotechnical Properties & Structures
🌍 Seismic Design & Earthquake Resistance
🏗 Steel & Composite Structures
🪟 Aluminum & Glass Design


📅 June 17, 19, & 21, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also streaming live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
📩 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

A big thank you to all our partners for making this series possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #Geotech #SeismicDesign #StructuralEngineering #FacadeDesign
2025/07/03 16:47:46
Back to Top
HTML Embed Code: