Telegram Web Link
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።

13 ዓመት ተፈርዶባቸዉ በማረሚያ ቤት የነበሩት የቀድሞው ከንቲባ በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበራቸው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰነባቸው የፍርድ ዉሳኔ በነፃ መሰናበታቸውን ተነግረዋል።

የቀድሞው ከንቲባ በአጠቃላይ ከቀረበባቸዉ 7 የክስ መዝገቦች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው 2 ክሶች  በነፃ ተሰናብተው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ3 ክሶች ነፃ በ2 ክሶች ደግሞ 13 ዓመት እስራት ፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ከፍርዱ በኃላ ባለቤታቸው ወ/ሮ ዜናዬ ተሰማ  በሰጡት ቃል ፤ " ፀጋዬ ቱኬ የፖለቲካ እስረኛ እንጂ ጥፋተኛ እንዳልሆነ፣ ለሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ያለ አግባብ በእስር ቤት እንደተንገላታ ፣ጉዳዩን የያዙ ዳኞች በባለስልጣን ጫና ሲቀያየሩ እንደነበር፣ በአጠቃላይ የፍርድ ዉሳኔዉ ጣልቃገብነት የታየበት እንደነበርና ይግባኝ እንደጀመሩ " ተናግረው ነበር።

የቀድሞው ከንቲባ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተዋል።

የዉሳኔዉን አፈፃፀም የክልሉ ማረሚያ ተቋም የወሰደ ሲሆን ከምሳ ሰዓት በኋላ ከእስር እንደሚለቀቁ ከስፍራዉ ማረጋገጥ ተችሏል።
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ

https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN

በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
  44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
  አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
🇪🇹🇦🇪 ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ሙያዊ እገዛ ጠየቀች

ጥያቄው የቀረበው በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን ከሀገሪቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሊድ መሐመድ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ አባል ለመሆን ባቀረበችው ጥያቄ የተገኘው ድጋፍ እንዲፋጠን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባንክ ዘርፍ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ የፋናንስ ዘርፉን ክፍት ማድረጓ እና መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች አዲሱ የልማት ባንክ ካነገበው የመሠረተ-ልማት እና ቀጣይነት ያለው ልማት ዓላማ ጋር በቀጥታ የሚዛመድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄዋን አቅርባ ከአባል ሀገራቱ የፖለቲካ ድጋፍ እንዳገኘች በዩኤኢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውሷል።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
Photo
አሜሪካ ብቻ ልመታው የምትችለው የኢራን ሚስጥራዊ ቦታ

ከቴህራን በስተደቡብ ባለው ተራራማ አካባቢ ተደብቆ ለኢራን የኒዊክሌር ስራዎች አስፈላጊ የሆነ ስፍራ ነው - የፎርዶ የኒውክሌር ጣቢያ።

ይሄ ስፍራ በትልቅነቱ እንግሊዝን እና ፈረንሳይን ከሚያገናኘው ዋሻ ይበልጣል ተብሎ ይገመታል። ታዲያ እስራኤል በኢራን ሰማይ ላይ የበላይነት ባገኘችበት በዚህ ሰዓት እንኳ ይሄን የኒውክሌር ጣቢያን መምታት አትችልም እየተባለ ነው።

የእስራኤል የጦር መሳሪያዎችም የፈለገ የሚሳኤል ደዶፍ ቢያወርዱ ሊደርሱበት አልቻሉም።

ፎርዶን ለማጥፋት የሚያስችል ትልቅ አቅም እንዳላት የሚታሰበው የትራምፕ ሀገር አሜሪካ ነች። ትራምፕ በዚህ የኢራን እና እስራኤ ውጊያ ከባችበት፣ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ባልተጠበቀ ሁኔታ ሊያሰፋው ይችላል።

ከዋና ከተማይቱ ቴህራን በስተደቡብ 96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የዩራኒየም ማበልፀጊያ ቦታ፣ ለኩም ከተማ ቅርብ በሆነ ተራራማ አካባቢ መሽጓል።

በፎርዶ የሚገኘው ኮምፕሌክስ፣ በመጀመሪያ በሀገሪቱ ከፍተኛ ኢስላሚክ አብዮታዊ ጥበቃ (IRGC) የሚጠቀምባቸው ተከታታይ ዋሻዎች የነበረ ቢሆንም፤ በኋላ ግን ኢራን ለማበልፀጊያነት እንደምትጠቀመውም እ.ኤ.አ በ2009 ገልፃለች።

ዩራኒየምን ለማበልጸግ የሚያገለግሉ ሁለት ዋና ዋሻዎችን ያቀፈ ነው ተብሎ ይታሰባል። ከመሬት በታች ባለው ጥልቀት ምክንያት ለእስራኤላውያን ጦር ሰራዊት ልዩ ፈተና ነው።

እስራኤል አሏት ተብሎ የሚገመተው የጦር መሳሪያዎች ከ10ሜ ባነሰ ጥልቀት ብቻ ጥቃት የሚያደርሱ ናቸው። በአንጻሩ ዩናይትድ ስቴትስ ግን 61 ሜትር ወደ መሬት ውስጥ ዘልቆ መግባት የሚችል መሳሪያ እንዳላት ጄንስ የተባለ የመከላከያ መረጃ ኩባንያ ገልጿል።

ነገር ግን የፎርዶ ቦታን ለማጥፋት ዩናይትድ ስቴትስም እንደሚከብዳት ይገለፃል፤ ምክንያቱም ዋሻዎቹ ከ80-90ሜ ወለል በታች ናቸው ተብሎ ይገመታል። ይሁን እንጂ የነዚህ ቦታዎች ሁኔታ በመሉ ሚስጥራዊ ናቸው።

Via:- NBC Ethiopia
@Yenetube @Fikerassefa
እጅግ አሳዛኝ ዜና😥

ቲክቶከርና የኮንታ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን የካሜራ ባለሙያ የሆነች ሊዬ ዛሬ በስራ ላይ እያለች በደረሰ የመኪና አደጋ ህይወቷ ማለፋ ተሰምቷል።

ሊዬ ከመደበኛ የመንግሥት ሥራ ጎን በቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያ ሊያ vlogs የእለት ውሏን፣ ከልጇቿ ጋር የሚታሳልፋቸውን ጊዜ በማጋራት የሚትታወቅ ነበረች።

በቅርቡም በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ከድምጻዊት ቬሮንካ አዳነ ዘንድ ቀርባ ማበረታቻ ሽልማት መረከቧ የሚታወስ ነው።

እጅግ ጎበዝ፣ ታታሪ ስራ ወዳድ የሆነችው የካሜራ ባለሙያ ዛሬ በስራ ላይ በነበረችበት ወቅት በደረሰ የመኪና አደጋ በሚያሳዝን መልኩ ህይወቷ አልፏል።

ፈጣሪ የእህታችንን ነፍስ በገነት ያኑር
ለቤተሰቦች፣ ለስራ ባልደረቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን።

Via Dawro Tube
@Yenetube @Fikerassefa
ነገ አርብ ቢሮዎች ይዘጋሉ ተባለ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ሁሉም የትግራይ ቢሮዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለነገ አርብ ዝግ እንዲሆኑና ሁሉም የክልሉ ነዋሪ "ይኣክል" (ወይም ደግሞ "በቃ") በሚል መሪ ቃል የተጠራውን ክልል አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተቀላቅሎ በተለያዩ መጠሊያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቹ ድምጽ እንዲሆን ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።

ውሳኔው የተላለፈው "ፅላል ስቪል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ" በመባል የሚታወቀውና የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አላማ አድርጎ የሚሰራ ስቪክ ድርጅት ባቀረበው ጥያቄ ነው ተብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 3 Sessions


We’re continuing our 14-part expert-led workshop series with four important sessions in Week 3:

🧱 Geotechnical Properties & Structures
🌍 Seismic Design & Earthquake Resistance
🏗 Steel & Composite Structures
🪟 Aluminum & Glass Design


📅 June 17, 19, & 21, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also streaming live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
📩 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

A big thank you to all our partners for making this series possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #Geotech #SeismicDesign #StructuralEngineering #FacadeDesign
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።

አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/leeltbridal

Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
Forwarded from YeneTube
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ

👉1መኝታ 75ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር
ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር
👉2መኝታ 94ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር
ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር
👉2መኝታ 103ካሬ
10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር
ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር
👉3መኝታ 132ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር
ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር
👉3መኝታ 146ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር
ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር
‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
በፎቶ፡ በትግራይ ክልል በመቀለ ከተማ “አምስተኛ ክረምት በሸራ መጠለያ ማሳለፍ ይብቃን” በሚል መሪ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ለሶስተኛ ቀን ዛሬም ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል።

ሰልማዊ ሰልፉ በትግራይ ጦርነት ምክንያት የተፈናቆሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለመጠየቅ የተጠራ ነው።

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም በሰልፉ ታደመዋል።በተመሳሳይ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለሰልፉ ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ ተከታዮቻቸው በከተማዋ ሮማናት አረባባይ በሚካሄደው ሰልፍ እንዲሳተፉም ጠይቀዋል። በመቀለ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተካሄደው ሰልፉ ዛሬ የመርሃ ግብሩ የመጨረሻው ቀን ነው።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ የፍትህ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ባለፈው ሰኔ 10 ቀን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባጸደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የቀረበውን አዋጅ ይዘት በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡መስሪያቤቱ አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም ብሏል፡፡

ስለ አዋጁ ማሻሽያ፣ ይዘት እና ምንነት ማብራርያ የሰጡት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው ብለዋል፡፡በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መቋቋሙን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ ተብሏል። ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ነደ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡ ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዱ ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት አቶ ሙሉቀን ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል ብለዋል፡፡እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው ሲሉ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታ ስተገለገልበት መቆየቷን ያስረዱት ዳይሬክተሩ የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው ብለዋል፡፡በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ ብለዋል፡፡

የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር ብለዋል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙለቀን አማረ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል  አቶ አዲስ ጌትነት በበኩላቸው አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል ብለዋል፡፡

አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም ያሉት አቶ አዲስ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌም መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል ሲሉ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት ተናግረዋል፡፡

ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው ያለው የፍትህ ሚኒስቴር እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም ፍጹም ስህተት ነው ብሏል፡፡

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

Via Sheger
@YeneTube @FkkerAssefa
በግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ተገለጸ!

በግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) በዘርፉ ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩ የንግድ ሥርዓቱን የሚረብሹ በርካታ ደላላዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በእህል ምርት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቁም እንስሳት ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ገልጸው፤ ከ3 ሺህ በላይ ደላሎች እና አገናኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በቀጣይ በገበያው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ሲሉ መግለጻቸውን የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው፡፡

በተመሳሳይ በሲሚንቶ ገበያ ዘርፍ ነጻ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት “የሲሚንቶ ዋጋ ከግማሽ በታች እንዲቀንስ” መደረጉን አብራርተዋል፡፡የሲሚንቶ ግብይት ሥርዓትን ሲረብሹ የነበሩ ደላላዎችና በተለያዩ አካላት ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ከዘርፉ እንዲወጡ መደረጋቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/04 11:22:31
Back to Top
HTML Embed Code: